ለሴራሊዮን ፍትሕ! ለኢትዮጵያስ?

Click here for PDF

ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ

የግፍ ጦረኛው ቻርልስ ቴይለር ወደ ወህኒ!

በአራት ዓመታት ውስጥ በ420 የፍርድ ሂደት፤ ቀናት: 115 ምስከሮች ተሰምተው፤ 50,000 ገጾች ያሉት ማስረጃ ተገናዝቦ፤ 1,520 መረጃ  ኤግዚህቢቶች ከተመሳከሩ፤ በህውላ ለሴራ ሊዮን በተባበሩት መንግስታት በተቋቋመው ልዩ ችሎት በቀረበበት 11 ዝርዝር ክስ ቻርልስ ቴይለር: የግፍ ጦረኛውና የቀድሞው የላይቤርያ ፕሬዝደንት: ጥፋተኛ ተብሎ ተፈርዶበታል፡፡ በሰብዊ መብት ላይ ባደረሰው ወንጀል፤ ግድያ፤ አስገድዶ መድፈር፤ ሲቪል ማህበረሰቡን አካሉን በማጉደል፤እጅ በመቁረጥ፤ ሕጻናትን በጦር ሜዳ በማሰማራት፤ የፍትወት ባርነት በማካሄድ፤ ከኖቬምበር 30, 1966 እስከ ጃንዋሪ 18, 2002 በሴራ ሊዮን ሽብር በመንዛትና በማስፋፋት ወንጀል ቻርልስ ቴይለር ተበይኖበታል፡፡ በሴራ ሊዮኑ ግጭት 50,000 ዜጎች ለሞት ተዳርገዋል ሲል የተባበሩት መንግስታት ተናግሮል፡፡ ቴይለር በጭካኔ የተሞሉትን አረመኔዎች እነ ፎዲ ሳንኮህ: ሳም ‹‹ቢንቢው›› ቦካሪን: እና ኢሳ ሴሳይን በመርዳቱና በመደገፉ፤ እንደባርያ በቁፋሮው ላይ ተሰማርተው በሚያወጡት የአልማዝ ማዕድን ሽያጭ በሚከፈለው የደም አልማዝ ገንዘብ እቅድ በማውጣት፤ የጦር ስልት በመንደፍ፤ መሣርያ በመስጠት ላደረገው የግፍና የጥፋት ትብብር ነበር የስወነጀለው፡፡ ቴይለር በሚቀጥለው ወር ላይ የፍርድ የስራት ቅጣት ውሳኔው ይሰጠዋል፡፡

Charles Taylor

በካሳሾች የምስክር ሂደት ላይ በማስረጃ አቀራረብ ከሴ ራሊዮን የጭፍጨፋ ቡድን ጋር ቴይለር የነበረውን ግንኙነት በተመለከተ የነበሩት ማስረጃዎች ጥቂት በመሆናቸው ከሳሽ ችግር ነበረበት፡፡ በማንኛውም ወቅት በአመጽያኑ ግንባር መገኙትን በትክክል የሚያሳይ ምንም ማስረጃ አልነበረም፡፡ ቴይለር ወደሴራ ሊዮን የላካቸው የላይቤርያ ተዋጊዎች በሴራሊዮን ውጊያ አውድ ላይ ለመገኘታቸው ተጨባጭ ማስረጃ አልነበረም:: ከሳሾች ክሳቸውን ለማጠናከርና ተቀባይነት እንዲኖረው ለማድረግ ከቴሌፎንና ከሬዲዮ ግንኙነት የተጠለፉ ንግግሮችን፤በቴይለር የደህንነት ቡድን ውስጥ የነበሩት ስዎች ከሰጡት የቃል ማስረጃ እና ሌሎችም ቴይለር ወደ ሴራ ሊዮን መሣርያ ለመላኩ ማስረጃ የሆኑትን በማሰባሰብና ለዚህ ቴይለር (የደም) የአልማዝ ክፍያ እንደተደረገለት የሚያሰይ ተጨባጭ ማሰረጃ ነበር ያቀረቡት፡፡

“የማዘዙን ሃላፊነት” (command responsibility) በተመለከተ ቴይለር ክሱን አልተቀበለም:: ለሴራ ሊዮን የተሰየመው ልዩ ፍርድ ቤት የሚመራበት ደንብ አንቀፅ 6(3) ግን እንደሚከተለው ያዛል “የበላይ ሃላፊው በእዙ ስር ያሉት በሕግ የተከለከለን ወንጀል እንደሚፈጽሙ ድርጊቱን ካወቀ ወይም የሚያውቅበት ሁኔታ ካለ፤ይህንንም ድርጊት እንዳይፈጸም ካላደረገና ፈጣሚዎችንም እንዲቀጡ ካላደረገ፤ ተጠያቂነት:  አለበት”ይላል:: ቴይለር የRUF አመጺአን ወንጀል እንደሚፈጽሙ ሰብአዊ መብትን እንደሚደፍሩ ቢያቅም ሙሉ ቁጥጥር እነሱ ላይ እንዳለው  በቂ ማስረጃ አልነበረም:: ቴይለር ስለማንኛውም በሴራ ሊዮን ስለተፈጸመው ወንጀልም ሆነ ሰብዊ በደል ጨርሶ እንደማያውቅና ሃላፊነትም እንደማይወስድ ለችሎቱ አስታውቋል፡፡ እራሱን የሠላም መልዕክተኛ በማድረግ ለሰባት ወራት ለራሱ ምስክርነት ቆሞ ሲከራከር ነበር፡፡

የፍርዱ ሂደት ከወጪ አንጸር 250 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር አስወጥቷል፡፡ ይህን ሁሉ ወጪስ ማውጣት ያስፈልግ ነበር? ፍትሕ የተቀመጠለት ዋጋ አለ እንዴ? ተመኑ ስንት ይሆን?

የአፍሪካውያን የጸረ ሰብአዊ መበት ስብስቦች መጠራቀሚያ ሰሌዳ

የዓለም አቀፉ የፍትህ ችሎት (ICC) አሁን በህይወት ላሉትና ላለፉትም የአፍሪካ አውሬ ጨቋኝና ግፈኛ ገዢዎችን ፍርድ ለማቅረብ ይጥራል፡፡ የኮት ዲ ቯሩ የቀድሞ ፕሬዜዳንት ላውረንት ባግቦ፤ የሱዳኑ ፕሬዜዳንት ኦማር አል በሺር፤ (ላለፉት ለሞአመር ጋዳፊ) የመያዣ ማዘዣ አውጥቷል፡፡ ጋብጎ ባስከተለው ግድያ፤አስገድዶ መድፈርእና ሌሎችም የግብረስጋ ግንኙነት ማስገደድ፤ያለፍርድ በመግደልና በሌሎችም የሰብአዊ ጥሰቶችና በምርጫው ወቅት ባስከተለው የሕዝብ እልቂት  በዓለም አቀፉ የሄይግ ፍርድ ቤት ፍርዱን ሊቀበልና በቴይለር ወንበር ላይ ሊቀመጥ ግርግር በሌበት ሁኔታ ወደ ዓለም አቀፉ ፍርድቤት አምርቷል፡፡ አልበሽር በዓለም አቀፉ ፍርድቤት የ2009 ማዘዣ ሲሳለቅና ሲዘባበትባቸው፤ ‹‹ንገሯቸው፡፡ለሁሉም ንገሯቸው፤ለአቃቤ ሕጎቹ፤ለችሎቱ አባላት፤እና ለዚህ ፍርድ ቤት ደጋፊዎች በሙሉ ንገሯቸው፤ሁላችሁም ከጫማዬ ስር ናችሁ በሏቸው›› አለ:: (ጊዜው ሲደርስ ግን በሺር በዓለም አቀፉ ግርድ ቤት ጫማ ስር መሆኑ አይቀሬ ነው፡፡) የተባበሩት መንግሥታት በበሺር አገዛዝ ወቅት 300,000 ሰዎች የገቡበት ጠፍቷል ብልዋል:: ከበሺር ጋር አዳብሎ የተባበሩት መንግሥታት በሌሎችም የሱዳን ዜጎች በእነ ጠበቃውና የሰብአዊ መብት ጉዳዮች ሃላፊው አህመድ ሃሩን፤ በዳርፉር ነጻ አውጪዎች ላይ ከበሺር ጋር የተባበረው የሚሊሺያ መሪ አሊ ኩህሻዬብ፤ ባህር ኢድሪስ አቡ ጋርዳ የነውጠኞች መሪና በሌሎች ሁለት ሱዳናውያን ላይ የመያዣ ትእዛዝ አውጥቷል፡፡

የዓለም አቀፉ የፍትህ ችሎት (ICC) በሰብአዊ ጥሰት በኬንያውያንም ላይ ክስ መስርቷል፡፡ የዝነኛው ኬንያዊ የነጻነት ታጋይና ነጻ አውጪ ጆሞ ኬንያታ ልጅ የገንዘብ ሚኒስትሩ ኡሁሩ ኬንያታ  በ2008 በተካሄደው ምርጫ ወቅት በፕሬዜዳንታዊ ምርጫ ተወዳዳሪዎቹ በራይላ ኦዲንጋና ሙዋይ ኪባኪ መሃል በተፈጠረው የምርጫ ግጭት ክስ ተመስርቶበት በዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት ማዘዣ እንደወጣበትና ለፍርድ እንደሚቀርብ ሲሰማ ሥራውን በፍቃዱ ለቋል፡፡ የተባበሩት መንግስታት ከዲሴምበር 2007 እስከ ፌብሪዋሪ 2008 ባለው ጊዜ በተፈጠረው የሳምንታት ግጭት ከ1,200 ሰዎች ያላነሱ እንደሞቱና፤ 600,000ሺ ሰዎች ደግሞ ተገድደው ተፈናቅለዋል፡፡ በዩጋንዳ የዓለም አቀፍ ፍርድ ቤቱ የ‹‹ሎርድ ሬዚዝስታንስ አርሚ› ቁንጮ አመራር አባላት ላይ ጉደኛውን ጆሴፍ ኮኒይን እና ምክትሉን ቪንሰንት ኦቲና ሌሎች ሶስት ከፍተኛ የጦር አዘዦች ላይ ክስ መስርቷል፡፡ በዴሞክራቲክ ሪፑብሊክ ኮንጎ የተለያዩ የአመጽ ተካፋዮች የኮንጎ ፖለቲከኞችና የጦር መሪዎች ወታደሮች፤ ቶማስ ሉባንጋን ዳዪሎን፤ ጄን-ፒየር ቤምባ ጎምቦ፤ቦስካ ኒታንጋዳ፤ማቲው ኡንጉዶሎ ቹ እና ሌሎች ሁለት አባላትም ክስ ተመስርቶባቸዋል፡፡የዓለም አቀፍ ፍርድ ቤቱ በሙአመር ጋዳፊ ልጅ ሳይፍ አል-ኢስላም ላይ፤ በሊቢያው የስለላ መዋቅር ሃላፊው በዚህ ዓመት ማርች ላይ በሞሪታንያ በተያዘው አብዱላህ አል-ሴኑሲ ላይም የመያዣ ማዘዣ አውጥቶባቸዋል፡፡ ሊቢያውያን በሁለቱ ሰዎች ላይ የዓለም አቀፍ ፍርድ ቤቱ ወደ ሄይግ እንዲላኩ ያወጣውን ማዘዣ በመቃወም ሁለቱ ሰዎች በሃገራቸው እንዲዳኙ እንዲፈቅድ ጠይቀዋል፡፡

በኢትዮጵያ ውስጥ ግን የዓለም አቀፍ ወንጀለኞች ፍርድ ቤት ክስም  ምርመራም  አልመሰረተም

በሱዳን፤በኬንያ፤በዩጋንዳ፤በዴሞክራቲክ ሪፑብሊክ ኮንጎ፤ በሊቢያ እና በሌሎች አገሮች የሰብአዊ መብት ጣሾችን ወንጀለኞችን እያሰሰ ማዘዣ ሲያወጣባቸው የተባበሩት መንግስታት ሴኪዩሪቲ ካውንስል ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያንን ችላ ብሏቸዋል፡፡ ሰብአዊ ጥሰትንና የጦር ወንጀለኛነትን ድርጊቱን በኢትዮጵያ በተመለከተ፤ በገሃድ የሚያመለክቱ በቂ ማስረጃዎች በዶኩሜንት ተካተው አሉ፡፡

በኢትዮጵያ በ2006 የተፈጸመውን እንዲያጣራ በመለስ ዜናዊ የተዋቀረው አጣሪ ኮሚሽን ባቀረበው ሪፖርት፤ በትንሹ ከሕግ ውጪ በሆነ መልኩ፤ባዶ እጃቸውን መብት ጥየቃ የወጡት 193 ሰላማዊ ኢትዮጵያውያን መገደላቸውን፤763 ሰዎች መቁሰላቸውን፤ወደ 30,000 ሺህ የሚጠጉ በ2005 የምርጫ ወቅት ለእስራት መዳረጋቸውን አጣሪ ኮሚሽን ይፋ አድርጓል፡፡ ኮሚሽኑ እንዲያጣራ የተፈቀደለት በጁን 8 2005 በአዲስ አበባ የነበረውን ሁኔታና እንዲሁም ከኖቬምበር 1 እስከ 10 2005 በሌሎች አካባቢዎች የነበረውን ሁኔታ ነበር የታዘዘው፡፡ አጣሪ ኮሚሽን በሌሎች አካባቢዎች ከሕግ ውጪ የተፈጸሙ ግድያዎችና የመቁሰል አደጋዎች እንዲሁም ለእስር መዳረግን በተመለከተ በቂ ማስረጃ ነበረውና ያ ከቀረበው ጋር ቢጣመር ኖሮ ቁጥሩን ከእጥፍ ባለፈ ባገዘፈው ነበር፡፡ ይህ ሁሉ ግድያ መቁሰል ለእስር መዳረግ የተፈጸመውም መለስ ዜናዊ ጦሩ፤የስለላ መዋቅሩ በራሱ የእዝ ሰንሰልት ስር መሆናቸውን በይፋ ለህዝብ  ካሳወቀ በኋላ ነበር፡፡

አጣሪ ኮሚሽኑ እነዚህ ለሞት የተዳረጉት ሰላማዊ ሰዎች በሙሉ ከጦሩና ከስለላ አባላት በተተኮሰና ግንባራቸውንና ደረታቸውን በመመታት የሞቱ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡ኮሚሽኑ የሰለጠኑ የበቁ ነፍሰ ገዳይ ተኳሾች በጭፍን አነጣጣሪ ቅልጥም ሰባሪነታቸውን በማረጋገጥ ያገኙት ላይ ሁሉ ቃታ እየሳቡ አላስፈላጊ የሆነ ግድያ ፈጽመዋል፡፡ ኮሚሽኑቀ በተጨማሪም ኖቬምበር 3 2005 ሰቀቀናዊ የቃሊቲ ወህኒ ቤት ትርምስ ተነሰትዋል ተብሎ የጥበቃ አባላቱ 1,500 ጥይቶቻቸውን በ15 ደቂቃዎች ውስጥ አርከፍክፈው 17 እስረኛ ገድለው 53ቱን ቁስለኛ አድርገዋል፡፡ ኮሚሽኑ በመረመረው 16,990 ገጽ ማስረጃ ከ1,300 እማኞች ባገኘው ምስክርነት፤ ወራት በፈጀው ምርመራው ይህን እውነታ አረጋግጧል፡፡ በዚህም ተግባር ላይ ተሰማርተው የነበሩ 237 የፖሊስና የደህንነት አባላት በቀጥታ ተካፋይ እንደነበሩና በመጨረሻም ከነበሩበት ስራ ገለል መደረጋቸውን ኮሚሽኑ ማስረጃ አለ፡፡ በዚህ ተሳትፎ የነበሩት የፖሊስና የደህንነት አባላት ቢረጋገጡም በመለስ ዜናዊ ገዢ መንግስት አንዳቸውም በወንጀለኛነት አልተጠየቁም፤ አልተመረመሩም፤ አልተያዙም፤አልተከሰሱም ለፍርድም አልቀረቡም፡፡

በግድያው ተካፋይ የነበሩ አለያም ግድያውን በትዕዛዝ ያስፈጸሙ፤ ለፈጸሙት የጦር ወንጀል ተጠያቂነት አለባቸው፡፡ ይህን ወንጀል የሚያውቁና ሊያውቁ የሚገባቸው ቁንጮ ወታደራዊና የሲቪል ባለስልጣኖች እርምጃ በላመውሰዳቸው በእዝ ተዋረድ ስልጣናቸው ሃላፊነቱ ሊለቃቸው አይችልም፡፡ ሂውማን ራይትስ ዋች ሲያብራራ: “በሶማልያ በሰፊው በአጠቃላይ በየመንደሩና በሃገሪቱ ላይ በተካሄደው የዘዴ ጭፍጨፋ ትእዛዝ የሰጡት የኢትዮጵያ ጦር አዘዦች በሲቪሉ ሕብረተሰብ ላይ ለተፈጸመው ግፍ፤ በጦር ወንጀለኛነት ሊጠየቁ ተገቢ ነው፡፡የሶማሌ ሪጂን ለተፈጸመው ስቃይ፤ አስገድዶ መድፈር፤በግዳጅ ማፈናቀል የሰብአዊ መብት ጥሰት ወንጀል ነውና የኢትዮጵያ መንግሥት ዋነኛው ሃለፊነት አጉዳይ ነውና ከተጠያቂነት አያመልጥም፡፡ በነዚህ በተጠቀሱት አስከፊና ዘግናኝ ወነንጀሎች ማንም ሰው በወንጀለኝነት አልተጠየቀም፤በቁጥጥር ስር አልዋለም፤ክስ አልተመሰረተበትም፤ በመለስ መንግስትም ተጠያቂም አልሆነም፡፡”

በ2010 ለተባበሩት መንግስታት ኮሚቴ ኤጌንስት ቶርቸር ሲያትት:

አስከፊ የስቃይ ሁኔታዎችንና ሌሎችንም አስከፊ ድርጊቶችን አስመልክቶ ኢትዮጵያ ውስጥ በሚፈጸመው ሰብአዊነትን በሚያዋርድ ድርጊት ላይ አቤቱታ አቅርቦ ነበር፡፡ስቃይና ሰብአዊ ያልሆነ ድርጊት በኢትዮጵያ የጦር አባላት፤ ፖሊሶችና በደህንነት አባላት ይፈጸማል፡፡ የሽብርተኛነት ተጠርጠሪዎች፤ በዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች፤ በተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ አባላትና መንግስት በሚፈራቸው ሁሉ ላይ ከሰብአዊ ውጪ የሆነ መከራ ይፈራረቅባቸዋል፡፡በተለያዩ ጊዜያት የተፈጸሙትን የስቃይ የመከራና የግፍ ተግባራትን የሚመሰክሩ ማስረጃዎች ሁማን ራይተስ ዎች ሰብስቦ ማስረጃዎችን አከማችቷል፡፡ በመንግስቱ የደህንነት አባልት የሚፈጸመው ግፍና ስቃይ በአዛዥ ፖሊስ አባላት፤ ከተራው አባል በጣም የረቀቀና የመረረ ነው፡፡በሁማን ራይትስ ዎች ዘገባ መሰረት ወታደራዊ የዕዝ ባለስልጣኖች በነዚህ ግፎች አፈጻጸም ላይ ተሳታፊ እንደነበሩ ማስረጃ አላቸው፡፡

የዓለም  አቀፍ  የፍትሕ  ችሎት ወይስ  የዓለም አቀፍ  መድልዎ  ችሎት?

ለሴራ ሊዮን የተቋቋመው ልዩ ፍርድ ቤት ታሪካዊና የሚደገፍ የሚሆንበት ምክንያት በሰው ልጆች ላይ ባደረሰው የመብት ጥሰትና የጦር ወንጀሎችን ለፍርድ ማቅረቡ ነው፡፡የሚደረስበትም ውሳኔ የአፍሪካን ቅንጡ ገዢዎች ከአረመኔያዊ ተግባራቸው የሚገታና የአፍሪካ የፈላጭ ቆራጭ ገዢዎችም ከተጠያቂነት ነጻ ነን ብለው ማሰብን ጊዜው ያለፈበት ተረት ተረት መሆኑን እንዲገነዘቡ የሚያደርግ እንደሚሆን አያጠያይቅም፡፡ በ2003 ቴይለርን ለፍርድ እንዲቀርብ ክስ የመሰረተበት ዴቪድ ክሬን በጥንቃቄ እንዳሰፈረው ‹‹ይህ በዓለም አካባቢ መሰማት የጀመረው ደወል እስከመጨረሻው ይህን ጣእመኛ ድምጹን ማሰማቱን አያቆምም፡፡ የሃገርህ መሪ ሆነህ የሃገርህን ሕዝብ የምትጨፈጭፍ ከሆነ፤ቀጣዩ በደወሉ ተጠሪው አንተ ነህ፡፡›› የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሃፊ ባንኪ ሙን የቴይለርን አመለካከት ‹‹ለዓለም ወንጀለኞች ፍትሕ አንድ ትልቅ መሰረት ነው፡፡ በዚህም ለዓለም ዙርያ ማንም ባለስልጣን ቢሆን ከእንግዲህ ከተጠያቂነት እንደማያመልጥ ያሳስባል›› ሆኖም ግን የዓለም አቀፉ ፍርድ ቤትና የተባበሩት መንግሥታት ሴኪውሪቲ ካውንስል በመድልዎ ለሚከናወን አሳፋሪ ድርጊት መዳረግ የለባቸውም፡፡ በሰብአዊ መብት ጥሰትና በሌሎችም ኢሰብአዊ ድርጊቶች በሱዳን፤ ኡጋንዳ.፤ በዴሞክራቲክ ሪፑብሊክ ኮንጎ፤በኬንያ፤ፍትሕን እየሰፈኑና ያቂዎችን ለፍትህ እያቀረቡ በኢትዮጵያ በሚደረገውና እየተደረገም ባለው፤ ለእያንዳንዱ ወንጀል ተጨባጭ ማስረጃ በዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ተጠናቅሮ መኖሩን እየሰሙ “ጆሯቸውን መድፈን፤ እያዩ አይናቸውን መጨፈን፣ስለሁኔታው ትንፍሸሽ ላለማለት አፍን መለጎም” ሌላውን ድርጊት ሁሉ የለበጣና ሚዛኑን የሳተ በገደዳው የሚዳኝ ያደርገዋል፡፡ የሰብአዊ መብት ጥሰትን ለረገጡና የጦር ወንጀል ለፈጸሙ የተለያየ የአመለካከት ደረጃ ሊወጣለት አይገባም፡፡ መመዘኛው የምት ጥሰት፤ ፍትህ አልባ ግድያ፤ አስገድዶ መድፈርና በግዳጅ ማፈናቀል ከመሆን ውጪ ሌላ መመዘኛ አልተቀመጠለትም፡፡ጥሩና መጥፎ ተብለው የሚፈረጁ  የጦር ወንጀለኞችና የሰብአዊ መብት ጥሰት ወንጀለኞች የሉም፡፡ ወንጀለኞች እንጂ፡፡የጦር ወንጀለኞችና የሰብአዊ መብት ጥሰት ወንጀለኞች፤ ‹‹ሥብርተኞችን ለመዋጋት›› በሚለው ማስመሰያና ማጭበርበርያ ሕጋቸው ሊጫወቱብንና ሊያሳስቱን ጨርሶ አይችሉም፡፡ ይህን እንደመደበቂያ የሚጠቀሙበት እራሳቸው ሽብርተኞችና ሥብር ፈጣሪዎች ናቸውና፡፡ ለጦረኞችና ለግፈኞች የተዘጋጀ የጭካኔ ቁንጅና ውድድር የለም፡፡ ለሱዳን ኬንያ ኡጋንዳ ለዴሞክራቲክ ሪፓብሊክ ኮንጎ ጥሩ ነው ተብሎ የተቀመጠውና ያገለገለው ድንጋጌ ለኢትዮጵያም ጥሩ ሆኖ ሊያገለግል ይገባል፡፡ ተጠናቅሮ ባለው ማስረጃና ዶኩሜንት መሰረት ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በኢትዮጵያ የዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት ከተሰየመበት ከ2002 ጀምሮ በተፈጸሙ የጦር ወንጀሎችና የሰብአዊ መብት ጥሰት ወንጀሎች ሌላው ቢቀር ምርመራ እንዲካሄድ የማድረግ የአደራ፤የህግና ፤የሞራል ግዴታም አለበት፡፡

በእኢትዮያ የታሰሩ ጋዜጠኞችና የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ!!!

ካሁን በፊት የቀረቡ የጸሃፊው ጦማሮች ለማግኘት እዚህ ይጫኑ:
http://www.ecadforum.com/Amharic/archives/category/al-mariam-amharic

Similar Posts

Leave a Reply