እስክስ! ጅቡ ከደራጎኑ ጋር፣ አይ ጉድሽ አፍሪካ!
ከፕሮ. ዓለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም ከነጻነት ሃገሬ
የቻይናው ደራጎን (ጭራቅ)ከአፍሪካውያን ጅቦች ጋር አሸሸ ገዳሜ ጭፈረውን እያስነካው ነው፡፡ለዚህ ደራጎን አፍሪካ በምንም መልኩተስማሚ ሁኔታ አትፈጥርለትም፡፡ታሪክ እንደሚያስረዳው በአንድ ወቅት የአፍሪካውያን መኩሪያና መመኪያ የነበረችው ምድር አሁን የጅቦች መሰባሰቢያ ትልቅ ዋሻ ፈጥራ (የአፍሪካ ሕብረት) የጅቦቹ መፈንጪያ መናሃርያ ሆናለች፡፡ለዚህ የጅቦች መገናኛ፤መዶለቻ፤መለመኛ፤ሕዝባዊ ማነቆ መፍተያው ሁሉ ለሚከናወንበት ግንባታ የሚያስፈልገውን ወጪ 200 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የተሸፈነው በቻይና ነው፡፡ ሲባልም፤ ይህ ቻይና ለአፍሪካ የሰጠችው የሰው በላዎቹ (ጅቦች) የአፍሪካ መሪዎችልመና መልስ ነው በማለት ጅቦቹ የታላቁን ደራጎን ስጦታ ለማመስገን በተሰበሰቡበት ወቅት የተሰነዘረ አባባል ነው፡፡
ይህ ውብ ግንባታ… ከእንግዲህ የአህጉራችን የሕብረት አባላት የሚሰበሰቡበት ማዕከላዊ ቢሮ ሲሆን፤የተገነባውም በቀድሞው የሃገራችን ዓለም በቃኝ በመባል ይጠራ በነበረው ነፈሰ ገዳዮች፤ ሌቦች፤አስገድዶ ደፋሪዎች፤ፍትህን የሚያዛቡ፤አጭበርባሪዎች፤ወዘተ ይታሰሩበት በነበረበት የወህኒ ቤቱ ፍራሽ ላይ ነው፡፡ ይህ ታላቅና ግዙፍ ሕንጻ የሚያመላክተው የአህጉሪቱ መሪዎች ለዓመታት በሕዝብና በሃገር ላይ ጭነውት ያለው መከራና ስቃይ፤የነዚህ ሰው በላዎች የጅብነት ዘመን ማለቂያውንና እንደፈረሰው የወንጀለኞች ማጎርያ የነሱም የግዛት ዘመን አብቅቶ፤ አህጉሪቱና ሕዝቦችዋ ለዘመናት ከተጫነባቸው ሰቆቃ ነጻ የሚሆኑበት ዘመን መቃረቡን ነው፡፡ ስለዚህም ቻይና ይህን ግንብ ማስገንባቷ ትክክልና ተገቢም ነው፡፡ምክንያቱም ተከታዩ ዘመን የአፍሪካ ትንሳኤ ነውና፡፡ ዘመኑ ያለቀባቸውም በግፍ ሥልጣን ላይ ያለሕዝባዊ ፈቃድ የተጎለቱት መሪዎችም ለፍርድ የሚቀርቡበት ወቅት መዳረሻው በመሆኑ፡፡
ይህን የአፍሪካን ትንሳኤ የሚያመላክት አዳራሽ፤የአፍሪካን ራዕይ የሚጠቁመውን ግንባታ በመገንበታችሁ… ለቻይና መንግስትና ሕዝብ ከፍተኛ ምስጋናችን ይድረሳችሁ፤ ይህ ግኑኝነታችንም ዘላቂነት ያለው ሆኖ በየጊዜው እንዲያብብ እንመኛለን ስልም የምናገረው ሁላችንንም በመወክል ነው፡፡
ስለቻይና መንግሥት ችሮታ ምስጋናውና ጫማ መላሱ መጨረሻ አልነበረውም፡፡‹‹ስጦታው›› በአፍሪካና በቻይና መሃል የተገነባውን ወዳጅነት በከፍተኛ ደረጃ እያደገ መሄዱን አመላካች ነው፡፡የአፍሪካ ሕብረት የወቅቱ ፕሬዜዳንትና ከ1979 አንስቶ የኤኳቶሪያል ጊኒ ፈላጭ ቆራጭ ፕሬዜዳንት ቴዎድሮ ኦቢያንግ ኢንጉዌማም በባለ 20 ባለመስታወት ፎቅ ላይ ሆነው መጪው በሚገባ ታየይቷቸዋል፤ለዚህም ነው… የአዲሲቱ አፍሪካ የነገው ነጻ አፍሪካና አፍሪካውያን የብርሃን ፍናጣቂ፤ ለወደፊቷ አፍሪካ የምንፈልገው›› በማለት ሳይገባቸው እውነቱን የተናገሩት፡፡
ደራጎኑም በበኩሉ ተስማምቷል!
‹‹… በቻይናና በአፍሪካ መሃል የቆየ ልማዳዊና ባሕላዊ ግንኙነት አለ፡፡ቻይና ምንጊዜም ቢሆን የአፍሪካ ጥሩ ወዳጅ፤መልካም አገር፤እና ታማኝ ወንድም ነች፡፡አንድነትና መረደዳት ልማታዊ ድጋፍ በቻይናና በአፍሪካ መሃል የኖረና ወደፊትም ቢሆን ዘለቄታ ያለው እንዲሆን እቅዳችን ነው፡፡ … ሠላም መረጋጋትና ልማት ቅድሚያ ትኩረት ልንሰጠው የሚገባን ነው፡፡ በሁለተኛ ደረጃም አፍሪካውያን ችግራቸውንና አለመግባባታቸውን በራሳቸው እንዲፈቱ ምርጫቸውን እናከብራለን፡፡ በአፍሪካ የውስጥ ጉዳይ በራስ ወዳድነት በመነሳትና የራስን ጥቅም በማስቀደም መግባት ችግሩን በመፍታት ፈንታ ይበልጡን ያወሳስበዋል፡፡ ሶስተኛም አፍሪካውያንን በህብረት ጥንካሬያቸውን እንዲያጎለብቱ ድጋፋችን አይለያቸውም፤አራተኛ የአፍሪካን ልማት በማስቀደም የበለጠ ድጋፍ ልናደርግ ተገቢ ነው፡፡ በቻይና አፍሪካ ወዳጅነት ዕድገት ሂደት ውስጥ ጣልቃ አለመግባትንና የየሃገራቱን ልእልና አክብረን በውስጥ ጉዳያቸውም ላላመግባት ውሳኔያችንን እናከብራለን… ለአፍሪካ ከምናደርጋው ድጋፍ ጋር የፖለቲካን ክር እንደማነቆ ጨርሶ አናያይዝም… የአፍሪካንና የቻይና ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከርም ከምንም ነጻ የሆነ የ600 ሚሊዮን ብር እርዳታችንን ለአፍሪካ ሕብረት በሚቀጥለው ሶስት ዓመታት ውስጥ ተግባራዊ እናደርጋለን፡፡››
በአፍሪካ የ‹‹ቻይና ሞዴል››
የአፍሪካ ፈላጭ ቆራጭ ገዢዎች በቻይና ሞዴል የኤኮኖሚ ልማት በሚለው መርሃ ግብር ላይ የእኔ እቀድም እኔ እቀድምና የቻይና ፍቅር ለእኔ ለእኔ ማለትንና መሽቀዳደምን እንደፈሊጥ ይዘውታል፡፡ የሕዝብን ይሁንታ አግኝቶ የማያውቀውና የኢትዮጵያ ፈላጭ ቆራጭ ገዢው መለስ ዜናዊ የቻይና ሞዴል የሚለውን በመከተል ታማኝነቱን አረጋግጧል፡፡
ሁላችንም ስንመኘውና ስንጓጓለት የነበረው የአፍሪካ ትንሳኤ እውን ለመሆን መንገዱን ጀምሯል፡፡ለዚህም ማስረጃ ሊሆን የሚችል አልኩ ባዮችና ምሁራን በአደባባይ ስለአፍሪካ ዳግም ወደ ቅኝ ግዛትነት መመለስን ሲያውጁ ቢከርሙም አሁን ግን መታቀብ ግድ ሆኖባቸዋል፡፡ የአህጉራችን ይህ ውብና ድንቅ ሆኖ የታነጸው አዲሱ ማከላችን የአፍሪካ ሕብረት በትግላችን መሀላ በመተግበሩ የአፍሪካን ትንሳኤ አመላካች ነው፡፡
የቻይና ሞዴል ማለት ግን በእርግጠኝነት ምንድን ነው?
የአፍሪካ ፈላጭ ቆራጭ ገዢዎች የቻይና ሞዴል የሚለውን ቃል በግልጽና በትክክል ለማስረዳት ፈቃደኛ ከመሆን ይልቅ፤ እንደ ኮከብ ቆጣሪና መወድስን እንደማያውቀው አጭበርባሪ ጠምጣሚ ከንፈራቸውን በማላወስ ብቻ ያልፉታል፡፡ እነዚህን ፈላጭ ቆራጭ ሰው በላ ጅቦች የማመን ትንሽም ቢሆን ፈቃደኝነቱ ካለን፤‹‹የቻይና ሞዴል አፍሪካን ከተጫናት ድህነትና ችጋር አላቆ፤ የሕዝቡን መሰረታዊ ፍላጎት አሟልቶና ነጻነቱን አስረክቦ፤በኢኮኖሚና በኢንዱስትሪው ዘርፍ እድገቱን ለማፋጠን የሚያስችል ነው፡፡››ቻይና የዓለም የኦኖሚ ሃይል ልትሆን የበቃችው፤ ለሃገር ውስጥና ለውጭ ተወላጆች ኢንቬስተሮች በሯን በመክፈትና ታክስን በመቀነስ፤ አስፈላጊ በሆኑትም ሂደቶች የጋራ አዋ|ጪ በመሆን፤እንዲሁም የጉልበት ሥራን ሰፋ በማድረግ ነው፡፡ይህ ነው ለቻይናና ለአፍሪካ የእኩል በእኩል ሁኔታን ይፈጥራል የሚባለው፡፡
እዚህ ላይ ግን አንድ ማነቆ ተቀምጧል፡፡ ቻይና ይህን እመርታ ልታሳይ የሄደችበት መንገድ እኮ ማንኛውንም ጉዳይ በአንድ ፓርቲ ስርአት ውስጥ ጠፍራ በመያዝና፤ማንኛውንም እንቅስቃሴ፤የሲቪል ማህረሰቡንም፤ ወታደራዊ ተቋማትን፤የደህንነቱን መዋቅር፤በአጠቃላይ ስርአቱ ሥር ያሉትን ሁሉ የመንግሽትን ጥቅምና ፍላጎት፤ ደህንነት ጠባቂዎች በማድረግና ሕዝቡን በማግለል የሕዝቡን የእለት ተእለት እንቅስቃሴና ሃሳቡን የመግለጽ ፍላጉተቱን ሁሉ መቆጣጠርያና የቅድሚያ ማክሸፊያ መዋቅር በመዘርጋት ነው፡፡
ስለ የቻይና ሞዴል ወደ አፍሪካ ስለመምጣቱ ጉዳይስ ቻይና ምን እሳቤ አላት?
‹‹ብዙ እሳቤ የለንም›› ይላሉ በአፍሪካ ጉዳይ ልዩ የቻይና ወኪል የሆኑት ሊዩ ጉጂን በእርግጠኝነት ሲገልጹ ‹‹አሁን እያደረግን ያለነው ልማዳችንን ማካፈል ብቻ ነው፡፡እውነት እላችኋለሁ እመኑኝ ቻይናውያን የፖለቲካ እምነታችንን፣ የአገዛዝ ስርአታችንን፤ ወደ አፍሪካ እንደውለታ ክፍያ ለማስተላለፍ ሃሳብም ሆነ ፍላጎት የለንም፡፡ እኛ ራሳችን ገና ሞዴላችን የዳበረና የተዋጣለት፤ ብቃቱ የተረጋገጠለት የቻይና ሞዴል ነው ብለን አናምንም››
ታዲያ የቻይናውያን መሪዎች እምነታቸው ይህ ከሆነ፤ በአፍሪካ ፈላጭ ቆራጭ ገዢዎች ሞዴል እያሉ የሚያጨበጭቡለትንና ሰማየ ሰማያት እያወጡ የሚጨፍሩለትን ሞዴል ባለቤቶቹ ገና ያላደገ ያልለማ፤… ነው የሚሉትን ሞዴል ይዘው አሸሸ ገዳሜ የሚያምቧርቁት? ምናልባት እነዚህ ደም መጣጭ የሆኑ የአፍሪካ ዲክታተሮች የቻይና ሞዴል የሚሉትን እንደአይነርግብ መከለያቸው በማድረግ ኢኮኖሚውን ከአፍሪካ ጥገት አላበው ለመጨረስ ማስመሰያ የእድገት መስመር አድርገውት ይሆን?‹‹ቀልቀሎ ስልቻ ስልቻ ቀልቀሉ›› እንዲሉ አይነት ነው እንጂ የ‹‹ቻይና ሞዴል›› ያው እንዳለው የአንድ ፓርቲ ስርአትከ1960 የቅኝ ግዛት ማነቆ ወጡበት ጊዜ ጀምሮ የነበረና ያለ ነው፡፡የዩጋንዳው ዩዌሪ ሙሴቪኒ፤የሩዋንዳው ፖውል ካጋሚ፤የ86 ዓመቱ የዝምባዌው ሮበርት ሙጋቤ የግዛት ዘመናቸውን ለማራዘም የተጠቀሙበት ሞዴል ነው አሁንም ተመልሶ የቻይና ሞዴል ተብሎ የሚለፈፈው፡፡ባለፉት የፍቅር ወቅቶች መለስ፤ሙሴቪኒና ካጋሚ (በክሊንተንና በብሌር ይሁንታ በተጫነላቸው ክብረ ዘውድ) ‹‹የአዲሲቱ አፍሪካ አዲስ ትውልድ መሪዎች›› በመባል የግዛት ዘመናቸውን ለማራዘም እንዲችሉ ተብሎ ይጠሩበት ነበር፡፡አሁን ደሞ የምእራቡ ዓለም መልእክተኞችና ጉዳይ ፈጻሚ በመሆን በየተላኩበት ሰብአዊ መብትን በመግፈፍ፤ የሕግን ልዕልና በመድፈር፤ ሰብአዊ መብትን በመጣስ የተልእኮ ክፍያቸውን ግብር ከፋዩ ሕዝብ በማያምንበት ቦታ እንዲውል እየተደረገ ለነዚህ ሰው በላ ፈላጭ ቆራጮች የአገልጋይነታቸውን እየተከፈሉ ነው፡፡ በሌላ በኩሉ ግን ጉዳዩ ያሳሰባቸው ሁሉ ስለነዚህ አፍሪካውያን አገልጋዮች ተግባር በአግባቡ ከማጋለጥና አለአግባብ ከሕዝብ የሚሰበሰብም ክፍያ መቆም እንዳለበት ትግላቸውን አላቆሙም፡፡የአንድ ሰው ለገዢነት የአንድ ፓርቲ መመሪያነት ተጨፍልቆና አዲስ ስመ ጥምቀት ተሰጥቶት አሁን ‹‹የቻይና ሞዴል›› የሚባለው ቀደም ሲል ክዋሚ ንክሩማህ የሰብ ሰሃራው አፍሪካ መሪ ሞክሮት ተስፋ በሚያስቆርጥ መልኩ የከሰፈ ተሞክሮ ነው፡፡ንክሩማህ ልክ እንዳሁኑ ወቅታዊው የቻይና ሞዴል አራጋቢ ብርማ መሳይ ምላስ፤ ንክሩማህም በዚያን ወቅት ኒኦ ኮሎኒያሊስምን (ንክሩማህ የፈጠረው የማስጠያ ቃል) እና ኢምፔሪያሊዝምን አፍሪካን በመበዝበዛቸውና ለድህነት በመዳረጋቸው ይረግምና ያወግዝ ነበር፡፡ የንክሩማህ ፈጣን የኢንደስትሪያላይዜሽን ፕሮጋራም ጋናን ከውጭ ምጸዋትና እርዳታ፤ በሀሃገሪቱ የካካዋ የዓለም ግብይት ላይ ከፍተኛ ውድቀት አድርሶ ነበር፡፡ሌሎችም ተግባራዊ ያደረጋቸው የኤኮኖሚ ልማት እቅዶችም በማያዳግምና ትንሳኤ በሌለው መልካቸው ለውድቀት ተዳረጉ፡፡
በ1966 ዓም በወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ከስልጣን በወረደበት ጊዜ ጋና በአፍሪካ ከፍተኛ ሃብታም ከመባል ደረጃ ወርዳ ዝቅተኛ የችጋር ሃገር ሆና ነበር፡፡በተመሳሳይም በአፍሪካ ከፍተኛ የእርሻ ምርት ውጤት ላኪነት አሽቆልቁላ ወደ ከፍተኛ የእርሻ ምርት ውጤት ገዢነት ወርዳለች፡፡የአንድ ሰው አንድ ፓርቲ መኖር እንደብሔር ግጭት አስወጋጅ፤የዘር ግጭት ፈጪ ከመሆን ይልቅ በይበልጥ አጉልቶ ያሳየው የጭግሩ አባባሽና የግጭቶቹ አመንጪና አባባሽ መሆኑን ነው፡፡እንዲያውም ከበርካታ ተሞክሮዎች እንደታየው የዚህ አገዛዝ ዋናው ተግባር እነዚህን ችግሮችና ግጭቶች በመፍጠር በሕብረተሰብ መሃል አለመግባባትና ግጭት ተጠናክረው የሃገሮች የአንድነት ነቀርሳ እንዲሆኑ ማድረግ መሆኑ ታይቷል፡፡ይህ እውነታም በአፍሪካ አህጉር ከሃገር ሃገር እንደ ሰደድ እሳት በመያያዝ ተዳርሶ የሃገሪቱን መኩሪያን ታሪካዊነት የሚመሰክሩትን፤ የውጭ ጎብኚዎችን የሚስቡትን የዱር አራዊት ጭምር ለስደትና ለርሃብ ዳርጓል፡፡ያም ሆኖ ግን የአፍሪካ ፈላጭ ቆራጭ ገዢዎች፤የወታደራዊ ጁንታ ገዢዎች፤አለ ያሉትን ዘዴያቸውን ሁሉ አንድ ገዢ አንድ ፓርቲ ያለውን ጠቀሜታ ለማሳመን የቱንም ያህል ቢፍጨረጨሩ ውጤቱ ግን ከገሃዱ እውነታ ሊያልፍላቸው አልቻለም፡፡ያም እውነታ ባለብዙ ፓርቲ መሆንን ብቻ ማዋጣቱንና ጠቀሜታው ነው፡፡ አሁን ያሉት ፈላጭ ቆራጭ የአፍሪካ እርባና ቢስ ገዢዎች ደግሞ እንደገና ወደ ኋላ መልሰው አፍሪካን ሊገድል ማነቆ አስሮባት ሲያስጨንቃትና አላላውስ ብሎ እንደግመል ሽንት ወደኋላ ሲጎትታት የኖረውን ስርአት ሊያመጡ ያረጀውንና የአግልግሎት ዘመኑን የጨረሰውን የማይላስ የማይቀመሰውን ጉዳይ በአዲስ ካባ ደርተው ‹‹ምርጡ የቻይና ሞዴል›› ብለው ሊያለብሱን ይዳዳቸዋል፡፡ያንኑ ተዝካሩ የተባላውን አንድ ሰው አንድ ፓርቲ፡፡
የ‹‹ቻይና ሞዴል›› በአፍሪካ ያለው ሁኔታ
መለስ ዜናዊና ሌሎቹ የተባበሩት የአፍሪካ ፈላጭ ቆራጭ ገዢዎች ይህን ገና ‹‹እምቦቀቅላ›› የሆነውን ‹‹ቻይና ሞዴል›› በእውነት መልኩ እየተቀበሉትና እየተከተሉት ነው? የሃገር ውስጥና የውጪ ኢንቬስተሮች በአፍሪካ ሥራቸውን ለማከናወን ነጻ እንቅስቃሴና ትግበራ አላቸው? ባልተብብራሩና ምንነታቸው በግልጽ መረዳት በማይቻል፤ ባቃዣቸው ቁጥር በሚወጡ ደንቦችና መመርያዎች ሳይታሰሩና ለችግር ሳይዳረጉ ይንቀሳቀሳሉ? እውቀት የለሽ የባለስላጣኑ ጃዊሳዎች ሳይጎሽሟቸውና መላ ቅደሱን ሳያጠፉባቸው ድርጅቶቻቸውን ይነራሉ? የነገው አዋጅና ደንብ ምን ይለን ይሆን ብለው ከማሰብ ይልቅ ለገበያው አስፈላጊው፤ ለፈላጊው ጠቃሚው ምን ይሆን ብለው ማቀድስ ይችላሉ? ለመሆነጁ በኢትዮጵያ ካለው ሥራ ውስጥ ስንቱ ነው ለመደራደር በሚያመችና ግልጽ በሆነ መመርያ የታቀፈው የኢንቬስትመንት አካል?የ2011ዱ የዓለም ባንክ ያወጣውና 183 ሃገራትን የፈረጀበት መመዘኛ (The 2011 World Bank Ease of Doing Business Index) በኢትዮጵያ ያሉትን ሁኔታዎች መመዘኛው በአሳዛኝ ደረጃ ላይ ያስቀምጣል፡፡ በአጠቃላይ ግምገማው 11ኛ ያደርጋትና፤ ሥራን ለመጀመር (99) የግንባታ ፈቃድ ለማከናወን (56) የመብራት ተጠቃሚ ለመሆን (93) ንብረትን ለማስመዝገብ (113) ብድር ለማግኘት (150) ኢንቬስተሮችን ጥቅም ማስጠበቅ (122) ታክስ ለመክፈል (40) ወደ ውጭ ገበያ ለማቅረብ (157) ውልን ማስከበር (57) አለመግባባትን ለመፍታት (89) የ‹‹ቻይና ሞዴል›› ለመለስ ዜናዊና ለግብረአበሮቹ ፈላጭ ቆራጮች በስልጣን ለመቆየት የሚያጠልቁት ጭንብላቸው ነው፡፡ ይህንኑ ጭምብል ደሞ በሕዝቡ አመለካከት ላይ አጥልቀው እውነቱን እንዳያውቅ ሊያደርጉታ ይሞክራሉ፡፡ ይህን በማድረግም ግልጥነትና ተጠያቂነት እንዳይኖራቸው፤ተወዳዳሪና ተቀናቃኝ ያሉበት ነጻና ፍትሃዊ ምርጫ እንዳይኖር፤ሕዝቡ የንብረት ባለቤትነት መብት እንዳይኖረውና ሁል ጊዜ የስርአቱ ለማኝና የሃገሩ ባይተዋር እንዲሆን፤ሃሳብን በነጻነት እንዳይገልጽ፤ነጻ ፕሬስ እንዳይኖር፤የፍትህ አካላት ታዛዥነታቸው ለፍትህ ስርአቱ ሳይሆን ለገዢዎች ጥቅም ማስጠበቂያ እንዲሆን የሚያደርጉትን ጸረ ህዝብና ጸረ ሃገር ድርጊታቸውን ለመሸፈን ይጠቀሙበታል፡፡ በዚህ ድርጊታቸው ሕዝቡ የስርአቱ ተገዢና አገልጋይ እንዲሆን፤ ለመቆጣጠርያነት ፖለቲካውን በማነቆነት በማስቀመጥ፤ ኤኮኖሚውን ተብትበው በማሰርና በኪሳቸው በመክተት ሃገሪቱን ለችጋርና ለምድረባዳነት፤ ሕዝቡን ለመከራ ስቃይና ኑሮን ለመጥላት ማድረጊያነት ሆን ብለው ይጠቀሙበታል፡፡የ‹‹ቻይናን ሞዴል›› የኤኮኖሚ ልማትን በመቃዠት ደረጃ እያራገቡ የፖለቲካ ነጻነትን በገሃድ ለመጨፍለቅ የሕዝቡን ዴሚክራሲያዊ ነጻነት መርገጥ ስለሚያስችላቸው ሕዝቡን በዚህ እያማለሉ የሃገሪቱን ብሔራዊ ኤኮኖሚ በግላቸው ይመገምጉታል፤ያደርቁታል፡፡
በቅርቡ፤ፋይናንሻል ግሎባል ኢንተግሪቲ ሲጽፍ፡- ‹‹… ኢትዮጵያዊያን ደማቸው ተመጦ ተመጦ ባዷቸውን እየቀሩ ነው፡፡ከአዘቀጠው የድህነት አረንቋ ለመውጣት ምንም ያህል ቢጠሩና ቢድሁ ዋናቸው ወንዙ ወደሚፈስበት ሳይሆን ወደሚመነጭበት ስለሆነ እስከማዕዜኑ ከዚያ መውጣት ዘበት ነው፡፡›› ይህ ነው እንግዲህ ለኢትዮጵያና ለአብዛኛዎቹ የአፍሪካ ሃገራት የ‹‹ቻይና ሞዴል›› የሚባልላቸው፡፡