አ! ቃጣሪ መዝናኛ በአዲስ አበባ! ኢትዮጵያውያኖች ለምንስ ኬክ አይበሉም ?

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም    

ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ

Qatar Eth Resortበአሁኑ ጊዜ 15 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን አውዳሚ በሆነ ረሀብ በመሰቃየት ላይ ይገኛሉ!

የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ (ህወሀት) የመዝናኛ ሆቴል አልሚዎችን ከመካከለኛው ምስራቅ የአረብ ሀገሮች እያፈላለጉ በመጋበዝ ላይ ይገኛሉ፡፡

ባለጥቁር ፈረሱን ረሀብ የሚጋፈጡ 15 ሚሊዮን ህዝቦች ጉዳይስ ምንድን እየተደረገ ነው?

ዘ-ህወሀት እንዲህ ይላል፣ “ኬክ መብላት ይችላሉ!“

የንጉስ ሌውስ XVI ባለቤት የነበረችው ንግስት ማሪያ አንቶኔት በድህነት የዳሸቁ እና በረሀብ እየሞቱ የነበሩትን የፈረንሳይ አርሶ አደሮች ለምን ኬክ አይበሉም በማለት ጠይቃ ነበር፡፡

እንደዚሁም ሁሉ እኔም 15 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን እየተራቡ በሞት አፋፍ ላይ ሆነው እየተሰቃዩ ባሉበት ሁኔታ ዘ-ህወሀት ለምንድን ነው የመዝናኛ ሆቴል አልሚዎችን ለመሳብ ጥረት እያደረገ ያለው? በማለት እጠይቃለሁ፡፡

ባለፈው ሳምንት ገልፍ ታይምስ ቢዝነስ/Gulf Times Business የተባለው መጽሄት እንዲህ የሚል ዘገባ አቅርቦ ነበር፣ “ኢዝዳን ሆልዲን ግሩፕ/Ezdan Holding Group በአዲስ አበባ ውስጥ የቅንጦት የቱሪስት መዝናኛ ሆቴል ለመገንባት ዕቅድ ይዟል… እንዲገነባ የታሰበው ልዩ የሆነ የመዝናኛ ሆቴል ፕሮጀክት የኢትዮጵያ መናገሻ በሆነችው ከተማ እምብርት በ150,000 ካሬ ሜትር ስፋት ላይ የሚያርፍ ይሆናል…“

እንደገና ወደ ዘ-ህወሀት እንመለስ!

የካታርን የቅንጦት የመዝናኛ ሆቴል ለመገንባት ስንት አስር ሺ ኢትዮጵያውያን ከቤት ንብረታቸው ይናቀላሉ? እንዲሁም ቤት አልባ ይሆናሉ?

ዘ-ህወሀት የካታር የቅንጦት የመዝናኛ ሆቴል ግንባታ ስምምነት እንዲፋጠን ዋና አንቀሳቃሽ ሞተር ሆኖ እስከ አሁን ድረስ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል፡፡

እ.ኤ.አ ወደኋላ ወደ 2010 መለስ ብለን ስንመለከት ዘ-ህወሀት ካሩቱሪ ግሎባል ለሚባል የመሬት ተቀራማች ኩባንያ 100 ሺ ሄክታር አስረክቦ ነበር፡፡ ባለፈው ወር የካሩቱሪ ስምምነት ሙሉ በሙሉ ውድቅ ሆነ፡፡ ካሩቱሪ ዘ-ህወሀትን ልክ ለማስገባት የህንድን ኃያልነት እንደሚጠቀም ዝቷል፡፡

እ.ኤ.አ በ2014 የወባ ትንኝ ተመራማሪው እና በብርሀን ፍጥነት ወደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት የተተኮሰው ቴዎድሮስ አድሀኖም ከካታር የቢዝነስ ሰዎች ጋር በመገናኘት እንዲህ በማለት ነግሯቸው ነበር፣ ኢትዮጵያ እራሷን የአፍሪካ የህክምና ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ እያደረገች ባለቻቸው ጥረቶች ላይ ተሳትፎ አድርጉ፡፡

አዎ የህክምና ቱሪዝም!!!

ጉድ ጉድ ጉድ ጉድ!!!

ተጋዳላይ አድሀኖም ተሳስቶ ነው ወይስ ደግሞ የምላስ ወለምታ ነው? ይኸ ነገር ምናልባትም የፊት የወባ ትንኝ የህክምናው ምርምር ሸንጦ ወስዶት ይሆን?

ይህም ካልሆነ ማርቪን ጋዬ ስለጾታ ግንኙነት ፈውስ/sexual healing እና ስለህክምና ዋጋው እንደዘመረለት ሁሉ ተጋዳላይ አድሀኖም በእርግጠኝነት እንደዚሁ ሜዲካል ቱሪዝም ማለቱ መሆን አለበት::

ተጋዳላይ አድሀኖም የህክምና ቱሪዝም ከጾታ ግንኙነት ቱሪዝም ጋር ባለው ትርጉም ግራ ተጋብቶ ነውን?

የመዝናኛ ሆቴል? የሴተኛ አዳሪዎች መደብር? በሁለቱ መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው?

ምን አይነት የእብደት ስራ ነው፡፡ የአዕምሮ በሽተኝነት!

ለእኔ ግንዛቤ የህክምና ቱሪዝም  ማለት ህዝቦች ለበርካታ ምክንያቶች የተሻለ ህክምና ማግኘትን ጨምሮ በእራቸው ሀገር ሊገኝ የማይችልን ህክምና ለማግኘት፣ የህክምና ወጨው አነስተኛ የሆነ ህክምና ለማግኘት፣ ህክምና በማግኘት ዕድላቸው ላይ በሀገራቸው ውስጥ ይደረግ የነበረውን የመዘግየት ሁኔታ ለማስወገድ ወዘተ አብዛኛውን ጊዜ ከደኃ ሀገሮች የበለጠ ወደ በለጸጉት ሀገሮች ይጓዛሉ፡፡ ምርጥ የህክምና ቱሪዝም መዳረሻዎች ዩናይትድ ስቴትስን፣ ሜክሲኮን፣ ህንድን፣ ብራዚልን፣ ሲንጋፖርን እና ሌሎችንም ያጠቃልላል፡፡ በእነዚህ ሀገሮች ሁሉ በህክምናው ረገድ የረቀቀ ቴክኖሎጂን በእጃቸው ያስገቡ በጣም በከፍተኛ ሁኔታ የሰለጠኑ የህክምና ባለሙያዎች አሉ፡፡

ለመሆኑ ህወሀት ኢትዮጵያን የህክምና ቱሪዝም ሳቢ ማግኔት ለማድረግ የፈለገው ምንድንን መሰረት በማድረግ ነው?!

ኢትዮጵያ 1,936 ሀኪሞች (1 ሀኪም ለ40,000 ህዝብ)፣ 15,544 ነርሶች እና አዋላጆች (1 ነርስ ለ5,000 ህዝብ)፣ 1,343 የፋርማሲ ባለሙያዎች (1 ፋርማሲስት ለ60,000 ህዝብ)፣ 2,703 የላቦራቶሪ ምርመራ ሰራተኞች (1 የላቦራቶሪ ሰራተኛ ለ30,000 ህዝብ) እና ለ10,000 ህዝብ ሁለት የሆስፒታል አልጋዎች ያሏት ሲሆን በህክምና ክትትል እየተደረገላቸው የሚወልዱ ሴቶች ብዛት ደግሞ 6 በመቶ ይሸፍናሉ፡፡ ከጠቅላላው የሀገር ውስጥ ምርት ለህክምና የሚደረገው ወጭ 4.9 በመቶ ይሸፍናል፡፡ ይህ መረጃ የተገኘው በምስጢር የተዘጋጀው አስተማማኝ ከሆነው የአፍሪካ የጤና ኢንቨስትመንት ፈንድ/Investment Fund for Health in Africa ከተባለው ድርጅት (ገጽ 24) ዘገባ ነው፡፡ ኢትዮጵያ 93 የጥርስ ህክምና ባለሙያዎች (1 የጥርስ ሐኪም ለ80,0000 ህዝብ) አሏት፡፡

እ.ኤ.አ በ2014 የተዘጋጀው የዓለም የጤና ጥበቃ ድርጅት አሀዛዊ የመረጃ ዝርዝር እውነታ እንደሚያመላክተው በአእምሮ ጤንነት ዘርፉ ተሰማርተው በማገልገል ላይ ያሉት የአዕምሮ ህክምና ባለሙያዎች ብዛት 0.04 ለ100,000 ህዝብ ነው፡፡ ለተወሰኑ አገልግሎቶች እና ዋና ዋና የህክምና መገልገያ መሳሪያዎች በ100,000 ህዝብ ያለው ጠቅላላ ጥግግት/density እንደሚከተለው ቀርቧል፡

1ኛ) ልዩ ህክምና የሚሰጡ ሆስፒታሎች/specialized hospitals = 0.03፣

2ኛ) ሲቲ ስካነር = 0.03፣

3ኛ) የማግኔቲክ ሪሶናንስ ኢሜጂንግ (Magnetic Resonance Imaging (MRI)) ጠቅላላ ጥግግት በሚሊዮን ህዝብ =0.04፣

4ኛ) ራዲዮ ቴራፒ ዩኒትስ/Radiotherapy Units = 0.02፣ እና

5ኛ) የካንሰር ምርመራ ህክምና/nuclear medicine/cancer detection =0.01 ነው፡፡

እንግዲህ የአድሀኖም በኢትዮጵያ የህክምና ቱሪዝም ቢዝነስ ይህን ይመስላል!

በኢትዮጵያ ያለው ተስፋ የሚያስቆርጥ የጤና አጠባበቅ ሁኔታ በአጭር ጊዜ ውስጥ የሚሻሻል አይመስልም፡፡

እንደ የህዝብ ሬዲዮ ዓለም አቀፍ/Public Radio International ዘገባ በኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ 13 አዲስ የህክምና ትምህርት መስጫ ተቋማት ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የፕሮፌሰሮች እጥረት ስላለ ብዙ ጊዜ በቅርብ ጊዜ ውስጥ የተመረቁ አዲስ ምሩቃን እንዲያስተምሩ ይጠየቃሉ፡፡ ማንነቱ እንዲታወቅ ያልፈለገ በኢትዮጵያ ውስጥ ከ20 ዓመታት በላይ የሰራ አንድ የውጭ ዶክተር እነዚህ አዲስ የማሰልጠኛ ትምህርት ቤቶች ምን መስራት እንዳለባቸው የማያውቁ ትውልድ ዶክተሮችን በማፍራት መልካም ነገሮችን ከመስራት ይልቅ ብዙ ጉዳቶችን የሚያስከትሉ ነገሮችን እየሰሩ እንዳሉ ግልጽ አድርጓል፡፡

ኢትዮጵያ ለእራሷ ዜጎች መጥፎ የሆነ የጤና አገልግሎት እያቀረበች ባለችበት ሁኔታ እንዴት አድርጋ ነው የዓለም የህክምና ቱሪዝም ዋና ማዕከል መሆን የምትችለው?

ዘ-ህወሀት የሌለውን ነገር እንዳለ አድርገው በማቅረበ የህክምና ቱሪዝም ማዕከል በማለት እያደናገሩ ያሉት እኛን ለማናደድ ነው ወይስ ደግሞ እራቸውን ለማታለል ነው?

የህክምና ቱሪዝም እርባናየለሽ የዘ-ህወሀት ዋና የሸፍጥ መሳሪያ ሊሆን ይችላልን? ተጠቃሚዎችን ለማታለል የተዘየደ ሸፍጥ ነውን? የህክምና ቱሪዝም ለሽርሙጥና ቱሪዝም አገልግሎት ሊውል ነውን?

አድሀኖም ስለካታር የመዝናኛ ህንጻ የህክምና ቱሪዝም ሲናገር ማንን ነው ለማታለል የፈለገው?

ዘ-ህወሀት! ጥሩ የማታለል ሙከራ! ግን አልሰራም!

በደኃ ሀገሮች ስለሚደረጉት ስለቱሪዝም እና መዝናኛ ሆቴል፣ ስለህገወጥ የሰዎች ዝውውር እና ሌሎች እነዚህን ስለመሳሰሉት ነገሮች በርካታ ነገሮችን እየተማርኩ ነው፡፡ በኢትዮጵያ “ህፃናት አዶፕሺህን ቱሪዝምን ማስፋፋት“ በሚል ርዕስ ሳዘጋጃቸው ስለነበሩት ትችቶች የረዥም ጊዜ አንባቢዎቼ ታስታውሳላችሁ ብዬ አስባሁ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ስለካሊፎርኒያ ህገወጥ የሰዎች ዝውውር እና በተለይም በድንጋጌ አንቀጽ 35 የተጠቀሰው እና እ.ኤ.አ በ2012 “ካሊፎርኒያውያን ስለጸረ ጾታ ብዝበዛ ተነሳሽነት ድንጋጌ“ የተዘጋጀውን እና 81 በመቶ ድምጽ በማግኘት የጸደቀውን  ሙሉ በሙሉ አጥብቄ እደግፋለሁ፡፡

ሁልጊዜ በሶስተኛው ዓለም ደኃ ሀገሮች መዝናኛ ግንባታ እየተባለ የሰውን ክብር የሚያጠፋ እና አስከፊ የሽርሙጥና ተቋማትን የሚመሰርት፣ ህገወጥ የሰዎች ዝውውርን እና የህጻናት  የጾታ ብዝበዛን ማስፋፈት የተለመደ ተግባር ነው፡፡

የዶሚኒካን ሬፐብሊክ በዓለም ላይ በጣም ታላቁ የካሪቢያን የመዝናኛ መዳረሻ (ሪዞርት) ነው ይባላል፡፡ ደህና፣ የዚያ ቱሪዝምግን በጎኑ የግብረ ስጋ ቱሪዝም ነው፡፡ የጾታ ቱሪዝም በኬንያ እድሚያቸው እስከ 12 ዓመት የሆናቸው በድህነት እና በኢኮኖሚያዊ ችግር ሁኔታ አካላቸውን በመሸጥ ቢዝነስ እየሰሩ እንዲኖሩ ተገደዋል፡፡ የኬንያ ባለስልጣኖች ለዚህ ጉዳይ ጆሮ ደባ ልበስ ብለዋል፣ ምክንያቱም የጾታ ቱሪዝም የኢኮኖሚ እድገት ለዚያች ሀገር ያመጣል ተብሎ ስለሚታሰብ ነው፡፡

ታይላንድ በጾታ ቱሪዝም ዝርዝር ውስጥ በመጀመሪያው ረድፍ ላይ የምትገኝ ሲሆን የባንግኮክ ቀይ መብራት ወረዳ የጾታ ፊልሞቹ ዋና ማሳያ ቦታ ነው፡፡ በታይላንድ ህገወጥ የሰዎች ዝውውር ለጾታ ንግድ ሰራተኞች ዋና የገቢ ምንጭ ነው፡፡ እንደዚሁም ሁሉ በፊሊፒንስ ከ40- 60 በመቶ የሚሆኑት ሀገሪቱን የሚጎበኙ ቱሪስቶች እዚያች ሀገር የሚሄዱት ለጾታ ቱሪዝም ብቻ እንደሆነ ተመሳሳይ ታሪክ ነው፡፡ የጾታ ቱሪዝም እና ህገወጥ የጾታ ዝውውር የተንሰራፋባት ብራዚል ከዚህ የተለየች አይደለችም፡፡ የብራዚል መንግስት እ.ኤ.አ በ2016 ለሚካሄደው ኦሎምፒክ ችግሩን ለመፍታት ተጨማሪ እርምጃ መውሰድ ይኖርበታል ይባላል፡፡

በውጭ ምንዛሬ እጥረት ተጠፍንገው የሚገኙ እንደ ዘ-ህወሀት ያሉ አገዛዞች ገቢ ለማመንጨት ፊታቸውን ወደ ጾታ ቱሪዝም አዙረዋል፡፡ በዘ-ህወሀት አገዛዝ ስር ያለችው ኢትዮጵያም የአፍሪካ የሽርሙጥና ማዕከል ሆናለች፡፡ እኔ ያንን አላልኩም፡፡ ይልቁንም በዩናይትድ ስቴትስ የመንግስት መምሪያ “የ2014 ህገወጥ የሰዎች ዝውውር ዘገባ“ በሚል ርዕስ የተዘጋጀው ዘገባ እንዲህ ብሏል፡

ኢትዮጵያ ለግዳጅ የጉልበት ስራ እና ለህገወጥ የጾታ ዝውውር ለወንዶች፣ ለሴቶች እና ለልጆች ዋና ምንጭ እና ከዚህም ባሻገር ዋና መዳራሻ እና መተላለፊያ ሀገር ናት፡፡ ከኢትዮጵያ የገጠር አካባቢዎች ልጃገረዶች በሀገር ውስጥ የጉልበት ብዝበዛ ይካሄድባቸዋል፣ አልፎ አልፎም በሀገሪቱ ውስጥ ሽርሙጥናን እንዲያካሂዱ ተዳርገዋልበአፍሪካ ውስጥ ታላላቆቹ የሽርሙጥና ቤቶች መናኸሪያ ዋና የገበያ ከተማ አዲስ አበባ ስትሆን ልጃገረዶች እስከ 8 ዓመት እድሜ ያላቸው ህጻናት የሽርሙጥና ተግባራትን በማካሄድ ላይ የሚገኙበት ሁኔታ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ልጃገረዶች በሀገር ውስጥ የጉልበት ብዝበዛ እና በውጭ ሀገር ደግሞ በመጀመሪያ በጅቡቲ፣ በደቡብ ሱዳን እና በመካከለኛው ምስራቅ ሀገሮች ውስጥ ሽርሙጥናን እንዲያካሂዱ ተገደዋል፡፡“  (አህጽኖት ተጨምሯል፡፡)

በአሁኑ ጊዜ በአፍሪካ ውስጥ የህክምና ቱሪዝም ማዕከል ደቡብ አፍሪካ ስትሆን በርካታ የግል፣ በከፍተኛ ሁኔታ የሰለጠኑ ዶክተሮች እና የዘመኑን ምርጥ ቴክኖሎጂ በመጠቀም ህክምና መስጠት የሚችሉ ዓለም አቀፋዊ ደረጃውን ያሟሉ ተቋማት ይገኛሉ፡፡ ከታመኑ የዜና ምንጮች እንዳገኘሁት መረጃ ከሆነ ደቡብ አፍሪካ ለዘ-ህወሀት የህክምና ቱሪስቶች ዋና ተመራጭ መዳረሻ ናት፡፡

ከመካከለኛው ምስራቅ ሀብታም በሽተኞች ህክምና ለማግኘት ታይላንድን፣ ሲንጋፖርን፣ ማሊሲያን እና ህንድን ይጎበኛሉ፡፡

ይህንን ጉዳይ ፊት ለፊት እንጋፈጠው፡፡ የካታር የመዝናኛ ሆቴሎች በኢትዮጵያ ውስጥ ከተገነቡ በኋላ ዋጋቸውን ሊቋቋም የሚችለው ማን ነው?

በመዝናኛ ሆቴሎቹ ለመጠቀም ለሚመጡት ዋና መሳቢያ ሊሆን የሚችለው ምንድን ነው? ጭጋጋማው የአዲስ አበባ የአየር ሁኔታ ነው?

ምናልባትም ወጣት ሴቶችን በከተማ ለማደን…

በእርግጠኝነት ኢትዮጵያ የመዝናኛ ሆቴሎችን የምትፈልገው በሙስና ለበከቱ እና ሀብታም ለሆኑ ሽርሙጥና አሳዳጆች መዝናናት እና መስተንግዶ ለማቅረብ ትኩረት በማድረግ ነው?

አሁን በአዲስ አበባ ላይ የሽርሙጥና መዝናኛ ሆቴል የመገንባቱ ሀሳብ ለምን ጥልቅ የሆነ ጥርጣሬ እንደጣለብኝ እና ሀዘን እንደያዘኝ ልትገነዘቡልኝ እና መሰረተ ሀሳቤን ልትደግፉ እንደምትቸሉ እረዳለሁ!

ዘ-ህወሀትን በመውቀስ የማግኘው እርካታ የለኝም፣ ሆኖም ግን የእኛን የማሰብ ችሎታ የሚዘልፍ ነገር በግለጽ ሲያደርጉ በማስተውልበት ጊዜ ጨርቅን ጥሎ የማበድ ያህል ያበሳጨኛል፡፡

Qatari 5ዋናውን ጠቃሚ ነገር እነሆ፡ 80 በመቶ የሚሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ በተጎሳቆለ በገጠር የሳር ቤት ጎጆ ውስጥ እየኖረ ባለበት ሁኔታ ኢትዮጵያ በእርግጠኝነት የመዝናኛ ሆቴሎችን የምትፈልገው በሙስና ለበከቱ እና ሀብታም ለሆኑ ሽርሙጥና አሳዳጆች መዝናናት እና መስተንግዶ ለማቅረብ ትኩረት በማድረግ ነው?

የእኔን ጭንቅላት ሙሉ በሙሉ የሚበጠብጠው ዋናው ጥያቄ እንዲህ የሚል ነው፡፡

15 ሚሊዮን የሚሆኑ ዜጎቹ የሚልሱት የሚቀምሱት አጥተው ለረሀብ እና ቸነፈር ተጋልጠው በእያንዳንዷ ዕለት በመቶዎች የሚቆጠሩት እየሞቱ ባሉበት ሁኔታ እንዴት ባለ መንገድ ነው አንድ አገዛዝ የሽርሙጥና ማስፋፊያ ሆቴል ሊገነባ ብቻ ሳይሆን ሊያልም የሚችለው?

ህጻናት እንደ ዝንብ እየረገፉ ባሉበት ሁኔታ አንድ አገዛዝ የሽርሙጥና ማስፋፊያ ሆቴሎችን የሚገነቡ ሰዎችን ፍለጋ መሄድ ኢሞራላዊ እና ሙሉ በሙሉ ሰይጣናዊ ዕኩይ ምግባር አይደለምን?

አውዳሚው እና ቀሳፊው ረሀብ ወደ ኢትዮጵያ እየደረሰ ነው፡፡ በእርግጥ ባለጥቁሩ ፈረስ የምጽዓት ቀን እየገሰገሰ መሆኑን ጨረፍታውን ካየሁበት ከ3 ዓመታት በፊት ጀምሬ ሳሳውቅ ቆይቻለሁ፡፡

በዚህ ባለፈው ጥቅምት ወር እንዲህ የሚል ቀላል ጥያቄ አቅርቤ ነበር፡ “በኢትዮጵያ ያለውን ረሀብ ዘ-ህወሀት ሊያቆመው ይችላልን?“

ዘ-ህወሀት እጁን ዘርግቶ ባለጥቁሩን ፈረስ እንኳን ደህና መጣህ በማለት በነጻ እንዲጋልብ በመፍቀድ ቆሻሻ ስራቸውን አንድሰራላቸው ይጋብዙታል፡፡

እስቲ የተባበሩት መንግስታት የህጻናት መርጃ ድርጅት/ዩኒሴፍ ያወጣውን እና እንዲህ የሚለውን ዘገባ እንመልከት፡

“ወደ 435 ሺ የሚሆኑ ህጻናት በአስከፊ የምግብ ንጥረ ነገር/severe acute malnutrition እጥረት ምክንያት ህክምና ይፈልጋሉ፡፡ እንደዚሁም ደግሞ ከ1.7 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ህጻናት፣ ነፍሰ ጡር ሴቶች እና የሚያጠቡ እናቶች ተጨማሪ አልሚ ምግቦችን ይፈልጋሉ፡፡ ከ5.8 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ዜጎች በአስቸኳይ ውኃ፣ የንጽህና እና የጤና አጠባበቅ አገልግሎቶችን ይፈልጋሉ፡፡ የውኃ እጥረት የጤና አጠባበቅ ጉዳዮችን ያስነሳሉ፣ ይህም በበኩሉ ከውኃ ጋር ወደተያያዙ የጤና አጠባበቅ ስጋቶች እከክን ጨምሮ ይመራል፡፡ ድርቁ የትምህርት ክትትልን በመጉዳት ላይ ይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ከ2 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ህጻናት ከትምህርት ገበታ ለማቋረጥ በቋፍ ላይ ይገኛሉ፡፡ እንደዚሁም ወደ 3 ሺ የሚሆኑ ትምህርት ቤቶች የመዘጋት አደጋ አንዣቦባቸው ይገኛሉ፡፡ ይኸ ሁኔታ የህጻናትን ለአደጋ ተጋላጭነት ስጋቶችን ማለትም የኃይል ጥቃት፣ ጉልበት ብዝበዛ፣ ያለዕድሜ ጋብቻ፣ ህገወጥ የሰዎች ዝውውር እና መብት ረገጣን በከፍተኛ ደረጃ ይጨምራል…“ (አህጽኖ ተጨምሯል፡፡)

ዘ-ህወሀት በአየር መዛባት ምክንያት በዓለም ላይ አስከፊ የሆነ የድርቅ እና የጎርፍ አደጋ ቀውስ የተፈጠረው ሙሉ በሙሉ  በኤል ኒኖ ነው ይላል፡፡ በሌላ አባባል ዘ-ህወሀት ዝናብ የለም፣ እናም ድርቅ ይከተላል፣ ከዚያም ረሀብ ይከሰታል ይላል፡፡ ዘ-ህወሀት ረሀቡን ለመቋቋም ከፍተኛ የሆነ ዕቅድ በማውጣት ወደተግባራዊ እንቅስቃሴ ከመሄድ ይልቅ ከዚህ ጋር ምንም ዓይነት ተያያዥነት ከሌለው ጋር በመሞዳሞድ የሽርሙጥና ሆቴሎችን የሚገነቡ ሰዎችን በመፈለግ ላይ ያለበት እውነታ ነው ያለው፡፡

ግርሀም ፒብልስ የአጻፋ መልስ ለመስጠት በቅርቡ ያዘጋጁት ጽሁፍ ደካማ አስተዳደር፣ የመንግስት ድግግሞሽ እና ማታለል አሰቃቂ የምግብ ቀውስን በማስከተል ጠቃሚ የሆነ ሚና ይጫወታሉ በማለት ገልጸዋል፡፡

እንደ ፒብልስ ዘገባ ከሆነ፡

“የተኩራራ አህጉራዊ ደረጃን በመያዝ፣ የኢኮኖሚ ልማትን በማምጣት (ጥቂት ዕድገት ቢኖርም ሀገሪቱ በዓለም ላይ በድህነት በሶስተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች) እና የተዛባ ብሄራዊ ገጽታ በመያዝ፣ ገዥው ፓርቲ- ጭካኔን የተላበሰ አምባገነን፣ ሆኖም ግን የማስመሰያ ዴሞክራሲን እያራመደ የሚሄድ ቢሆንም-የፖለቲካ ቁርጠኝነት እና ታማኝነት ይጎድለዋል፡፡ ስለሆነም አሁን ያለውን ሁኔታ በግልጽ መፍትሄ ለመስጠት ተስኖታል፡፡ በአዲስ አበባ እና በሌሎች አካባቢዎች ለድርቁ ሰለባዎች ገንዘብ እንዳይሰባሰብ ህዝብ አቁሟል፡፡ ካለፈው ክህደት ጋር በተጣጣመ መልኩ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በቢቢሲ ፕሮግራም ስለቀውሱ አስመልከቶ ለአንድ ለሀገር ውስጥ ጋዜጠኛ በሰጡት ቃል “በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ ረሀብ የሚባል ነገር የለም…“ ብሏል፡፡

ስለሆነም በ10 ሺዎች ለሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ሞት ተጠያቂው ማን ነው? ኤል ኒኖ ወይስ ደግሞ ኤል ዘ-ህወሀት?

በምግብ ዋስትና እጦት ቅድመ ማስጠንቀቂያ እና ትንታኔ በመስጠት ቀዳሚ የሆነው እና በዩኤስኤአይዲ/USAID የተቋቋመው የረሀብ ቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓት/Famine Early Warling System (FEWS) እ.ኤ.አ ከታህሳስ 2015 መጀመሪያ አካባቢ ጀምሮ 15 ሚሊዮን ኢትዮጵውያን አስከፊ ለሆነ የምግብ እጥረት ተጋልጠዋል የሚል ዘገባ አቅርቧል፡፡

ረቅማስ/FEWS ኢትዮጵያ “በዓለም ላይ በከፍተኛ ደረጃ ለምግብ ዋስትና ዕጦት የተጋለጠች ሀገር ህዝብ“ በማለት ገልጿታል፡፡

ረቅማስ/FEWS እንዲህ በማለት ደምድሟል፡ “የሰሜናዊ ሶማሊ ክልል እና ደቡባዊ አፋር በአስቸኳ ጊዜ ውስጥ ናቸው (IPC Phase 4) [የተቀናጀ የምግብ ዋስትና ምዕራፍ ምደባ/ Integrated Food Security Phase Classification] ትርጉሙም በህይወት ለመቆየት በቂ ምግብ ማግኘት አለመቻል እና በጣም እየጨመረ የመጣ የምግብ ንጥረ ነገር እጦት እና የሞት አደጋ“ የሚል ነው፡፡

በአሁኑ ጊዜ 15 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን በIPC 4 (አስቸኳይ የሰብአዊ እርዳታ) ውስጥ ናቸው፡፡

ቀጣዩ እና የመጨረሻው ደረጃ (ገጽ 4) የመጨረሻው ደረጃ እና IPC 5 (ረሀብ/ሰብአዊ እልቂት (Humanitarian Catastrophe) ነው፡፡ በቅርብ ጊዜ የወጣውን ረቅማስ/FEWS ለማየት የድርቅ ካርታ/drought map እዚህ ጋ ይጫኑ፡፡

እ.ኤ.አ የካቲት 2014 “ኢትዮጵያ 2.7 ሚሊዮን ዜጎችን ለመመገብ የለጋሽ ድርጅቶችን እርዳታ አጥብቃ ትሻለች“ የሚል ዘገባ ቀርቦ ነበር፡፡ ይህ ዘገባ በ2014 መጀመሪያ አካባቢ የተደረገ ነበር፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ ግብር ከፋይ ህዝብ 218 ሚሊዮን ዶላር ከፈለ፡፡

እ.ኤ.አ በ2013 ከ4 ሚሊዮን በላይ ዜጎችን ለመመገብ ኢትዮጵያ ወደ 700 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ሰብአዊ እርዳታ ተቀበለች፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ ግብር ከፋይ ህዝብ 236 ሚሊዮን ዶላር ከፈለ፡፡

እ.ኤ.አ መስከረም 2012 “የኢትዮጵያ መንግስት 3.7 ሚሊዮን የሚሆኑ ዜጎቹ በዚሁ ዓመት በነሀሴ እና በታህሳስ እንደዚሁም በጥር 3.2 ሚሊዮን ሰብአዊ እርዳታ እንደሚያስፈልግ አስታወቀ“ የሚል ተማጽዕኖ አቅርቦ ነበር፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ ግብር ከፋይ ህዝብ 3.7 ሚሊዮን ዶላር ከፈለ፡፡

እ.ኤ.አ በ2011 ዓለም አቀፍ ሰብአዊ ምግብ/International humanitarian food ለኢትዮጵያ ወደ 500 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ እርዳታ ሰጠ፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ ግብር ከፋይ ህዝብ 313 ሚሊዮን ዶላር ከፈለ፡፡

እ.ኤ.አ ነሀሴ 2010 የተባበሩት መንግስታት የምግብ እና እርሻ ድርጅት (ምእድ)/United Nations Food and Agricultural Organization (UNFAO) “ወደ 5.2 ሚሊዮን የሚገመቱ ኢትዮጵያውያን አሁንም በአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ ላይ ጥገኛ ናቸው፣ እናም ኤጅንሲዎች በረዥም ጊዜ ውስጥ በጣም ከፍተኛ የሆነ የረሀብ ሁኔታ እንደሚፈጠር ስምምነት አደረጉ“ በማለት ዘገባ አቅርቦ ነበር፡፡

እ.ኤ.አ በ2010 ሂዩማን ራይትስ ዎች የሚባለው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ዘ-ህወሀት አስመሳይነትን በተላበሰ መልኩ እና ቆሻሻ ጨዋታውን በመቀጠል የእርዳታን ገንዘብ ሰፊ መሰረት ያለው የአካባቢውን ባለስልጣኖች፣ ሚሊሻዎች እና ሰላዮችን በማሰማራት እርዳታ ማን፣ ምን፣ መቼ እና እንዴት ማግኘት እንዳለበት ለመቆጣጠር ለማዳበሪያ፣ ለዘር እና ለስራ ክፍያ አውሎታል የሚል ዘገባ አቀረበ፡፡ ዘ-ህወሀት 588 ሚሊዮን ዶላር የዓለም አቀፍ ሰብአዊ እርዳታን ተቀበለ፡፡

ማርቲን ፕላውት በቅርቡ በወጣው በኒውስ ስቴትስማን/News Statesman መጽሄት እንዲህ የሚል የክርክር ጭብጥ አቅርበዋል፣ “እ.ኤ.አ  በ1973-74 እና 1984-85 በኢትዮጵያ ተከስቶ የነበረው አውዳሚ ረሀብ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩትን ለሞት የዳረገ ሲሆን ምናልባትም እንደየአግባባቸው 200 ሺ እና 400 ሺ ይገመታል፡፡ የመጀመሪያው አጼ ኃይለ ሥላሴን ከዙፋናቸው አስወግዷል፡፡ ሁለተኛው ለማክሲስቱ መንግስቱ ኃይለማርያም ፍጻሜ አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡“

ስለሆነም ብቸኛው ጥያቄ ታሪክ እንደገና አንድ ጊዜ እራሱን ይደግማል ወይስ አይደግምም የሚለው ነው፡፡

ከታሪክ ለማይማሩት እና ሊማሩ በማይፈልጉት ታሪክ ሁልጊዜ እራሱን ይደግማል እላለሁ፡፡

ዩኒሴፍ እንዲህ ይላል፣ “ወደ 435 ሺ የሚሆኑ ህጻናት በአስከፊ የምግብ ንጥረ ነገር እጥረት /severe acute malnutrition ምክንያት ህክምና ይፈልጋሉ፡፡ እንደዚሁም ደግሞ ከ1.7 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ህጻናት፣ ነፍሰ ጡር ሴቶች እና የሚያጠቡ እናቶች ተጨማሪ አልሚ ምግቦችን ይፈልጋሉ፡

የተራበ ህጻን የተበሳጨ ህጻን ነው!

Qatari 2ዘ-ህወሀት በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ የሚቀርበውን ሁሉንም የረሀብ ዘገባ መቆጣጠሩን ቀጥሎበት ይገኛል፡፡ በዓለም ላይ የሚገኙ ህዝቦች ሁሉ የኢትዮጵያ ህጻናት በመራብ ወደ ሞት አደጋ በሚቃረቡበት ጊዜ የእርዳታ እጆቻቸውን ሊዘረጉ ይችላሉ፡፡

እስከ አሁን ድረስ የሰው እጅ ሲዘረጋላት ቆይቷል! “ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች፡፡“

ዘ-ህወሀት! ለህዝቦች ጥያቄ ምላሽ የመንፈግህን ጸጥታ፣ ማጭበርበርህን፣ ማስመሰልህን፣ ሸፍጥ መስራትህን እና ታማኝ አለመሆንህን ቀዳድህ እንጦሮጦስ ጣለው፡፡ ስለሆነም የዓለም ህዝብ ማየት ይችላል፣ እናም ባመጣኸው ረሀብ ሰለባ በወደቁት ፍርሀትን ያሳድራል፡፡

የዓለም አቀፉ ብዙሀን መገናኛ በረሀብ ወደደቀቀው አካባቢ እንዲሄድ እና በሰው ልጆች ላይ እየፈጸምከው ያለውን ወንጀል ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እንዲዘግብ ፈቃድህ ይሁን!

እንዲህ ተብሏልና፣ “ሶስት ነገሮች ለረዥም ጊዜ ተደብቀው አይቀሩም፡ ጸሐይ፣ ጨረቃ እና እውነት፡፡“

ከዚህም በተጨማሪ “እውነት አንተን ነጻ ያወጣሀል“፡፡

ሆኖም ግን ለረዥም ጊዜ ተደብቆ የቆየው የ2015-16 ረሀብ እውነታ አንድ ቀን በፍትህ አደባባይ የወጣ እንደሆነ ዘ-ህወሀትን ነጻ የሚያደርገው አይሆንም! 

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!         

የካቲት 11 ቀን 2008 .