አእምሯቸው “የደነዘ አማሮች”፣ የኦሮሞ “ወንጀለኞች እና አሸባሪዎች” በ2016 እየተነሱ ነውን?

 የተቆጡ ነብሮች

የተቆጡ ነብሮች!

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም 

ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ   

እውን አማሮች የደነዙ ሕዝቦች ናቸውን?

መሬታቸው በየጊዜው እየተወረሰ እንደ ዳቦ እየተቆረሰ ከነጻ መሬታቸው መፈናቀላቸውን በመቃወም የመሬት ቅርምት ዕኩይ ድርጊቱ እንዲቆም እና መብታቸው እንዲከበርላቸው በመጠየቃቸው ብቻ እውን የኦሮሞ ሰላማዊ አማጺዎች “ወንጀለኞች እና አሸባሪዎች” ናቸውን?

እነዚህ የግፍ አገዛዝ ቀንበር የተጫነባቸው እና ያመረሩ ብዙሁን የሀገሪቱ ሕዝቦች በአሁኑ ጊዜ በአናሳ የዘረኛ ቡድን ስብስብ እንደዚህ ያሉ የሰብአዊ መብቶችን መደፍጠጥ በመቃወም አስከፊውን የጭቆና አገዛዝ አፈር ድሜ በማብላት ግብዓተ መሬቱን ለመፈጸም ቆርጠው በመነሳሳት በተጨባጭ ምስክርነታቸውን በማሳየት ላይ ናቸውን?

ዘ-ህወሀት (የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ) እና ታዛዥ ሎሌዎቻቸው ስሜታዊነትን በተላበሰ መልኩ ስለአማሮች እና ኦሮሞዎች እንዲህ ይላሉ፣ “አማሮች እና ኦሮሞዎች የደነዙ፣ ደደቦች፣ ዝቅተኞች፣ ወንጀለኞች እና አሸባሪዎች ናቸው“ ጉድ እኮ ነው የእኛ ጠቢቦች እና ብልሆች የማይቀባጥሩት እና የማይዘላበዱት ነገር ይኖራል ብላችሁ ነው?!

የዘ-ህወሀት የጭፍን ጥላቻ አራማጆች የአማርኛው ንግግር እና አንዳንድ የእንግሊዝኛ ቃላት እና ሀረጎች እንደወረደ ቃል በቃል ከዚህ በታች እንደሚከተለው ቀርቧል፡

በድምፅ ለመስማት እዚህ ይጫኑ

  …በትግርኛ አረኩት እንዴ! አዎ እኔ እንግዲህ አሁን ምንድን ነበረ ስል የነበርኩት ቅድም እንደ voice of መለስ voice of መለስ ትርጉም ምን ነበር በChinese ያለው? ከዚያ ሲተረጎም (ሂ.ሂ.ሂ ሳቅ) ምንድን ነው ምን ‘አየር ላይ ብትሞትም አየር ላይ አትቀበርም‘ የሚል ምሳሌ አምጥቶ ነበር፡፡ Ok! አሁን እኔ ለማለት የፈለኩት ምንድን ነው እኔ I am not criticizing by any means እንትናን ጎበዛይን አይደለም፡፡ ስሜቱ ይገባኛል if he is right፡፡ Unfortunately አማራው በተለያየ መልኩ አንድ የሆነ ዓይነት ግጭት ፈጥረው ትግሬውን ለመከፋፈል ለመበጣጠስ ነው የሚፈልጉት እና ይኸንን አሁን በተለያየ ፎርም መጥተው እኛንም እዚህ እያበሳጩን ይኸ አንዱ ስትራቴጂ ነው፡፡ እዚያ ላይ እንትና አራት ኪሎ ላይ ጉብ ለማለት የሚል አካሄድ ስላላቸው ወደ አንዲት ኮርነር ወደ አንድ ጥግ ለማስጠጋት ብዙ ስለሚጥሩ ከተነቃባቸው በጣም ቆይቷል፣ ቆይቷል እና ልክ ነህ ወንድሞቻችን the ultimate price ከፍለዋል፡፡ ተዋግተውም ህይወታቸውን ሰውተዋል፡፡ ያ እኩልነት እነዚያ የሞቱት ወንድሞቻችን ትልቅ ዋጋ ከፍለው ይህንን እኩልነት ይህንን reality ኢትዮጵያ ውስጥ happen እንዲያደርግ ስላደረጉ ነው፡፡

ይኸ በጣም የሚያንገሸግሻቸው ያስጠላቸው ሰዎች እነዚህ ፍየል በመጠበቅ ላይ ያሉት ፍየል ጥበቃ ላይ ያሉት ኤርትራ ውስጥ (ሂ.ሂ.ሂ ሳቅ) ok anyway ከአንድ አካባቢ የመጡ retards, retards ማለት ነው፣ እና ከየት ነው የሚመጣው እንደዚህ ዓይነቱ የት ጎጃሜው (የአማራ ሕዝብ) they are called retards, retards (ደነዞች) ነው የሚባሉት፡፡ ጎንደሬው (ሌላው የአማራ ሕዝብ) ጠላት ነው ሊሸለሙ አይገባቸውም፣(ደነዞች) retards ናቸው በአስተሳሰብ፣ በጭንቅላት በጣም ዝቅ ያሉ ዝቅተኞች retards ናቸው፣ ሌላ category ናቸው፡፡ እና they represent retarded የሆነ idea, retarded የሆነ አካሄድ፣ ኢትዮጵያዊነትን ያልተላበሰ አካሄድ የሚከተሉ የወደቁ ዝቅተኞች ስለሆኑ እነዚህ ዝቅተኞች እያልን refer እናርጋቸው refer ማድረግ ካለብን አንተ ዝቅተኛ you don’t represent, you don’t dare talk to me ብለን ዝቅተኛ retard idiot እያልን ልንጠራቸው እንችላለን፡፡ ከዚያ ውጭ ግን እኔ የዚህ ምናምን እሱ ትላንትና ተንከባሎ የወደቀ፣ የወደቀ አመለካከት ነው፡፡ እሱን ልናነሳ ከተቀበረበት ቆፍረን ልናወጣ ጊዜውም የለንም፣ ወደፊት እየገሰገስን ነው፣ ህዳሴ damን እየገደብን ነው፣ የባቡር መንገድ እየተዘረጋ ነው አገራችን እና (ሂ.ሂ.ሂ ሳቅ) እና እነዚህ ሪታርዶቹ unfortunately አየህ filter ተደርገው የሚመጡ 90%ቱ part of ላይፋቸውን የሪታርድዶቹ ማለቴ ነው ቅድም describe ያረኳቸው 90%ቱ part of ላይፋቸው ነው የላቸውማ የላቸውም ምንም ስራ የላቸውም እኮ የላቸውም እና በደርግ ጊዜ ሻለቃ ምናምን ማንቴስ፣ መቶ አለቃ ምናምን፡፡ ወደድክም ጠላህም ዋጋ ተከፍሎ መጥተናል በቃ this is the end of the story ለሚቀጥለው ደግሞ እንጸልይላችኋለን አይ ጎንደሬ የትኛው ሚሊሻ እንደሚመጣ! (ሂ.ሂ.ሂ ሳቅ) ok” ነው እያሉ ያሉት፡፡ (አጽንኦ ተጨምሯል፡፡)

ዘ-ህወሀት የአማራ እና የኦሮሞ ሕዝቦችን በመዘለፉ እና በማዋረድ እርኩስ ምግባሩ ያለምንም ማቋረጥ አሁንም በተጠናከረበት ቀጥሎበት ይገኛል፡፡

ዘ-ህወሀት ከመጀመሪያው ጀምሮ ሲያራምደው የነበረው ጭፍን የሆነ የዘር ጥላቻ እና አጠቃላይ በሆነ መልኩ የአማራውን ሕዝብ የማጥፋት ፕሮፓጋንዳ እና እልቂትን መፈጸም እንደሆነ የቀድሞው የህወሀት የገንዘብ ግምጃ ቤት ኃላፊ እና የህወሀት የበላይ አመራር የነበሩት እና የድርጀቱ እኩይ ዓላማ ያልተዋጠላቸው በመሆኑ እራሳቸውን ከህወሀት በማግለል ፍርሀትየለሽ እና የማይበገሩ እውነት ተናጋሪ ኢትዮጵያዊ አርበኛ ሆነው እስከ አሁን ድረስ በመታገል ላይ የሚገኙት ገብረመድህን አርዓያ ያለምንም መሸፋፈን ግልጽ በሆነ መልኩ እውነታውን ፍርጥርጥ አድርገው ገልጸዋል፡፡

እንደ ገብረመድህን ገለጻ (ለ7 ደቂቃ ከ26 ሰከንዶች የሚዘልቀውን የቪዲዮ ክሊፕ ምስል ይመልከቱ) የዘ-ህወሀት አመራሮች ለአባሎቻቸው፣ ለተከታዮቻቸው እና ለደጋፊዎቻቸው እንዲህ በማለት ያስተምሯቸው እንደነበር ተናግረዋል፡

…አማራ የትግራይ ሕዝብ ጠላት ነው፡፡ ይህ ብቻም አይደለም፣ አማራ የትግራይ ሕዝብ ድርብ ጠላትም ነው፡፡ ስለሆነም አማራን መምታት አለብን፡፡ አማራን ማጥፋት አለብን፡፡ አማራ ካልጠፋ እና ካልተመታ እንዲሁም ከምድረገጽ እንዲጠፋ ካልተደረገ በስተቀር የትግራይ ሕዝብ በነጻነት ሊኖር አይችልም፡፡ እናም ለመመስረት ለምንፈልገው መንግስት አማራ ዋና አደናቃፊ መሰናክል ይሆናል፡፡ እንግዲህ ጉዳዩ ይህ ማለት ነው… 

(የዘ-ህወሀትን የጥላቻ ፖለቲካ ዝርዝር ትንታኔ ለማወቅ እ.ኤ.አ ሕዳር 2014 “ኢትዮጵያዊነትን እና ኢትዮጵያን ማጥፋት“ በሚል ርዕስ አዘጋጅቼው የነበረውን ትችት እንድትመለከቱት እጋብዛለሁ፡፡)

ዘ-ህወሀት ሰላማዊ የአሮሞ አማጺዎችን በማዋረድ እና ስማቸውን ጠላሸት በመቀባት “ወንጀለኞች እና አሸባሪዎች” በማለት ይጠራቸዋል፡፡ የዘ-ህወሀት የይስሙላ ፓርላማ አፈጉባኤ የሀሰት አሳፋሪ የውንጀላ ክስ በመመስረት ለሕዝብ ቁጣዉን ይፋ አድርጓል፡፡

የዘ-ህወሀት ደጋፊዎች አሁን በህይወት እንደሌለው እና አማራን እና ኦሮሞን ማንቋሸሽ እና ጥላሸት መቀባት ይወድ እንደነበረው እንደ ትንሹ አምላካቸው እና የዘ-ህወሀት ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ፈላጭ ቆራጭ መሪ እንደነበረው እንደ አምባገነኑ መለስ ዜናዊ ሁሉ ጥላቻን በመዝራት ላይ ይገኛሉ፡፡

የኦባማ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ሱሳን ራይስ በአምባገነኑ መለስ የቀብር ስነስርዓት ላይ እ.ኤ.አ 2012 አዲስ አበባ በመገኘት “መለስ ጠንካራ፣ ስሜታዊ ያልሆነ እና አንዳንድ ጊዜም የማይበገር ነበር፡፡ በእርግጥ ለሞኞች፣ ወይም ደግሞ እርሱ እራሱ ደደቦች እያለ ይጠራቸው ለነበሩት ሰዎች ምንም ዓይነት ትዕግስት አልነበረውም“ በማለት የሌለውን ስብዕና በመካብ አሞካሽታው ነበር፡፡

አምባገነኑ መለስ ለተቃናቃኞቹ የሚሆኑ በተለይም ለአማሮች የሚጠቀምባቸው ልዩ ትርጉም ያላቸው እና የንቀት ቃላትን ያስቀምጥ ነበር፡፡

አምባገነኑ መለስ ተቀናቃኞቹን ሁልጊዜ “ውዳቂ ቆሻሻዎች”፣ “የጭቃ ጅራፎች” (የጭቃ ሰዎች)፣ “ጠላቶች” እና “አሸባሪዎች” በማለት የዘለፋ ውርጅብኝ ያወርድባቸው ነበር፡፡

የዘ-ህወሀት አመራሮች፣ አባላት እና ደጋፊዎች ሁሉንም ኢትዮጵያውያን “ደነዞች፣ ሞኞች እና ደደቦች” በማለት ይፈርጇቸዋል፡፡

ዘ-ህወሀት የአማራ የፖለቲካ እስረኞችን እንኳ ሳይቀር ለማዋረድ አጋጣሚውን ሁሉ ከመጠቀም የሚያመልጣቸው ጊዜ የለም፡፡ የዓይን እማኞች እንዳረጋገጡት ጀኔራል አሳምነው ጽጌ በፍርድ ቤት ችሎት ላይ በነበሩበት ጊዜ በእርሳቸው ላይ ስቃይ የሚፈጽሙት አሰቃዮቻቸው “አማራ ሽንታም ነው!”…እና ምን ታመጣላችሁ?” ይህም ማለት “አማራ በራሱ ላይ ሽንቱን የሚለቅ ቦቅቧቃ ፈሪ ነው፣ ምን ልታመጡ ትችላላችሁ?” በማለት የጎሳ ስድብ ይሳደቡ እንደነበር ለፍርድ ቤቱ ማስረዳታቸውን ተናግረዋል::

የወሮበላ ዘራፊ ቡድን ስብስቡ ፈላጭ ቆራጭ መሪ የነበረው አምባገነኑ መለስ ዜናዊ በኢትዮጵያ ውስጥ የጅምላ የዘር ማጥፋት ወንጀልን ለመፈጸም ዓላማ ያለው ይመስል ነበር፡፡

አምባገነኑ መለስ በእርሱ እና በግብረ አበር ወንጀለኛ ጓደኞች ላይ ነገሮች ሁሉ እየጠነከሩ እና መልካቸውን እየቀየሩ በሚመጡበት ጊዜ የሩዋንዳን ዓይነት የኢንተርሀሞይ የዘር ፍጅት (በኪንያሩዋንዳ ወይም ደግሞ በሩዋንዳ የቋንቋ ትርጉም መሰረት “በአንድነት የሚቆሙ፣ የሚሰሩ፣ የሚዋጉ፣ በአንድነት የሚያጠቁ“) ዓይነት እልቂትን በኢትዮጵያ ውስጥ ለመፈጸም ሰፍሮበት የነበረው ጅኒ ተጠናውቶት ነበር፣ የልብን ጓዳ ፈልቅቆ የሚያየው አምላክ የእራሱን እርምጃ አስቀድሞ ወሰደ እንጅ፡፡

አምባገነኑ መለስ ዜናዊ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚሰራጨውን የአሜሪካ ድምጽ የአማርኛውን አገልግሎት ቪኦኤን እ.ኤ.አ. በ2010 ለማፈን በወሰነበት ጊዜ ለሚፈጽመው እኩይ ምግባር አመክንዮ ብሎ ያቀረበው ቪኦኤ የዘር ፍጅትን ይቀሰቅሳል በማለት እንዲህ የሚል ቅጥ አምባሩ የጠፋት የእብዶች ንግግር ነበር፡

“ከበርካታ ጉዳዮች አንጻር ለብዙ ዓመታት ስንመለከተው እንደቆየነው እና በውል እንደተገነዘብነው የቪኦኤ ድምጽ የአማርኛው አገልግሎት ትንሹን የጋዜጠኝነት የስነ ምግባር መርሆ መስፈርትን እንኳ የማያሟላ እና አፍራሽ የሆነ ፕሮፓጋንዳ በመንዛት በሩዋንዳ የነበረውን የሬዲዮ ሚሌ ኮሊንስን የሬዲዮ ጣቢያ ዓይነት አስከፊ የዘር ፍጅት አፍራሽ የስርጭት ፕሮፓጋንዳ በመንዛት ተሞክሮ ላይ ተጠምዶ እንደሚገኝ አምነናል“ ነበር ያለው፡፡

በዚያን ጊዜ እ.ኤ.አ ግንቦት 2011 “የአሜሪካ ድምጽ የአማርኛው አገልግሎት ቪኦኤን መከላከል“ በሚል ርዕስ ትችት በማቅረብ አምባገነኑን መለስ ዜናዊን ሞግቼ ነበር፡፡

የዚያ ዓይነቱ የዘ-ህወሀት ደጋፊዎች የጥላቻ የጅምላ የዘር ፍጅት መዝሙር ጥልቅ የሆነ ዘለፋ ብቻ ተደርጎ የሚቆጠር አይደለም፣ ሆኖም ግን ከዚህ በበለጠ መልኩ የዘ-ህወሀት ወሮበላ ዘራፊዎችን እና ቀማኞችን የጨለማ እርኩስ መንፈስ ቁልጭ አድርጎ የሚያመላክት መስታወት ጭምር እንጅ፡፡

የጥላቻ፣ የፍርሀት እና ስም የማጠልሸት አሰራጭ ህዋስ ተሸካሚዎችን ሁልጊዜ ማጋለጥ እና ከፍተኛ መገዳደር ሊደረግባቸው ይገባል፡፡

ይህን የመሰለ የጥላቻ ዕኩይ ምግባር ሲፈጸም ዝም ብሎ በጸጥታ መመልከት ማለት በእሳት ላይ ነዳጅ ሲርከፈከፍ ዝም ብሎ ከመመልከት ጋር መሳ ለመሳ ነው፡፡ ዝምታ ጥላቻን ይፈለፍላል፡፡ የዘ-ህወሀትን የጥላቻ አራማጆች ዕኩይ ድርጊት ዝም ብሎ በጸጥታ መመልከት ከሞራል ስብዕና ዝቅጠት ወንጀል ጋር መሳ ለመሳ ነው፡፡

የዘ-ህወሀትን ደጋፊዎች እና አፈቀላጤዎች በሁሉም የአማራ እና የኦሮሞ ሕዝቦች ላይ እንደዚህ ያለ አውዳሚ እና ቀስቃሽ የሆነ የቃላት ጦርነት የማድረግ ዝንባሌ እንዲይዝ ያደረገው ዋናው ዓላማ በሁሉም አማሮች እና ኦሮሞዎች ላይ አስፈሪ እና የአመጽ ጥላቻን ለመተግበር ሲባል የሚደረግ ዕኩይ ምግባር ነው በማለት ለመግለጽ ይቻላል፡፡

የዘ-ህወሀትን የጥላቻ አራማጆች ውዳቂ እና ዘባትሎ የርዕዮት ዓለም ፍልስፍና ባለመከተል እነርሱን ከነሰነዳቸው አሽቀንጥሮ ለመጣል ቀላል ነገር ነው፡፡ ሆኖም ግን ይኸ ትልቅ ስህተት ይሆናል፡፡

የዘ-ህወሀት ደጋፊዎች የህዝብን ስሜት የሚያስቀይሱ እና ለውድመት ሊዳርጉ የሚችሉ የብዙሀን መገናኛዎችን በእጆቻቸው ይዘዋል፡፡ ስለሆነም በእነርሱ የጥላቻ ንግግር የእርስ በእርስ ጦርነት እንዲካሄድ የጅምላ የዘር ፍጅት እሳቱን መጫር ይችላሉ፡፡

በሩዋንዳ የጅምላ የዘር ፍጅት እልቂት መጀመሪያ ላይ የታየውም ሌላ ምንም ነገር ሳይሆን በእርግጠኝነት ይኸ ክስተት ነበር፡፡

ፈርዲናንድ ናሂማና፣ ሀሰን ገዜ እና ጅን ቦስኮ ባራያግዊዛ የግል የሆነውን ኤፍኤም የሚሌ ኮሊንስን የሬዲዮ ቴልቪዥን በመያዝ የአገዛዙ ግብረ አበሮቸ በመሆን በጸረ ቱትሲዎችነት፣ በጥቂት ሁቱዎች፣ በቤልጀሞች እና በተባበሩት መንግስታት ተልዕኮ ላይ ቆጥቋጭ እና ከፍተኛ የሆነ ፕሮፓጋንዳ በማሰራጨት ለዕኩይ ተግባር  ተጠቅመውበታል፡፡

ባለሶስት የራድዮ ፕሮግራም አስተናጋጆች  የሚሌ ኮሊንስ ሬዲዮ ቴሌቪዥን ጣቢያ ቱትሲዎች እንደ በረሮዎች (ተባዮች) እንደሚቆጠሩ እና ቱትሲዎች እና ለዘብተኛ የሆኑት ጥቂት ሁቱዎች የት ቦታ እንደሚገኙ ለገዳዮቹ ወሮበላ ሁቱዎች በማመላከት ከፍተኛ የሆነ የማስተባበር ስራ ሰርቷል፡፡

የሩዋንዳ የራድዮ አሰራጭዎች ጭካኔ በተመላበት መልኩ እንዲህ በማለት ተማጽነዋል፣ “ቱትሲዎችን መግደል አለባችሁ፣ በረሮዎች ናቸውና“ ይሉ ነበር እነዚያ ሰይጣን የሰፈረባቸው አጋንንቶች፡፡

በሩዋንዳ የዘር ፍጅት ዕልቂት ፈርዲናንድ ናሂማና፣ ሀሰን ገዜ እና ጅን ቦስኮ ባራያግዊዛ ሬዲዮ ሚሌ ኮሊንን በመጠቀም በፈጸሙት የዘር ፍጅት ወንጀል እ.ኤ.አ 2003 በዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ችሎት ቀርበው ጥፋተኞች ሆነው በመገኘታቸው በጣም ረዥም የሆነ እስራት ተበይኖባቸዋል፡፡

ለመሆኑ ከዘ-ህወሀት የጥላቻ መልዕክተኞች “አማሮችን መግደል አለባችሁ፣ ደነዞች ናቸውና“ የሚለው መልክት ምን ማለት ነው?

ቱትሲዎችን “በረሮዎች” ናቸው በማለት ሲያቀርቡት በነበረው በሩዋንዳ ሬዲዮ አሰራጮች ገለጻ እና በዘ-ህወሀት የጥላቻ አራማጆች አማካይነት በተደጋጋሚ “አማራ ደነዝ ነው” በሚሉት መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው?

በሁለቱ መካከል ትንሽ ልዩነት ብቻ አለ፡፡ ለአንዱ “በረሮ” የሆነው ለሌላኛው “ደነዝ” የመሆኑ ጉዳይ ብቻ ነው፡፡

እስከ አሁን ድረስ ያልተመለሰ እና እንዲህ የሚል አንድ ጥያቄ ብቻ አለ፣ “በሩዋንዳ ‘በረሮዎች’ ላይ የተፈጸሙት ዓይነት ሰብአዊ የዘር ማጥፋት ወንጀሎች ‘በአማራ ደነዞች’ ላይ ሊፈጸሙ የሚችሉት መቼ ነው?” የሚለው ነው፡፡

ደነዝ አእምሮ ያላቸው እና ሌሎች የአካል ጉዳት አለባቸው ብለው የፈረጇቸውን ህዝቦች ለማጥፋት እና ለማኮላሸት ናዚዎች የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ከፍተው ነበር፡፡

የናዚ ጀርመኖች  በእነርሱ አባባል የአእምሮ ደነዞች ምርጦቹ የሆኑት የአሪያን ህዝቦች በሚሰሩት መንገድ መሰረት መስራት አይችሉም በማለት ፈርጀዋቸው እንደነበረው ሁሉ በተመሳሳይ መልኩ የዘ-ህወሀት ጎሰኛ እና ዘረኛ የጥላቻ አራጋቢዎች አማራን ኢትዮጵያዊነት በሆነ መንገድ መስራት የማይችሉ ደነዞች ናቸው በማለት ባዶ እና የድድብና ፕሮፓጋንዳቸውን በማናፈስ ላይ ይገኛሉ፡፡

የዘ-ህወሀት የጥላቻ አራጋቢዎች አማራን “ደነዞች” እና ዝቅተኞች እንደሚሏቸው ሁሉ በተመሳሳይ መልኩ በናዚ ጀርመን ናዚዎች የአእምሮ ደነዞች እያሉ ይፈርጇቸው የነበሩትን ዜጎች ሁሉ “ዝቅተኞች” ይሏቸው ነበር፡፡

ናዚዎች በጀርመን ሀገር ውስጥ በዘር የበላይነት (Ubermenschen [supermen]) አላቸው ብለው የሚያምኑባቸውን አሪያኖችን ለመግለጽ ትንሽ ለየት ያለ ቃል ይጠቀሙ ነበር፡፡

የዘ-ህወሀት ጥላቻ አራጋቢዎች እንዲህ በማለት አውጀዋል፣ “ወንድሞቻችን the ultimate price ከፍለዋል፡፡ ተዋግተውም ህይወታቸውን ሰውተዋል” ብለዋል፡፡ 

የዘ-ህወሀት የጥላቻ አራጋቢዎች ያልተሳሳተው ሀሳባቸው አማሮች፣ ኦሮሞዎች እና ሌሎች ህዝቦች ሁሉ ሞገሳቸውን ወይም ደግሞ ክብራቸውን ለመጠበቅ ሲሉ እጆቻቸውን ፍጹም ለማንሳት የማይችሉ ቦቅቧቃ ፈሪዎች እና ደካማ የሆኑ ሽባዎች ናቸው በማለት ላይ ይገኛሉ፡፡

የዘ-ህወሀት ውዳቂ እርባናየለሽ የዘራፊ ቡድን ስብስቦች በማለት ላይ ያሉት አማሮች፣ ኦሮሞዎች እና ሌሎች ህዝቦች የመጨረሻውን ዋጋ ከፍለው ሞገሳቸውን፣ ክብራቸውን እና ነጻነታቸውን ከመቀዳጀት ይልቅ ባሪያ ሆነው መኖርን ይመርጣሉ ነው በግልጽ እያሉ ያሉት፡፡

ለዚህም ነው የዘ-ህወሀት የጥላቻ አራጋቢዎች የእነርሱ ቦታ የበላይ እና የማያወዛግብ ገዥዎች መሆን እንዳለባቸው እራሳቸውን አሳምነው በኢትዮጵያ ውስጥ ግዛታቸውን መስርተው ሀገሪቱን እና ህዝቦቿን በማተራመስ ላይ የሚገኙት፡፡

ሆኖም ግን ለዘ-ህወሀት አማሮች ደነዞች ናቸው፡፡ በማሰብ ክህሎት ጭንቅላቶቻቸው ዝቅተኞች፣ በጣም ዝቅተኞች ናቸው፡፡ ዝቅተኛ ደነዞች ናቸው፡፡ አዎ እውነት ነው ሌላ category ናቸው፡፡

ለመሆኑ በተፈጥሮ ስብዕናቸው ዝቅተኛ የሆኑ ሌላ category ህዝቦች ሊኖሩ ይችላሉን?

የአማራ ደነዞች ለዘ-ህወሀት አዲስ የበላይነት እና በኢትዮጵያ ለዘ-ህወሀት የበላይነት ዋና መሰረት ድልዳል ሆነዋልን?

የዘ-ህወሀት የጎሳ ጥላቻ አራማጆች የአማራ ደነዞችን ለመግደል እና ለመጨረስ ዘመቻ በማድረግ ላይ ናቸውን?

ወይም ደግሞ ዘ-ህወሀት እና የእርሱ ተሿሚ የጎሳ ጥላቻ አራጋቢዎች የአማራ ደነዞች እና የኦሮሞ ወንጀለኞች እና አሸባሪዎች እንዲነሱ እና የበከተውን ስርዓት እንዲገዳደሩ ለማድረግ ጥረት እያደረጉ ነውን? በዘ-ህወሀት የባርነት አገዛዝ ላይ እንዲነሱ ለማድረግ!

ለ”ደነዝ” አማሮች ጸሎት እናድርስ!

የዘ-ህወሀት የጎሳ ጥላቻ አራጋቢዎች ተስፋ ከመቁረጥ እስከ የጭካኔ ድርጊት እስከመውሰድ እስከሚያደርስ እርምጃ ይለያያሉ፡፡

ጥቂቶች እርባናቢስ ለሆነው እና ድምጻቸውን ከፍ አድርገው ለሚያስተጋቡት የዘ-ህወሀት የጥላቻ አራጋቢዎች ምላሽ መስጠት ማለት ለእነርሱ የጥላቻ መልዕክቶች ክብር ከመስጠት እኩል ነው የሚል ሀሳብ ያላቸው አሉ።

እንደዚሁም ደግሞ ሌሎች ጥቂቶች ጥላቻ አራጋቢዎች ዝም ከተባሉ እና ከተናቁ በእራሳቸው ብን ብለው ይጠፋሉ ብለው ያምናሉ፡፡

በእኔ በኩል ለጥላቻ አራጋቢዎች ነጻ የይለፍ ወረቀት በመስጠቱ እረገድ አላምንም፣ የጥላቻ አራጋቢዎች ዶናልድ ትራምፕ-አሪያኖች ወይም ደግሞ የትራም የአፍሪካ ዘረመል እየተባሉ ቢጠሩ ለእኔ ጉዳዬ አይደለም፡፡

ሊካድ የማይችለው ዋናው እውነታ ግን እነዚህ እርባቢስ የጥላቻ አራጋቢዎች በብዙሀን መገናኛዎች የሚያደርጓቸው መቅኖቢስ እና እርባናየለሽ ንግግሮች የዘ-ህወሀት አመራሮች፣ አባላት እና ደጋፊዎች በየመኖሪያ ቤቶቻቸው፣ በሮቻቸውን ዘግተው በግል እና በጉባኤ አዳራሾች እና በየቦርድ መሰብሰቢያ ክፍሎች ከሚያወሯቸው ጋር አንድ እና አንድ የመሆናቸው ጉዳይ ነው፡፡

በጥላቻ ለተሞሉት ለሁሉም ለዘ-ህወሀት እና ለደጋፊዎቻቸው መግለጫዎች ምንም ዓይነት ምላሽ ባለመስጠት ጆሮዳባ ልበስ ማለት ቀላል ነው፡፡ በፍርሀት ርደው የሚይዙትን እና የሚጨብጡትን በማጣት በመዘላበድ ላይ የሚገኙትን ደደቦች፣ ልሳናቸው ሁሉ በድምጽ በተሞላ ቦቅቧቃዎች እና በፍርሀት በተሞሉ ሆኖም ግን ምንም ዓይነት ጠቃሚ ነገር በማያመጡ የጥላቻ አራማጆች እንደሚነገረው ባዶ ተረት አድርጎ በመቁጠር ምንም ባለማለት መዝጋት ቀላል ነገር ነው፡፡

እውነታው ፍርጥርጥ ተደርጎ ሲታይ ግን የዘ-ሀወሀት አመራሮች፣ አባላት እና ደጋፊዎች የአማራ እና የኦሮሞ ህዝቦችን በመጥላቱ ረገድ በአንድ ረድፍ የሚቀመጡ ናቸው፡፡

የዘ-ህወሀት የጥላቻ አራጋቢዎች ጥላቻቸውን፣ ፍርሀታቸውን እና ጥልቅ ጥላቻቸውን የቀመሩት ማቆሚያ በሌለው እና እየተቃጠለ ባለው በዘ-ህወሀት አመራሮች፣ አባላት እና ደጋፊዎች ልብ እና አእምሮ ውስጥ ነው፡፡

እርባናቢስ የጥላቻ አራጋቢዎች የጥላቻ ንግግሮቻቸውን በቀጥታ ያገኙት ከመጀመሪያ እና በጣም በጣም ቁንጮ ከሆኑት ከዘ-ህወሀት አመራሮች ነው፡፡ እነዚህ የጥላቻ አራጋቢ ታዛዥ ሎሌዎች ጥላቻን እንዲያራግቡ በጌቶቻቸው ታዝዘዋል፡፡

በዚህ ዓይነት ሁኔታ ነው የዘ-ህወሀት ጓዶች ሌላ ማንም የውጭ ሰው ሳይሰማ በየቀኑ ብቻቸውን በመነጋገር ላይ ያሉት፡፡

ይህንን ነገር በሚገባ አውቃለሁ ምክንያቱም ነግረውኛልና፡፡

ምንም ዓይነት ጥርጣሬ እንዳይኖራችሁ፡ ከዘ-ህወሀት መካከል ዘ-ህወሀት ወይም ደግሞ ሌላ ምንም ነገር ከመሆናቸው በፊት በመጀመሪያ ደረጃ ኢትዮጵያዊ እንደሆኑ የሚያምኑ በጣም ጥቂት የሆኑ ሰዎች አሉ፡፡ የዘ-ህወሀትን ካባ የደረቡ ሁሉ ከልባቸው ዘ-ህወሀት አይደሉም፡፡ ልባቸውን ይባርከው!

ከዘ-ህወሀት የጥላቻ አራጋቢዎች ጋር በመሆን የጭቃ ጅራፋቸውን ለማጮህ የሚሞክሩ ጥቂቶች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡

ይህንን ነገር እኔ አይደሁም ያልኩት፡፡ እንደ ጆርጅ በርናንድ ሻው ሁሉ “ከዓሳማ ጋር መታገል ወይም ሀሳብ ማቅረብ ፍጹም አስፈላጊ እንዳልሆነ ከብዙ ጊዜ ጀምሬ ተምሪያለሁ፡፡ ያንን ካደረግህ ትቆሽሻለህ፣ ዓሳማው ግን ይህንን ቁሻሻ ከልቡ ይወደዋል፡፡“ 

ሁልጊዜ እንደምለው ሁሉ ወሮበላ ዘራፊውን ከጫካ ማውጣት ትችላለህ፣ ሆኖም ግን ጫካውን ከወሮበላ ዘራፊው ልታወጣው አትችልም፡፡ የፈለገውን ያህል የወርቅ ክምር ቢከመር እና የተዋቡ እና ያማሩ ልብሶች እና የእጅ ቦርሳዎች ቢቀርቡም ቅሉ ወሮበላውን ወይም ወሮበላዋን ሊለውጡ አይችሉም፡፡ ወሮበላ ዘላለማዊ ነው አይቀየርም! ይኸ የህይወት እውነታ ነው!

ሆኖም ግን ሁሉንም የጎሳ ቡድን ደነዞች፣ ደደቦች እና ሞኞች እያሉ የሚዘልፉ እነዚህ የጎሳ ጥላቻ አራጋቢዎች አመልካች ጣታቸውን ወደ ህዝቡ ሲቀስሩ ሶስቱ ጣቶቻቸው ደግሞ ወደ  ወደ እራሳቸው እንደሚያመላክቱ በጥንቃቄ መመልከት ይኖርባቸዋል፡፡

የዘ-ህወሀት የጎሳ ጥላቻ አራጋቢዎች ለአማራ ደነዞች ጸሎት እንደሚያደርጉላቸው ያታልላሉ፡፡

የእነርሱን ጸሎት አድራጊዎች ለእራሳቸው እና ለዘ-ህወሀት የወንጀል አጋሮች ያቆዩ፡፡ የአማራ ደነዞች ከሚፈልጉት የበለጠ ለእነርሱ አስፈላጊ የሚሆንበት ጊዜ ሊመጣ ይችላል፡፡

የዘ-ህወሀት የጎሳ ጥላቻ አራጋቢዎች እራሳቸውን ጸሎት አድራጊ  አድርገው ካቀረቡበት ጊዜ ጀምሮ እንዲህ ከሚለው መንፈሳዊ ጥቅስ መማር ይችላሉ፡ “በሕዝቦቻው ላይ ችግርን የሚፈጥሩ ሁሉ በመጨረሻ ጉምን ይዘግናሉ፣ እናም ሞኞች የልበ ብልሆቹ አገልጋዮች ይሆናሉ፡፡“

ጸሎትን ለማድረግ የሚተጉ የዘ-ህወሀት የቅጥፈት ባህታዊ የጎሳ ጥላቻ አራጋቢዎች አሁንም ህያው ከሆነው ጥቅስ እንዲህ የሚል ትምሀርት ሊማሩ ይገባል፣ “ለሁሉም ነገር ጊዜ አለው፡፡“

አሁን ህዝቡ ከዘ-ህወሀት ማስፈራሪያ ነጻ የሚሆንበት ጊዜ ነው!

ዘ-ህወሀት፣ አባላት እና ደጋፊዎች በቆሻሻ የታሪክ ቁልላቸው የአካሄድ መንገድ መሰረት በመጓዝ ጉምን ይዘግናሉ፡፡

ሁሉም አመላካከቾች እንደሚያሳዩት የአማራ ደነዞች በአይበገሬነት በአንድነት በመቆም እንዲህ በማለት በማወጅ ላይ ይገኛሉ፡ “ጌታዬን አመሰግናለሁ! ከእውነተኛዎቹ የክርክር ጭብጦቼ ጋር በጽናት አቁመኝ፡፡“

ሆኖም ግን “ደነዝ ጎጃሜዎች” ለዘ-ህወሀት እንዲህ የሚል እና የመጨረሻ እና ሊመለስ/ሊገለበጥ  የማይችል ምለሽ አላቸው፡

ጎጃም የጀግኖች ምድር ናት፡፡ ለሀገራችን እንሞታለን 

ወልቃይት የእኛ ነው፡፡

ጠንካራ መሪ እንጅ ጭፍን እና እውር መሪ አንፈልግም፡፡

ኢትዮጵያዊነት ቋንቋችን ነው፡፡

ወያኔ የቦቅቧቃ ፈሪዎች ስብሰብ ነው፡፡

ትግራይን ከኢትዮጵያ ነጻ ለማውጣት የተመሰረተ ግንባር ተልዕኮው ምንድን ነው?

ወታደሩ የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው፡፡

የትግራይ ድንበር ተከዜ ነው፡፡

የታሰሩ የፖለቲካ እስረኞች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ አሁኑኑ ይፈቱ፡፡

አንዳርጋቸው የእኛ ጽጌ መሪ እንጅ አሸባሪ አይደለም፡፡

አንዷለም አራጌ የእኛ መሪ እንጅ አሸባሪ አይደለም፡፡

በቀለ ገርባ የእኛ መሪ እንጅ አሸባሪ አይደለም፡፡

በኮሎኔል ደመቀ ጉዳይ ላይ ምንም ዓይነት ድርድር ሊኖር አይችልም፡፡

የዘ-ህወሀት ታሪክ ፍጻሜ ነውን? 

የዘ-ህወሀት የጎሳ ጥላቻ አራጋቢዎች እንዲህ ይላሉ፣ “ለአማራ ደነዞች የፍጻሜ ታሪክ ነው“

በእርግጥ ነውን?

ከ25 ዓመታት በፊት የተጀመረው አስፈሪው እና አስደንጋጩ ታሪክ መቋጫው የተቃረበ ለመሆኑ እርግጠኛ ይመስላል፡፡

ዘ-ህሀወሀት ለ25 ዓመታት ሙሉ የ”አማራ ደነዞችን” ገዝቷል፡፡

ዘ-ህወሀት ለ25 ዓመታት ሙሉ የ”ኦሮሞ ወንጀለኞችን እና አሸባሪዎችን” ገዝቷል፡፡

ሆኖም ግን ለ25 ዓመታት ያህል የተኙ መስለው የቆዩት ደነዞች እና ወንጀለኞች እና አሸባሪዎች በአሁኑ ጊዜ ከተኙበት በመንቃት በዘ-ህወሀት ላይ ዘለው እመር ለማለት አቆብቁበው የሚገኙትን እና የተቆጡ ነብሮችን ዘ-ህወሀት ዘግይቶ እና በሚያስገርም ሁኔታ ለመገንዘብ ችሏል፡፡

ነብሮቹ ሽንጦቻቸውን በመለንበጥ እና ዓይኖቻቸውን በማጉረጥረጥ በወያኔ አናት ላይ እመር ብለው ለመውጣት በመሳት ላይ ናቸው፡፡ ነብሮቹ በሚያስፈራው ድምጻቸው በማጉረምረም ላይ ናቸው፡፡ ነብሮቹ የሰለባዎቻቸውን ግዳይ ለመጣል በመቋመጥ ላይ ናቸው፡፡

እናንት ዘረኞች ነብሩን ጠብቁ!

ዘ-ህወሀት የነብሮቹን ጅራት ይዞ መቆም ፍፁም አልቻለም፡፡

ነብሮቹ እራሳቸውን ነጻ ያወጣሉ፡፡

ዘ-ህወሀት ቀጥታ በሆነ መንገድ በአንድ ላይ ተሰባስበው፣ በፍርሀት የለሽነት፣ በአይበገሬነት እና በተራበ የቁጡነት አንደበት ዓይናቸውን የሚያጉረጠርጡትን የኢትዮጵያን ነብሮች ዓይኖች በመመልከት ላይ ይገኛል፡፡

ዘ-ህወሀት በአሁኑ ጊዜ እንዲህ የሚለውን እውነታ በመጋፈጥ ላይ ይገኛል፡ የኢትዮጵያ ነብሮች!

ዘ-ህወሀት እውነታውን መያዝ እና መቆጣጠር ይችላልን?

ዘ-ህወሀት የኢትዮጵያን ነብሮች በመግደል፣ በቁጥጥር ስር በማዋል፣ በማጎሪያ እስር ቤት ዘብጥያ በመጣል፣ በማሰቃየት እና የቅጣት ዓይነት በመደርደር ሊቆጣጠር ይችላልን?

ዘ-ህወሀት የኢትዮጵያን ሕዝቦች ልብ እና አእምሮ መግዛት ሳይችል በጦርነት አሸንፎ መግዛት በምንም ዓይነት መልኩ አይችልም፡፡

ለረዥም ዓመታት ከሕግ አግባብ ውጭ በጭቆና ሲገዙ የቆዩ ሕዝቦችን፣ ዕለት በዕለት ክብራቸውን በማዋረድ እና መጥፎ የአገዛዝ ስልትን በመጠቀም የተቆጡ እና የተበሳጩ ህዝቦችን ለማሸነፍ ወይም ዝም ለማሰኘት የሚችል ወታደራዊ ኃይል በዓለም ላይ ከቶውንም ሊኖር አይችልም፡፡

የተባበሩ የኢትዮጵያ ሕዝቦችን ሊያሸንፍ የሚችል ምንም ዓይነት ወታደራዊ ኃይል ሊኖር አይችልም፡፡

የኢትዮጵያ ሕዝቦች ተባብረዋል፣ በምንም ዓይነት መንገድ ሊሸነፉ አይችሉም!

በማህተመ ጋንዲ የተነገረውን እና እንዲህ የሚለውን ዘላለማዊ የሆነውን እውነታ ዘ-ህወሀት እንዲያስብበት ሁልጊዜ አስታውሰዋለሁ፡ “በታሪክ ሂደት ምንጊዜም ቢሆን እውነት እና ፍቅር ሁልጊዜ ያሸንፋሉ፡፡ ጨቋኞች እና ገዳዮች ለጊዜው ሊኖሩ ይችላሉ፣ የማይበገሩ ኃይለኞች መስለው ይታያሉ፣ ሆኖም ግን በመጨረሻው ጊዜ ይወድቃሉ፡፡ ይህንን ነገር ሁልጊዜ አስቡ“ ነበር ያሉት፡፡

በአሁኑ ጊዜ ዘ-ህወሀት ያለው ብቸኛው አማራጭ፡ ሰላማዊ ዜጎችን በከፍተኛ ሁኔታ በናዚ ደረጃ እልቂትን በመፈጸም በስልጣን ላይ ተጣብቆ ለመቆየት ጥረት ማድረግ ነው፣

ዘ-ህወሀት እራሱን እና ሀገሪቱን ከእልቂት ለማዳን በርካታ አማራጮች አሉት፡፡ ሆኖም ግን አንዱንም ዓይነት አማራጭ ቢሆን አይወስድም ምክንያቱም የዘ-ህወሀት አመራሮች፣ አባላት እና ደጋፊዎች የአማራ ደነዞችን፣ የኦሮሞ ወንጀለኞችን እና አሸባሪዎችን እንዲሁም በሀገሪቱ ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙትን ሁሉንም ተቃዋሚዎች እንደዚያው እንደተለመደው በብልጥነት፣ የበለጠ በማሰብ፣ በልጦ በመገኘት፣ የማታለል ጨዋታ በመጫወት፣ በማሞኘት እና ነገሮችን ሁሉ በማጦዝ በዝረራ ማሸነፍ እንደሚችሉ ያምናሉ፡፡ የሞኝ ዘፈን ሁልጊዜ አበባዬ፣ እንዲሁም የሞኝ ለቅሶ መልሶ መላልሶ ይባል የለ! ነገሩ እንደዚያ መሆኑ ነው!

ዘ-ህወሀት ነገሮችን በቀላሉ በአጭር ጊዜ ውስጥ መቆጣጠር ካልቻል የአስቸኳይ ጊዜ ለማወጅ መጠባበቂያ ዕቅድ/contingency plan/ የወታደር አገዛዝ አለው፡፡

ዘ-ህወሀት በአሁኑ ጊዜም ቢሆን  በስልጣን ላይ ያለበት ምክንያቱም ወታደራዊ ኃይሉን ስለተቆታጠረ ነው። ሆኖም ግን በእርግጠኝነት ይኸ ቁጥጥር በጣም አናሳ ነው፡፡ ሁሉም ኃላፊዎች ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ የዘ-ህወሀት ካድሬዎች ቢሆኑም ቅሉ ተራው ወታደር በብዛቱ  ከሌላው ጎሳ ቡድን የሚበልጥ ቢሆንም ገንዘብ እና ሌላም ጥቅማጥቅም በመስጠት እየደለሉ የተለመደውን የግድያ እንዱስትሪ ማሽኑን እቀጥላለሁ ብሎ የሚያምን ከሆነ ትልቅ ስህተት መስራቱን መገንዘብ ይኖርበታል፡፡

ዘ-ህወሀት በዓለም ላይ ቀደም ሲል ከፍተኛ የሆነ ወታደራዊ ኃይል ከነበረው ጋር ጦርነት ገጥሞ ያሸነፈውን እና እንዲህ የሚለውን የሆችሚንን አባባል ልማርበት ይችላል። “እኛ ከእናንተ ወገን አንድ በገደልን ቁጥር እናንተ ደግሞ በአጻፋው 10 የሚሆኑ ወገኖቻችንን ልትገድሉ ትችላላችሁ፡፡ ሆኖም ግን በዚህ ዓይነት ሁኔታ ጉድለት ቢኖር እና ብዙ የምናጣ ቢሆንም በመጨረሻ እናሸንፋለን“ ነበር ያለው፡፡

ዘ-ህወሀት ይሸነፋል፡፡ ጉድለቶች ሁሉ ተንሰራፍተው የሚገኙት በእርሱ በኩል ነው፡፡ ቀላሉን የሂሳብ ስሌት ስሩ!

የሚናገር አፍ እንጅ የሚሰማ ጆሮ እና ማገናዘብ የሚችል አእምሮ ካለው እስቲ ዘ-ህወሀትን እንዲህ በሚሉት የማርቲን ሉተር ኪንግ ቃላት እናስጠንቅቀው፡ “ጥላቻ ጥላቻን ይወልዳል፣ ኃይል ኃልን ይወልዳል፣ ጠንካራነት የበለጠ ጠንካራነትን ይወልዳል፡፡“

በመጨረሻ ዘ-ህወሀት ኢትዮጵያን የግድያ ቀጣና ሊያደርጋት የነበረው ዕቅዱ ይከሽፋል ምክንያቱም በወታደራዊ ኃይሉ ውስጥ ያለው ተራው ወታደር የእራሱን ወገኖች እየፈጀ ለእርሱ የስልጣን መራዘም እና የጭቆና አገዛዝ በፍጹም ሊቆም አይችልም፡፡

ሆኖም ግን በዘ-ህወሀት የጭቆና አገዛዝ ቁጥጥር ስር የሚኖርን ህዝብ አንድ መግደል ማለት  ከሺዎች ግድያ ጋር መሳ ለመሳ ነው፡፡

አሁን በቅርቡ በአንድ በቪዲዮ ምስል በቀረበ ምልከታ አንድ በመንገድ ላይ የሚጓዝ ሰው እንዲህ ሲል ተደምጧል፣ “በዘ-ህወሀት አገዛዝ ሁላችንም የቁም ሞት ሞተናል፡፡ የሞት ሞት ሞተናል፡፡ አሁን ካለንበት የበለጠ ምንም ዓይነት ሞት ልንሞት አንችልም፡፡“

ሆኖም ግን ዘ-ህወሀት በአጠቃላይ የኢትዮጵያን ሕዝብ ጀግንነት አሳንሶ እና አንቋሽሾ ይመለከታል፡፡ የኢትዮጵያ ጀግኖች የአውሮፓን ኃያል ቅኝ ገዥ ከአንዴም ሁለት ጊዜ አሳፋሪ ሽንፈት እንዲከናነብ ማድረጋቸውን እና መራራ በሆነው ትግላቸው በስኬታማነት ማሸነፋቸውን የዘ-ህወሀት ዘረኛ ቱልቱላዎች አሳንሰው ይመለከታሉ፡፡

ዘ-ህወሀቶች ባላቸው የድንቁርና ግትርነት ኢትዮጵያውኖች ፈሪዎች፣ ደነዞች፣ ሞኞች፣ ደደቦች፣ ወንጀለኞች እና አሸባሪዎች እንደሆኑ እና እነርሱ ብቻ የጀግኖች ሁሉ ጀግኖች እንደሆኑ አድርገው ይቆጥራሉ፡፡

አሁን በህይወት የሌለው አምባገነኑ መለስ ዜናዊ እና ዘ-ህወሀት አማሮችን፣ ኦሮሞዎችን፣ ትግሬዎችን እና ሌሎችን የኢትዮጵያ ሕዝቦች ሁሉ ኃይላቸውን በመጠቀም በመምታት እና በመለያየት ለዘላለም በስልጣን ኮርቻ ላይ እንደ መዥገር ተጣብቀው የሚኖሩ ይመስላቸዋል፡፡

በእርግጠኝነት ከዛሬ አራት ዓመታት በፊት በአሁኑ ወር አምባገነኑ መለስ ጥላቻ በሚባል ሞት አሰቃቂ ሞት ሞተ፡፡

እ.ኤ.አ ነሀሴ 2016 ዘ-ህወሀት ላለፉት 25 ዓመታት ሲዘራው የቆየውን የጥላቻ አዝመራ ለማጨድ በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡

አማሮች እና ኦሮሞዎች ፍጹም ቦቅቧቃ ፈሪዎች እና ደካሞች ናቸው በማለት የሚያምነውን ለከት የለሽ እና እርባናቢስ ቅጥፈቱን ለሚያሰማው ዘ-ህወሀት የለየለት ስህተት፣ የሞተ እና የበከተ ስህተት ሰርተሀል እለዋለሁ፡፡

አማሮች እና ኦሮሞዎች ለትግሬዎች፣ ለሲዳማዎች፣ ለወላይታዎች፣ ለሀድያዎች፣ ለአፋሮች፣ ለጋሙዎች፣ ለኦጋዴኖች፣ ለአኙዋኮች… ለክርስቲያኖች፣ ለሙስሊሞች…. ወንድሞች እህቶች ናቸው፡፡

ሌላ ምንም ነገር ከመሆናቸው በፊት በመጀመሪያ ደረጃ ሁሉም ኢትዮጵያውያን ናቸው፡፡

እንደኢትዮጵያውያን አብረን እንነሳለን ወይም አብረን እንወድቃለን!

በቅዱሱ መጽሐፍ “ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች” ተብሎ ተጽፏልና፡፡

ያም ጊዜ መቼም ሳይሆን አሁን ነው!

ኢትዮጵያውያን እጆቻቸውን በመዘርጋት በሰላም፣ በወንድማማችነት፣ በእህትማማችነት እና በጓደኝኝነት ስሜት በፍቅር እርስ በእርሳቸው የመተቃቀፍ አስፈላጊነት ከመቸውም በላይ አሁን አንገብጋቢ ጉዳይ ነው፡፡ ይኸ መንገድ የተቀደሰ ተግባር ነው፡፡

ለደነዝ አማሮች እንጸልይላቸዋለን እያሉ ለሚመጻደቁት ለዘ-ህወሀት አመራሮች፣ አባላት እና ደጋፊዎች በአሜሪካ የአፍሪካ የባሪያ ንግድ ሲጧጧፍ በነበረበት ጊዜ በአፍሪካ የሙዚቃ ቅላጼ ከተዜመው እና እንዲህ የሚለውን ነብያዊ ግጥም እንዲያስታውሱት ላሳስባቸው እወዳለሁ፡ “እግዚአብሄር ለኖህ የቀስተ ደመና ምልክት ሰጠው፡ ከዚያ በኋላ ምንም ዓይነት ውኃ አልነበረም፡፡ በመቀጠልም እሳት መጣ!“

የኢትዮጵያ ኦሮሞዎች፣ አማሮች፣ ትግሬዎች፣ ጉራጌዎች፣ ሲዳማዎች፣ ወላይታዎች፣ ሀድያዎች፣ አፋሮች፣ ጋሙዎች፣ ኦጋዴኖች፣ አኙዋኮች… ክርስቲያኖች፣ ሙስሊሞች፣ ሌሎች ፍጡሮቸ ሁሉ ግኡዝ ቢሆኑም እንኳ ነብስ አላቸው ብለው የሚያምኑት ሳይቀር፣ ወጣቶች፣ ሽማግሌዎች፣ ወንዶች፣ ሴቶች… እያንዳንዳችን እርስ በእርስ ተቃቅፈን፣ እጅ ለእጅ በመያያዝ በአንድነት አንድ በመሆን እየተነሳን ለመሆናችን ዘ-ህወሀቶች የኢትዮጵያውያን የቀስተደመና ምልክት ሊታያችሁ ይችላልን?!

ኢትዮጵያውያን ሁሉ እጆቻችሁን ዘርጉ! 

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!  

ነሐሴ 10 ቀን 2008 ዓ.ም