በካምፕ ዴቪድ የአፍሪካ የችጋር ትርኢት

Click here for PDF

ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ

ባለፈው ሳምንት የሁዋይት ሀውስ  ቤተ  መንግስት ቃል አቀባይ ጄይ ካርኒ ፕሬዜዳንት ኦባማ የጋናን፤ የታንዛንያን፤የበኒን ፕሬዜዳንቶችንና  መለስ ዜናዊን የስምንቱን የኤኮኖሚ ሃያላን Ethiopian Newsሃገሮች (G8) ስብሰባ ላይ በካምፕ ዴቪድ ሜሪላንድ በሜይ 19 ስለ ምግብ ዋስትና በሚካሄደው ውይይት ላይ እንዲገኙ መጋበዛቸውን ይፋ አድርገዋል፡፡ የአሜሪካን መንግሥት ለዘመናት ለአፍሪካ አህጉር የምግብ እርዳት ሲያደርግ መክረሙ ይታወቃል፡፡ አሁንም በድጋሚ አፍሪካን ‹‹የመረረ የችጋር ወቅት›› ገጥሟታል ይላሉ ፕሬዜዳንት ኦባማ፡፡ ኦክስፋም በበኩሉ ከአሁኑ አስፈላጊው ሁሉ ካልተደረገ በስተቀር በመታየት ላይ ያሉ ጠቋሚ ምልክቶች ሁሉ እጅጉን ዘግናኝ የሆነ መአት እንደሚከተል ያሳያሉ ይላል፡፡ የተባበሩት መንግስታት የምግብና የእርሻ ድርጅት በበኩሉ ባስተላለፈው የድረሱ ጥሪው፤ በሳሄል ምእራብ አፍሪካ ለ800,000 በችጋሩ ለተጎዱት ረሃብተኞች መርጃ የሚሆን 70 ሚለዮን የአሜሪካን ዶላር እንደሚያስፈልግ፤አስቀድሞ ማስጠንቀቂያው መተንበዩን መሰረት አድርጎ ኢትዮጵያና ሶማልያ በጉዳቱ ወደ አዘቀዘቀው ደረጃ እንደሚወርዱም ይፋ አድርጓል፡፡ የዝናቡ አናሳ መሆንም አስፈላጊውን ምርት ስለማያስገኝ የግጦሽ መሬትንም መልሶ ስለማያለማው፤በአጠቃላዩ  አካባቢም የውሃ እጦት ሌላው ችግር በመሆኑ የደቡብ ኢትዮጵያውን ክፍል በእጅጉ የሚጎዳና ሕዝቡንም ለመረረ ችጋር ከብቱንም ለእልቂት የሚዳርግ ክፉ ቀን እንደሚመጣ ይተመናል::  ይህ ደሞ በገሃድ እየታየ ያለ በመሆኑ አደጋው ከአደጋዎች ሁሉ የባሰ በሆነ መልኩ ነው፡፡ አንባቢዎቼ እንደሚያስታዉሱት ሁሉ ባለፉት ሁለታ ዓመታትና ከዚያም ባለፈ በኢትዮጵያ ስለሚከሰተው ችጋር በርካታ አስተያየቶችን አስመልክቼ  ጽፌ ነበር፡፡

 የችጋር  ትርኢት በኢትዮጵያ

ባለፉት ዘመናት የነበሩት አሁንም ያሉት የኢትዮጵያ ገዢዎች ስለችጋር መከሰት የራሳቸውን ቸልተኛነት፤ አቅምየለሽነት በመካድ ነጻ በማድረግ በተጠያቂነት ያልወቀሱትና ሃላፊነት ያልሸሹበት ዘዴ የለም፡፡ በ1974 ዓ.ም. ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ ዲምብልቢይ ይፋ እስኪያደርገው ድረስ ረሃብ የለም ሲሉ ከርመው ነበር፡፡ በዲምብልቢይ ፊልም ሕዝቡ ረሃቡን አየ፤አዘነ፤ አንገቱን ደፍቶ አለቀሰ፡፡ የወገኑ በችጋር መቆላት ቅስሙን ሰበረው፡፡ የቀድሞው የሶሻሊስት ጁንታ መሪ መንግስቱ ሃይለማርያምም በ1984-85 የተከሰተውን ችጋር በድፍረተና በማንአለብኝት ክዶ ሁኔታውን በዓይናቸው ያዩትንና የታዘቡትን ሁሉ ገሸሽ በማደረግ ስችጋሩና እልቂቱ አንስተው ሲጠይቁት በመመጻደቅ ‹‹የምን ችጋር›› ነበር እያለ ያሾፍ ነበር፡፡

መለስ  ካለፉት መሰል ገዢዎች ሁሉ የተለየ ብልጣ ብልጥ ነው፡፡ በሃገሪቱ በላይ በሚንሰራፋው የችጋር ወቅት ሁሉ የህዝብ ግንኙነት መሳይ ተግባር ይወጣል፡፡ያለው “የምግብ እጥረት” በሚል ሽፋን በመጠቀም በጣም የጎላውን “ረሃብ” የሚለውን ቃል አይጠቀም እንጂ ከዚያ ባሻገር ምንም አይቀረውም፡፡ ለመለስ በሃገሪቱ ላይ ችጋር የለም፡፡ ያለው የምግብ እጥረት ነው፡፡ የከፋ የተመጣጣነ የምግብ እጦት ነው: ያለው የምግብ ዋስትና ማጣት ነው፤ የምግብ አቅርቦት ችግር ነው፤ እና ሌላም ልላም ይላል መለስ፡፡ እንደሱ የማሳሳቻ ጥምጥም አካሄድ እነዚህ ሁሉ የየእርሻ ዘዴን አጠቃቀም አለማወቅ ያመጣቸው ችግሮች፤የባለስላጣናቱ የእውቀት ድህነት፤ሙስና፤እና የወንጀለኛነት ውጤት ወዘተ  አይደሉም ቢልም፤እነዚህ ሁሉ ግን በችጋርና ድርቅ፤በተደጋገመ የዝናብ እጥረት ሳቢያ የሰብል መበላሸት፤የደኖች መጨፍጨፍ፤የመሬት መሸርሸር፤ ከመጠን በከላይ የመሬቱ ምርታማነት ማጣት እና በሌሎችም ሰበቦች የተፈጠሩ ችግሮች ናቸው፡፡ መለስ ባለፈው ጃነዋሪ 2011 ላይ ለሲ ኤን ኤን በሰጠው የቅጥፈት መግለጫ ላይ፡ “ኢትዮጵያ በጣም አሰቃቂ የሆነ የችጋር ወቅት ውስጥ ሆና፤ ሕዝቡም ለችጋር ተጋልጦ ሳለ አንተ በሌላ ሃገር ጉዳይ ጣልቃ ገብ በመሆን ይህን ያህል ገንዘብ እንዴት ታባክናለህ? ለሚለው የሰጠው ዓይን ያወጣ የቅጥፈት ምላሽ፤‹‹ማንኛቸውም ሰብአዊ ድርጅቶች ሊነግሩህ እንደሚችሉ በኢትዮጵያ ውስጥ ችጋር የለም ድርቅ ቢኖርም እኛ ግን ሕዝባችንን በአግባቡ ልንመግብ እንችላለን…….›› ብሎ አድበስብሶታል::

ዓለም አቀፎቹ የድህነት ቃራሚዎች/ አጎብጓቢዎች (poverty mongers/pimps “PMPs”) የምግብ እጥረትን ለማስረዳት ‹‹ሳይንሳዊ›› መገለጫ ፈጥረውለት፤ መለስ ደግሞ ያንን በሃገሪቱ ላይ ያንሰራፋውን የችጋር መጠንና በሕዝቡ ላይ የሚያደርሰውን እልቂት ለመደበቂያና መሸሸጊያነት እየተጠቀመበት ነው፡፡ እነዚህ ቃራሚ/አጎብጓቢዎች  ምንም ያህል የምግብ እጥረት ቢኖርና ገጦ ቢታይም ችጋር የሚለውን መግለጫ እየሸሹትና ሳይንሳዊውን መደባበቂያ መግለጫ በመስጠት ላይ ናቸው፡፡ መለስ ደግሞ በዚህ በተፈጠረው መግለጫ ውስጥ በመሸጎጥ ችጋረ የለም ይለናል፡፡ በነሱ ብልጥታዊ ሰበብ ደግሞ ሁኔታው በ‹‹የከፋ የምግብ ዋስትና እጦት›› ጭንቀት፤አጉል ገጠመኞች›… እያሉ ያሾፋሉ፡፡ በአፍሪካ ውስጥ በሳይንሳዊ ማስረጃ እንደተረጋገጠው ችጋር ሊኖር ጨርሶ አይችልም ብለው ሳያምኑበት ሊያሳምኑ ይጥራሉ፡፡ ስለዚህም የዚህ ሁኔታውን አፍኖ በዝምታ የማለፉ አድማና ዱለታ በማጭበርበሪያ ጭንብል በመሸፈን የኢትዮጵያን የችጋር አሰቃቂ መልክ ለመደበቅ ከፍ ያለ ጥረታቸው ነው፡፡

መለስና ከፍተኛ መኮንኖቹ በድርቅ ሳቢያ የተፈጠረውን የምግብ አቅርቦት እጥረት በአጭር ጊዜ ውስጥ ተቆጣጥረን እናሸንፈዋለን ብለው ምለው ተገዝተው ነበር፡፡የሃገሪቱ የድርቅ መከላከያን የአስቀድሞ ጥንቃቄ ሹም ስምኦን መቻሌ፤ መኩራራትና በእርግጠኝነት ‹‹ኢትዮጵያ በቅርቡ የምግብ ዋስትናን ጣረጋግጣለች›› ብሎ ነበር፡፡ ላለፉት በርካታ ዓመታትም መለስ “የሴፍቲ ኔት ፕሮግራም”፤ በምግብ ተረጂነት ላይ መተማመንን ለማስቆም፤ፈላጊውንና አቅራቢውን በማቀራረብና በቂ ምርት በማስገኘት የፕሮግራሙን  ስኬታማነት በማስተዋወቅ ላይ ይገኛል፡፡ በኦክቶበር 2011 መለስ ለታማኝ የፓርቲው ሰዎች የተለመደ ቅልመዳውን ሲያቀርብ ‹‹ከምግብ ተረጂነት የሚያወጣንንና እራሳችን በበቂ ለመመገብ የሚያስችለንን፤ በ2015 ከምግብ እርዳት ጋር የምንለያይበትን ዘለቄታዊ እቅድ ነድፈናል ብሎ ነበር፡፡ የመለስ የበቂ ምርት ማግኛ ዘዴም፤የሃገሪቱን በሚሊዮን ሄክታር የሚቆጠር ለም መሬት ለውጭ ኢንቬስተሮች ለሚላቸው ባዕዳን የተመረጡ የእርሻ ቦታዎችን በሊዝ በመችብቸብና ዓላማቸውም የሃገሪቱ ሕዝብ በችጋር እያለቀ ምርታቸውን ወደ ውጭ ሃገራት ለመሸጥና ለማትረፍ የሆነውን አሰራር ነው፡፡ መለስ የመሬቶችን የህዝብ ሃብት በማድረግ ከተረጂነት መውጫ መንገዱን ጥርቅም አድርጎ ዘግቶ የህዝቡን ባለንብረትነት ፈጽሞ ይቃወማል:: ይህ ደግሞ በየትም ቦታ ታይቶ የማይታወቅ ስርአት ነው፡፡ባለፈው ዓመትም የምግብ አቅርቦት ዋጋ ግሽበት 47.4 በመቶ እንደሆነ ቀጥሏል፡፡

በኢትዮጵያ የምግብ አቅርቦት እንደፖለቲካ መሳርያነት ጥቅም ላይ እየዋለ ነው፡፡ችጋር አዲሱ የተቃዋሚዎች ማጥፊያ፤ ማዳከሚያ ተስፋ ማስቆረጫ መሳርያ በመሆን በማገልገል ላይ ነው፡፡ መለስ ኢትዮጵያውያንን በችጋር ማጥ ውስጥ በመዝፈቅና ሆዳቸውን ባዶ በማድረግ ሕዝቡ አንገቱን እንዲደፋ ሞራሉን እንዲያጣ፤ ጥንካሬው ተሰብሮ አገልጋዩ እንዲሆን፤መንፈሱ እንዲላሽቅና ህሊናው የመከራ ቋት እንዲሆንና ማሰብ እንዲያቅተው በማድረግ ገዢነቱ ተሳክቶለታል፡፡ ሕዝቡም አቅሙን ተገፏል ወኔው ተዳክሟል፡፡ የመለስን አገዛዝ የሚቃወሙ ሁሉ ሰብአዊ የምግብ ተረጂነት መብታቸውን መገፈፍ ብቻ ሳይሆን፤ለስደት በሚዳርገው ዘዴ ስደተኛ በማድረግ፤እነሱነታቸውን በማጣጣልና ተስፋ በማስቆረጥ፤አለያም የያዙትን የእርሻ ማሳቸውን በሰበብ አስባቡ በመቆራረጥና በማሳነስ፤የብድር ተጠቃሚነት መብት እንዳይኖራቸው፤ የማዳበርያና የዘር እህል እንዳያገኙ በማድረግና በሌላም ሌላ ግፍ ማዳከሙ ተሳክቶለታል፡፡ የጋምቤላን ጉዳይ በተመለከተም የዓለም አቀፉ የሰብአዊ መበት የሚጥሰውን ነዋሪዎች ከያዙትና ካለሙት መሬታቸው ላይ በግዴታ እንዲለቁ በማድረግ አንድ ሙሉ ነዋሪ ቦታውን ሕንዶች በኢንቬስተርነት እንዲነጥቋቸው ተደርጓል፡፡ ከብዙዎቹ ተሟጋቾች መሃል ሁማን ራይትስ ዎች፤ በሰብአዊ የምግብ እርዳታ ፕሮግራሙ ላይ: ሲዘግብ ‹‹የኢትዮጵያ መንግስት በተከታታይ የምግብ እርዳታውን እንደ ፖለቲካ መጠቀሚያ፤ ተረጂውን ማግለያ፤ ለመቆጣጠርያነት እያዋለው ነው፡፡ የገዢውን ፓርቲ ጨዋታ ለመቀላቀል ፈቃደኛ ካልሆንክ በተገቢው የተቆጣጣሪ የውጭ ታዛቢ ግበረ ሃይል እንዳትታገዝ ሆነህ ከጨዋታው ውጪ ትደረጋለህ፡፡ ስለዚህም የተጠናከረና ወለም ዘለምን የማይቀበል በራሱ ተማምኖ የሚንቀሳቀስና ግድፈቱን ይፋ የሚያወጣ የውጪ ታዛቢ ካለተፈጠረል በስተቀር ይህን ጨቋኝ ኢሰብአዊ የሆነ ገዢ መንግስት ማስተካከል የማይሞከር ነው›› ብልዋል:: በ2011 ላይ በሃገሪቱ ውስጥ ካለው ገዢ ፓርቲ ጋር ተወዳጅተውና ተቀብለው ከሚንቀሳቀሱት ውጪ በፖለቲካ አመለካከት ልዩነታቸው ሳቢያ ከአሜሪካን መንግስት ተችሮ የነበረው 850 ሚሊዮን ዶላር የማግለል ስርጭት በመለስ ፓርቲ ስለተፈጸመው የስርጭት ደባ የአሜሪካው ስቴት ዲፓርትመንት ለማጣረት ቃል ቢገባም፤‹‹እስካሁን ድረስ ስለጉዳዩ አንድም የወጣ ዘገባ የለም››:: በ2011 የአሜሪካው የምርምር ቢሮ የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር በ2050 በመጠን በመግዘፍ ወደ 278 ሚሊዮን ያሻቅባል፤ ብሎል:: በዚህም በሽታ ችጋር ጦርነትና እልቂት ሌላም  ሌላም ሰበብ ሕዝቡን ወደ ምግብ አምራችነት ግዳጅ ያሰድገባዋል፡፡ የመለስ ገዢ መንግስት ብሔራዊ የቤተሰብ መምሪያ እቅድ በአግባቡ መዘርጋት ስላልቻለ ወደ ተፈራው ችጋርና ችግር በተፋጠነ ሂደት መግባቱ የማይቀር ነው፡፡

በኢትዮጵያ የሚከሰተው ችጋር 90 በመቶው ሰው ሰራሽ ነው፡፡

የዓለም ባንኩ መሪ ኤኮኖሚስት ዎልፍጋንግ ፌንግለር በኦገስት 17 2011 ላይ እንደ ዓለም አቀፍ የባንክ ሰውነቱ ለአስተያየቱ እጅጉን ታማኝ ነበር፡፡ ሲናገርም፡- ‹‹ በአፍሪካ ቀንድ ያለው የችጋር ጉዳይ ለዋጋ የሚጠየቀው የተጋነነነ ዋጋና በሚፈጠረው የእርስ በእርስ ግጭት የመጣ እንጂ በተፈጥሮ ሳቢያ የተከሰተ አይደለም፡፡ይህ ችግር ሰው ሰራሽ ነው፡፡ድርቅ በተደጋጋሚ ተከስቷል፡፡በኢትዮጵያ ውስጥ ሁኔታው ወደ ርሃብ እንዲቀየር ያደረገው ግን ዋነኛው ሁኔታ መጥፎ ፖሊሲ መፈጠሩ  ነው፡፡በሌላ አገላለጥም በኢትዮጵያ ውስጥ መጥፎና እኩይ አስተዳደርየችጋሩ መንስኤ ነው እንጂ ድርቅና የአካባቢ ዓየር ያመጣው ጣጣ አይደለም፡፡ የኦክስፋም ዓለም አቀፍ ዳይረክተር የሆኑት ፔኒ ላውረንስ፤ኢትዮጵያን ከጎበኙ በኋላ የደረሱበት ድምዳሜ ‹‹ሕብረተሰቡ ለሰብሉ የመስኖ ውሃ ቢኖረው፤የሰብሉ ማጠራቀሚያ ጎተራ በብቃት ቢያገኝ፤እና በቂ ውሃ ከዝናቡ ማቆርያ ቢሰራለት ማንኛቸውንም የሚያጋጥማቸውን ችግር ሁሉ በቀላሉ ሊቋቋሙት ይችላሉ በማለት ዘግበዋል፡፡ የዓለም አገልግሎት የአፍሪካ ኤዲተር የሆኑት የቢቢሲው ማርቲን ፕላውት ሲሉ፤ያሁኑ በገበሬው ላይ የወረደበት ችግር መንስኤ መንግስት መሬቱን የራስህ ነው ግን አታዝበትም አይነት ደንብ በማውጣት ገበሬው ከዚያ እንዳይነቀሳቀስ ለማድረግ ያወጣው ደንብ  በመሆኑ ሊነሱ የሚገባቸው መሰረታዊ ጉዳዮች፤ ሶሻሊዝምን ያወገዘው መንግስት እና ነጻ የገበያ ኤኮኖሚን እተላለሁ የሚል አካል፤ መሬትን በተመለከተ ከመንግስት ቁጥጥር ውጪ ሊሆን አይችልም በማለት መመጎቱ ለምንድን ነው? ለምበንስ ስርአት ያለው የመስኖ ውሃ እንዲዘረጋ አልታቀደም? የሰብል ማከማቻ ሰፋፊ ቋትስ ለምን የለም? የዝናብ ውሃ መማቆርያስ ለይስሙላ ሳይሆን በወጉ ለምን አልተዘጋጀም? በእርግጥና በእውነት ግን ለኢትዮጵያ መለስ ዜናዊ የምግብ ዋስትና ፖሊሲ አለው?

ለዓመታት በሰብአዊ  የእህል ምጥዋት አረንቋ ውስጥ የተዘፈቀችው ኢትዮጶያ በቅርቡ የምግብ ዋስትናን ታረጋግጣለች ብሎ ማሰብ ከቅዠት ውጪ ሊሆን አይችልም፡፡ የመጪው ዐመታት በአፍሪካ ቀንድና በሳህል ሊያጋጥም በሚችለው ችጋርና የረሃብ ሰደድ እጅጉን ያስጨንቃቸዋል፡፡ ባለፈው ወር የአሜሪካን መንግስት ሊከተል የሚችለውን የዝናብ እጥረትና የሚያመጣውን የድርቅ ሁኔታ ለመቋቋምና ሕዝቡን ከችጋር ሞት ለመታደግ ተጨማሪ የ200 ሚሊዮን የምግብ ዕርዳታ ለመቸር ቃል ገብቷል፡፡የአሜሪካን መንግስት ለኢትዮጵያ፤ ኬንያና ሶማልያ የ1.1 ቢሊዮን ዶላር የሰብአዊ ዕርዳታ ሰጪ ነው፡፡

በሜይ 19 ላይ ፕሬዜዳንት ኦባማና የ G8 መሪዎች እንደገና ሊያጤኑት የሚገባቸው 3 መሰረታዊ ጥያቄዎች አሉ፡፡ማለቂያ የሌለው እርዳታ ለአፍሪካ ቀንድ ሃገራት መስጠቱ የሚያስከትለው የሞራል ድቀት ምን ሊሆን ይችላል? እነዚህን ፈላጭ ቆራጭ ግፈኛ ገዢዎች መርዳቱና እነሱ ያንን መተማመኛ በማድረግ ተደላድለው ለግፍ አገዛዝ በእርዳታው ገንዘብ የበለጠ መመቻቸታቸው የረጂዎቹን የሞራል ኪሳራ አያስከትልም? በአፍሪካ ውስጥ በተደጋጋሚ በመከሰት ላይ ያለውንስ የችጋርና የድርቅ መፈራረቅና በተደጋጋሚ መከሰት ዘወትር ሰበቡ የዓየር ለውጥ በመሆን መቀጠሉስ በአፍሪካ ላለው የማይነቀል የምግብ እጥረት አስተዋጽኦ አያደርግም? የ G8 መሪዎች ለመለስ ዜናዊ ሊያቀርቡለት የሚገቡ ሌሎች ጥያቄዎች አሉ፡፡በሚሊዮን ሄክታር የሚቆጠር ለም መሬቶቹን ለህንድና ለአረብ ሃገራት የምግብ ዋስትና ማምረቻነት እየሸጠ የራሱን ሕዝብ ወደ ችጋርና ሞት የሚዳርግን ሃገር፤ ዓለም መርዳት ያለበት በምን መመዘኛና ሰበብ ነው? ለምንስ ተብሎ ነው የሚሰጠውን የሰብአዊ የምግብ አቅርቦት መርጃ ለፖለቲካ መጠቀሚያ በማድረግ ተቃዋሚዎቹን ለመጉጃ፤ ለማስደንበርያ፤ ለማስራቢያ፤ ለማፈናቀያ፤ዴሞክራሲን ለመጨፍለቂያ፤ሰብአዊ መብትን ለመድፈሪያ፤ ፍትህን ለማጥፋት መጠቀሚያ ለሚያደርግ ሃገርስ ለምን ተብሎ ነው የሚረዳው?

የ G8 መሪዎች ስለ‹‹ምግብ እጥረት›› መነጋገር ይችላሉ፡፡ በኢትዮጵያና በአፍሪካ ቀንድ ላለው ችጋር ምላሽ ግን፤በረሃብ በመሰቃየት ላለው ሕዝብ እፍኝ ምጽዋት መቸርና፤ ለፈላጭ ቆራጭ ጨካኝ ገዢዎች  የመዝናኛ ወቅትና የነጻ ምሳ አቅርቦት የችግሩ መቅረፊያ ሊሆን አይችልም፡፡ እፍኝ ምጽዋት ችጋርን ከማጥፋት ይልቅ የሞራል ውድቀትን በማስከተል የዘልአለም ተመጽዋችነትን ፍላጎት ያበረታታል፡፡ መለስና መሰለቹ ግፈኛ የአፍሪካ ጨቋኝ ገዢዎች የምግብ እጥረቱን አስመልክቶ ለሕዝቡ ዘላቂ መፍትሔ የማስቀመጥ ሃሳብም ፍላትም የላቸውም:: ምክንያቱም ዓለም ሁል ጊዜ ረሃብን በተመለከተ እንደማይጨክን ስለሚያውቁ ችግሩን እያወቁት አፍነው በመያዝ በመጨረሻው ደቂቃ ላይ ጩኸታቸውን ማቅለጣቸው የተለመደ ዘዴያቸው ነው፡፡የአሜሪካን መንግስት እነደዓለም ቀደም ሹመኛነቱ ርሃብ በገባበት ሁሉ ደርሶ እርዳታ በመስጠት ተጠቂዎችን ከችጋር ማዳንን የሞራልና ሰብአዊ ግዴታ አድርጎ ያየዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ለዚህ ሁኔታ የሚሰጡትንም የልማት እርዳታ ችሮታ፤ብድርን፤የበጀት ድጋፍ ችሮታውንም ለዴሞክራሲ ማበብና ተግባራዊነቱ፤ የሰብአዊ መብት መከበርና መየበቅ፤የህግ የበላይነትን ማክበርና ለሱም መገዛትን ማረጋገጫ ጉልበትም አድርገው የመያዝ የውዴታ ግዴታ አለባቸው፡፡

በ2010 በተካሄደው የማስመሰያ ምርጫ የመለስ ፓርቲ 99.6 የፓርላማ ወንበሮችን አሸነፍኩ ብሎ ስልጣን መያዙ ይታወሳል፡፡ ባለፉት ዓመታት ውስጥ መለስ ዜናዊ አስገራሚ የኤኮኖሚ እድገት አሳይተናል በሚል የማይጨበጥ ተስፋ ቢስ እድገት ከመፎከር ውጪ እድገቱን ግን ማሳየት ካለመቻሉም ባሻገር፤በሃገሩ ውስጥ ያለውን የምግብ እጥረት ለማሸነፍ እዚህ ግባ የሚባል ስትራቴጂ ማቅረብ አልቻለም፡፡ በሃያ አንድ ዓመታት የመለስ አገዛዝ ውስጥ፤ኢትዮጵያ ከእርዳታ ለማኝነት ሳትላቀቅና በየጊዜው የልመናዋ ቋትም እየበዛ ከመሄድ አልተላቀቀም፡፡ ኢትዮጵያውያን እጅጉን በከፋና መፍትሔ በሌለው የምግብ እጥረት ውስጥ መዘፈቁ፤ከችግሩ ጋር በቀጥታ ሊታይ በሚችል መልኩ የፖለቲካ አሰራር ባለመዘርጋቱ ነው፡፡ የሕንዱ የኤኮኖሚ የኖቤል ሽልማት አሸናፊው አማርቲያ ሴን ርሃብን ለማስወገድ ትክክለኛው መንገድ፤ዴሞክረሲን ሕዝባዊ በማድረግ ሰብአዊ መብትንም በማጠናከር ነው በማለት ያስረዳል፡፡ በዓለም ታሪክ ውስጥ፤ዴሞክራሲ በትክክለኛው መልኩ በሚተገበርበት ቦታ ችጋር ደርሶ አያውቅም፡፡ ምክንያቱም ዴሞክራቲክ አደስተዳዳሪዎች ምርጫቸውን ማሸነፍ ስለአለባቸውና  የህዝብንም ሂሳዊ አመለካከት በግላጭ ስለሚቀበሉ ያጋጠማቸውን ችጋርና ድርቅ መቋቋምና አጥጋቢ መፍትሔ የማስገኘት ግዴት ስለአለባቸው ነው፡፡

የሴን ዴሞክራሲያዊው ‹‹የድርቅን አስቀድሞ ማስጠንቀቂያ አውታሮች”  የሉም:: ተቃዋሚ ፓርቲዎች አላአንዳች ሰበብ ይጨፈለቃሉ፤ መሪዎቻቸው ለመከራ ይዳረጋሉ፤ይወነጀላሉ ይታሰራሉ፡፡ ነጻው ፕሬስም ይታፈናል፤ ነጻ ጋዜጠኞችም ገዢውን መንግስትና ሹመኞቹን በሚፈጽሙት ደባና ሙስና በማጋለጣቸውና ገዢዎችም ለሚከተሉት ጭፍን የማንአለብኝ አገዛዝ አስተሳሰባቸውን በመግለጽና ትክክለኛውን መንገድ በማመላከታቸው ለወህኒ ይዳረጋሉ፡፡ ስለችጋሩ እውነታውን ሊዘግቡ አይፈቀድላቸውም፡፡ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፤ድርቅን ለማስወገድ የተቋቋሙት ድርጅቶችም ጭምር አረማመዳቸው ሁሉ ጥንቃቄን ባጠናከረ መልኩ በፍርሃት  መሆን እንዳለበት ተረድተዋል፡፡ ህጉ ሀገሬውንም የውጭውንም የእርዳታ ተግባር ፈጻሚውንና የሰብአዊ መብት ተሟጋቹን በወንጀለኛነት የሚያካትት ሆኗል፡፡ መለስ ዜናዊ አመጣዋለሁ እያለ በማይተገበር የሃሰት የዴሞክራሲ ነጻነት እውነታ በመዋሸት የተካነ ነውና የዓለም አቀፍ እርዳታ ድርጅቶችን በዚህ መንገድ ሲያታልልና ሲዋሻቸው ኖሯል፡፡ ባለፉት በርካታ ዓመታት ሂደት ውስጥ መለስ ሊመጣ ነው ደርሷል፤ በዝግታ እንደርስበታለን ብለን አቅደን ፈጥነን ደረስንበት የሚለውን የዴሞክራሲ ነጻነት እንኳን ልናየውና አካሉ ልንሆን ቀርቶ በሕልማችን እንኳን ለማየት ተስኖናል፡፡ ይልቁንስ የመለስ አገዛዝ ጭካኔ በየቀኑ ከአቅም በላይ እየሆነ፤ አገዛዙ ሕዝብን ኑሮ እንዲመረው የሚያደርግ፤ ሲጨንቀው በሚያወጣቸው እዛዞችና አዋጆች ግራ መጋባት፤ የተማረው ዲግሪውን ታቅፎ ኮብል ስቶን መጥረብ፤ ያን ኮብል ስቶን ሊጠርበው የሚገባው የተማረው የሚቀመጥበት ወንበር ላይ በድፍረት መጎለትና የመለስን እድሜ መለመንን በየቀኑ እያደገና የሕዝቡም ችግርና ስቃይ በዚያው ልክ ሰበዛ ማየት ግን ተችሏል፡፡

አሜሪካ ለኢትዮጵያ ምን ሊያደርግ ይገባል?

አሜሪካ ለኢትዮጵያ ሊያደርግ የሚገባው፤አደርጋለሁ በማለት ሲያውጅ የነበረውን ብቻ ነው፡፡ በ2009 ፕሬዜዳንት ኦባማ ጋና: አክራን በጎበኙ ወቅት፤ ሲናገሩ እንዳሉት:-

ልማት ሁል ጊዜ የሚሳካው መልካም አስተዳደር ሲኖር ነው፡፡ ታሪክ ትክክለኛውን ውሳኔ ያቀርባል፡፡የራሳቸውን ሕዝቦች ውሳኔ ሚያከብሩ መንግስታት፤በጉልበትና ማንአለብኝነት የሚገዙ ሳይሆኑ በሕዝባዊ ይሁንታ የሚያስተዳድሩ፤የበለጠ ፍሬያማ፤ የተረጋጉ፤ከፈላጭ ቆራጭና በግፍ ከሚገዙ የበለጠ የተሳካላቸው ናቸው፡፡ የራሳቸውን ምቾትና የግል ሃብታቸውን በማሰቀደም ሃገራቸውንና ሕዝባቸውን የሚበዘብዙ መሪዎች ሃገር ጨርሶ ለሃገራቸው ጠቀሚ ንብረት አያተርፉም፡፡ ማንም ቢሆን የሕግ የበላይነት ተረግጦ በሙስናና በዘረፋ በሚመራ ሃገር ውስጥ መኖርን አይመኝም፡፡ ይህ አይነቱ ስርአት ዴሞክራሲያዊ ሳይሆን የግፍና የመከራ አገዛዝ ነው፡፡ ያን የመሰለውን የግዛት ዘመን ጨርሶ ለመጣልና ለማስወገድ ወቅቱ አሁን ነው…….. በ21ኛው ክፍል ዘመን  ችሎታ ያላቸው፤ ታማኝ የሆኑ፤ለተጠያቂነት የበቁ ኢንስቲቲዩሽኖች የስኬት ማረጋገጫዎች ናቸው—– ጠንካር ምክር ቤቶች፤የሲቪል ማሕበረሰብ አባላት፤ታማኝ የፖሊስ አባላትና የመከላከያ ሃይል፤ ነጣ ይፍትህ ስአት አባላት፤ነጣ የመገናኛ ብዙሃን፤ንቁ የሲቪል ማሕበረሰብ አባላት፤ እነዚህ ናቸው ለዶሞክራሲያዊነት ነፍስ ዘርተው የሚያገለግሉት ምክንያቱም በሕዝቡ የእለት ተእለት ኑሮ ውስጥ አስፈላጊዎቹ መዘውሮች፡፡ …ታሪክ ከነዚህ ጀግና አፍሪካውያን ጎን ይቆማል እንጂ በጉልበትና አላስፈላጊ በሆነ መንገድ ስልጣንን የሙጢኝ የሚሉትና ሕገ መንግስታቸውን ለራሳቸው እንዲሆን በዘፈቀደ ራሳቸውን በስልጣን ለማቆየት በሚለውጡትና በማያከብሩት ጎን አይኖርም፡፡ አፍሪካ ማን አለብን ባዮችንና በጉልበታቸው የሚመኩትን አትፈልግም፡፡ የምትፈልገው ጠንካራና ጉልበታም የሆኑ ድርጅቶች (ኢንስቲቲዩሽኖች) ነው፡፡ በተሻለ አስተዳደር  እርግጠኛ  ነኝ አፍሪካ ተጨባጭ  የሆነ ሰፊ ልማትና የእድገት ራዕይዋን የማሳካት ተስፋዋ እውን ይሆናል፡፡

ካሁን በፊት የቀረቡ የጸሃፊው ጦማሮችን  ለማግኘት እዚህ ይጫኑ >> http://www.ecadforum.com/Amharic/archives/category/al-mariam-amharic

Similar Posts

Leave a Reply