ኢትዮጵያ፡ ወደ ሕገ መንግስታዊ ዴሞክራሲ ጎዳና

Click here for PDF

ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ

ላለፉት ጥቂት ወራት  በኢትዮጵያ ከፈላጭ ቆራጭ መንግስት ወደ ዴሞክራሲ በሚል ርዕስ ስጽፍ ነበር፡፡ከነዚህ አስተያየቶች በመጨረሻው ጦማር ላይ ስጥፍ “በዴሞክራሲው መሸጋገርያ Roadblocks to Constitutional Democracy in Ethiopia?ድልድይ ላይ ስልጣንን በሚየነፈንፉ ግለሰቦችና ቡድኖች መሃል ግጭትና ግብግብ አይቀሬ ሲሆን፤ተራው የህብረተሰብ ክፍል ስልጣናቸውን በሚያኮላሹትና ለግል መጠቀሚያ በሚያደርጉት ላይና ሥልጣናቸውን የሙጢኝ ባሉት ፈላጭ ቆራጮች ተሰላችቷል መሮታልም፡፡ይህ ከፈላጭ ቆራጭ ስርአት ወደ ዴሞክራሲ በሚደረገው ሥግግር ወቅት የሚፈጠረው ግርግር ስልጣንን ለመጥለፍ ላቆበቆቡት መንገድ ይከፍትላቸዋል፤ ስለዚህም ዴሞክራሲን አስገድዶ በመጥለፍ በዴሞክራሲ ስም መልሰው ያን አረመኔያዊ ፈላጭ ቆራጭ ስርአትን ሊያስቀምጡ እንደሚተጉ አሳስቤ ነበር፡፡” በዚህኛው ጦማሬ ላይ ደግሞ በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚፈጠረው ሕገመንግስታዊ ዴሞክራሲ ሕገመንግስታዊ ‹‹ቅድመ ውይይት›› አስፈላጊነት አተኩራለሁ፡፡

ለዴሞክራሲ ሰላማዊው አጥር

አብዛኛዎቹ የሕብረተሰብ አባላት ከመራር አገዛዝ ወደ ዴሞክራሲ በሚያደርጉት ጉዞ ላይ በጣም ፈታኝና ውስብስብ የሆኑ አጥሮች ተጋርጠውባቸዋል፡፡በ1776 አሜሪካ ከግፈኛው የእንግሊዝ ጨቋኝ ስርአት ከተላቀቁ በኋላ፤13ቱ ቅኝ ግዛቶች፤እስከ 1781፤አርቲክል ኦፍ ኮንፌዴሬሽን እስኪፈርሙና ወቅታዊ የሆነ መንግስተ መስርተው ለጊዜው እስኪቀላቀሉ ድረስ በራሳቸው ቆይተው ብሔራዊ መንግስት መሰረቱ፡፡ይህ ሁኔታ ግን አላዋጣም ምክንያቱም ግዛቶቹ ዋነኛ የሚባሉትን የስልጣን ቁልፎች እንደያዙ በመቆየታቸው ግብይትን፤የውጭ ንግድን ስርአትና ሁኔታን በመቆጣጠር መንግሰት ታክስን እንዳየሰበስብ ገደብ ስለጣሉበት ይህንኑ ለማስተካከልና ፈር ለማስያዝ ጦር ማሰለፍ ግድ ሆነ፡፡ ይህንንና ሌሎቹንም ዋነኛ የተባሉትን ችግሮች በመፍታት ለመረጋጋትና ለዴሞክራሲያዊ ሂደት የተማመነ ሁኔታ ያስገኙት አሁን በስራ ላይ ያለውን ሕገ መንግስት በ1787 ከተቀበሉት በኋላ ነው፡፡

የቅርብ ሁኔታዎችም ሃገራት ከፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ ወደ ዴሞክራሲ በሚያደርጉት ሽግግር፤ ውስብስብ የሆነ ችግር እንደሚጋረጥባቸው ነው፡፡ ‹‹ከአረቦች ስፕሪንግ››ሂደት በኋላ 1 ዓመት ጊዜ ውስጥ የዴሞክራሲ ማዋቀሩ ሂደት በሊቢያ ግብጽ፤ቱኒዝያ፤የመን እና ሌሎችም የመካከለኛው ምስራቅ ሃገራት ውስጥ በጣም አወዛጋቢና ፈታኝ ፈተና ገጥሟቸዋል፡፡በግብጽ፤ ጊዜያዊ ወታደራዊ መንግስቱ ወደ ሕገ ምንግስታዊ የሲቪል አስተዳደር እየመራው ነው፡፡የግብጹ ወታደራዊ ስብስብ በግብጽ የሚታየውን የዴሞክራሲ ጫጩት ቅፈቅፍ ቤት በመጠበቅ ላይ ነው፡፡ በርካታ ግብጻዊያንም በግልጽ እንደሚያነሱት ጥያቄ ከሆነ፤ ወታደራዊው ባለአደራ በማለባበስ ሂደቱ ግብጽን ወደ አለፈው የሙባረክ ስርአት ለመመለስ እያቆበቆበ ነወይ ይላሉ፡፡ በቅርቡ በሚካሄደው የምርጫ ሂደት ውስጥ የሙባረክ የመውደቂያው ሰአት ጠቅላይ ሚኒስትር የነበረው አህመድ ሻፊክ ለጁን 16-17 ለመጨረሻው ወሳኝ ፍልሚያ ለከተሰለፉት ተወዳዳሪዎች አንዱ ነው፡፡ በታህሪር አደባባይ ከፈነዳው የበቃኝ አብዮት አንስቶ 12000 ግብጻዊያን ለእስር ተዳርገዋል፤ብዙዎችም በወታደራዊው ፍርድ ቤት ቀርበዋል፡፡ በርካታ ስመጥር የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ድርጅቶች ምንግስትን በግድ ለመለወጥ በሚል በሃገሪቱ የአቃቤ ሕግ ቢሮ ተወንልለዋል፡፡ወደ ዲክተቴርሽፕ ፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ መንሸራተትና የኋልዮሽ ጉዞ?

በቱኒዝያ ባለፈው ኦክቶበር የተመረጠው የሕገ መንግስት አርቃ ኮሚሽን በአንድ ዓመት ውስጥ ተስፋ የሚያጭር ውጤት እያሳየ ነው፡፡በጣሙን የሚያበረታታው ሂደታቸው ደግሞ የሕገ መንግስት አርቃቂዎቹ በተወሳሰቡ የፖለቲካ ምናምኖች ላይ ያተኮሩ ሳይሆኑ ሥላጣንን በአግባቡ በስራ ላይ የሚያውልና የፈላጭ ቆራጭነትን ስርአት ድጋሚ መከሰት የሚገታ ሕገመንግስት በማርቀቅ ላይ መሆናቸው ነው፡፡ልዩ ል ‹‹ኮሚሽኖች›› በማዋቀር  እነዚህ አርቃቂዎች ምን አይነት ምንግስት በሚለው ምርጫ ላይ በማትኮር (በፓርላሜንታሪና በፕሬዜዳንታዊ) የስልጣኑን ሚዛን በመጠበቅ፤ የፍትህ ስርአቱን ሚዛናዊነት ሕዝባዊነት፤ሥላጣንን በአግባቡ በማከፋፈል ስርአት ላይ ትኩረት በማድረግ እየሰሩ መሆናቸው ነው፡፡

በሊቢያ ያለው የዴሞክራሲ ሂደት ግን እስከዚህም ተስፋ የሚታይበት አይደለም፡፡ በኦገስት 2011 ‹‹ለሽግግር መንገዱ የሕገመንግስት ረቂቅ››(እውነተኛነቱን ማረጋገጥ አልተቻለም) በሊቢያ ውስጥ በሰፊው ይዘዋወር ነበር፡፡ ከምእራብያኑ ሊበራል ዴሞክራሲ ሃገራት ሕገመንግስት ላይ ተቆርጦ የተለጣጠፈ፤ ስለየህግ የበላይነት፤የግለሰብ ሰብአዊ መብቶች፤ ስለመናገር ነጻነት ስለሃይሞነት ነጻነት፤ ስለመድበለ ፓርቲ ያወራል፡፡ ሌሎችም የሕገመንግስት ረቂቆች በመዘዋወር ላይ ናቸው፡፡ባለፈው ማርች 60 አባላት ያሉት የሕገመንግስት አርቃቂ ኮሚቴ ተዋቅሮ የሊቢያን ዋነኛ የሚባሉትን 3 ግዛቶች እንዲወክል ተሰይሞ ነበር፡፡ነገር ግን ሊቢያውያን በጣሙን አጣዳፊና አንገብጋቢ የሆኑ የመረጋጋት ችግሮች አሏት፡፡መደበኛ የሆነ ቋሚ ጦር በሌለበት፤ጋዳፊን ለመጣል በዘፈቀደ ተሰባስበው የነበሩት አማጽያን አሁንም እርስ በርስ በመቆራቆስ ላይ በመሆናቸውና እንቅስቃሴያቸውም ባለመገታቱ ችግር አለባቸው፡፡ጨለማ በጋረደው ሕገመንግስታዊ ማርቀቅ ሂደት ውስጥ ብልጭታ የሚያሳየው የነጻው ስብስቦች የሊቢያ ጠበቆች፤ምሁራን፤ ጁሪስቶች፤መምህራን፤ እና ሌሎችም በትጋት በማርቀቁ ስራ ላይ ናቸው፡፡እንደዚህ የተገነጣጠለ አካሄድ ደግሞ የማርቀቁን ተግባር ለብጥብጥና አለመግባባት እንዲያመራ ያደርገዋል፡፡በዚህም ሰበብ በመጨረሻው ላይ ሰፋ ያለውን የሕብረተሰብ አካል በማንቃት ለክርክርና ለተሳታፊነት በመጋበዝ ሕገመንግስቱ በሊቢያ ሲነደፍ በባለቤትነት ይሰለፋል፡፡

ከሌሎች ውድቀትና ስህተት መማር፤  ሕገመንግስትን ለመንደፍ ቅድመ ውይይት በኢትዮጵያ

ከፈላጭ ቆራጩ አገዛዝ መውደቅ ጋር ከምንም በፊት ዋነኛና መሰረታዊ ሆኖ የሚነሳው ጥያቄ፤ አሁን ስላለው ሕገመንግስት መደረግ ያለበት ጉዳይ ነው፡፡አሁን በሥራ ላይ ያለው ሕገመንግስት የአንድ ፓርቲ የአንድ ግለሰብ ስርአት ማካሄጃ መሳርያ ነው፡፡ሕብረተሰቡን ለመከፋፈል በአንድ ሰው ፍቃድና ‹‹እውቀት›› በዘር ላይ፤በጎጥ፤በክልል፤በወረዳ፤በቋንቋ እና በመሳሰሉት ላይ ያነጣጠረ ነው፡፡ በኢትዮጵያ በሚካሄደው ሽግግር በጣም ጠንካራ የሆነ የሽግግር ሕገመንግስት አስፈላጊነት የሚጠበቅ ነው፡፡(ወታደራዊው ድርጅት ስልጣንን በግርግር ካልነጠቀ) አሁን ስላለው ሕገመንግስት በአብላጫው የሕብረተሰብ ክፍል ከቅሬታ ያለፈ ስሜት ይታያል፡፡ ሕገመንግስቱ በየወቅቱ በገዢዎቹ ይደፈራል፤የገዢውንና የአገዛዙን ግፈኛና የበደል ሁሉ መጋዘን የሆነውን ግለሰብ ስልጣን ለማጠናከርና ለማቆየት የሚጠቅም ሆኖ ነው ያለው፡፡በ2009  የዓለም አቀፍ የክራይስስ የሚባለው በተግባሩ እጅጉን ከበሬታ የተቸረው፤ ለተባበሩት መንግስታት፤ ለአውሮፓ ዩኒየን፤ ለዓለም ባንክ በአደገኛ ግጭትና ሊወሰድ ስለሚገባው መፍትሄ አማካሪ የሆነው ቡድን፤በጣም አሳሳቢ የሆነውን ርዕስ አንስቶ ነበር፡፡

የኢህአዴግ በዘር ላይ የተመሰረተ ፌዴራሊዝም አለመግባባትንና ግጭትን ከማስወገድ ይልቅ በፌዴራል መንግስታት መሃል በመሬት፤በተፈጥሮ ማእድናት፤የግዛት ክልል አያያዝና ከመንግስት በሚሰጥ ዓመታዊ በጀት ላይ ላይ ግጭቶችን አባብሷል፡፡ከዚህ ባለፈም በዘር ላይ የተመሰረተው ፌዴራሊዝም ብሄራዊውን ጥያቄ መመለስ ተስኖታል፡፡የኢህአዴግ የዘር ፖሊሲ የአንዳንድ ወገኖችን ስልጣናቸውን ሲያጎለብት ፤በውይይትና በመነጋገር የተደረሰበት ውሳኔ አይደለም፡፡ ለአማራውና ለብሔራዊ ምሁራን ክፍል የዘር ፌዴራሊዝም የጠነከረ አንድነት ያለው መንግስት ይፈጥራል፡፡እንደ ኦ ኤን ኤል ኤፍ (የኦጋዴን ነጻ አውጪ) እና ኦ ኤል ኤፍ (የኦሮሞ ነጻ አውጪ)የጎሳ ፌዴራሊዝም አርቲፊሻል ነው፡፡

ተጠያቂነትና ስልጣንን አለአግባብ መጠቀም የሰብአዊ መበት መደፈር፤ሙስና፤ ለሽግግር መንግስቱ ሌላ የሽግግር ሕገመንግስቱ መፍትሄ ሊያገኝለት የሚያስፈልገው ጉዳይ ነው፡፡ይህ ደግሞ በቅርቡ የዩናይትድ እስቴትስ ባወጣው የሃገራት የሰብአዊ መብት አካሄድ በ2011 ባወጣው ዘገባ ላይ ተቀምጧል:

የኢህአዴግ (የገዢው ፓርቲ) አባልነት ለአባላቱ የሚያስገኘው የጠቀሜታ መጠን ሰፊ ነው፡፡ ገዢው ፓርቲ በርካታና መጠነ ሰፊ የሆኑ ስራዎችን ያካሂዳል፤በዚህ ሳቢያም ስራና የስራ ኮንትራት ውሎችን ለአባላቱ ብቻ ይሰጣል፡፡ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በተደጋጋሚ እንዳነሱት የአካባቢ ባለስልጣናት ፓርቲያቸውን በመተው ወደ ኢህአዴግ ፓርቲ እንዲገቡና መንግስታዊ ድጋፍ ያለውን ማዳበርያ፤የእርዳታ ምግብ ተጠቃሚነትን፤የስራ እድል ማግኘትን፤እድገትን፤ተማሪዎችም በጥሩና ቅርባቸው ወደሆነው ዩኒቨርሲቲ መመደብን፤፤በመጀመርያ ዲግሪም ስራ የማግኘት እድልና ሌሎችም መንግስታዊ የሆኑ እድሎችን ማግኘት እንደሚችሉ ያግባቧቸዋል፡፡ አንዳንድ የመንግስት ባለስልጣናት የፕራይቬታይዜሽን ትግበራውን አለአግባብ ሲጠቀሙበትና ሲገለገሉበት ይታያሉ፡፡

በሕጉ መሰረት ይግል ንብረቶችን ለመመርመር ሕጋዊ ፈቃድ ማግኘት አለባቸው፤ በተግባር ፖሊሶች ይህን ሕግ ሲጥሱት እንጂ ሲያከብሩት አይታዩም፡፡ መንግስት የሚከፈላቸው አሳባቂዎች በመሰማራት በግለሰቦች ላይ ስለላ እንዲያካሂዱ ያደርጋል፡፡የደህንነት አባላት በመንግስት ለጥያቄ የሚፈለጉትን ቤተሰብ አባላት በማሰርና በማንገላታት ላይ ተሰማርቷል፡፡ ብሄራዊ መንግስታትና እና ሪጂናል መንግስቶች ‹‹የመንደር ምስረታ›› በሚል ጋምቤላ፤ ቤንሻንጉል፤ጉሙዝ፤እና ሶማልያ ክልሎች ውስጥ (እንደ ሂዩማን ራይትስ ዎች ዘገባ) የስለላው አባላት ነዋሪዎችን በመደብደብ (ለሞት የተዳረጉም አሉ) ያለ ፍርድ ቤት ትእዛዝ በማሰር በማጉላላት በመንደር ምስረታው ላይ ጣያቄ ያነሱትን ዝም ለማሰኘት ሞክረዋል፡፡በዚህም የተነሳ ሌሎቹ የአካባቢው አባላት አለመናገርን መርጠዋል፡፡ሕገ መንግስቱ ሃሳብን በነጻ መግለጽን የመናገር መብትን፤ የፕሬስ ነጻነትን ያወጀ ቢሆንም ገዢው ፓርቲና ልዩ ልዩ መዋቅሮቹ ግን በየቀኑ በየሰአቱ በየደቂቃው ይከበር እያሉ የሚጮሁለትን ሕገመንግስት ከማንም በባሰ መልኩ እየደፈሩትና እየጣሱት ይገኛሉ፡፡መንግስት አሁንም ጋዜጠኞችን አታሚዎችን ባለንብረቶቹን፤ኤዲተሮቹን በግብታዊ ውሳኔና በይሆናል አለያም ሌሎችን ዝም ለማሰኘት ያስራቸዋል፡፡ በየትምህርትቤቱና በዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቹ በኢህአዴግ መርህ መሰረት በአብዮታዊ ዴሞክራሲ እየታነጹ ነው፡፡  በኢትዮጵያ የፈላጭ ቆራጭን የግፍ አገዛዝ መወድቅ ተከትሎ፤አብዛኛዎቹ የጉዳዩ ባለቤቶች በሽግግሩ ወቅት የሚያገለግል ሕገመንግስት እንዲቀረጽና የሚነሱትን አሳሳቢ ጉዳዮች ሁሉ የሚፈታ እንዲሆን መጠየቃቸው አይቀርም፡፡ በቅርቡ የፈላጭ ቆራጭን አገዛዝ ገርስሶ የጣለው በሰሜን አፍሪካ የተከናወነው ሂደት ለኢትዮጵያ የሚቸረው ትምህርት ካለ ሁሉንም የጉዳዩን አካላት ያካተተ ‹‹ባለ አደራ መንግስት›› መፍጠሩ አስፈላጊ ይሆናል፡፡ በኔ አመለካከት ለዚህ አማራጭ የሚሆነው መጨረሻውን ጊዜ ከመጠበቅና ግብታዊ የሆነ ሁኔታ ከመፈጠሩ በፊት አሁኑኑ ውይይቱን(እኔ ቅድመ ውይይት የምለው) መጀመሩ ነው፡፡የተዋጣ የሽግግር ሂደት ለማምጣት እንዲቻልም በፓርቲዎችና በተደራጁ ሃይሎች ላይ የተወሰነ ሳይሆን ከሁሉም የሕብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ አባላት የታቀፉበት እንዲሆን ማድረጉ ተገቢ ነው፡፡

ከዲክታተር የጭቆና አገዛዝ የተላቀቁትን የአረብ ሃገራት የሽግግር ሁኔታ በመመልከት ኢትዮጵያ ብዙ ትምህርት ልትቀስም ትችላለች፡፡ቀዳሚውና ማነኛው ትምህርትም፤ሰፋ ያለና ዘላቂነት ያለው ቀጣይ ውይይት ሕገ ምንግስቱን በማዘጋጀቱ ርእስ ላይ ማካሄዱ ነው፡፡የአዲሲቱ ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ቁልፍ ጭብጥ ምን ሊሆን ይገባል?ካለፉት መንግስታት የግዴት የዘርና የጎሳ አደረጃጀት ወጥተን አንድ ወጥ የሆነና የአንድነታችን መገለጫ ወደሆነ ስርአት እንዴት እንደርሳለን? በሕገመንግስቱ አቀራረጽ ላይ ተገቢ የሆነውን የዜግነት ድርሻቸውን ሊወጡ እንዲችሉ ሁሉንም የሕግረተሰብ ክፍሎች ማስተማርና መስገንዘብ የምንችለው እንዴት ነው፡፡ሁከሉም የዴሞክራሲ ተሟጋቾች በአንድነት የሚሰሩበትን መንገድ በማምጣት የሽግግር ሂደቱን ሰላማዊ ማድረግ የሚችሉበትን ሁኔታስ እንዴት ነው የምንፈጥረው?ውይይትና  ድርድርንስ እንዴት እናካሂዳለን፡፡

ከፈላጭ ቆራጭ የአረመኔ አገዛዝ ውድቀት በኋላ የሕገ መንግስት አቀራረጽ

የቅርቡ ታሪክ እንደሚያሳየው ከሰሜን አፍሪካው የአረብ በቃኝ ባይነት ሕዝባዊና ሰላማዊ አመጽ ኢትዮጵያ የምታገኘው ትምህርት፤ከተለያዩ የጉዳዩ ባለቤቶች የተውጣጡ አባላት የተካተቱበት ‹‹የባለአደራ ምንግስት››መሰየም ነው፡፡ይህ አይነቱ መንግስት ደግሞ የሚመራበትና ስራውን የሚያከናውንበት የሽግግር ወቅት ሕገ መንግስት ያስፈልገዋል፡፡ይህም ዘላቂውንና ዋነኛውን የሃገሪቱን መመርያ ሕገመንግስት ለማርቀቅ ስለሚረዳውን በሂደቱም የሚነሱ ጥያቄዎችን መመለስ እንዲያስችለው ነው፡፡በኢትዮጵያ ስላለው ፈላጭ ቆራጭ የድንፋታና የግፍ አገዛዝ መውደቅ ተከትሎ ሌሎች አጋጣሚዎችም ሊታዩ ይችላሉ፤(እንደ ቀጥተኛ የሆነ የወታደራዊ ክፍል ጣልቃ ገብነት) እንደኔ እንደኔ ችግሩን እስኪከሰት ከመጠበቅ ወዲያውኑ ሁሉንም የሚያስማማ ውይይትና ድርድር ማካሄድ፡፡ የሕግ የበላይነትን ማእከል ያደረገ መንግስታዊ ስርአት ይመጣል የሚለውን መላ ምት ኢትዮጵያዊያን በአረቡ ሃገራት ከተካሄደው የዴሞክራሲያው ስርአተ መንግስት ግናባታ መማር የግድ ነው፡፡ በአረኑ ዓለም የበቃኝ ትግል ቅድመ ግንዛቤ ያልተወሰደበት ጉዳይ፤በሽግግሩ ወቅት የሕገመንግስቱን ማርቀቅና መመርመር ሃላፊነት ሊሸከም የሚገባው ማነው የሚለው ነው፡፡ የምእራቡ ዓለማት የሕገመንግስት አነዳደፍ ባለሙያዎች፤ችሎታና ብቃት ያላቸው ምሁራንና ጠበብት፤ የማስተማርያ ዶኩሜንቶች በገፍ፤በመላክ እንከን የለሽ ዴሞክራሲያዊ ስርአት እንዴት መገንባት ይቻላል ለሚለው እገዛ ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡በፓርቲዎች የሚወከሉ ሃገራዊ የጉዳዩ ባለቤቶችእና ድርጅቶችበሽግግር መንግስቱና በደጋፊያቸው ወታደራዊ ክፍል ፈቃደኝነት መሰረት የተካፋይነት ሚና እንዲጫወቱ ይፈቀድላቸዋል፡፡ይህ አካሄድ ግን ሌላውን አብላጫ ቁጥር ያለውን ዜጋ፤የሲቪሉን ማህበረሰብ አካል፤እና ከስርመሰረቱ ያሉትን ዜጎች ድምጻቸው እንዲሰማና የውይይቱ አካል ሊሆኑ እንዲችሉ  አላካተታቸውም፡፡ የዚህ አካሄድ ደግሞ በይበልጥ ባለቤት ያደረገው ምሁሩን ክፍል ብቻ በመሆኑ ተራው የዜጋ ክፍል የኔነትና የይገባኝ ጥያቄው ባለመመለሱ የራሱ አድርጎ አይቀበለውም፡፡ እርግጥ ቴክኒካል የሆኑ ርእሶች ስለሚነሱ የምሁሩ አስፈላጊነት አያጠያይቅም፡፡በአረቡ ዓለም እንደታየው ከሆነ ግን በኮሚቴው የተካተቱት ምሁራንና ሊቃውንት አማራጮችን በመክፈት በሕገመንግስቱ አቀራረጽ ሂደት እጅግም  ጠቀሜታ ያለው ሁኔታ አልፈጠሩም፤ሰፊው ዜጋ ያለተሳተፈበትና ድምጹን በነጻና ዴሞክረሲያዊ በሆነ መንገድ በማሰማት ያልተሳተፈበት የሕገመንግስት አነዳደፍ የብዙሃኑን ፈቃደኝነት የሚያሳይ ሳይሆን የጥቂት አዋቂዎችና ተጠቃሚዎች ፈቃድ የሚያረጋግጥ ነው፡፡የሕገመንግስቱ ማርቀቅ ተግባር ለብዙሃኑ ዜጎች ተሳትፎ መንገድ መክፈት ይገባዋል፡፡

ለዚህ ማሰረጃ የሚሆነውም በአረቡ የበቃኝ ትግል ማግስት የታየው የሲቪል ማህበረሰቡን፤የብዙሃኑን ድርጅቶች፤ሴቶችን፤ ወጣቱን፤ያገለለ ነበር፡፡ሙባረክን መንግሎ ለመጣልና የፈላጭ ቆርጭ ስርአቱን ማክተሚያ በማምጣቱ ትግል ክፍተኛውን ሚና የተጫወቱትና ሕይወታቸውን የሰዉት ወጣቶች አጋር ተፋላሚዎች በማረቀቁ መንደር አለመታየታቸው አየስገርምም?

ኢትዮጵያ ከአረቡ የሽግግር ሕገመንግስት አቀራረጽ በመነሳት ሌሎች እጅግ አስፈላጊ የሆኑና ኢትዮጵያ ልትጠቀምበት የምትችላቸው ነጥቦች አሉ፡፡ በኢትዮጵያ ያሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች፤ድርጅቶች፤መሪዎች፤ምሁራን፤የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች፤ በአንድነት ስርአት ያለው ፐሮግራም በመንደፍ ህብረተሰቡን ማስተማር፤ለዴሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ ትምህርት፤ወሳኝና የተዋጣለት የዴሞክራሲያ ስርአተ ማሕበር ለመመስረት የሚረዳ ተግባር ማከናወን ይጠበቅባቸዋል፡፡ አሁን ስላለው ሕገመንገስት ጭላንጭሉ የሚታየውን ውይይተ በማዳበርና ይፋ በማውጣት በግልጽና በነጻነት ሕዝቡ እንዲነጋገርበትና ጥቅምና ጉዳቱን በመንቀስ በምትኩ ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ለመገንባት የሚያበቃ ሕገመንግስት መንደፍ አለባቸው፡፡ሕዝቡን በማስተማሩ ረገድ ተግባብተው፤ለአንድ ግብ በመቆም፤ተስማምተው ሊንቀሳቀሱ የግድ ነው፡፡

ለኢትዮጵያ የኬንያ ሕገመንግስት በምሳሌነት

በኬንያ በ2007-07 በተከናወናው ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ ወቅት በታየው ውጥንቅጥ ሁኔታ የተወሰደው የህገመንግስት ሪፎርም፤በተለያዩ ዓለም አቀፍ ድርጅቶችና መንግስታት እይታ በእጅጉ ተደንቆ ነበር፡፡ኬንያዊያን ወደ ሕገመንግሥታዊ የማርቀቅ ተግባር ከመግባታቸው በፊት ‹‹ብሄራዊ አንድነት›› አረጋግጠው ተስማሙ፡፡ በርካታ ነጻ አካላት ሃሳብ አቅራቢዎች፤የአረቃቀቁን ስርአት በተመለከተ ግልጸንትንና ተሳትፎን ፤ ረዘም ያለውን የባለጉዳዮቹን አካላት ውይይት፤ ይፋ የነበሩትን አማካሪዎች፤ የሕገመንግስት ምንነትን የሚያስረዱና የሚያስተምሩ የሲቪክ ማህበረሰብ አባላት በሰፊው ሲንቀሳቀሱ እንደነበር ተመልክተዋል፡፡በ2010 የተስተካከለው አዲሱ ሕገመንግስት፤በወሳኝ ባለስልጣነት ስልጣን ላይ ሕገመንግስታዊ ገደብ በመጣሉና በስራ ላይ የነበረውን ክፍለ አህጉራዊ ጉልበተኛነት የፈረጠሙ መንግስታትን አነስተኛ በሆኑት ወረዳዎች በመለወጡ፣የዜጎች ቢል ኦፍ ራይትስ፤ባለፈው የተፈጸመውን ደባ የሚያጣራና የመሬት ኮሚሽን፤የተሰረቁ ንብረቶችን የሚያስመልስ አካል እና ባለፈው የተካሄደውን የማን አለብኝ ድርጊት በመመደቡ ጠቀሜታው ታይቷል፡፡ይሄው ሕገ መንግስት ይፋዊ የሆነ ውይይትና የሁሉም ተሳትፎ ታክሎበት በ70 በመቶው የኬንያ ዜጋዎች ጸደቀ፡፡

ዴሞክራሲያዊ ሕገ መንግስትና ሕገመንግስታዊ ዴሞክራሲ ፍለጋ

ዴሞክራሲያዊ ሕገመንግስትን ፍለጋና በኢትዮጵያ የዴሞክራሲያዊ ሕገመንግስት ተግባራዊነት አድካሚና ፈታኝ እንደሚሆን የተረጋገጠ ነው፡፡ተግባራዊ ማድረግ ግን ይቻላል! በጉዳዩ ላይ የኔ አመለካከት ቀጥተኛ ነው፡፡ሕገመንግስት ታላቁ ዋነኛውና የሕጎች ሁሉ የበላይ ነው፡፡ማንኛቸውም ሕጎች በሱ ላይ ተመስርተው የሚወጡና በዚሁ ዋነኛ ሕግ የሚታዘዙ ናችው፡፡ ሕገ መንግስት በመንግስት አካሄድ ላይ ገደብ የሚጥል (ለመንግስታት ስላጣንን የሚሰጥ ብቻ አይደለም) በኔ አመለካከት ሕዘቡ በመንግስት ላይ የሚያጠልቀው የውሻ ሰንሰልትን የሚመስል ነው፡፡ሰንሰሎቱ ባጠረ ቁጥር ለውሻው ጌታ የተሸለ ማዘዣ ሃይል ይሆነዋል፡፡ሕገመንግስት የግለሰብ መብቶችን የሚያረጋግጥ የሰብአዊ መብትን መረጋገጥ የሚዳኝና የሚያስተካክል፤መንግስታት እንዳሻቸው እንዳይተገብሩት መቆጣጠርያ መሳርያ ነው፡፡ በአስተዳዳሪነት የሚሰየሙት ሁሉ የተቀደሰ ተግባር በሚያከናውኑበት ወቅት ይህን የህግ ሰይፍ አክብረውት ሲገኙና ነጻ በሆነ የፍትህ ስርአት ሲያምኑና ሲቀበሉ ከዚህ ሲያፈነግጡም ተጠያቂነት እንደሚመጣባቸው ማወቅ ሲችሉ ብቻ ነው በኢትዮጵያ እውነተኛው ሕገመንግስታዊ ዴሞክረሲ ሊመሰረት የሚችለው፡፡

ካሁን በፊት የቀረቡ የጸሃፊው ጦማሮችን  ለማግኘት እዚህ ይጫኑ::

http://www.ecadforum.com/Amharic/archives/category/al-mariam-amharic

http://ethioforum.org/?cat=24

Similar Posts

Leave a Reply