Amharic Translations Archive

በዘ-ህወሀት የውሸት ምድር የማወንበጃ መረጃ ዘመቻ፡ ቀጣፊው በኢትዮጵያ ዉሸትን  እዉነት ነው እያለ ሲሰብክ? 

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም  ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ የጸሐፊው ማስታዋሻ፡ በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ እየተጠናከረ የመጣውን የዘ-ህወሀት (ዘራፊ ህወሀት) የመረጃ ማወናበጃ ዘመቻ ለማጋለጥ ሲባል በተከታታይ እያቀረብኩ ካለሁት ትችት ይህ ሶስተኛው ክፍል ነው፡፡ እ.ኤ.አ መስከረም 5/2016 አቅርቤው በነበረው ትችት በኢትዮጵያ ውስጥ ተንሰራፍቶ የሚገኘውን የዘ-ህወሀትን የጭቆና አገዛዝ በመቃወም እየተስፋፋ እና እየተጠናከረ የመጣውን ሕዝባዊ የእምቢተኝነት አመጽ አሳንሶ እና አኮስሶ ለማቅረብ በሚል እኩይ

በኢትዮጵያ የዘ-ህወሀት የዘር ማጥፋት ተራ ውሸት እና ማወናበጃ ማስረጃ ሲጋለጥ

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም  ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ የጸሐፊው ማስታዋሻ፡ ይህንን ትችት የማቀርበው ለበርካታ ምክንያቶች ነው፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ እ.ኤ.አ መስከረም 5/2016 አቅርቤው በነበረው ትችቴ በአሁኑ ጊዜ በሀገሪቱ ውስጥ መጠነ ሰፊ በሆነ መልኩ ተቀጣጥሎ የሚገኘውን ሕዝባዊ አመጽ ዋጋ ለማሳጣት እና የኢትዮጵያን ሕዝብ እውነተኛ የጀግንነት እና የደፋርነት ታሪክ አዛብቶ ለማቅረብ ዘ-ህወሀት (የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ) ስልታዊ የሆኑ

“ደስታ ነገ ጠዋት አሸብርቆ ይመጣል!”፡ ለ2009 ዓ.ም የኢትዮጵያውያን አዲስ ዓመት መልዕክቴ

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም  ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ  ያለ መራራ ትግል ምንም ዓይነት ዕድገት ሊኖር አይችልም!  እ.ኤ.አ መስከረም 11/2016 የኢትዮጵያውያን አዲስ ዓመት የ2009 ዓ.ም የመጀመሪያ ዕለት ነው (እንደ ኢትዮጵያውያን ዘመን አቆጣጠር መስከረም 1 ቀን)፡፡ “2009 መልካም አዲስ ዓመት ይሁንልዎ“ የሚሉትን ቃላት መናገር ለእኔ በጣም የሚያም እና የሚቆጠቁጥ ነገር ነው፡፡ ወገኖቻችን በየቦታው በገዛ ሀገራቸው መብታቸው ተገፍፎ እንደ ፋሲካ

የዘ-ህወሀት ተራ ቅጥፈት እና የማወናበጃ መረጃ የማዛባት ዘመቻ፣

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም  ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ “TPLF” በሚለው የእንግሊዝኛው አህጽሮ ቃል ውስጥ የሚገኙት እና “LF” ተብለው የተጻፉት ሁለት የመጨራሻ ፊደሎች ሲተነተኑ “Lie Factory/የቅፈት ማሽን/ፋብሪካ” የሚለውን ይወክላሉን?  እንደዚሁም ሁሉ “ህወሀት” በሚለው የአማርኛው አህጽሮ ቃል ውስጥ የሚገኙት እና “ሀት“ በማለት የሚነበቡት የመጨረሻዎቹ ሁለት ፊደሎች “ሀሰት ትረካ“ የሚለውን ይወክላሉን?  ዘ-ህወሀት (የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ)

የኢትዮጵያ ነብሮች ሲበሳጩ ያጉረመርማሉ!

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም  ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ  አሜሪካውያን የጀግንነት በላይነት የላቸውም፣  ማለትም  የኦሎምፒክ ጀግንነት ጠቅላይነት፡፡ እ.ኤ.አ ነሐሴ 21/2016 የ26 ዓመቱ የኢትዮጵያ የረዥም ርቀት ማራቶን ሯጩ ፈይሳ ሌሊሳ በአንድ ወቅት በኦሎምፒክ ጨዋታዎች ታሪክ “የኦሎምፒክ ጨዋታዎች የፖለቲካ እንቅስቃሴ መግለጫ መድረኮች ሊሆኑ አይችሉም” በማለት ይገለጽ የነበረውን ሕግ ወደ ጎን አሽቀንጥሮ በመጣል በሪዮ ኦሎምፒክ ውድድር አስደናቂ የሆነ ታሪካዊ ድርጊትን ደግሟል፡፡ እ.ኤ.አ ጥቅምት

ኢትዮጵያ፡ ከጭፍን የፖለቲካ ጥላቻ ባሻገር፣

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም  ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ   የእምነቴ መርሆዎች፡ በአሁኑ ጊዜ ጥላቻ በኢትዮጵያ ሕዝብ እና በነጻነት፣ በዴሞክራሲ እና በሰብአዊ መብት ጥበቃ የተፈረከሰከሰ ግድግዳ መካከል የቆመ ነገር ሆኖ ይገኛል፡፡ የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ (ዘ-ህወሀት) ጥላቻን የፖለቲካ መጠቀሚያ መሳሪያ አድርጎት ይገኛል፡፡ ሆኖም ግን በአሁኑ ጊዜ በዘ-ህወሀት እየተቀነቀነ ያለው የጭቃ ግድግዳ ጥላቻ በሕዝባዊ የእሳተ ገሞራ

አእምሯቸው “የደነዘ አማሮች”፣ የኦሮሞ “ወንጀለኞች እና አሸባሪዎች” በ2016 እየተነሱ ነውን?

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም  ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ    እውን አማሮች የደነዙ ሕዝቦች ናቸውን? መሬታቸው በየጊዜው እየተወረሰ እንደ ዳቦ እየተቆረሰ ከነጻ መሬታቸው መፈናቀላቸውን በመቃወም የመሬት ቅርምት ዕኩይ ድርጊቱ እንዲቆም እና መብታቸው እንዲከበርላቸው በመጠየቃቸው ብቻ እውን የኦሮሞ ሰላማዊ አማጺዎች “ወንጀለኞች እና አሸባሪዎች” ናቸውን? እነዚህ የግፍ አገዛዝ ቀንበር የተጫነባቸው እና ያመረሩ ብዙሁን የሀገሪቱ ሕዝቦች በአሁኑ ጊዜ በአናሳ የዘረኛ ቡድን ስብስብ

“ሲመረው የማይነሳ ህዝብ የለም ባለም፣” አለ አቦይ ስብሐት ነጋ!

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም  ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ የኢትዮጵያውያን የጸደይ አብዮት በ2016 የክረምት ወቅት መጀመሩ ነውን?  አንድ ህዝብ ታምቆ ፣ ታምቆ ማለት ተጨቁኖ  በዘመንታ አይቆይም ። ዩኒቨርሳል universal  ማለት ነው ።  አንድ ህዝብ እንደ ህዝብ መጠን  በዓለም ታሪክ  አንዳስቀመጡት አንደፈለጉት  የሚቀመጥ አይደለም። ሲመረው ይፈነዳል።  ይሄ ዓለም አቀፋዊ  እውነታ /universal  truth  ነው። ሲመረው የማይነሳ ህዝብ የለም ባለም።  በታሪክም /historically።  አሁንም።  ለወደፊትም

ኢትዮጵያ በእሳተገሞራ ጫፍ ላይ ተቀምጣ! 

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም  ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ “በሰላማዊ መንገድ ለውጥ እንዳይመጣ የሚከላከሉ ሁሉ ሞገደኛውን እና የማይቀረውን የአብዮት ማዕበል እንዲያስተናግዱ ይገደዳሉ” ጆን ኤፍ. ኬኔዲ እንዲፈጸምልህ በምትመኘው ነገር ላይ አስቀድምህ ተጠንቀቅ ምክንያቱም የሚሆነው አይታወቅም የተመኘኸውን ልታገኝ ትችላለህና… በአሁኑ ጊዜ በህይወት የሌለው እና የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ (ዘ-ህወሀት) ፈላጭ ቆራጭ መሪ የነበረው አምባገነኑ መለስ ዜናዊ

“ከዚህ በላይ ምን ትሆናለህ? ክተት! አትነሳም እንዴ?” አለ ዘረኛው ኒዮ ፋሺስት ዶናልድ ትረምፕ በሪፑብልካኑ ጉባዬ ላይ 

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም  ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ በጁሊየስ ቄሳር ተውኔት ውስጥ የቄሳርን ሞት ተከትሎ ጣሊያንን ሽባ የሚያደደርግ የእርስ በእርስ ጦርነት ሊከሰት እንደሚችል ሸክስፒር የማርክ አንቶኒን ገጸ ባህሪነት በመላበስ እንዲህ በማለት አስጠንቅቀው ነበር፡ “…እናም አቴ በእርሱ በኩል ከጋነም እሳት ሆኖ በመምጣት የቄሳርን መንፈስ በመላበስ የንጉሱን ድምጽ በመያዝ ለበቀል ተዘጋጅቷል፡፡ እናም እናልቅስ፣ እናም እነዚህን የጦርነት ውሾች እናስወግድ“ ብለው