የመለስ ዜናዊ ድንቀኛ ተረቶች – ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም

Click here for PDF

ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም

ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ

Ethiopia: The Bedtime Stories of Meles Zenawi

ባለፈው ሳምንት በኢትዮጵያ በተካሄደው በ‹‹ ዓለም አቀፉ የኤኮኖሚ ስብሰባ ላይ›› የግፍ ገዢው የፈላጭ ቆራጩ መለስ ዜናዊ አርቲ ቡርቲ መነባንብ:

በኔ እምነት  በታሪክም ሆነ በቲዎሪ የኤኮኖሚ እድገትና ዴሞክራሲ ቀጥተኛ ግንኙነትም ሆነ ተዛምዶ የላቸውም፡፡ በኔ አመለካከት፤ በኤኮኖሚ እድገት ላይ የሚያስከትለውን ጫና ገሸሽ አድርገን ዴሞክራሲ በራሱ ጥሩ ነገር ነው፡፡በኔ አመለካከት አፍሪካውያን በጣም ስብጥሮች ነን፡፡ ስለዚህም ነው ብዬ አምናለሁ በመሃላችን ያለውን ግንኙነት ሰላማዊ የሚያደርገው፡፡እነዚህን ስብጥር ሰዎች በአንድነት ለማቆየት ያለው አማራጭም ዴሞክራሲ ነው  ብዬ አምናለሁ፡፡ስለዚህም ዴሞክራሲን መዘርጋት ይኖርብናል: ግን ለእደገት ብለን አይደለም፡፡ዴሞክራሲን መዘርጋት ያለብን ስብጥር የሆኑትን በአንድነት ለማቆየት እንድንችል ነው፡፡ የኔ አመለካከት ይሄ ነው፡፡ያም ሆኖ ግን በዚህ የምሽት ተረት ተረት፤የእንቅልፍ ማምጫ ተረብ እና  የኤኮኖሚን ልማትና ዴሞክራሲን የሚያገናኝ ፈጠራና የውሸት ተረት አላምንም፡፡በታሪክ ይህን የሚያረጋግጥ መሰረት የለም: በኔም አመለካከት ከልማት እድገት ጋር የሚያገናኘው መሰረት የለም፡፡ ይህንን የቅዠት ክርክር ማካሄድ ጨርሶ አያስፈልግም: ምክንያቱም ዴሞክራሲ ብቻውን ቆሞ ብቻውን ሊያበራ ይችላልና፡፡

ከዚህ በተቃራኒው ደግሞ የኤኮኖሚ ዕድገትን ከዴሞክራሲ ጋር የተገናኘ ነው ብለው ““የቅዠት ተረት ተረት” የተናገሩት ፕሬዜዳንት ኦባማ በ2009 በጋና አክራ  ይሄ ነው፡፡

ልማት በመልካም አስተዳደር ላይ ይመሰረታል፡፡ታሪክ ትክክለኛውን ውሳኔ ያመላክተናል፡፡የሕዝቦቻቸውን ፍላጎት የሚያከብሩ፤በሕዝቦች ፈቃደኝነት የሚያስተዳድሩ  በሃይልና በማንአለብኝነት ከሚገዙ የበለጠ ልማታዊ የበለጠ የረጉ፤እና የበለጠ ስኬታማ ናቸው፡፡ መሪዎች ራሳቸውን ለማሳበጥና በሃብትም ለመክበር ጥረት የሚያደርጉ ከሆኑ፤ ማንኛውም ሃገር ሃብት ሊኖረው አይችልም፡፡ፍትህ የሕግ የበላይነት በሚጨፈለቅበትና በሙስናና በሌብነት በተመሳቀለ ሃገር ውስጥ ለመኖር የሚመኝ ማንም የለም፡፡ ይህ አይነቱ ሁኔታ ያለበት የዴሞክራሲ ሃገር ሳይሆን የግፍ ሃገር ነው፡፡ያንን የመሰለውን አስከፊ ስርአት መገላገያው ደግሞ አሁን ነው… 21ኛው ክፍለ ዘመን፤ችሎታ ያላቸው፤ታማኝነት ያላቸው፤እና ግልጽነትን የሚቀበሉ ኢኒስቲቲዩሽኖች ለዚህ ስኬት ቁልፍ ናቸው፡፡—–ጠንካራ ፓርላማ፤ታማኝ የሆነ የፖሊስ ሃይል፤ነጻና ለራሳቸው ሕሊና የሚገዙ የፍትህ ስርአት አባላት፤ነጻና ዴሞክራሲያዊ ፕሬስ፤ ንቁና ልማታዊ የሆነ የግል ዘርፍ፤የሲቪል ማህበረሰብ፡፡ ለዴሞክራሲ ነፍስ የሚዘሩበትና መከታ የሚሆኑት እነዚህ ናቸው፤ ምክንያቱም በሕብረተስቡ የእለት ተእለት እንቅስቃሴ አስፈላጊው ይሄው በመሆኑ፡፡…. ታሪክም ከነዚህ የአፍሪካ ጀግኖች ጋር  ይቆማል እንጂ ራሳቸውን በሥላጣን ለማክረም ግፍ ከሚሰሩትና ለግለሰብ ፍላጎታቸው አመጽ ከሚያስነሱትና ሕገ መንግስቱን እንዳሻቸው ከሚያመሳቅሉት ጋር አይሰለፍም፡፡አፍሪካ ጡንቸኞች አየስፈልጋትም፤የሚያስፈልጋት የፈረጠሙ ዴሞክራሲያዊ ኢንስቲቲዩሽኖች ነው፡፡አፍሪካ የተሻለና ስፋት ያለው እድገት እንደሚኖራት ጥርጥር የለኝም፡፡

 እኔ የምወዳችው ተረቶች

እንደሌላው ሰው እኔም የእንቅልፍ ማምጫ ተረቶች እወዳለሁ፡፡ የምመርጠው ደግሞ  “ፒኖኪዮ በአፍሪካ” የተሰኘው፤ ነው:: ከአሻንጉሊትነት ወደ ሰውነት መለወጥ የሚመኘውን ፒኖኪዮ ሰው መሆን ሊችል ይችላል ግን ተአማኒነት ይጠበቅበታል፡፡ ፒኖኪዮ መዋሸት በጣም ይወዳል ያውም ገደብ የሌለው ትላልቅ ውሸት፡፡ፒኖኪዮ በዋሸ ቁጥር አፍንጫው ይረዝማል፡፡

‹‹ፐፍ: ዘ: ማጂክ ድራጎን እና ሕያው የሆኑ ውሸቶች ሃገር›› የተባለዉን ተረት እወደዋለሁ፡፡ ፐፍ: በቤቷ ያለውን ችግር ለመሸሽ የምትፈልገውን ሳንዲ የተባለች ልጅ ሕያው የሆኑ ውሸቶች ሃገር ወሰዳት፡፡ በዚያም ፒኖኪዮንና ጂብ መጣ እያለ  በዉሸት የሚያስፈራራውና የሚጮኸውን  ልጅ አገኘች:: ከዚያም ሌላ ማንም አይቶ የማያውቀውን ወይን ጠጅማ ላምና: ሮዝማውን ዝሆን አየች፡፡

ጥንታዊውን የኢትዮጵያ ታሪክ ተናጋሪ የኤሶፕን ግብረገባዊ ተረቶችም እወዳቸዋለሁ፡፡ ድሮ ዱሮ አንድ በጎችን ጠልፎ ለመውሰድ ችግር ያለበት ተኩላ ነበር፡፡የችግሩ መነስኤም ጠባቂው ንቁና ጠንቃቃ ስለነበር ነው፡፡አንድ ቀን ቀበሮው የተጣለ የበግ ቆዳ አገኘና ያንን ቆዳ ለብሶ በጎቹን ተመሳስሎ ከመንጋዎቹ ጋር ተደባለቀ፡፡እያደባ አንድ ባንድ በጎቹን በመብላት ላይ እያለ አንድ ቀን እረኛው አወቀበትና ከዚያን ዕለት ጀምሮ  ሰርቆ ገድሎ መብላት አልቻሃለም::

ተምሳሌታዊና ድርብ ትርጉም ሰጪዎችንና የተረት አነጋገሮችን እወዳለሁ፡፡ እንደ ጆርጅ ኦርዌል የፖለቲካ ቋንቋ ያዘሉት::  ጀርጅ ሲተርት ፖለቲከኖች: ሃሰትን እንደ እውነት ግድያን የተከበረ ተግባር አድርገው ያቀርባሉ፡፡በዚህም መልኩ ጦርነት ሠላም፤ነጻነትም ባርነት፤መሃይምነት ምሁርነት፤ድህነት ሃብት፤ችጋር የተትረፈረፈ ምግብ፤ የጸሁፍ ቁጥጥርን የፕሬስ ነጻነት፤ግፍን መልካምነት፤ እያሉ ያቀርባሉ፡፡

አዎንና የልጆችን የጨዋታ ግጥምም እወዳለሁ፡-

ሃምፕቲ ዳምፕቲ የተባለ እንቁላል ግድግዳው ላይ ተቀመጠ፤

አወዳደቁም ተአምራዊ ነበር!

ጤናማ ሕብረተስብ፤ ዴሞክሬይዚ  እና  ንኮቹ ዲክታተሮች

“ብቸኛው ሕዝቦችን በሰላም ለማቆየት ያለው አማራጭ ዴሞክራሲ ነው” ይላል መለስ፡፡ ሃሰት ከሚኖርበት ሃገር አንዳንድ እውነተኛ ታሪኮች፡ እንመልከት-

ፍሪደም ሃውስ የዩናይትድ ስቴትስ ስቴት ዲፖርትመንት

በኤፕሪል 2008 በአጠቃላይ ኢትዮጵያ ምርጫ ተካሂዶ ነበር፡ፍሪደም ሃውስ እና ፡ ያሜሪካ ዉጭ ጉዳይ ሚንስትር  ባደረጉት ዘገባ መሰረት፤የተቃዋሚ ፓርቲ ተፎካካሪ ተመራጮች ከምርጫው በፊት በመንግስት ሃይላት በመንገላታትና ከምርጫው እራሳቸውን እንዲያገሉ በመያዝና መሳደድ ስቃያቸውን ይበሉ ነበር፡፡በዚህም የተነሳ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ከምርጫው ራሳቸውን በማግለል ስለተዉት መንግስትና ፓርቲው ብቻውን ተወዳድሮ ደጋፊዎቹ የምርጫ ተፎካካሪዎች ከፍተኝ ብልጫ አኙ፡፡ ገዢው ፓርቲ ለምርጫ ከቀረቡት ከ3 ሚሊዮን ያላነሱ መቀመጫዎች 99 በመቶውን አሸነፈ፡፡

የዓለም ባንክ (2012)

በሜይ 2010 በተካሄደው ምርጫ ገዢው ፓርቲ ኢሕአዴግ (ኢፒአርዲኤፍ) እና አጋሮቹ  99.6 በመቶ ምርጫውን በማሸነፍ የተቃዋሚውን ቁጥር በሕዝብ ተወካዮች 547 ወንበር ከ174 ወደ ሁለት አወረደው፡፡ ኢትዮጵያ በሰብ ሰሃራ አፍሪካ ከሚገኙት ሃገራት በሕዝብ ቁጥር ሁለተኛዋና፤ በዓለም ካሉት ድሃ ሀገራት አንዷ ነች፡፡የኑሮ ደረጃውም ቢሆን በዓለም ካሉት ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ውስጥ ካሉትም የባሰች ዝቅተኛ ነች፡፡በዚህም በዓለም 6ተኛ ደረጃ ላይ ያለች ድሃ ሀገር ናት፡፡

አምነስቲ  ኢንተርናሽናል (2009)

የኢትዮጵያ መንግስት ለሃገርም ውስጥ ሆነ ለውጭ ሃገራት እርዳታ ሰጪ ድርጅቶች፤ አዲስ አሳሪና አፋኝ ሕግ አውጥቶ፤ የሰብአዊ መብትን በመግፈፍ ወንጀለኛ አድርጎል፡፡የበጎ አድራጎትና የማህበራት ሕግ (2009) የተፈጠረበት ዋነኛ መንስኤ፤የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችን፤ የሲቪል ማህበረሰቡን እንቅስቃሴ፤ለመቆጣጠርና እንቅስቃሴያቸውን ለመግታት ታስቦ ነው፡፡ይህንንም በማድረግ መጪውን የ2010ን ምርጫ ከወዲሁ ለራስ ድል ለማዘጋጀትና ተቃዋሚውን ከምርጫ ውጪ ለማድረግና በሰበብ አስባቡ ለመወንጀል እንዲያመች የታሰበ ነው፡፡

ሁማን ራይትስ ዎች (2010)

ኢትዮጵያዊያን በነጻ መናገር፤ ሃሳባቸውን መግለጽ፤የፖለቲካ ስብሰባዎችን ለማዘጋጅት፤የመንግስትን መግለጫዎችና አግባብነት የሌላቸውን አዋጆች ለመቃወምም ሆነ የተለየ ሃሳብ ለማቅረብ፤ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ፤ በነጻ ፕሬስ ሃሳባቸውን ማስፈር ጨርሶ የማይችሉበት የፍርሃትና የጭንቀት ሁኔታ ውስጥ ናቸው፡፡የዴሞክራሲ ቴክኒካል አሰራር ፍሬም ለዘለቄታው ማታለያና የገዢው ፓርቲ የመከላከያ ብረት ግንብ  ሆኖ የገዢውን ፓርቲ ፍላጎት ማሟያ ብቻ እንዲሆን የታቀደ ከመሆኑም አልፎ የገዢው ፓርቲ ባለስልጣኖች ለሚያደርሱት ሕዝባዊ ግፍ ተጠያቂነት የለባቸውም፡፡

የዓለም የፋይናንስ እውነታ ዎል ስትሪት ጆርናል (2011)

ኢትዮጵያ  ከ2000 እስከ 2009 ባለው ጊዜ ውስጥ በተለያየ እኩይ ድርጊት ብክነት 11፣7 ቢሊዮን ዶላር ተመዝብራለች፡፡የኤኮኖሚው አቅም ደካማና የኑሮ ውድነት ሕዝቡን አላላውስ ብሎ ወጥሮ በያዘው ሃገር ላይ እንዲህ አይነት ብክነትና ስርቆት እጅጉን አሳዛኝ ነው፡፡ ሕጋዊ ባልሆነ መንገድም አውቀው እንዳላወቁ በመሆን ባለስልጣናት ከባለስላጣናት ጋር በመወዳጀት በ2009 ብቻ ከሕግ ውጪ 3.26 ቢሊዮን ዶላር ካለፉት ሁለት ዓመታት በእጥፉ ከሃገር ወጥቷል፡፡

የጋዜጠኞች መብት ጠባቂ  ኮሚቴ (2011)

በአፍሪካ ጋዜጠኞችን በማሰር፤ በማሰቃየት፤ በማንገላታት ዝና ካተረፉት ሃገራት መሃል ከኤርትራ ቀጥላ የግፍ ከረጢት በመባል የተመዘገበችው ኢትዮጵያ ነች፡፡ግፉና መከራው እያሰቃያቸው ብዙ የነጻው ፕሬስ አባላት ሃገራቸውን ጥለው ለስደት ተዳርገዋል፡፡ይህም በቁጥር በዓለም ቀዳሚውን ስፍራ ይዟል፡፡እውነታው  ይህ ሆኖ ሳለ መለስ ግን፤ለኖርዌጂያኑ (Aftenposten) ጋዜጣ‹‹ ለሕግ ልዕልና መከበር ከፍተኛው ደረጃ ላይ ደርሰናል፤ ሰብአዊ ምብትንም በአግባቡ እናከብራለን፡፡ሃገራችን የህዝቦቿ የዴሞክራሲ መብት በአግባቡ የተከበረባት ሃገር ነች››በማለት የሌለ ነገር አለ በማለት ይቀላምዳል፡፡

ሁማን ራይትስ ዎች (2011)

የኢትዮጵያ መንግስት ስለ ሽብርተኛነት መከላከል ያወጣውን የይስሙላ አዋጁን ሰላማዊ ሰዎችን ለማሰርና ለማሰቃየት ሊጠቀምበት የፈጠረው ነው፡፡የጸረ ሽብር ሕጉ በራሱ ትልቁ ችግር ነው፡፡ዓለም አቀፉ ሕብርተሰብ በተለይም የአውሮፓ ዩኒየን፤ ዩናይትድ ስቴትስ፤ዩናይትድ ኪንግደም  የኢትዮጵያ ገዢ መንግስት ይህን ሕግ ለምን ሰላማዊ እንቅስቃሴንና የሰላመዊውን ሕዝብ ድምጽ ለማፈኛነት እንደዘረጋው ሊጠይቁት ተገቢ ነው፡፡

የኮንግሬስማን ዶናልድ ፔይን ዘገባ (2007)

ሰብአዊ መብት 2003 ( ዴሞክራሲና ተጠያቂነት አክት 2007 የተወካዮች ምክር ቤትን ድጋፍ አግኝቶ በኦክቶበር 2 2007 አለፈ) የአገር አስተዳደር ሚኒስቴር የሰብአዊ መብትን በመደገፍ አንድ ማዕከል ፈጥሮ ለሃገር በቀል የሰብአዊ መበት ተሟጋቾች የፋይናንስ ድጋፍ የሚያደርግበትን ዘዴ መቀየስ አለበት፡፡ሕጉ፤የዴሞክራሲን ሂደት በመደገፍ የዴሞክራሲን እውነታ ማጎልበትን ሲደግፍ፤የአሜሪካ መንግስት ሰብአዊ መብትን ለማደርጀት የሚያደርገውን ጥረትና እንቅስቃሴ የኢትዮጵያ ገዢ ፓርቲ የሚያውክ ከሆነ ይህን መሳዩን የሰብአዊ መብት አፈና ለማቆም የሚደረገው እርዳታ ሁሉ ከሰብአዊ መበት መከበር ጋር ተጓዳኝ መሆን እንዳለበት ያስገነዝባል፡፡የ2005 ውን ሰላማዊ እንቅስቃሴ በተመለከተ፤ ከመንግስት በኩል ያስከተለውን ኢሰብአዊና ጸረ ዴሞክራሲ ተግባር አስመልክቶ የደህንነት ክፍሉን ተጠያቂ ያደርጋል፡፡

የአሜሪካው ሴኔተር  ረስ ፌይንጎልድ እና ፓትሪክ ሌሂ  ረቂቀ ህግ 3457 (2008) ላይ አስተያየታቸው

ሚስተር ፌይን ጎልድ፤ – ሚስተር ፕሬዜዳንት፤በዛሬው እለት በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብትንና የዴሞክራሲን ረቂቀ ህግ 3457ን ድጋፍ ለማስታወቅ በመቻሌ ደስተኛ ነኝ፡፡የዚህ ረቂቀ ህግ ዋናው ጥቅም በኢትዮጵያ ውስጥ የፖሊሲውን ግብ ለማረጋገጥና እውነተኛው ዴሞክራሲ ከተጫነበት ጫና ተላቆ ለሕዝቡ ጠቀሜታ የሚውልበትን ነጻ ሂደት ለማረጋገጥ ነው፡፡ ነጻ የሆነ የህግ ስርአትና የሕግ የበላይነት፤የሰብአዊና የፖለቲካ መብቶች መከበርን፤በነጻው ሚዲያ ላይ እና መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች ላይ የተጣለውን አፋኝ ገደብ ማስንሳት፡፡… እየባሰባት በሚሄደው የፖለቲካ ውጥረት ላይ ሰምተን አልሰማንም አይተን አላየንም በማለት ችላ ካልነው፤በግፍ ወደ ወህኒ የሚጣሉትን ንጹሃን ከረሳናቸው፤መንግስታዊ ያልሆኑ እርዳታ ሰጪ ድርጅቶች ገደብ ከተጣለባቸውና ስራቸው እንዲዳከም ሲደረግ ችላ ካልን፤በኦጋዴን አስተዳደር ቀደም ሲል በኦሮሚያ፤በአማራው፤በጋምቤላ የተፈጸመውን በቸልታ እንዳለፍነው ሁሉ አሁንም ሰዎች በግፍ ሲገደሉ ጆሮ ዳባ ልበስ ካልን፤ከተጠያቂነት አናመልጥም………

2010 የአውሮፓ ዩኒየን  የምርጫ ታዛቢዎች ቡድን የሜይ 2010 የምርጫ ዘገባ

በአብዛኛው የሃገሪቱ ክልሎች የገዢው ፓርቲና መንግስታዊ እንቅስቃሴዎችና ምርጫው ላይ የነበረው ልዩነት ጨርሶ አይታይም ነበር፡፡ ገዢው ፓርቲ መልሶ መንግስት ነው፡፡የአውሮፓ ዩኒየን የምርጫ ታዛቢ ቡድን፤የመንግስትን መገልገያና ሌሎችም ያና መጠቀሚያ ሲውሉ ተመልክቶ ታዝቧል፡፡ገዢው ፓርቲና አጋር ፓርቲዎች በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከ547 መቀመጫዎች 544ቱን  አሸነፉ፡፡ በዚህም የምርጫው ሂደት ዓለም አቀፍ ደረጃውን መመዘኛ ማሟላት አቅቶታል፡፡ግልጽነት አልነበረውም እንዲሁም ለሁሉም ምርጫ ተፎካካሪዎች መድሎ የሌለበት ሂደትም አላሳየም፡፡ ለገዢው ፓርቲ በሁሉም መልኩ የወገነ ሁኔታ ነበረው፡፡

የመለስ  መልስ፡2010 ለአውሮፓ ዩኒየን የምርጫ ታዛቢ ኮሚቴ ሪፖርት

የአውሮፓ ዩኒየን የምርጫ ዘገባ ከቆሻሻ ማጠራቀሚያ ቅርጫት ውስጥ መወርወር ያለበት ቆሻሻ ነው፡፡ዘገባው ስለእኛ ምርጫ አይደለም፡፡ገዢው ፓርቲ በመፈርጠሙ የተነሳ የአንዳንድ አውሮፓውያን ኒዮ-ሊበራልስ የቅናትና ምቀኝነት ዘገባ ነው፡፡ማንም ወረቀትና ብዕር ያለው የፈለገውን መሞንጨር ይችላል፡፡

ይህ ነው የመለስ ዜናዊ በኢትዮጵያ ያለው ዴሞክራዚ!

ካሁን በፊት የቀረቡ የጸሃፊው ጦማሮችን  ለማግኘት እዚህ ይጫኑ:: http://www.ecadforum.com/Amharic/archives/category/al-mariam-amharic

Similar Posts

Leave a Reply