ለዶናልድ ፔይን የሰብአዊ መብት ችሮታ – ከዓለማየሁ ገብረማርያም

Click here for PDF

ከዓለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ

ዶናልድ ፔይን መሪ የዴሞክራሲና የሰብአዊ መብት ጥሪ፤መሪ የከበሮ ጎሳሚ ነበሩ

ባለፈው ሳምንት ባሰደነገጠን የዶናልድ ፔይን ከመሃላችን መለየት፤ሁሉም የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች በእጅጉ አዝነናል፡፡ፔይን በአሜሪካ ኮንግሬስ ተወዳዳደሪ የሌላቸው ብቸኛ ጠበቃችን ነበሩ፡፡ድንገተኛ መለየታቸው ለኢትዮጵያ ብሎም ለአፍሪካ የነጻነት የዴሞክራሲና የሰብአዊ መብት ትግል ማዝገምን ያስከትልብናል፡፡ሆኖም ግን ፔይን ትተውልን የሄዱት የሰብአዊ መብት፤ጥብቅናና ለረጂም ዓመታት በፍትጊያና በትግል ውስጥ የነበረውን ሂደት ነው፡፡አሁን ደሞ የዚህ ፍትጊያ እጣ ፈንታ በኛ ላይ ተጥሏልና፤ ሸክሙ የኛ የሞራል ግዴታችን ነው፡፡ይህንንም ችሮታቸውን አጠናክረን፤ በሰፊው ሙግቱን አቀነባብረን፤የውጤቱን ጊዜ ማፋጠን ግዴታችንም፤አደራም፤ያውም ታላቅ የመብት ተሟጋቹ ጥለውብን ያለፉት አደራ ነው፡፡

ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ውስጥ የዶን ፔይንን ሕለፈት መሸከምና ማመን ባቃተው ሕሊናችን ስንጨነቅ ብንሰነብትም፤በሌላ ጎን ደግሞ፤እኛ በዲያስፖራው ያለን ኢትዮጵያውያን በቡድንም ይሁን በተናጠል፤ ጥለውልን ላለፉት ታሪካዊ አደራና ችሮታ፤ምን ልናደርግ እንችላለን በሚለው እሳቤ ላይ ስንቆዝም ነበር፡፡ሁሉም የማይወድቅ ሃሳብ አላቸው፡፡ላደረጉት ከፍተኛ አስተዋጽኦ የነጻ ትምህርት እድል የሚያስገኝ ተቋም እንመስርት፡፡ በስማቸው የሰብአዊ መብት ኮንፍራንስ እናዘጋጅ፡፡ እሳቸው ቆመውለት ለነበረው የእርዳታ ለጋሽ ድርጅት ገንዘብ እናሰባስብ፡፡ በስማቸው የሚሰየም ልዩ በአል እንመስርት፡፡እና ሌሎችም፡፡

እነዚህ ሁሉ እዚህ ቀረሽ የማይባሉ ታላቅ ቁም ነገሮች ናቸው፡፡በኔ አመለካከት ግን፤ለዶናልድ ፔይን ለትግላቸው፤ልፋታቸውና ጥረታቸው ዘልአለማዊነት ልናደርገው የሚገባን ጉዳይ፤ የጀመሩትንና ታላቅ ውጣ ውረድና ጊዜያቸውን የሰዉለትን ዓላማቸውን፤ሳንዘናጋና ቀጠሮ ሳንይዝለት፤አሁኑኑ ተጋባራዊ በማድረጉ፤እንቅስቃሴያችንን በማጠናከር ለውጤት ማብቃት ነው፡፡ ለአፍሪካ የፔይን ታላቅ ችሮታ ለሰብአዊ መብትና ዴሞክራሲ ተግባራዊነት ያካሂዱ የነበረው ጥረት ነው፡፡ለኢትዮጵያም ብቸኛ ስጦታቸውና ያላሰለሰ ጥረታቸው፤የሰብአዊ መብት፤ግልጽነትና ተጠያቂነት በኢትዮጵያ ውስጥ በአሜሪካ ስርአት ደረጃ እንዲስተካከል ማድረግ ነበር፡፡

በምርጫ ጣቢያቸው በኒው ጄርሲም ሆነ፤በታላቁ አህጉራዊ ወረዳቸው አፍሪካም ውስጥ፤የዶናልድ ፔይን ተግባር፤ ኑሯቸውና የእለት ተእለት እንቅስቃሴያቸው፤ሕዝባዊ አገልግሎት ማበርከት ነበር፡፡ በአፍሪካ ድምጻቸው ለታፈነባቸውና ማንነታቸው በጨካኞችና እርባና ቢስ ጀብደኞች ለተደፈረባቸው፤መታወቂያቸው ለተገፈበባቸው ሁሉ፤ድምጽ ለመሆን፤ከቦታ ቦታ፤ከሃገር ሃገር ተዘዋውረዋል፡፡ ለአፍሪካና ለአፍሪካውያን ላደረጉት አስተዋጽኦና ለወጡ ለወረዱበት ፈተና ሁሉ አንዳችም ምስጋናም ሆነ አድናቆትን አልጠበቁም፡፡ ላጋጠማቸው ችግርና ፈተናም አንድም ጊዜ ቅሬታ አላደረባቸውም፤ ይልቁንም በነዚህ አረመኔ ዲክታተሮች የተሰነዘረባቸውን ጥቃት ሁሉ ኢላማውን እንዲስትና እሳቸውም በእውነተኛውና በትክክለኛው የሰው ልጅ ከተፈጥሮ በተሰጠው ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ እጦት የሚሰቃዩተን በማገዝና አቤቱታቸውን በማሰማት ሂደት ላይ ነበር ተጠናክረው የኖሩት፡፡

ስለዶናልድ ፔይን ችሮታ ግንዛቤ

ዶናልድ ፔይን፤ማርቲን ሉተር ኪንግ የፍትሕ፤የሰላምና የብልጽግና ግንባር ቀደም ከበሮ ጎሳሚ ሊሏቸው ይችል የነበሩ ሰው ነበሩ፡፡ እኛም ግንባር ቀደም የዴሞክራሲ፤ሰብአዊ መብት፤የአፍሪካ ነጻነት ከበሮ ጎሳሚነታቸውን በሚገባ እናውቃለን፡፡በኢትዮጵያም ነጻና ፍትሃዊ ምርጫ እንዲተገበር መሪ የነጋሪት መቺ ነበሩ፡፡የነጻና እውነተኛ የፍትሕ ስርአት፤የነጻው ፕሬስ ነጻ እንቅስቃሴ መሪ ባለአታሞ ነበሩ፡፡በታወቁና በሚስጥራዊ ቦታ በግፍኞች ታፍነው ለሚገኙ የፖለቲካ እስረኞች ያለአንዳች ቅድመ ሁኔታ መለቀቅ ግንባር ቀደም ከበሮኛ ነበሩ፡፡ግንባር ቀደም አታሞ ጎሳሚነታቸው፤በአፍሪካ ለረጋና ለሰከነ ሁኔታ፤ ለዴሞክራሲ፤ ለኤኮኖሚ ልማት ነበር፡፡የከበሮ ምታቸው በኢትዮጵያና በአሜሪካ ሕዝቦች መሃል የኖረውን ወዳጅነትና ግንኙነት አጠናክሮ በመቀጠሉ ስርአት ላይ ነበር፡፡ዶናልድ ፔይን በኢትዮጵያ ውስጥ ለተጠያቂነትና ለዴሞክራሲ መተግበር ቀዳሚ የከበሮ መቺ ነበሩ፡፡

በዶናልድ ፔይን ግንዛቤ ላይ መነጋገር ማለት፤ አሜሪካ ለአፍሪካ፤በተለይም ለኢትዮጵያ በገባችው የዴሞክራሲ ግንባታ ቃል ላይ መነጋገር ማለት ነው፡፡ በዲሴምበር 2009፤ የሃገር አስተዳደር ሚኒሰቴርዋ ሂላሪ ክሊንተን፤የአሜሪካን የሰብአዊ መብት ፖሊሲ መሠረት፤በግልጽ አስቀምጠዋል፡፡ ሲያብራሩም፤‹‹የሰብአዊ መብትና የነጻነት እሳቤዎች ከፊል ዓለማችን ውስጥ እንዳለው የለበጣና የይስሙላ መፈክር ሊሆን አይችልም፡፡›› ለጥቂት ጊዜ ታይቶ እንደሚተንም ውሃ ጠብታ አይሆንም፡፡ ሰብአዊ መብት ዓለማቀፋዊ ነው፡፡ የኢትዮጵያ፤የአፍሪካ፤ የአውሮፓ፤ የአሜሪካ አለያም የሌላው ዓለም ተብሎ የሚደለደል የሰብአዊ መብት አይነትና ቅርጽ የለም፡፡

‹‹ዴሞክራሲ፤ነጻነት፤ሰበአዊ መብት በዓለም ላይ አንድ አይነት ትርጓሜ እያገኙ ናቸውና በምንም መልኩ ቢሆን ማንኛውም ሃገር ላይ፤ በማንኛውም መሪ፤ ትረጓሜያቸው እንዲለወጥና በዲክታተሮች ሊታገዱ ሊፈቀድላቸው አይገባምም፡፡አይቻልምም፡፡የሃገር አስተዳደር ክሊንተን፤ ‹‹የአዲሱ ዓለም ስርአት የሰብአዊ መብቶችን በማስከበር ላይ የተመሰረተ ሊሆን ተገቢ ነው›› በማለት አሳስበዋል፡፡‹‹እነዚህ መብቶች››ቀላልና በቀላሉም ሊተረጎሙ የሚችሉ ናቸው፡፡የንግግር ነጻነት፤ነጻ የመገናኛ ብዙሃን፤ የሃይማኖት ነጻነት፤ የመሰብሰብና ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት፤ማንኛውም ሰው በሚኖርበት በነጻነት መኖርና አለአግባብ ከመፈተሸ፤ ከመያዝ፤ከመቀጣት ነጻ እንዲሆን፡፡ እነዚህ መመርያዎች ማንም በየትም በሰላም ለመኖር መቻሉን የማረጋገጫ መነሻዎች ናቸው፡፡እነዚህ የማይተረጎሙና ለመረዳት አዳጋች የሆኑም አይደሉም፡፡ይልቅስ ሕይወትን የምንመራበትን መንገድ የሚቀይሱ ናቸው፡፡ በመኖሪያነት ነጻነትን እያደነቅን ነጻ የምንሆንባቸው ናቸው፡፡ ሰዎች በነጻ ምርጫቸው የሚሻላቸውን አስተዳደር የሚመርጡበት የዴሞክራሲ ቁልፋቸው ይህ እድልና መብት ሲኖራቸው ብቻ ነው፡፡

‹‹እነዚህ መብቶች››ቀላልና በቀላሉም ሊተረጎሙ የሚችሉ ናቸው፡፡የንግግር ነጻነት፤ነጻ የመገናኛ ብዙሃን፤ የሃይማኖት ነጻነት፤ የመሰብሰብና ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት፤ማንኛውም ሰው በሚኖርበት በነጻነት መኖርና አለአግባብ ከመፈተሸ፤ ከመያዝ፤ከመቀጣት ነጻ እንዲሆን፡፡ እነዚህ መመርያዎች ማንም በየትም በሰላም ለመኖር መቻሉን የማረጋገጫ መነሻዎች ናቸው፡፡እነዚህ የማይተረጎሙና ለመረዳት አዳጋች የሆኑም አይደሉም፡፡ይልቅስ ሕይወትን የምንመራበትን መንገድ የሚቀይሱ ናቸው፡፡ በመኖሪያነት ነጻነትን እያደነቅን ነጻ የምንሆንባቸው ናቸው፡፡

ሰዎች በነጻ ምርጫቸው የሚሻላቸውን አስተዳደር የሚመርጡበት የዴሞክራሲ ቁልፋቸው ይህ እድልና መብት ሲኖራቸው ብቻ ነው፡፡ የሃገር አስተዳደር ሚነስትር ክሊንተን፡- ለኛ የሕዘቡ የመጨረሻ የሃሳባቸው ውሳኔ የሚገኘው ተመራጮች በሚያሰተላልፏቸው መሰረታዊ በሆኑ ጉዳዮች ከነጻና ፍትሃዊ ምርጫ ነው፡፡እነዚህ መመርያዎች ለይስሙላ የተቀመጡ ሳይሆኑ፤ሊጠበቁ፤ ልንከላከልላቸውና ልናስተላልፋቸው የሚገቡ ናቸው፡፡በአንዳንድ ሃገሮች‹‹መሪዎች እያወቁ ለመተግበርና ሕዝቦችም እንዲገለገሉባቸው ፍቃደኛ ባለሆኑባቸው ሃገራት፤የአሜሪካ መንግሥት እነዚህን መሰል መሪዎች ጭቆናቸው እንዲያበቃና ሕዝቡ ነጻ እንዲሆን ግፊት ማድረግና፤ ይህን በትክክለኛው ጎዳና ማቃናት ላይ ያሉትን ደግሞ ለመርዳት ዝግጁ ልንሆን ይገባል፡፡ ቆራጥ የሆኑ ግለሰቦችና ድርጅቶችንም ሕዝቡ ለሚያካሂደው ትግል የሚያደርጉትን ተሳትፎ በመደገፍ፤ማበረታት ዓላማችን ሊሆን ተገቢ ነው፡፡የኦባማ የሰብአዊ መብት ፖሊሲ የሚመራባቸው አራት ቋሚ ምሰሶዎች አሉት፡፡

የመጀመርያው፤ለሰበአዊ መብት መከበር ቁርጠኝነት እኛን ጨምሮ ያለን ቆራጥነት ነው፡፡ሁለተኛው፤የሰብአዊ መብት አጀንዳዎችን ተግባራዊ ለማድረግ የሚደረገው እንቅስቃሴ በትክክለኛነቱና እርግጥኛነቱ በተረጋገጠበት አካሄድ ሊሆን ይገባል፡፡ወደግድግዳው ስንንደረደር ሊገጥመን በሚችለው አስቸጋሪ ሁኔታ ለመወጣት፤ ወደ ኋላ በማፈግፈግ ሳይሆን፤ችግሩን አስወግደን፤ወደ አለምንበት አቅጣጫ ልናልፍ የምንችልበትን መንገድ በማመቻቸት ላይ የተመሰረተና፤የሕብረተሰቡን ኑሮ በማሻሻል ላይ ያነጣጠረ ሊሆን ይገባል፡፡ ሶስተኛ፤ በዜጎችና በነዋሪዎች ፍላጎትና ፈቃደኝነት ላይ ለውጥን እንደግፋለን፡፡ የሰብአዊ መብትን የሰብአዊ እውነታ የማድረግ እቅድ የመንግሥታት እቅድ ብቻ ሊሆን አይገባም፡፡የግለሰቦችንና የድርጅቶችን ትብብር የሚጠይቅና በነዋሪዎችና ከድንበር ባሻገር የሚታሰብም፤ የስብእና ክብርን፤ሰብአዊነት ባስተሳሰራቸው መሃል ሊሆን ይገባል፡፡ አራተኛ፤ ተስፋ በሚታይባቸው አካባቢም አዎንታዊ ምላሻችን ሊደርስና፤እንቅስቃሴውም ሊደገፍ ሲገባ፤የሰብአዊ ሕይወትም በሚዛኑ ላይ ተንጠልጥሎ ሲገኝ ሚዛኑ ወደ ተሻለ ኑሮና የሕዝብ ነጻነት እንዲያጋድል የሚቻለንን ሁሉ ማድረግ ይኖርብናል፡፡

ለኦባማ አስተዳደር የሰብአዊ መብት ግዴታውን ማስገንዘብ

የሰበአዊ መብትን በተመለከተ ተጠያቂነት ከቤት መጀመር አለበት፡፡ ‹‹ከራሳችን››፡፡ በአፍሪካ በተለይም በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብትን ለማበራታት ለመጠበቅ፤ የኦባማ አስተዳደር ምን አድረጓል? በግንቦት 2010 የመለስ ዜናዊ ገዢ መንግሥት 96.6 በመቶ ምርጫ አሸነፍኩ ሲልስ አሜሪካ ምን አደረገች?አሜሪካ መለስ ዜናዊ ነጻና ፍትሐዊ ምርጫ እንዲያካሂድ ገሃዳዊ ጫና አድርጓል? በሚታወቅና ሚስጥራዊ በሆኑ የመለስ ዜናዊ አገዛዝ ያፈናቸውን የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ ማድረጉ ላይ አሜሪካ አስቦበታል? የመለስ ዜናዊ የግፍና ጨቋኝ አገዛዝ የነጻውን ፕሬስ እንቅስቃሴ ሲያዳክምና ሲዘጋ፤የአሜሪካ ድምጽን የአማርኛ ድምጽ ፕሮግራም በኤሌክትሮኒክ መሳርያዎች በመታገዝ ሲያፍን የአሜሪካ መንግሥት ምን እርምጃ ወሰደ?

ዘይቤያዊ የሆነ ምላሽ

የሃገር አስተዳደር ክሊንተን፤ ‹‹ሩጫችን ከግንቡ ትይዩ ሲያደርሰን›› እና ጭቆናና የሰብአዊ መብት መረገጥን ሲያሳየን፤ ‹‹በተስፋ መቁረጥ ከማፈግፈግ ይልቅ ዘይቤያዊ ዘዴን በመጠቀም በጭቆና ውስጥ ያሉትን በማገዝ ምላሹን እንሰጣለን፡፡›› በግንቦት 2010 የዓለም የነጻነት ቀን በተከበረበት ጊዜ ፕሬዜዳንት ኦባማ ባደረጉት ንግግራቸው፡- ያለፈው ዓመት በዐለም አቀፍ ደረጃ የነበረው የፕሬስ ነጻነት መጥፎ ነበር፡፡ከቀድሞው በተሻለ ሁኔታ ሕዝቦች በኢንተርኔት መረጃዎችን በማግኘት፤በእጅ ስልኮች፤እና በሌሎችም የቴክኖውሎጂ መገናኛ ዘዴዎች መጠቀም ሲችሉ እንደ በኢትዮጵያ ያሉ ገዢ መንግሥታት ግን……………ሕዝቡ በእነዚህ የቴክኖውሎጂ ውጤቶች እንዳይጠቀምና መረጃዎችን እንዳያገኝ እያፈኑት ነው፡፡›› አሁን አሁንማ የመለስ ገዢ መንግሥት ከእነዚህ አፈናዎች አልፎ ነጻ ጋዜጦችን መዝጋትና የአሜሪካ ድምጽ የአማርኛ ፕሮግራምን የኢትዮጵያ ህዝብ እንዳያዳምጥ እስከማድረግ ደርሷል፡፡በዚህስ ጉዳይ ላይ የአሜሪካ መንግሥት የመለስ ዜናዊ አገዛዝ ጭቆናና የነጻው ፕሬስን ሲያፍን ዘይቤያዊ የሆነ ምላሽ ሰጥቷል?

በሕዝቡና በነዋሪው መነሳሳት ለተገኘ ለውጥ ድጋፍ መስጠት

የሃገር አስተዳደር ክሊንተን፡ ‹‹ሰብአዊ መብት›› ‹‹የሰብአቸዊ መበት እውነታ›› ሊሆን የሚችለው ግለሰቦችና ድርጅቶች ከነዋሪዎቸና ከዚያም አልፈው ከድንበር ባሻገር ተዋህደውና ተስማምተው ለመስራት ሲችሉ ብቻ ነው፡፡ ያ ካልሆነ እውነታ ሊሆን ጨርሶ የማይታሰብ ነው፡፡ በየካቲት 2010 ምክትል የሃገር አስተዳደር የሆኑት ማርያ ኦቴሮ የሲቪል ማሕበረሰብ ሕግ የተባለውን የመለስ ገዢ መንግስት ያወጣውን እወጃ በተመለከተ፤ ቅሬታቸውን አሰምተው ነበር፡፡ አንድ ዘገባ እንዳመላካተው፤በዚህ ደንብ ሰበብ የተነሳ፤ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ቁጥር ከ4600 ወደ 1400 በሶስት ወራት ጊዜ ውስጥ አሽቆልቁሏል፡፡ የድርጅቶች አባላት ቁጥርም እንደ ደረሰኝ ጥቆማ በ90 በመቶ ቀንሷል፡፡‹በኢትዮጵያ ‹በዜጎች እና በቆራጥ ዜጎች ግለሰቦችና በተደራጁ ቡድኖች መነሳሳት ላይ የተመሰረቱ››ግልጋሎትና ሕዝባዊ ድጋፍ ሰጪዎች፤ በጨቋኝ ገዢዎች ፈላጭ ቆራጭ መመርያ ብትንትናቸው ሲወጣ የአሜሪካ መንግሥት ምን እርምጃ ወሰደ?

የሚዛኑን ተዳፋት ወደ ተስፋ ሰጪው ወገን እንዲያዘም ማድረግ

የአገር አስተዳደር ክሊንተን እንዳሉት፤ የአሜሪካን መንግሥት ተስፋ የሚታይበትን እያገናዘበ፤ከዚያ አቅጣጫና ከሱ ጋር መስራትን ይመርጣል፡፡በግንቦት 2010 የምርጫ ወቅት፤የአሜሪካን መንግሥት የኢትዮጵያን ሁኔታ ወደተሻለ አቅጣጫ ለመውሰድ እድሉ ነበረው፡፡በምርጫው ማግስት የአሜሪካን መንግሥት ጠንካራ መግለጫ አወጣ፡፡ከኢትዮጵያ ጋር ሰፊና ጠንካራ መሰረት ያለው ግንኙነት ቢኖረንም ገዢው መንግሥት በመከተል ላይ ያለውን ዴሞክራሲና መልካም አስተዳደርን በተመለከት ግን ጥርጣሬያችንን ለመንግሥት ገልጸናል፡፡…….በአሁኑ ምርጫ የኢትዮጵያ ገዢ መንግስት የሚወስደው አቋምና የምርጫው ሂደት የወደፊቱን የአሜሪካንንና የኢትዮጵያን ግንኙነት ይወስናል፡፡…..ይህም በኢትዮጵያ በኩልም ስለግንኙነታችንን ማሰብን ይጨምራል፡፡ከዚህም በመነሳት የኢትዮጵያ መንግሥት ይህን ቀጥተኛ የሆነውን መግለጫ በጥሞና ሊያስተውሉ ተገቢ ነው፡፡…..ከዚህ መንግሥት ጋር ውይይታችንን እንቀጥላለን፤ የዴሞክራሲያዊ ተቋማትም ግንባታ ደረጃዎች እንዳሉትና ጊዜ እንደሚጠይቅ እንገነዘባለን፡፡

ኤች አር 2003 የኢትዮጵያ ዴሞክራሲና ተጠያቂነት አክት፤

የሃገር አስተዳደር ሂላሪ ክሊንተን የአሜሪካንን የሰብአዊ መበት ፖሊሲ በግልጽ ከማስቀመጣቸው ቀደም ብሎ፤ዶናልድ ፔይን፤ከእሳቸውም በፊት የነበሩት የኒው ጀርሲው ኮንግሬስማን ክሪስቶፈር ሰሚዝ ተግባራዊ ለማድረግ ጥረት ያደርጉ ነበር፡፡ኤች አር 2003 (በአሜሪካ ተወካዮች ምክር ቤት በ2007 አለፈ) በትክክልና በብቃት የኦባማ አስተዳደር ያዋቀራቸውን የሰብአዊ መብት ምሰሶዎች መስፈርት በሚገባ ያካተተ ነው፡፡ በትክክልም በቂ ጥርስ ለሃገር አስተዳደር ሂላሪ ክሊንተን ጠንካራና ብርቱ አባበል የሚሰጥ ነው፡፡የዶን ፔይንን ሕይወትና ክቡር፤የተግባር ችሮታቸውን የምንጠብቅላቸው ፤እራሳችንን በኤች አር 2003 ወስጥ ለተካተቱት መግቢያ ቃላቶቸ እና ለአጠቃላይ ኤች አር 2003 ለተሸከማቸው ግዙፍ መብቶች አፈጻጸም ስንሰለፍና ስንጥር ብቻ ነው፡፡ለማንም ያልወገነው፤ የተከበረውና የኮነግሬስ በተመጻሕፍት የቀኝ እጅ የሆነው የኮንግሪስ የጥናት ማዕከል ሕግ የተቀመጠበት የተግባር ድርጊት፡-

(1) ሰብአዊ መብትን፤ዴሞክራሲን፤የፍትህ አስፈጻሚ አካላትን በነጻነት መንቀሳቀስ፤የነጻውን ፕሬስ ነጻነት፤የፌዴራል ዴሞክራቲክ ኢትዮጵያን መንግሥት የኤኮኖሚ እድገት (2) በሽብርና ሽብርተኘነት ላይ ያለውን ዓለም አቀፋዊ መከላከልን መተባበር (3) በኢትዮጵያ ያሉትን የፖለቲካ እስረኞችና ሁሉንም የሕሊና እስረኞች የሚፈቱበትን ሁኔታ ማመቻቸት (4) በአካባቢው መረጋጋትን፤ዴሞክራሲን፤የኤኮኖሚ ልማትን ማበረታታት፡፡ (5) ሰበአዊ እርዳታዎችን በተለይም በአጋዴን ክልል ማበረታታት እና (6) በኢትዮጵያና በአሜሪካ መሃል ያለውን የኖረ ወዳጅነት ማጠናከር፡፡

(2) የሰብአዊ መብት ተጠያቂነት በኢትዮጵያ፤ደንቡ በአሜሪካ ኮንግሬስ መቀረጽ የጀመረው የ2005ን ምርጫ ተከትሎ በተከሰተውና በማስረጃ በተደገፈው የ193 ንጹሃን ዜጎች መገደልና፤ከምርጫ በኋላም በተጨፈጨፉት 73 ንጹሃን ዜጎች ምክንያት ነው፡፡በኖቬምበር 2005፤ የኒው ጀርሲው ኮንግሬስማን ክሪስተፈር ስሚዝ፤ የወቅቱ የአፍሪካ ንኡስ ኮሚቴ ሊቀመንበር፤4423 በመባል የታወቀውን (‹‹ኢትዮጵያ ኮንሶሊዴሽን አክት››) አረቀቁ፡፡

(3) ሕጉ በተጨማሪም የአሜሪካን መንግስትን ዓለም አቀፍ የልማት ድርጅትን ጠቀሜታ ያካተተ፤የሲቪል ህብረተሰቡን ስብስብ መርጃ የፋይናንስ ድጋፍን፤የነጻ ሰበአዊ መብት ተሟጋቾች መቆጣጠር የሚየስችላቸውን መንገድ፤ለፖለቲከ ድርጅቶች ዴሞክራሲያዊ ችሎታ ማዳበርያ፤የፖሊስና ደህንነት አባላት፤ የግድቦች ግንባታዎች እና የትብብር የደህንነት እንቅስቃሴ ሁሉ ኢትዮጵያ፤ዓለም አቀፍ ሰብአዊ መብት ድንጋጌዎችን ማከበሯ ማረጋገጫ እስኪገኝ ድረስ እንዲታቀብ፡፡ ኤች አር 4423 ወደ ኤች አር 5680 ተሻሻለ፡፡(‹‹በኢትዮጵያ ነጻነት፤ዴሞክራሲ፤ሰብአዊ መብትን ተግባራዊ ለማድረግ የወጣ››) በ2007 ፔይን የአፍሪካን ንኡስ ኮሚቴ ለመምራት በተሰየሙበት ወቅት፤ ድንጋጌው በአዲስ ቁጥራዊ አጠራር ተለወጠ፡፡ኤች አር 2003 ተባለ)እና በኦክቶበር አለፈ፡፡ ይህም ማለት በኦባማ መስተዳደድር እንደመመርያ ሆነው የተዋቀሩትን የአራቱ ምሶዎች ትግበራ በትክክል ለኢትዮጵያም ሆነ ለአፍሪካ እንዲሰሩ የሚያደርግ ነው፡፡

ሚኒስትር ሂላሪ ክሊንተን የሰብአዊ መብት ድንጋጌ ፖሊሲያቸውን መመርያ ንግግር ሲያጠናቅቁ፤የሰብአዊ መብት ጥበቃን ሂደትና ተግባራዊነት ለማስፈጸም ጠንክሮና ተግቶ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

በመጨረሻም፡- ይህ እኛ የምናከናውነው ጉዳይ ብቻ አይደለም፤ ስለእኛነታችንም እንጂ፡፡አስፈላጊውን ትግልና ቆራጥነት ካላደረግን በስተቀር፤እኛ ነን የምንለውን ልንሆን አንችልም፡፡ በሰብአዊ መብት ማመን ማለት ለተግባራዊነቱ ሁሉ የሚጠይቀውን ለመክፈል ፈቃደኛና ቆራጥ መሆን ማለት ነው፡፡ይህንን መብት በሁሉም ቦታ፤ ለሁሉም ሃገራትና ዜጎች ለማስፈጸም የውዴታ ግዴታ ሰነዱን ስንፈርም፤ይህንንም እውን ለማድረግ ሂደቱ የሚጠይቀውን መስዋእትነት ሁሉ ለመክፈል ፈቃደኛነታችንንም ነው የምንፈርመው፡፡

በኮንግሬስማን ፔይን ሕልፈት የኤች አር 2003ን ሕይወት እንዲያንሰራራ በማድረግ እነዚያን ግዙፍ ቃላቶች የአሜሪካን ሰብአዊ መብት ፖሊሲ በኢትዮጵያና በአፍሪካ በአጠቃላይ እንዲፈጸም ለማድረግ እንችላለን፡፡ወይም በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብትን ጉዳይ ጨርሶ እንዲወድም ለማድረግ ትግላችንን በማቆም ዳግም በኢትዮጵያ ስለሰብአዊ መብት ጉዳይ ላለማንሳትና እንዲረሳ ለማድረግ እራሳችንን እናዘጋጃለን፡፡

ከኤች አር 2003 በኋላ ስለተዋቀረው ረቂቅ ሕግ (ቢል)፤ ትግላችን ቀላል አለያም የዋዛ ውጣ ውረድ አይሆንም፡፡ጉዟችን ዳገታማና አስቸጋሪ፤ ፈታኝ ነው፡፡ የትግላችንም ቀና መንገድ በጨቋኞችና ግፈኞች ተገዢ፤ በወር 50.000 የሕዝብ ደም ዶላር በሚከፈለው የ ኬ ጎዳና ተሟጋች ስለተያዘብን በየቀኑ የኮንግሬስን የግራናይት ወለል እየተሳለመና ለገቢ ወጪው ኮንግሬስማን እጅ እየነሳ፤ተቀባይነት ለማግኘት እየጣረ፤ የኢትዮጵያውያንን ሰብአዊ መብት ለማሳፈንና፤ በአረመኔዎች ጥይት ለማስደብደብ፤ በቡጢያቸው ለማስወገር፤ በወህኒ ቤታቸው ለማሳጎር፤ጉብ ቂጥ በማለት ላይ ነውና ትግላችን እንዲህ ቀላል አይሆንም፡፡ስለዚህም ኢትዮጵያውያን በተለይም በአሜሪካ ነዋሪ የሆንን ኢትዮጵያውያን፤ቀላል ምርጫ ቀርቦልናል፡፡ለዚህ ፈታኝና አስቸጋሪ ግን ወሳኝ ፍልሚያ መፈረም፡፡ከባዱን ጫና ለመሸከም ቆርጠን መነሳት፡፡ዶናልድ ፔይን ለኢትዮጵያ የነበራቸውን የሰብአዊ መብትና የዴሞክራሲ ሕልምና ራዕይ፤ምኞትና ፍላጎት እውን ማድረግ፡፡ ሌላው መንገድ ደግሞ ይህን ጅማሮ አቋርጦ የበቃኝ ሽሽት መያያዝ፡፡

ዶን ፔይን ለኢትዮጵያ የገቡትን የማይታጠፍ ቃላቸውን እኛ ኢትዮጵያውያን ዕውን እናድረገው!

Similar Posts

Leave a Reply