ሬፐብሊካን እብዶች በአሜሪካ የፕሬዚደንት ምርጫ ክርክር ላይ?

 Republunatics 

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም    

ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ  

የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ የመጀመሪያው የሬፐብሊካኖች ፕሬዚዳንት የነበሩት አብርሀም ሊንከን በአንድ ወቅት እንዲህ ብለው ነበር፣ አንድ ሰው ሀሳቡን በማሳወቅ ሌሎች እንዲቀበሉት ሲያስተምር በምሰማበት ጊዜ እንደ ተናዳፊ ንቦች ሆኖ ሲሰራ ነው ማየት የምፈልገው፡፡

እ.ኤ.አ ነሐሴ 6/2015 በሬፐብሊካን የመጀመሪያ ዕጩ ፕሬዚዳንታዊ ክርክር መድረክ ላይ በጦርነት ላይ ያሉ የተቆጡ ተርቦችን/wasps (የበላይነትን የሚያንጸባርቁትን እና የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ የሆኑትን የአንግሎ ሳክሰን ዝርያዎችን አላልኩም) የተመለከትን ለመሆናችን ምስክርነታችንን እንሰጣለን፡፡

ሀምሌት በሚለው ድራማ ላይ ሸክስፒር አንዲህ ብሎ ፅፎ ነበር: “ሰው ምን ዓይነት ታላቅ ስራ ነው!“

ሙሉ በሙሉ ከቁጥጥር ውጭ የሆኑት የርፑብልካን ፓርቲ እጭዎች መሪ ዶናልድ ጥሩምፕ (ጥሩምባ ነፊ አላልኩም) ታላቅ ስራ ናቸው፡፡ 

ትሩምፕ ስለ ኢራን፣ ቻይና እና ራሽያ ጉዳይ አጭር እና አስደንጋጭ አስገምጋሚ የሆነ ድምጻቸውን እንደ መብረቅ በማጮህ የቃላት ጎራዴያቸውን ከአፎቱ መዝዘው አውጥተዋል፡፡

ትሩምፕ ኦባማ ከኢራን ጋር እያደረገ ያለውን የኒኩሌር ጦር መሳሪያ ስምምነት አፈር ድምሜ እንደሚያበሉት ቃል ገብተዋል፡፡

ከማንኛውም ሰው ጋር በማንኛውም ጊዜ እና ቦታ ትግል ለማድረግ እና የጭቃ ጅራፋቸውን ለማጮህ ዝገጁ አንደሆኑ ግልጽ አድርገዋል፡፡

የክርክሩ መድረክ አሳላጭ መሪ ከሆኑት ከመጊ ኬሊ ጋር በቴሌቪዥን እና በትዊተር (ኢንተርኔት) የቃል ጦርነት ለማካሄድ ዝግጁ መሆናቸዉን አስታውቀዋል።

የ “ሬፐብሊካኑ የዶናልድ ስብስብ” የ”ዴሞክራቱን መጊ ኬሊን ምንም ዓይነት እውቀት የሌላቸው ነፈዝ” እንደሆኑ አድርጎ በሰላ ትችት ወርፏቸዋል፡፡

ትሩምፕ የቁጣ ትችታቸውን በመቀጠል ይኸ ነገር ለመጊ ኬሊ ትክክለኛ እና የሚገባቸው ነው። ምክንያቱም ትሩምፕ ለሴቶች ያላቸው ንቀት አንደተናገሩት “ሴቶች የደለቡ አሳሞች፣ ውሾች፣ ጤናቸውን የማይጠብቁ ንጽህና የለሽ ልክስክሶች እና የሚያስጠሉ እንስሶች ናቸው ” በማለት የስደብ ዉርጅብኝ ጥለዉባቸዋ።

ስድቡን ትሩምፕ በሲኤንኤን ቃለ መጠይቅ ጨመሩበት። ኬሊ  “ከዓይኗ ደም ይወጣ እንደነበር መመልከት ችለሀል፡፡ በሌላ ሰውነት አካልዋም ደም ይዎጣ ነበር ጥያቄ ሲጠይቀኝ አሉ ትሩምፕ፡፡“ (ሴት ልጅ በተፈጥሮ ያላትን ሁኔታ በማንቁአሸሽ።)

ትሩምፕ ይቅርታ ላለመጠየቅ አነ ያልኩት ካይኗ አንጂ ሌላ አይደለም።  ከተለመደው አስተሳሰብ ውጭ የሚያስብ ባለጌ ብቻ ነው አሉ ትሩምፕ (የባለጌዎች መሪ።)

ትሩምፕ ማለት ዉዳቂ የሬፐብሊካን ፓርቲ አባል ማለት ነው።

ለሬፐብሊካን ፓርቲ እንደዚህ ያለ እርባና የለሽ ሰው በግንባርቀደምትነት ቦታ ላይ ሆኖ መገኘት እንዴት የሚያሳፍር ነገር ነው!

እንደ ጆርጅ ቤርናርድ ሻው  እንዲህ ብለው ነበር፣ “ከዓሳማ ጋር በፍጹም ትግል አትግጠም፡፡ ምክያቱም አንተ ቆሻሻ ትሆናህ ዓሳማው ግን ይህንን ነገር ይወደዋል፡፡“

መጊ ኬሊ ይህን ትመርጥ ተምራ  ከዓሳማ ጋር ትግል አልገጠመችም።

ትሩምፕ ያሳማ ትግልን  ይወዱታል!

ከእያንዳንዱ ታላቅ ሰው ጀርባ ታላቅ ሴት እንደምትኖር እምነት አለኝ፡፡

ከዚህች ታላቅ ምስኪን ሴት ጀርባ ምን ዓይነት የትልቅ ትንሽ ሰው ነው ያለው ?

አንዳንድ ጊዜ ትሩምፕ ሰው ወይም ደግሞ የ”ታስማኒያ ሰይጣን” (አውስትራልያ የሚገኝ ቁጡ አውሬ) ናቸው በማለት እገረማለሁ፡፡

እንደ “ታስማኒያ ሰይጣን“ የሆኑት ትሩምፕ ያጉረመርማሉ፣ የጥላቻ ድምጽ ያሰማሉ፣ በቁጣ እና በደም ፍላት ይናገራሉ፣ እናም በትዊተር፣ በሲኤንኤን እና በፎክስ ቆጥቋጭ የሆነ ትችታቸውን በማቅረብ ያገኙትን ሁሉ ይናደፋሉ ይነክሳሉ ፡፡

ከጥቂት ወራት በፊት ትሩምፕ በእራሳቸው እንዴት ቻይናን አንደገረፉ በጉራ እንዲህ በማለት አንባርቀዋል፡ “በንግድ ስምምነት ለምሳሌ ያህልም በቻይና አየተሸነፍን ነው። ገደሉን እኮ ! እኔ ግን  ሁልጊዜ ቻይናን አገርፋለሁ፡፡“ ብለው ቱሪናፋቸዉን  ለቀቁት ።

አንደው ለመሆኑ እነዚያን ውድ የሆኑትን የትሩምፕ  ከረባቶች፣ ሸሚዞች፣ የከረባት ማስያዣ ቁልፎችን እና የሸሚዝ እጅጌ ማስያዣ ጌጣጌጦችን የሚያመርቷቸው የት ነው

በቻይና የተሰሩ ናቸው ወይስ ደግሞ ትሩምፕ በቻይና ከተማ፣ በጀፈርሰን ግዛት፣ በቴክሳስ  እንዲሰሩ ትዕዛዝ ሰጥተው ነው?)

ትሩምፕ ስለ ነግድ ችሎታቸው ጉራቸዉን አሰሙ።

ለነገሩ እ.ኤ.አ ከ1991 ጀምሮ ዶናልድ ትሩምፕ በሚል ስያሜ ሲንቀሳቀሱት የቆዩት 4 ኩባንያዎች ከስረው አልተዘጉምን?)

ትሩምፕ በምዕናባቸው የዩኤስ-ሜክሲኮን የወሰን ክልል የሚያቋርጡትን ህገወጥ ስደተኞች ለማስቆም ሲሉ መቆጣጠሪያ የሚሆን ግንብ ገንብተዋል፡፡ ትርምፕ እንዲህ በማለት አውጀዋል፣ “ በወሰኑ ጥሰው የሚገቡትን እንደ ጎርፍ የሚፈስሱት ገዳዮች ወንጀሎች፣ አደንዛዥ ዕጾች ነጋዴዎች አንዳይገቡ ወደአሜሪካ ትልቅ ሁኔታ የድንጋይ አጥር መገንባት አለብን በፍጥነት።”

ትሩምፕ እንዲገነባ የሚፈልጉት ግንብ የበርሊንን ግንብ ወይም ደግሞ ታላቁን የቻይናን ግንብ ይምሰል አይምሰል ግልጽ ያደረጉት ነገር የለም፡፡

ትሩምፕ ቻይናን ከመግረፍ ተቆጥበው የነሱን የግንብ መሀንዲሶች ብያነጋገሩ ይሻላል ፡፡

የትሩምፕን ግድግዳ ላይ የሚከተለው ፁሁፍ አንደሚኖር አምናለሁ።

“ወንጀለኞችን፣ ነብሰ ገዳዮችን፣ አስገድዶ ደፋሪዎችን፣ አደንዛዥ ዕጽ አዘዋዋሪዎችን እና ሌሎችን ህገወጥ ነገር የሚሰሩትን አዚያው ያሉት ይቀመጡ።

የደከመው፣ ደካማው እና በአንድ ላይ የተሰባሰበው አካል በሌላ ቦታ አጥቶ አሜሪካ መተንፈስ የሚፈለገው አዚያ ያለበት ይቀመጥ።  ቤት አልባዎችን እና ሌሎችን የተበሳጩ ፍጡሮች  እዚያው ፓስፊክ ውቅያኖስ ውስጥ መሪ የሌለው መርከብ ዉስጥ ይተዋቸው። ወርቃማው ያሜሪካ በር ተዘግቷል! ወደዚህ ልትገቡ አትችሉም!

ትሩምፕ ፕሬዚዳንት የመሆን አጋጣሚውን ማግኘት ቢችሉ ትሩምፕኖሚክስን ወደ ተግባር በመተርጎም አሜሪካንን ከምጣኔ ሀብት ቀውስ (በአሁኑ ጊዜ ከ18 ትሪሊዮን ዶላሩ ብሄራዊ ዕዳ የቱንም ያህል ቢቀር) ወደ ሙሉ ኪሳራ ያስገቧታል።

ሊንድሰይ ግራሃም በአንድ ወቅት እንዲህ ብለው ነበር፣ “ዶናልድ ትሩምፕ በሬፐብሊካን ስብስቦች መካከል ምንም ዓይነት ቁጥጥር የማይደረግበት ተሽከርካሪን በማሽከርከር ላይ ይገኛል፡፡ ስለሆነም አንድ ሰው ሊያስቆመው ይገባል፡፡ ይህንን ጉዳይ እልባት እስካልሰጠነው ድረስ እ.ኤ.አ በ2016 የኋይት ሀውስን ቤተመንግስት በማሸነፍ ስልጣንን ለመቆጣጠር የሚያስችል መንገድ አይታየኝም፡፡“

ትሩምፕ የጫካ ገጀራ (ቆንጮራ ) በመያዝ የሬፐብሊካንን ስብስብ አባላት በመጨፍጨፍ ላይ እንዳለ አድርጌ ነው የማየው፡፡

ማርኮ ሩቢዮ ስለድህነት ተማጽዕኖ አቀረቡ፣

ቀደም ሲል ማርኮ ከደሃ ቤተሰብ ነኝ የወጣሁት አሉ።  አሁን ግን ከፍተኛ ባለስልጣን፡፡ እንዲህ በማለትም ተናግረዋል፣ “እኔ የእኛ ዕጩ ተጠቋሚ ከሆንኩ በምን ዓይነት ሁኔታ ነው ሄላሪ ክሊንተን ስለገንዘብ ለእኔ ስብከት ልታቀርብ የምትችለው?  እርሷ እንዴት ነው እኔን ድሃዉን ስለገንዘብ  ልታስተምር የምትችለው።  ስለተማሪዎች ብድር በምን ዓይነት ሁኔታ ነው ለእኔ ልታስተምር የምትችለው? ከአራት ዓመታት በፊት በእርግጥ 100 ሺ ዶላር የትምርት ብድር ነበረብኝ ፡፡“

ወይ ማርኮ! ሂል እና ቢል (ሂላር ና ቢል  ክሊንቶን ኋይት ሀውስን በሚለቅቁበት ጊዜ ቤሳ ሳንቲም እንዳልነበረ ማርኮ ያውቃል?

ሂልሪ  እንዲህ አሉ፣ “ለማስታወስ ምንም ምክንያት የለም፣ ሆኖም ግን ከኋይት ሀውስ ስንወጣ ሳንቲም አልነበረንም ግን በእዳ እስከ አንገታችሁ ድረስ ተዘፍቀን ነበር፡፡ እኛ እዚያ በምንገባበት ጊዜ ምንም ዓይነት ገንዘብ አልነበረም፣ እናም ለቤት ግንባታ የሚውል ገንዘብ በማሰባሰብ በአንድ ላይ በማድረግ ለሞርጌጅ ባንክ እና ለቸልሲያ ትምህርት በማቅረብ ጥረት በማድረግ ላይ ነበርን ፡፡ ይህ ቀላል ነገር አልነበረም፡፡ በእርግጥ ቢል ጥንካሬ በተመላበት ሁኔታ ሲሰሩ ነበር፡፡ ይህ ለእኔ በጣም አስደናቂ ነገር ነው፡፡ በጣም ጠንካራ በሆነ መልኩ ሰርተዋል፡፡“

(ሂል እና ቢል የክሊንተንን ፋውንዴሽን ከመመስረታቸው በፊት “በሀምፕቶንስ (የነጠጡ ሀብታሞች መኖሪያ ሰፈር) መጠለያ” ተኮልኩለው በአንተ ማርያም አያሉ ሲለምኑ ይታየኛል!)

ስለድህነት ማርኮ ብያወሩ ይሻላል። አንዴ ቢል ና ህልሪ ያለ ደሃ የለም።

ጀብ ቡሽ የሬፐብሊካን ፓርቲ ክርስትና አባት” (ማለትም የማፊያ ዋና አዛዥ)  ነውን?

እንዲህ ብለው ነበር ቡሽ ፣ “በፍሎሪዳ መዝገብ አለኝ፡፡ በእርግጠኝነት በአባቴ እና በወንድሜ ከፍተኛ የሆነ ኩራት ይሰማኛል፡፡ በፍሎሪዳ  ባለ ሰይፉ ብለው ይጠሩኝ ነበር ፡፡ ቪቶ ኮርሊዮን (የማፊያ ዋና አዛዥ) እያሉ መጥራቱን እንደጠበቁ ነው፡፡ ምክንያቱም በበጀቱ ላይ 2500 የተለያዩ ነገሮችን ነጣጥዬ በማንሳት ወስኘ ነበር። “

ማፊያ ክርስትና አባት ዶን ቪቶ ኮርሊዮን እንዲህ ብለው ነበር፣ “እምቢ የማይለው አይነት ገጸ በረከት አቀርብለታለሁ፡፡“

ቡሽ ለትሩምፕ እምቢ የማይለው ገጸ በረከት ሰጠው ብያባርሩት ጥር ነበር።

ሚኬ ሁካቢ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱን ሰይጣናዊነት እንዲህ በማለት በቀጥታ ተጋትረውታል፡ “በአሁኑ ጊዜ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ያምላክ ፍርድ ቤት አይደለም።

በዚያ ዓይነት መንገድ በፍጹም አስቤ አላውቅም፡፡ ህም! ጠቅላዩ ፍርድ ቤት ሊባል?

በአርካንሳ ግዛት የኢማኑኤል መጥምቃዊት ቤተክርስቲያን የሆኑት ሁካቢ በማቴዎስ ወንጌል በምዕራፍ 25 ላይ ሰፍሮ የሚገኘውን “የመጨረሻ ፍርድ” የሚለውን አሰበው ይሆናል ይህን የተናገሩት።

ቴድ ክሩዝ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩት በሕጋዊ መንገድ ወደ ሀገር ያልገቡት በማንኛውም ጊዜ መውጣት እና መባረር እንዳለባቸው ያምናሉ፡፡

በአሜሪካ ውስጥ ያሉትን ሕገ ወጥ ነዋሪዎች የሚደግፉን ለመዋጋት ቆርጠው ተነስተዋል፡፡ እንዲህም ይላሉ፣ “ምህረት (አምነስቲን) በአሜሪካ ውስጥ ያሉትን ሕገ ወጥ ነዋሪዎች በምንም ዓይነት ሁኔታ እስከ አሁን ድረስ ደግፌው አላውቅም፡፡ እናም የቹክ  ሹመር በሴኔቱ ውስጥ ያሉትን አነዚህን ነዋሪዎች 8 ደጋፊዎች  ግንባር ቀደም ሆኘ እዋጋለሁ ብለዋል ፡፡“

የክሩዝ “8 ወሮበሎች” ሰነተሮች  በማኦ ሴቱንግ ይመራ የነበረውን የቻይናን ኮሙኒስት ፓርቲ ጋንግ ኦፍ ፎር አስታወሰኝ፡፡

ክሩዝ ከትሩምፕ ጋር በመዶለት 8 ወሮበሎችን በማደራጀት የቻይና ከኮሙኒስት ፓርቲው ውስጥ ያሉትን ቢዋጉ ጥሩ ነበር።

ማባረር አይችሉምን?

ክሩዝ የተወለዱት ካናዳ ነው፡፡ ባለፈው ዓመት ክሩዝ የካናዳ ዜግነታቸዉን ክደው ነበር።

የትወለዱ ነገር ለክሩዝ ችግር ሆኖ አይቀርብም ምክንያቱም ኦባማ የተወለደው ኬንያ ነው እናም አሁንም በፕሬዚዳነት የስልጣን እርካብ ላይ ይገኛል፡፡

ማርኮ ሩቢዮ በኦባማ ላይ ጸረ አብዮት እንቅስቃሴን በመምራት ድል አድራጊ እንደሚሆኑ እንዲህ በማለት ተናግረዋል፡፡ “የኦባማን የጤና ፖሊሲ መሻር እና በሌላ መተካት አለብን፣ ዶድ ፍራንክን በመሻር ከፍተኛ ትምህርትን በሚያሻሽል ሕግ መተካት አለብን፣ እናም ሕዝቦች ለ21ኛው ክፍለ ዘመን ስራዎች ብቁ ለሚያደርጉ ክህሎቶች ተደራሽ መሆን አለባቸው፡፡“

ዶድ ፍራንክ በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ከታላቁ የምጣኔ ሀብት ቀውስ ጀምሮ ከተደረጉት የፖሊሲ ማሻሻዎች ቁጥጥሮች መካከል የፋናንሻል ማሻሻያ በጣም ጠቃሚ የሆነ የፖሊሲ ለውጥ ነው ይባላል፡፡ የማርኮ ሮቢዮ ቀጣይ ቀን 2008 እንኳን ደህና መጣህ፡፡

“ማርኮ“?

“ፖሎ“ ከ16 ሌሎች ሬፐብሊካን ህልም አላሚዎች ጋር በመሆን መጮኽ ጀመሩ፡፡

ማርኮ የትሩምፕን ጥሩንባ ሊነፉ ይችላሉን?

ክሪስ ክሪስቴ በጸረ ሽብር ጦርነቱ ላይ የተመለከተውን አራተኛ የሕግ ማሻሻያ በመሰረዝ ድራሹን ለማጥፋት ቃል ኪዳን ገብተዋል፡፡ 

ክሪስቴ እንዲህ በማለት እንደ ብራቅ ጮኸዋል፣ “በዚህ መድረክ በመዳኘት፣ በመመርመር እና እ.ኤ.አ ከመስከረም 2011 በኋላ አሸባሪዎችን በማሰር ላይ ያለሁት ብቸኛው ሰው እኔ ነኝ፡፡ የአሜሪካንን ህዝብ ሕይወት እና ደህንነት ለመጠበቅ ምንም ዓይነት ይቅርታ በምንም ዓይነት መልኩ አላደርግም፡፡ ጥቂት ያልሆኑት ያንን ነገር ለመስራት እንዲችሉ ለአፈታሪኮቻችን የበለጠ መሳሪያዎችን በመስጠት በህዝቦች ላይ እምነትን በመጣል በትክክለኛው መንገድ እንዲሰራ ማድረግ ይኖርብናል፡፡“

“እነዚያን ሰዎች ታምኗቸዋላችሁ”? አምላክ ሁላችንንም “ከእነዚያ ሰዎች” ይጠብቀን!

ብቸኛው አፍሪካአሜሪካዊው ቤን ካርሰን ፕሬዚዳንት ሆነው የሚመረጡ ከሆነ ሁሉንም የማሰቃያ መንገዶች ያላቸውን ሃሳብ ለመግለፅ አልፈለጉም ነበር

ጉዳያችን ለሆነው ነገር የምንፈልጋቸውን መረጃዎች ለማግኘት የምናደርገው ነገር እና ምን ማድረግ እንዳለብንም በዜና ማሰራጫ ለብዙሀኑ ህዝብ የግዴታ ማስተላለፍ የለብኝም፡፡

ቤን ስለሰቆቃ  ከጀሴ ቨንትራ ጋር መነጋገር አለባቸው፡፡ ጀሴ እንዲህ ብለው ነበር፣ “ዲክ ቸኔ የሰቆቃ መሳሪያን አንድ ሰዓት ስጠኝ። ከዚአ ቼንን የሆነዉና ያልሆነዉን አናዝዘዋቸዋለሁ።  “ ጀሴ አይቀልዱም ፡፡ የባህር መርከበኛ ነበሩ፡፡

ምርጥ የሆነ የአሰራር ስርዓት! ማሰቃዬትን፣ ጭካኔን እና በእስር ቤቶች በቁጥጥር ስር ያሉ እስረኞችን ኢሰብአዊ በሆነ መልኩ ማስተናገድ “የጀኔቭ ስምምነት” እየተባለ በሚጠራው ሰነድ ውስጥ ምንም ነገር የለምን? ይህንን ነገር ነቅሶ ለማውጣት የአዕምሮ ጠጋኝ ቀዳጅ ሐኪም መሆንን ይጠይቃል፡፡

ራንድ ፓውል ጎርድ  ትሩምፕን ልብ አቆሰሉ፡፡ “ሁሉንም ዓይነት ፖለቲከኞች መግዛት እና መሸጥ እንደሚችሉ አረጋገጡ ትሩምፕ…በክሊንተንን እሽ በሚል ፖሊሲ ላይ ገደብ ጣሉ፡፡ ስለሆነም እንደ ሬፐብሊካን መስራት የማይችል ከሆነ ምናልባትም ክሊንተንን ይደግፋሉ ወይም ደግሞ ነጻ ሆኖ ብቻን መስራትን ይተገብራሉ፣ ሆኖም ግን የእራሳቸውን ክልከላ መጣል ጀምረዋል ምክንያቱም ፖለቲከኞችን መግዛት ይችላሉና፡፡

ራንድ በእጩ ፕሬዚዳንትነት የሕልም ምድር ውስጥ!

ስኮልት ወከር ከአራት ዓመታት በፊት ከነበረው ሁኔታ በበለጠ መልኩ በዕቅድ የሚመራ የቤተሰብ ኑሮን በማራመድ እንደሚያሻሽሉ እና ያልተወለዱ እና በማህጸን ውስጥ ያሉ ህጻናት ጤንነትም እንደሚጠበቅ በመግለጽ እንደ ብራቅ በመጮህ ተናግረዋል፡፡ ስለ ህዝብ የዘርፍ ማህበራት እና የወል መብቶቻቸውን እንዴት ማስከበር እንዳለባቸው በኩራት ምንም ያሉት ነገር የለም፡፡

እኒህ ጆን ካሲች የሚባሉት ሰው ማን ናቸው?

ከሬፐብሊካኖች መካከል ብቸኛው እብድ ናቸው፡፡ (ሌሎቹ አጭዎች ጨርቃቸዉን ጥለው ሄደዋል ማለት ነው ።)

ካሲች የአዕምሮ በሽተኛ የሆኑትን ወደ እስር ቤት ወስጀ ከማጎር ይልቅ ወደ አዕምሮ ሕክምና በመሄድ እንዲታከሙ አደርጋለሁ፡፡

ምን ዓይነት ቀውስ ሀሳብ ነው?

በእስር ቤቶቻችን 80 በመቶ ያህሉን የሚሸፍኑትን የአደንዛዥ ዕጽ ሱሰኞችን በእስር ቤቶች ውስጥ ሆነው ሲማቅቁ ከሚኖሩ ይልቅ ከዚህ መጥፎ ደዌ እንዲያገግሙ አደርጋለሁ፡፡

(ካሲች ጤና የላቸዉም አንዴ?)

ከዚህም በተጨማሪ እንዲህ ብለው ነበር፣ “የምጣኔ ሀብት ዕድገት የሁሉም ነገር ቁልፍ ነው፡፡“ እና በጨለማ ውስጥ የሚኖሩ ወገኖቻችን እና ፍትሀዊ በሆነ መልኩ የሀብት ክፍፍሉ ተጠቃሚ አይደለንም ብለው ከሚያስቡት ህዝቦች ጋ መድረስ መቻል አለብን፡፡ እንደዚሁም በአናሳው ማህበረሰባችን ውስጥ ያሉትን፣ ለመንቀሳቀስ እና ለመሻሻል ምንም ዓይነት ዕድል የለንም ብለው የሚያስቡ የህብረተሰብ ክፍሎችን ያካትታል፡፡

ካሲች እጅግ በጣም መሳጭ የሆኑ እና የተጋነኑ ንግግሮች አድርገዋልን?

ካሲች በሬፐሊካኖች ውስጥ ከሌሉ አብዛኛውን ጊዚያቸውን የሚያሳልፉት በየትኛው ፕላኔት ላይ ሆነው ነው?

በሚሊዮን ዶላሮች የሚቆጠሩትን የኮችን ቸኮች ሀብታሞች (ብር ) የሚያገኛቸው ማን ነው?

ስለገንዘብ እና ስለኃይል እንዲሁም ስለኃይል እና ገንዘብ በሚወራበት ጊዜ ጂሚ ካርተር ባለፈው ሳምንት እንዲህ ብለው ነበር፣ “አሜሪካ በፖለቲካ ስርዓት ታላቅ ሀገር እንዳትሆን ውስጣዊ ይዘቷን ይቃረናል፡፡ በአሁኑ ጊዜ በሀገሪቱ ውስጥ ለፕሬዚዳንትነት ዕጩ ሆኖ ለመቅረብ ወይም ደግሞ ፕሬዚዳንት ለመምረጥ ማቋረጫ በሌለው የፖለቲካ ሙስናን በማራመድ በጥቂት ግለሰቦች የምትገዛ ሆናለች፡፡“

በፖለቲካ በዴሞክራሲ እና በጥቂቶች የአገዛዝ ስርዓት/Oligarchy መካከል ያለው ልዩነት ዴሞክራሲ ነጻ እና ደሀዎቹ ህዝቦች ከፍተኛ የሆነውን የህዝብ ቁጥር የሚይዙ እና የሚገዙም እነዚህ ህዝቦች ሲሆኑ ኦሊጋርኪ ደግሞ ሀብታሞች እና የተሻለ ሆነው የሚወለዱት እና በቁጥርም በጣም ጥቂት የሆኑት የህበረተሰብ ክፍሎች የሚገዙበት ሁኔታ ነው በማለት አርስቶትል ግልጽ አድርገዋል፡፡

ሆኖም ግን በዴሞክሬዚ/የእብደት ዴሞክራሲ (የእብዶች)  እና በዴሞክራሲ መካከል ያለው ልዩነትስ ምንድን ነው?

በአሁኑ ጊዜ የአሜሪካ ሬፐብሊክ ከተመሰረተ ከ228 ዓመታት በኋላ የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት በነበሩት ሰው የተመሰከረለት ኦሊጋርኪ፣ በዚህ መነሻነት ደግሞ ዴሞክሬዚ፣ ዴሞክሪሲ (የአስመሳይነት አገዛዝ) ወይስ ደግሞ ዴሞክራሲ ነው ያለን?

እ.ኤ.አ ነሐሴ 6/2015 ምንድን ነው የታዘብነው?

የተዛባ? የተመሰቃቀለ የመድረክ ላይ ተውኔት?

እውነተኛ የቴሌቪዥን እይታ? 

ይህ የመድረክ ላይ ትወና የክርክር ድርጊት “የልቦች ንጉስ/King of Hearts” በሚል ርዕስ ተዘጋጅቶ ለህዝብ ዕይታ ቀርቦ የነበረውን የፈረንሳይ አስቂኝ የመድረክ ላይ ተውኔት አስታወሰኝ፡፡

በዚያ ተውኔት ላይ ስርዓት እብዶች ከእብዶች ሆስፒታል አምለተው ከተማዋን ይይዛሉ ፡፡ (አይዟችሁ አትጫነቁ ኋይት ሀውስን እስከ አሁን ድረስ አልተቆጣጠሯትም፡፡)

ሆኖም ግን እንዲህ የሚል ጥያቄ ይመጣብኛል፡ ማን ነው የበለጠ አጥፊው ? የእራሳቸው የተሟላ ስብዕና ሳይኖራቸው ሌሎችን በመምሰል የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ለመሆን ሲያሽቃብጡ የሚውሉት የስርዓተ አልበኞች ስብስብ ወይስ ደግሞ እነዚህ የወሮበላ ስብስቦች እንዳሻቸው ሲፈነጩ በአንክሮ እየተመለከቱ በእነዚህ ስብዕና የለሽ ስብስቦች እና ኃላፊነት በማይሰማቸው ወሮበሎች ላይ ምንም ዓይነት እርምጃ በማይወስዱት ላይ ነው?

በ21ኛው ክፍለ ዘመን ሁለተኛው አስርት ዓመት የነጻዋ ዓለም መሪ ለመሆን ሌት ከቀን ሲፍጨረጨሩ የሚውሉ እና የሚያድሩ ኃላፊነት የማይሰማቸው የደናቁርት ስብስብ እና እነዚህን ዕኩይ ስብስቦች ዝም ብለው በሚመለከቱ እና ምንም ዓይነት እርምጃ የማይወስዱ ደንታ ቢስ ስብስቦችን እየተመለከትን ነው፡፡

በክርክሩ ላይ አሸናፊ ሆኖ የሚወጣው የፎክስ ዜና ነው (የማስመሰል ዜና አላልኩም፡፡)

መጌ ኬሊ እንደ ምላጭ የሰሉ ነበሩ፡፡ በኃይለኛው እና አስደናቂ በሆነው ችሎታቸው ትሩምፕን አሸንፈዋቸዋል፡፡

ክሪስ ዋላስ እና በሪት ባዬር ኃላፊነት የማይሰማውን ፕሬዚዳንቶች እግሮች በመያዝ ወደ እሳት ጨምረዋቸዋል፡፡ ለሰሩት ስራ አድናቆት ይገባቸዋል!

ወደፊት የእጩ ፕሬዚዳንታዊ ክርክሮች እነዚህ ኃላፊነት በማይሰማቸው ዕጩ ወሮበሎች ዓይነት የሚካሄዱ ከሆነ በመጨረሻ 4ኛው መንግስት ህዝቡን/ሬፐብሊኩን (ሬፐብሊካንን አላልኩም) ያድናል፡፡

የባልቲሞር ሸማቂው ኤች.ኤል ሜንከን እንዲህ ብለው ነበር፣ “ማንም ቢሆን የአሜሪካንን ህዝብ የግንዛቤ ክህሎትን ተምኖ የከሰረ ሰው የለም “ ብለው አሹፈው ነበር።

በእርግጥ መንከን ሂል እና ቢል በኋይት ሀውስ ከ8 ዓመታት ቆይታ በኋላ የኖሩትን ዓይነት ሁኔታ ለማየት አይፈልጉም፡፡

(ቴድ ክሩዝ ምን ማድረግ እንደሚሻል በተጠናና እና በጥንቃቄ ይሄዱበታል፡፡)

ከዚህም በተጨማሪ መንከን እንዲህ ብለው ነበር፣ “በአሁኑ ጊዜ ያለው የተለመደው ሕግ አውጭ (ፖለቲከኛ) በአጠቃላይ መርህን የማይከተል መርህ አልባ ሆኗል፡፡ በጣም አስፈሪ እና የማጭበርበር የቁማር ጨዋታን የሚጫወት ሆኖ ይገኛል፡፡ ትክክለኛው ጫና በሚደረግበት ጊዜ አንድ ሰው ለብዙ ሚስቶች እና ባሎች፣ ስለ ፕላኔቶች እና ስለ ሰው ልጅ ባህሪ ወይም ደግሞ ስለቡዳነት ማቀንቀን ይጀምራል፡፡“

በእርግጥ ጆን ካሲችን እወዳቸዋለሁ፡፡ ምናልባትም የሬፐብሊካን ቡዳነትን በማቆም  ሬፐብሊካን ፓርቲን ሊታደጉት ይችላሉ፡፡

ብዙ ትርጉም ያለው ነገር ይሰራሉ፡፡ በሁለት የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል ስለሚካሄዱ አፈጻጸሞች ጠንካራ የሆነ ታሪክ አላቸው፡፡

በእርሳቸው ላይ ነጻ የሆነ እና ጭቆናን የማያስተናግድ ባህሪ ይታባቸዋል፡፡ እንደዚህ ያለውን ባህሪ እወደዋለሁ!

ካሲች የሬፐብሊካን ዕጩ ሆነው የሚቀርቡ ከሆነ ስለሂላሪ ገንዘብ እንደሚናገሩ እገምታለሁ፣ እናም ትሩምፕ ለቻይናዎች እንደሚያደርጉት ሁሉ እንዲያደርጉ ይነግሯቸዋል፡፡

የኦሂኦን ግዛት ህዝብ ድምጽ ሳያገኝ ማንም የሬፐብሊካን ዕጩ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሊሆን አይችልም ይላሉ፡፡ ጆን ካሲች የኦሂኦ ግዛት አስተዳዳሪ ናቸው፡፡ እ.ኤ.አ በ2014 ካሲች የ64 በመቶ የድምጽ ውጤት በማግኘት እንደገና ለሁለተኛ ጊዜ በዝረራ አሸንፈዋል፡፡ ሬፐብሊካኖች ለማሸነፍ ከፈለጉ ሊሰራ የሚችል የሂሳብ ስሌት አለ፡፡

በነገራችን ላይ ጓደኛዬን ጆን ኸንትስማንን በቅርብ ጊዜ ውስጥ ያዬ ሰው አለ? ለፕሬዚዳንትነት ወንበሩ ለምንድን ነው የአሜሪካ ምርጦች እና ባለ ብሩህ አዕምሮዎች የማይወዳደሩት? (መንከን የአሜሪካንን ህዝቦች የግንዛቤ ክህሎት ማሳነስ በሚመለከት ምንድን ነበር ያሉት?)

የለንደን የልብ ወለድ መጽሐፍት ደራሲ እና የሕግ ባለሙያ በሆኑት በአዛውንቱ በሩምፖል ባይለይ ሀሳብ ላይ እምነት አለኝ፡፡

በአንድ ታሪካዊ ሂደት ላይ ሊከሰቱ የሚችሉ ነባራዊ ሁኔታዎችን ከግንዛቤ በማስገባት ሩምፖል እንዲህ በማለት ግልጽ አድርገው ነበር፡ “ለውጥ እና መበስበስን በሁሉም አቅጣጫ እየተመለከትኩ ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ ያሉት ጌቶቻችን አንዳንድ ደህና ሆነው በተሻሻለ መንገድ ሊሰሩ የሚችሉ ነገሮችን በሚያዩበት ጊዜ ተግባራዊ እንዳይሆኑ ከፍተኛ የሆነ ተቃውሟቸውን በማሳየት ተግባራዊ እንዳይደረጉ መሰናክል ይፈጥራሉ፣ ሊሰሩ የታቀዱ ነገሮችም ካሉ ቀዳድደው እና በጣጣሰው ይጥላሉ፣ እናም ሌላ መጥፎ የሆነን ነገር ይገነባሉ፡፡“

ጆርጅ ዋሺንግተን፣ ጀምስ ማዲሰን፣ አሌክሳንደር ሀሚልተን፣ ኤልብሪጅ ጌሪ፣ ሩፉስ ኪንግ፣ ጆርጅ ማሰን፣ ገቨርነር ሞሪስ፣ ጀምስ ዊልሰን…ቶማስ ጀፈርሰን ሁላችሁም በመቃብሮቻችሁ ውስጥ ተገለባበጡ፡፡

አቤ ሊንከን በመቃብርዎ ውስጥ ይገላበጡ!

ማርቲን ሉተርኪንግ በመቃብርዎ ወስጥ ይገላበጡ!

ከኋይት ሀውስ በር ጋ ያበዱ ሬፐብሊካኖች ቆመዋል !

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!

ነሐሴ 4 ቀን 2007 .