Amharic Translations Archive

ስለጡት ካንሰር ለኢትዮጵያኖች የጥሞና ማሳሰቢያና ማስገንዘቢያ

ወርሃ ኦክቶበር (ጥቅምት)በአለም የጡት ካንሰር ማሳሰቢያና ማስገንዘቢያ ወቅት ነው፡፡ ወሩን በሙሉ በዓለም ላይ ሕዝባዊና የግል ድርጅቶች የፕሮግራሞቻቸውና የእንቅስቃሴዎቻቸው ትኩረት ሁሉ በጡት ካንሰር መንስኤ ላይ በማትኮር፤ አደጋውን ለመቀነስ፤ ቅድመ ጥንቃቄ ስለማድረግ፤ ህክምናና ምርምር በማከናወን ላይ ይገኛሉ፡፡ በእርግጠኝነት በተረጋገጠው መሰረት በአብላጫ በዓለም ላይ ሴቶችን በማጥቃት ላይ ያለው የጡት ካንሰር ነው፡፡ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሴቶች በበሽታው በየዓመቱ ሲለከፉ

ኢትዮጵያ፡- ከረጂም ርቀት ሯጮቻችን የምንማረው

ኢትዮጵያ በመልካም ስሟም፤በአስከፊ ገጽታዋም ትታወቃለች:: ኢትዮጵያ በመልካም እንግዳ ተቀባይነቷና አስተናጋጅነቷ፤በሕዝቦቿ መልካም ባሕሪ፤ በመልክአ ምድሯ ውበት፤እና በግሩሙ ቡናዋና በማይደፈሩት ጅጋኖች ረጂም ርቀት ሯጮቿ ትታወቃለች፡፡ ተወዳዳሪ በሌለው የሰብአዊ መብት ጥሰት፤የፕሬስ ማፈኛ ተቋሟም፤በአፍሪካ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የፖለቲካ እስረኞች የሚገኙባት ሃገርም ሆና ኢትዮጵያ ትታወቃለች፡፡ በሚያሳዝን ሁኔታ ችጋር (ኤክስፐርቶቹ እንደሚሉት፤ “ሥር የሰደደ የማይነቀል የምግብ እጥረት”) ከውቢቷ ኢትዮጵያ ጋር ከተሳሰረ ዘመናት

የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፖለቲካ የደሞክራሲ ጮራ ሰትወጣ

ላለፉት በርካታ ዓመታት ስለሥልጣን ተጠቃሚዎች ዕውነትን ስናገር ነበር፡፡ የጦማሬ ገጼ መግቢያ መስመሩ ‹‹ለሰብአዊ መብት ተሟገት፡፡ ስለሥልጣን ተጠቃሚዎች እውነትን መስክር›› ነው የሚለው፡፡ ይህ ደሞ ልዩ ትርጉም ያለው፤ ጠንካራ ሞራልና ስልጣናቸውን መከታ በማድረግ አላግባብ የሚጠቀሙበትን፤ ከመጠን በላይ ለሚተማመኑበት ኢሰብአዊ ድርጊት ማስገንዘቢያ የሆነ ስንኝ ነው፡፡ ለባለስልጣናት ነን ባዮች እውነትን መናገር፤ተናጋሪው በነዚህ ባለስልጣናት ላይ ስልጣናቸው የተዘረጋው በሃሰት ላይ መሆኑን

ኢትዮጵያ፤ በአዲስ ዓመት አዲስ ጠ/ሚኒስቴር

ኢትዮጵያዊያኖች አዲሱን ዓመታቸውን የዘመን መለወጫ በሴፕቴምበር 11 አክብረዋል፡፡ አሁን በኢትዮጵያ 2005 ዓም ነው፡፡ በሴፕተምበር 21 ደግሞ አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር ተሰጥቷቸዋል፡፡ አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር ከአዲስ ዓመት መግባት ጋር ተዳምሮ ሲቀርብ እንዴት ደስ ያሰኛል!! ከልብ የመነጨ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልእክትና መልካም ምኞት ለኢትዮጵያ ሕዝቦች ተገቢ ነው፡፡

በኢትዮጵያ ወቅቱ ወደፊት መራመጃ ነው (ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም)

በኢትዮጵያ ወቅቱ መጥረቢያውን ቀብሮ ወደፊት መራጃ ነው፡፡ ኔልሰን ማንዴላ እንዳስተማሩት ‹‹ከጠላትህ ጋር ሰላምን መመስረት ከፈለግህ፤ከጠላትህ ጋር አብረህ መስራት አለብህ በዚህን ጊዜ ጠላትህ አጋርህ ይሆናል፡፡›› እኔ ደግሞ ትንሽ ላክልበትና፤ጠላትህ ወዳጅህና ተባባሪህ ይሆናል፡፡ከታሪክ እንዳየነው፤ ብሔራዊ አሜሪካኖች (አሜሪካን ኢንዲያንስ) በመሃከላቸ ሰላምን ሲፈጥሩ፤መጥረቢያቸውን፤ መቁረጫቸውን በመሬት ውስጥ ይቀብሩታል:: ይህም በመሃላቸው ተነስቶ የነበረውን አለመግባባት መቋጨቱን ማረጋገጫ ነው፡፡ዛሬ ለኢትዮጵያውያን ሁሉ ያንን

አቶ መለስ እልፈት ስንብት (ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም)

መለስ ስለፈጸመውና ስላመለጠው ጉዳይ በሕይወት ዘመኑ እያለ በብቃት ያነሳሁት ስለሆነ አሁን ከህልፈቱ በኋላ ብዙም የምለው የለኝም፡፡ ሕልፈተ ሞቱ ያሳዝነኛል፤ ምክንያቱም፤ ጆን ዶን እንዳለው ‹‹የማንም ሰው ሞት ያሳንሰኛል፤ ምክንያቱም እኔም ቁጥሬ ከሰብአዊያን ጋር ነውና ፡፡ሞት ለሁላችንም በእኩል መንገድ መጪ ነው፡፡ሲመጣም ሁላችንንም በእኩል ደረጃ ያስቀምጠናል፡፡›› እንደ ሃቀኛ የሰብአዊ መብት ተሟጋች፤የለየለት ፈላጭ ቆራጭ ባለ ስልጣን ቢሞትም ያሳዝነኛል ምክንያቱም

ህገ መንግስታዊ ቀዉስ በኢትዮጲያ

ለአሜሪካ ድምጽ በቅርቡ በስጠሁት ቃለ ምልልስ ላይ በኢትዮጵያ ሕገ መንግስት መሰረት ጠቅላይ ሚኒሰተሩ በህመም፤ በእክል በሞት በአካለ ጉዳት በተለያዩ ሰበቦቸ በሰራው ላይ መገኘት ባይችል የስልጣን ዝውውሩ አንደት ይሆናል የሚል ጥያቄ ቀርቦልኝ ነበር ነበር። መልስ የሰጠሁት ብዙዎችን አሰግረምዋል፤ አሰደነግጦአል። ባጭሩ በኢትዮጲያ ሕገ መንግስት ስለ ስልጣን ዘውውር በግልጥ ያስቀመጠው ድነጋጌ ምንም የለም።

የሠላም ራዕይ ለኢትዮጵያ – ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም

ሕልምና ቅዠት ስለ ውቧ ኢትዮጵያ የሰብአዊ ተሟጋችና የምሁር ለሰሚ መናገር እውነትን ለስልጣን ያዦች መከሰትና ወደፊት ካለፈው ይሻላል የሚለውን ተስፋ ይዞ መጓዝ ነው፡፡ እውነተኛ የሰብአዊ መብት ተሟጋች የፖለቲካ ስልጣን ፍላጎት የለውም፡፡ የሰብአዊ መብት ፖለቲካ፤ የሰው ልጅ ክብርና ሞገስ መጠበቅ ፖለቲካ ነው፡፡ ስለ አይዲዎሎጂ አለያም ወገናዊነት ፖለቲካ ወይም የሥልጣን ሽሚያ አይደለም፡፡የሰብአዊ መብት ተሟጋች ስለወደፊት ተስፋ ነው የሚያተኩረው፡፡

እሪ! እንበል ለኢትዮጵያ (ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም)

በነጻነት መናገር የሁሉም የሰብአዊ መብቶች መሰረት ነው፡፡ በኔ ግምት፤የህብረተሰቡ ሃሳብን የመናገርን ነጻነት የሚሰጠው ዋጋ፤ ያ ሕብረተሰብ ነጻ መሆን አለመሆኑን የሚያረጋግጥበት መንገድ ነው፡፡ ግለሰቦች ያሻቸውን ለመናገር ፍርሃት ካደረባቸው፤ እንደህሊናቸው ፈቃድ ማሰብ፤ መጻፍ አለያም መንግስትን በመፍራት ከፈጠራ ተግባራቸው ከተገደቡ፤ ሊደርስባቸው በሚችል ማስፈራሪያና ዛቻ ወከባና እስር በመፍራት ያሰቡትን ማድረግ ካልቻሉ፤ያ ህብረተሰብ ነጻነቱን የተሰለበ ይሆናል:: ሃሳብን በነጻነት

ኢትዮጵያ የኛ፥ የምጽዋት ምርኮኛ? ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም

የዓለም አቀፍ ድጋፍ ሰጪ ደርጅቶችን፤የተባበሩት መንግስታትን የእርዳታ ኤጀንሲን፤ዩ ኤስ ኤይድስን፤የዓለም ባንክንና አይ ኤም ኤፍን ያካተተውን ‹‹ኢንዱስትሪ›› ግራሃም ሃንኮክ ‹‹የችጋራሞች ጌቶች›› በሚለው መጽሃፉ ምንነታቸውንና ማንነታቸውን ከነተግባራቸውና ከሃብታምነት ወይም የጌትነታቸውን መሰረት ቁልጭ አድርጎ አስነብቧል፡፡ደፋር አቀራረቡ ብዙዎችን ‹‹የዓለም አቀፍ መጽዋቾችን›› ቢያበሳጭም ሃቁን መካድና እውነትን መሸሽ የሚቻል አልሆነም፡፡የደራሲው መሰረታዊው ክርክሩ፤ ‹‹የዓለም አቀፍ እርዳታ የጊዜም፤የገንዘብም ብክነት›› ከመሆኑም አልፎ፤ተረጂ ምጽዋተኞችን