የዓለም ባንክ እና የኢትዮጵያ “የዕድገት እና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የቁማር ጨዋታ”

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ

የዓለም ባንክ ይዋሻል፣ ኢትዮጵያ እጅግ በጣም አስቸጋሪ በሆነ እና “ጥላቻን፣ ንቀትን ወይም ደግሞ መከፋትን በሚቀሰቅስ ዕዳ” ውስጥ በመዘፈቅ በመሞት ላይ ትገኛለች…

እ.ኤ.አ በ2010 የተዘጋጀው እና የዕድገት እና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ እየተባለ ስለሚጠራው ሙያዊ ክሎት እና እውቀት ያልተንጸባረቀበት የዕቅድ ሳይሆን የምኞት እናThe World Bank and Ethiopia’s “Growth and Transformation” የቅዠት ሰነድ ባለፈው ሳምንት የዓለም ባንክ እስከሚያስታውሰኝ ድረስ ስለመኖሩም ፍጹም በሆነ መልኩ ረስቸው ነበር፡፡ ያ ዕቅድ አሁን በህይወት የሌለው የመለስ ዜናዊ ታማኝነት የጎደለው እና ሸፍጥ የታጨቀበት የኢትዮጵያ የይስሙላ የኢኮኖሚ ዕድገት የቅጥፈት ሰነድ ነው፡፡ እ.ኤ.አ በ2010 መለስ ይህንን የውሸት እና ህዝቡን ለማታለል በጠራ የባለሙያ የክህሎት እና ዕውቀት ዕቅድ ሳይሆን አድርጉ የተባሉትን ብቻ የሚፈጽሙ እንጅ ስለኢኮኖሚ ባህሪያት ካለው ዓለም አቀፋዊ፣ አህጉራዊ እና ሀገራዊ ነባራዊ ሁኔታዎች ጋር አገናዝበው ማዘጋጀት በማይችሉ የድሁር አስተሳሰብ በተጠናወታቸው እና አቅም በሌላቸው ተራ ካድሬዎች አማካይነት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት [2010 – 2015] በየዓመቱ በአማካይ በ14.9 በመቶ ያድጋል የሚል በቅጥፈት የተሞላ ባዶ የዕቅድ ሰነድ እንዲዘጋጅ አደረገ፡፡ መለስ ስለእኛ ያለው የክህሎት ዕውቀት የማጣታችን ንቀቱ እኛ በእርሱ የተራ የአጭበርባሪነት ድንቁርና ላይ ያለን ንቀት ብቻ ነበር የሚበልጠው፡፡ የእርሱ ሁልጊዜ የተጠናወተው አባዜ “የኢትዮጵያን ህዝብ ክህሎት፣ ዕውቀት እና የነገሮችን አካሄድ ከሁሉም አቅጣጫ በመመልከት ማገናዘብ የማይችል ነው የሚለውን የንቀት መንፈስ ከእርሱ ሌላ እስከ አሁን ድረስ በማንም የማይደረግ እንደሆነ እና እርሱ ግን የማያውቅ ተራ የሽፍጥ መሀንዲስ ክፋትን ሲፈለፍል የሚያድር መሆኑን ረስቶ እራሱን እንደ አዋቂ አድርጎ ያላዋቂ የድንቁርና ንቀቱን በህዝብ ላይ ሲያቀርብ ነበር፡፡”

ባለፈው ሳምንት የዓለም ባንክ “የኢትዮጵያ ሀብት ለዕድገት እና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ አስተዋጽኦ ሊያደርግ ይችላልን?“ በሚል ርዕስ አንድ ትረካዊ እና ታሪካዊ ጽሁፍ አቅርቦ ነበር፡፡ በዚያ ጽሁፍ ላይ የዓለም ባንክ እንዲህ የሚል መልዕክት አስፍሮ ይገኛል፣ “ባለፉት አስርት ዓመታት ኢትዮጵያ በአማካይ በ10.7 በመቶ የኢኮኖሚ ዕድገት በማስመዝገብ ከሰሀራ በታች ካሉ ሀገሮች አማካይ ዓመታዊ የኢኮኖሚ ዕድገት 5.2 በመቶ ካስመዘገቡት ከሁለት እጥፍ በላይ አስመዝግባለች“ በማለት አይናችሁን ጨፍኑ ላሞኛችሁ በሚል የንቀት መንፈስ በተጨባጭ በመሬት ላይ የሌለ የሀሰት ዘገባ አሰራጭቷል፡፡ የዓለም ባንክ በእኛ በኢትዮጵያውያን/ት እውቀት እና ክህሎት ላይ ያለው ድንቁርና የተሞላበት ንቀት በተመሳሳይ መልኩ በህዝብ ላይ የድንቁርና ንቀት በማራመድ ላይ የነበረው መለስ በኢትዮጵያውያን/ት ላይ ያደርገው የነበረው ንቀት ብቻ ይበልጠዋል፡፡

እንደዚሁም ደግሞ የዓለም ባንክ ከኢትዮያ የምጣኔ ሀብት ዕድገት ጋር በተያያዘ መልኩ እያራመደ ካለው የቅጥፈት ማደናገሪያ ሌላ ተመሳሳይ በሆነ በሆነ መልኩ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ እ.ኤ.አ መስከረም 25/2014 እንዲህ የሚል አራምባ እና ቆቦ የሆነ ባዶ ዲስኩር አሰምተው ነበር፣ “በኢትዮጵያ እየሆነ ካለው እውነታ አንጻር ሲታይ በዓለም ላይ ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት በማስመዝገብ ላይ ካለችው ከኢትዮጵያ የተሻለ ምሳሌ የሚሆን የለም፡፡“ እውነት ኦባማ የይስሙላ አስመሳይነት ምስጋና በመጫወት ላይ ነበሩን?

ባለፈው ሳምንት “የዓለም ባንክ የሞራል ኪሳራ በኢትዮጵያ“ በሚል ርዕስ ትችት አቅርቤ ነበር፡፡ ከሁለት ሳምንታት በፊት የዓለም ባንክ የምርመራ ቡድን/Inspection Panel (እ.ኤ.አ ህዳር 2014 ለባንኩ ዋና ኃላፊዎች ተብሎ ውሱን ዘገባዎች እንዲሰራጩ ተዘጋጅቶ የነበረ ሰነድ) መሰረታዊ አገልግሎቶች ጥበቃ ፕሮጀክት 3 (መአጥፕ 3) እየተባለ በሚጠራው በምዕራብ ኢትዮጵያ የአኟክ ማህብረሰብ የመንደር ምስረታ ፕሮግራም ስላሰገኘው ፋይዳ ጥናት ለማድረግ የተዘጋጀው መርማሪ ቡድን ዘገባ በሚስጥር በድረ ገጽ እንዲለቀቅ ሆኖ ነበር፡፡ የመርማሪ ቡድኑ ዘገባ በምዕራብ ኢትዮጵያ ጋምቤላ እየተባለ በሚጠራው ክልል የዓለም ባንክ ቢሮክራቶች ዜጎችን ከሰፈሩበት ቦታ ያለፈቃዳቸው በግዴታ ወደ ሌላ ቦታ በማዛወር፣ የአካባቢው ዜጎች በቋሚነት ባህላቸውን አዳብረው ከሚኖሩበት ቦታቸው በግዳጅ በማፈናቀል መሰረታዊ አገልግሎቶች ጥበቃ ፕሮጀክት 3ን (መአጥፕ 3) ተግባራዊ በማድረግ ሰበብ “የማታለል ጨዋታ” በመጫወት ላይ መሆኑን ግልጽ አድርጌ ነበር፡፡ (እንደ አጋጣሚ በአንድ ላይ እንዲቀርቡም ታስቦ ሊሆን በሚችል መልኩ ታቅዶበት ይሁን አይሁን የሚታወቅ ነገር የለም) እኔ ያንን “የዓለም ባንክ የሞራል ኪሳራ በኢትዮጵያ“ የሚለውን ትችቴን ለህዝብ ይፋ ለማድረግ በድረ ገጽ እንዲለቀቅ ባደረግሁበት ዕለት የዓለም ባንክ “የኢትዮጵያ ዕድገት እና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ” የሚለው ትረካዊ የቅጥፈት ዘገባም እንዲለቀቅ ተደረገ፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ባለፈው ሳምንት “የኢትዮጵያ የድህነት ዳሰሳ“ በሚል ርዕስ የዓለም ባንክ ያዘጋጀውን እና እ.ኤ.አ ጥር 20/2015 በድረ ገጽ የለቀቀውን ዘገባ አንብቢያለሁ፡፡ የዳሰሳ ጥናቱ እንዲህ የሚል ዘገባ አቅርቧል፣ “ድህነት በኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2000 ከነበረበት 44 በመቶ እ.ኤ.አ በ2011 ወደ 30 በመቶ በመውረድ በድህነት ከሚኖሩ ህዝቦች መካከል በ33 በመቶ ቅነሳ አሳይቷል፡፡ ይህ የድህነት ማሽቆልቆል ከፍተኛ በሆነ እና ቀጣይነት ባለው የኢኮኖሚ ዕድገት አማካይነት የመጣ ነው፡፡“ (ምናልባትም እነዚህ ዓይን አውጣዎች በዚህ ዓይነት የቅጥፈት አካሄድ እና ስሌት ድህነት እ.ኤ.አ በ2012 እና በ2015 ባሉት ዓመታት ውስጥ ከ30 በመቶ ወደ ዜሮ በመቶ ይወርዳል ሳይሉን አይቀሩም፣ ምክንያቱም በአሁኑ ጊዜ 2015 መግባቱን በውል አያጤኑትምና፡፡) አበው ሲተርቱ አይነጋም መስሏት… በቋት እንዳሉት!

እንደዚህ ያለውን በሸፍጥ የተሞላ ሰነድ ማንበብ ምን ዓይነት ጊዜን የማባከን የማጥፋት ስራ ነው! (ከዚህ ይልቅ “ኢትዮጵያ የዓለም መፋረጃ“ (በእራሴ የተተረጎመ) የሚለውን በበሳል ችሎታ እና ዕውቀት በኑብረ ዕድ ኤርሚያስ ከበደ ወልደየስ የተዘጋጀውን ትችት በማንበብ ጊዜየን ብጠቀምበት የተሻለ ነበረ፡፡

የአፖሎ 13 የህዋ ምርምር የጥናት ቡድን ተልዕኮውን በማሳካት ሂደት ላይ በነበረበት ጊዜ እየከሰተ የነበረውን ቀውስ ለመግለጽ በማሰብ እንዲህ የሚል መልዕክት አስተላልፎ ነበር፣ “ሀውስተን ከተማ እባክሽን በችግር ተተብትበንልሻል፡፡“

እኔ ደግሞ እንዲህ እላለሁ፣ “ኢትዮጵያውያን/ት ወገኖቼ እዚህ በችግር ተጠፍንገን እንገኛለን!“ ይህንን ነገር የምናገረው በአሁኑ ጊዜ የዓለም ባንክ እና መሰሎቹ ስለኢትዮጵያ ትክክለኛ የምጣኔ ሀብት ዕድገት እውነትን መናገር ባለመቻል እያሳዩት ያለውን ቀውስ ለመግለጽ ፈልጌ ነው፡፡ ስለኢትዮጵያ የምጠሰኔ ሀብት ዕድገት እና ልማት በእውነት ትክክለኛው መረጃ ወደየት ይገኛል? ኢትዮጵያ ባለፉት አስርት ዓመታት በእርግጥ በየዓመቱ በአማካይ በ10.7 በመቶ ዕድገት ስታስመዘግብ ቆይታለችን? ለእንደዚህ ዓይነቱ አባባል እና መግለጫስ ማስረጃው ምንድን ነው? መለስ በነበረበት ወቅት ሲደሰኩረው እንደነበረው ሁሉ በሩቁ ሲታሰብ እ.ኤ.አ ከ2010 እስከ 2015 ባሉት ዓመታት ውስጥ ኢትዮጵያ በየዓመቱ በአማካይ የ14.9 በመቶ የምጣኔ ሀብት ዕድገት ልታስመዘግብ ትችላለችን? ያም ሆነ ይህ ለመሆኑ የዓለም ባንክ የተባለው ዓለም አቀፋዊ ቀጣፊ ድርጅት እንደዚህ ያለውን የኢትዮጵያን የምጣኔ ሀብት ዕድገት ገላጭ የሆኑትን አሀዞች የሚያገኘው ከየት ነው?

የዓለም ባንክ እጅግ በጣም አጠራጣሪ እና ሙሉ በሙሉ በቅጥፈት ላይ የተመሰረቱትን እንደዚህ ያሉትን አሀዛች ነጻ እና ገለልተኛ በሆነ መልኩ ሙያዊ ትንተና በማድረግ አዘጋጅቶ የማያቀርብበት ምክንያት ምንድን ነው? የዓለም ባንክ የኢትዮጵያን የምጣኔ ሀብት አግባብነት በሌለው መልኩ እየመዘበረ እና ክህሎት ያልታከለበትን የምጣኔ ሀብት ፖሊሲ በማውጣት የሚያስተዳድረውን አምባገነኑን የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሀት) የወሮበላ ስብስብ ቡድን ጨርሶ የሌለውን የአስተዳደር ብቃት እና ችሎታ እንዳለው አስመስሎ በቅጥፈት ለኢትዮጵያ ህዝብ ለማቅረብ የሚያደርገው የሸፍጥ አካሄድ ነውን? በአንድ ወቅት የረሀብ ሰለባ የነበረችን ምስኪን ሀገር ከድህነት አራንቋ መንጥቆ በማውጣት በአሁኑ ጊዜ ልገሳን እና ብድርን መሰረት ባደረገ መልኩ እነዚህ ለጋሽ እና አበዳሪ ድርጅቶች ባደረጉት ዕውቀት የተሞላበት አካሄድ እና ችሎታ (እውነታውን በማይገልጹ እና ተጻራሪ በሆኑ ቃላት የውሸት ድሪቶቻቸውን እያሽሞነሞኑ) ነው በማለት ለእራሳቸው ክብር እና አድናቆት በመስጠት ለመሞጋገስ ያቀነባበሩት ዕቅድ ነውን? በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ደባ ለመፈጸም የሚያካሂዱት የማጭበርበር የቁማር ጨዋታ ነውን? “በአፍሪካ ዕድገትን ከማስመዝገብ አንጻር ከኢትዮጵያ የተሻለ ምሳሌ ሊገኝ አይችልም” በማለት የቅጥፈትን ቅጥፈት የሚያስታጋቡት ባራክ ኦባማ የእነዚህን ቀጣፊ እና ሀሰተኛ ድርጅቶች ቃል ተማምነው ሊሆን ይችላልን? ወይስ ደግሞ ስለዘንድሮው የኢትዮጵያ ምርጫ የማውቀው ነገር አለ ብለው እንደተናገሩት ሁሉ አሁንም ደግሞ ስለኢትዮጵያ የምጣኔ ሀብት የማውቀው ነገር አለ በማለት ሊያደናግሩ ፈልገው ይሆን?

የዓለም ባንክ እና መሰሎቹ እንደሚያናፍሱት ኢትዮጵያ በአፍሪካ አንጸባራቂ የሆነ የምጣኔ ሀብት ዕድገት በማስመዝገብ ምሳሌ ናት እንደሚሉት ከሆነ “ታዲያ ለምንድን ነው ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ከምድራችን ካሉ ሀገሮች ሁሉ በድህነት አንዲትን የባሰባት ደሀ ሀገር ብቻ በመብለጥ ሁለተኛዋ ደኃ ሀገር ልትሆን የቻለችው? (ለዚህ ምላሽ ሊሆን የሚችል በተመሳሳይ ርዕስ እ.ኤ.አ ሰኔ 2014 ያቀረብኩትን ትችት ማንበብ ተገቢ ይሆናል፡፡)

በዓለም ታሪክ በመጥፎ የፕሮፓጋንዳ ስራው የሚታወቀው ጆሴፍ ጎቤልስ እንዲህ የሚል የሸፍጥ ንግግር አድርጎ ነበር፣ “ታላቅ ውሸት በዋሸህ ቁጥር እናም ይህንኑ ውሸት ደግመህ እና ደጋግመህ በተናገርህ ቁጥር ህዝብ በመጨረሻው ሰዓት እውነት ይመስለው እና ያምንሀል፡፡“ ያ ታላቅ ውሸት በዓለም በታላቁ መሪ በተደጋጋሚ ጊዜ በተነገረ እና ጉልበተኛው የዓለም ባንክ ደግሞ የውሸት ጥሩንባውን በለቀቀ ጊዜ ትንሽም ቢሆን ወደ እውነታነት ሊቃረብ የሚያስችል እንደምታ ሊኖረው ይችላል፡፡ ሆኖም ግን ምንም ዓይነት ታላቅ ውሸት እየተዥጎደጎደ ቢሆንም እንኳ የቅንጣት ፍሬ የምታህል እውነት ሊወጣው አይችልም፡፡ የቱም ዓይነት ስህተት ትክክል ሊሆን አይችልም ምክንያቱም ምንም ያህል ኃይለኞች እና በከፍተኛ ስልጣን ላይ ያሉት ቢናገሩትም ወይም ደግሞ ሰይጣናዊነት ድርጊት በወርቅ ልባስ ተጠቅልሎ ቢቀርብም እንኳ ጥቅሉ ሲፈታ ያ ሰይጣናዊነት ድርጊት ደግ ነገር ሊሆን ከቶውንም አይችልም፡፡ ውሸት በብዙሀኑ ህዝብ ዘንድ ለጊዜውም ቢሆን በተለያዩ ምክንያቶች ተቀባይነት ቢያገኝም እንኳ ምንጊዜም ቢሆን ውሸት ያው ውሸት ነው፡፡ ከእባብ እንቁላል እርግብ አይፈለፈልምና! ወይም ደግሞ ስንክሳሩ የበዛለት እንክርዳድ አንዲት የስንዴ ፍሬን ሊሆን አይችልምና!

በእርግጠኝነት ለመናገር በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ 11 በመቶ ከዚህም በላይ 15 በመቶ ዓመታዊ አማካይ የምጣኔ ሀብት ዕድገት አለ እየተባለ በወያኔ እና በለጋሽ እና አበዳሪ ድርጅቶች የሚደሰኮረውን ባዶ የቅጥፈት ዲስኩር፣ የወረደ እና የበከተ የቅጥፈት ፍብረካ እና የሀሰት የአሀዝ እና የቁጥር የቅጥፈት ጨዋታ የትኛውንም ቢሆን ልቀበል አልችልም፡፡

የዓለም ባንክ እንዴት ያለ የውሸት፣ ያፈጠጠ ቅጥፈት እና አሀዛዊ በሆነ መልኩ እንደ አቡጀዲ የሚቀደድ ዓለም አቀፋዊ የቅጥፈት ቀበኛ ተቋም ነው!

የዓለም ባንክ መቸ ነው “አሀዛዊ የቅጥፈት ድራማውን” ሊያቆም የሚችለው?

ቤንጃሚን ዲስራኤል በአንድ ወቅት እንዲህ የሚል ዘገባ አቅርበው ነበር፣ “ሶስት ዓይነት ውሸቶች አሉ፡ ውሸቶች፣ የነቀዙ ውሸቶች እና አሀዞች፡፡“

አዲስ ቃላትን በማያያዝ (ባለፉት ጊዚያት ሳቀርባቸው በነበሩት ትችቶቸ ላይ እንደማደርገው ሁሉ) አሀዝን በመጠቀም ለመዋሸት፣ ለማሳሳት እና ለማጭበርበር፡ “አሀዛዊ ቅጥፈት” በማለት ለመግለጽ ይቻላል ብዬ ሰይሜዋለሁ፡፡

የዓለም ባንክ በቁጥር ቁማር በመጫወት አሀዛዊ ቅጥፈትን ይፈጽማል፡፡ “ባለፉት አስርት ዓመታት ኢትዮጵያ በአማካይ በ10.7 በመቶ የምጣኔ ሀብት ዕድገት በማስመዝገብ ከሰሀራ በታች ካሉ ሀገሮች አማካይ ዓመታዊ የምጣኔ ሀብት ዕድገት 5.2 በመቶ ካስመዘገቡት ከሁለት እጥፍ በላይ አስመዝግባለች የሚለው ውሸት ብቻ ሳይሆን ዓይን ያወጣ አሀዛዊ ቅጥፈት ነው፡፡“

በዚህ አገላለጽ የዓለም ባንክ በመጠኑም ቢሆን ትንሽ ታማዕኒነት ያለው ይመስላልን? በቅርቡ እራሱ የዓለም ባንክ ያቋቋመው የምርመራ ቡድን በኢትዮጵያ ስላለው የዓለም ባንክ እንቅስቃሴ ትክክለኛ፣ እውነተኛ እና በተጨባጭ መረጃ ላይ የተመሰረተ ዘገባ ሊያቀርብ ይችላልን? የዓለም ባንክ ቀደም ሲል ተበልተው፣ ተቀቅለው እና ተዘጋጅተው የተቀመጡ አሀዞችን በመጠቀም አሀዛዊ ቅጥፈትን ሊፈጽም ይችላልን?

የእራሴን መረጃ እንደሚከተለው ላቅርብ፣

በኢትዮጵያ ያለው የዓለም ባንክ የይስሙላ ተቋም ነው፡፡ ባንኩ በበሰለ መልክ አውጥቶ እና አውርዶ እውነታን ባገናዘበ መልኩ የሚሰራ ሳይሆን በባንክነቱ ብቻ በሚተላለፉ ተራ ውሳኔዎች የሚንቀሳቀስ እርባና ቢስ ባንክ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ያሉ የዓለም ባንክ ባለስልጣኖች ከወያኔ ጋር የቡድናዊ ጥቅም አሳዳጆች እና አገልጋዮች ናቸው፡፡ የባንኩ ስራ አስኪያጆች እና በኢትዮጵያ ያሉ ባለስልጣኖች ምን መስራት እንዳለባቸው በውል የተገነዘቡ አይደሉም፣ ወይም ደግሞ የእነርሱን የባለሙያነት ኃላፊነት በአግባቡ መወጣት ያለባቸው መሆናቸውን አያቁም፣ እንደዚሁም ደግሞ ስራቸውን በታማኝነት የተገነዘቡት እና በአግባቡ ኃላፊነታቸውን መወጠት ያለባቸው መሆናቸውን አያውቁትም፡፡ ይህ የእኔ ድምዳሜ አይደለም! ይልቁንም ይህ ድምዳሜ እ.ኤ.አ ህዳር 21/2014 የባንኩ የምርመራ ቡድን ድምዳሜ ነው፡፡

የዓለም ባንክ የምርመራ ቡድን የምርመራ ስራውን ካጠናቀቀ በኋላ በኢትዮጵያ ባሉ የዓለም ባንክ ስራ አስኪያጆች ላይ ብቃት የለሽ፣ ደንታቢሶች እና በስሜታዊነት ከወንጀለኞች የማዕለዩ ናቸው የሚል ዘገባ አቅርቧል፡፡ የህዝብ የመሰረታዊ አገልግሎቶች ፕሮጀክት 3ን ፕሮግራም በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ በማድረጉ እና በማስተዳደሩ ረገድ ሙያዊ የሆነ ባህሪ የሌላቸው እና የአኟክን ማህበረሰብ እና ፍላጎት ከቁብ የማይቆጥሩ ደንቆሮዎች እና ለባንኩ ዋና ዋና መርሆዎች እና መመሪያዎች የማይገዙ ፈጣጣዎች መሆናቸውን ገልጿል፡፡ ስራ አስኪያጆች የመሰረታዊ አገልግሎቶች ፕሮጀክት 3 በአኟክ ማህበረሰብ ላይ ተግባራዊ ከመደረጉ በፊት ምክንያታዊ እና ሙያዊ በሆኑ ትንበያዎች መሰረት ወደፊት ሊከሰቱ የሚችሉ ጉዳቶችን ነቅሰው ሳያወጡ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ከፍተኛ የሆነ የሰብአዊ መብት ድፍጠጣ እና ጉልህ የሆነ ውርደት እና ቅሌትን ፈጽመዋል፡፡

የባንኩ ስራ አስኪያጆች በብቃት ማጣት እና የመሰረታዊ አገልግሎቶች ፕሮጀክት 3ን በመተግበሩ በኩል ምንም ዓይነት ተገቢ የሆነ ምላሽ መስጠት ወይም ደግሞ ተገቢ የሆኑ እርምጃዎችን ለመውሰድ ወይም በትግበራ ወቅት በሚፈጠሩ ሁኔታዎች ጊዜ መወሰድ ያለባቸውን አንገብጋቢ ሁኔታዎች እልባት ለመስጠት አልቻሉም፡፡ ቀኝ እጆቻቸው ግራ እጆቻቸው የሚሰሯቸውን ስራዎች አያውቁም፡፡ የባንኩን የማህበረሰብ ልማት አገልግሎት ፕሮጀክት (በህብረተሰቡ ማህበራዊ እና የመሰረተ ልማት ግንባታ ላይ ትኩረት በማድረግ የህዝቦችን የኑሮ ሁኔታ ቀጣይነት ባለው ሁኔታ ማሻሻል) እንዲሁም የመሰረታዊ አገልግሎቶች ፕሮጀክት 3ን (በዝቅተኛው የመንግስት አስተዳደራዊ እርከን ላይ የሚገኙትን የአቅም ግንባታ፣ የግልጽነት፣ የተጠያቂነት እና የገንዘብ አስተዳደር ስራዎች ማጠናከር) በማሳለጡ በኩል ምንም ዓይነት የማስተባበር ስራ አልሰሩም፡፡ ከዚህም የተነሳ የአኟክ ህዝቦች ላይ ጉዳት ደርሷል እናም የኑሮ ሁኔታዎቻቸው በእጅጉ ተጎድተዋል፡፡

እ.ኤ.አ መስከረም 12/2012 የመሰረታዊ አገልግሎቶች ፕሮጀክት 3ን ለመተግበር በሚል የዓለም ባንክ 600 ሚሊዮን ዶላር በብድር ሰጥቷል፡፡ የመሰረታዊ አገልግሎቶች ፕሮጀክት 3 መተግበር ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ሶስት የጋራ የምክክር እና የትግበራ ድጋፎች በኢትዮጵያ ባሉ የባንኩ ኃላፊዎች ተደርገዋል፡፡ በሶስቱም የጋራ የምክክር ስብሰባዎች በህብረተሰቡ ላይ በእንዝህላልነት የጉዳት ትንተና ጥናት ቀደም ሲል ሳይካሄድ ወደ ትግበራ የተገባ በመሆኑ በህዝቡ ላይ ስለደረሰው ጉዳት ጉዳይ የዓለም ባንክ ኃላፊዎች አንዲትም ቃል ትንፍሽ አላሉም፣ ጉዳዩ እንዲነሳም አልፈለጉም፡፡ በኢትዮጵያ ያሉ የባንኩ ባለስልጣኖች የባንኩን የኢንቨስትመንት የብድር ፖሊሲ (OP/BP 10.00) (ዝርዝር የሆኑትን እና የተብራሩትን ፖሊሲዎች፣ የአሰራር ስርዓቶች እና በፕሮጀክቱ አፈጻጸም እና የህግ ሂደት ላይ ያሉትን መመሪያዎች) ሆን ብለው እና አስበውበት በከፍተኛ ደረጃ አስፈላጊ እና ወሳኝ የሆኑትን በህዝቦች የኑሮ ሁኔታ ላይ ጉዳት ሊያስከትሉ የሚችሉትን ጉዳዮች ከባንኩ መመሪያ በተጻረረ መልኩ በመዝለል እንዳይተገበሩ አድርገዋል፡፡ በፕሮጀክቱ የአፈጻጸም ሂደት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ያሳድራሉ ብለው የሚያምኑባቸውን መረጃዎች እና እውነታዎች ሁሉ ለመደበቅ እና ሚስጥራዊ ሆነው እንዲቀሩ ለማደርግ የተቻላቸውን ጥረት ሁሉ አድርገዋል፡፡

የመሰረታዊ አገልግሎቶች ፕሮጀክት 3ን በመተግበሩ ረገድ የምርመራ ቡድኑ (ምቡ) ዘገባ ለምሳሌ “ሙስና” እና የመሳሰሉትን የሚሉ ቃላትን ፍጹም በማስወገድ ከዚህ ይልቅ “ሊከሰቱ የሚችሉትን ጉዳቶች ለማካተት በዕቅድ ስራው የመጀመሪያ ጊዜ ብቁ መሆን አለመቻል“ እና የመሰረታዊ አገልግሎቶች ፕሮጀክት 3ን በመተግበሩ ረገድ የዓለም ባንክ ባለስልጣኖች አሳፋሪ የሆነ የስራ ግድየለሽነትን እና ተጠያቂነት የሌለው አሰራር ተንሰራፍቶ መቆየቱ እንዳይታወቅ ስልታዊ በሆነ መልክ ሳይገልጹት አልፈውታል፡፡ የመሰረታዊ አገልግሎቶች ፕሮጀክት 3ን በሚመለከት ሳይካተቱ የቀሩት ጉዳቶች ሙስና፣ ማጭበርበር፣ ስልጣንን የአለአግባብ መጠቀም እና የባንኩን ገንዘብ ማባከን ብቻ ነበሩ፡፡ በእነዚህ አራት ጉዳዮች ላይ ሶስቱ የጋራ የምክክር እና የትግበራ ድጋፍ ስብሰባዎች አንድም ነገር ትንፍሽ ሳይሉ በድብቅ አልፈውታል፡፡ ዉሾን ያነሳ ውሾ ይሁን በሚል የቅጥፈት ስሌት!

የምርመራ ቡድኑ ዘገባ እንደሚያሳየው በኢትዮጵያ የዓለም ባንክ ባለስልጣኖች የባንኩን ገንዘብ ከወያኔ ወኪል ሙስና ለመከላከል ያደረገው አንዳችም ነገር የለም፡፡ (እርማት፡ የዓለም ባንክ በኢትዮጵያ ህዝብ ስም 600 ሚሊዮን ዶላር ለወያኔ አበድሮታል የሚል ግንዛቤ ይወሰድ፡፡) ይህንን አግባብ ያልሆነ የዕዳ ነቀርሳ የኢትዮጵያ የወደፊቱ ትውልዶች እንዲከፍሉት ይጠየቃሉ፡፡ ሆኖም ግን ከህግ አንጻር ቀጣዩ ትውልድ ይህንን ገንዘብ እንዲከፍል ሊገደድ ይችላልን!?! እም!)

በአሁኑ ጊዜ የእራሱን ፕሮጀክት ፍጹም ብቃት እና ሙያዊ ስብዕናን በተላበሰ መልኩ ማቀድ፣ መተግበር እና መከታተል የማይችል እንዲሁም በኢትዮጵያ ህዝብ ስም በብድር የተገኘው ገንዘብ በምን ዓይነት ሁኔታ በስራ ላይ መዋል እንዳለበት የማያውቅ ድሁር ተቋም “ኢትዮጵያ ባለፉት አስርት ዓመታት ጊዜ ውስጥ በአማካይ በየዓመቱ 10.7 በመቶ ዓመታዊ የምጣኔ ሀብት ዕድገት አስመዝግባለች በማለት“ ይነግረናል፡፡ በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ በህዝብ ስም በሚሰጥ የብድር ገንዘብ እና በወገኖቻችን ሰብአዊ መብት ላይ ቁማር የሚጫወት ዓለም አቀፋዊ እምነተቢስ ተቋም ስለኢትዮጵያ የምጣኔ ሀብት ዕድገት ለመናገር የሚያስችል ምንም ዓይነት የሞራል ብቃት የለውም፡፡ በእራሱ የፕሮግራም ትግበራ እና አፈጻጸም የተከሰቱ አሉታዊ የሆኑ መረጃዎችን በሙሉ በሶስቱም የምክክር ጉባኤዎቹ ጊዜ ህዝብ እንዳያውቅና የበከተው እና የነቀዘው የሸፍጥ አሰራሩ እንዳይታወቅ የሚደብቅ ተቋም በአሁኑ ጊዜ ላለፉት አስርት ዓመታት በመላ ሀገሪቱ መጣ ያለውን የኢትዮጵያን የምጣኔ ሀብት ዕድገት አሀዛዊ መረጃዎች እውነታውን እርሱ እራሱ ሳያውቅ የለየለት ቅጥፈቱን ለእኛ ለማሳወቅ እየነገረን ይገኛል!

በኢትዮጵያ ውጤታማ እና ጠቃሚ ያልሆኑ ስራዎችን በማካሄድ የምስክር ወረቀት ያገኘ ምንም ዓይነት አዎንታዊ ለውጥ ለማምጣት የማይችል ድሁር ድርጅት በመንታ ምላሱ “የመሰረታዊ አገልግሎቶች ፕሮጀክት” በሚል የተከበረ እና ቅዱስ የሆነ ርዕስ ተሽሞንሙኖ በባለስልጣን ቢቀርብ የሚያምነው ወይም ደግሞ የሚቀበለው ሰብአዊ ፍጡር ሊኖር ይችላልን?

የዓለም ባንክ “ባለፉት አስርት ዓመታት ኢትዮጵያ በየአማቱ በአማካይ በ10.7 በመቶ የምጣኔ ሀብት ዕድገት በማስመዝገብ ከሰሀራ በታች ካሉ ሀገሮች ዓመታዊ የምጣኔ ሀብት ዕድገት 5.2 በመቶ ካስመዘገቡት ከሁለት እጥፍ በላይ አስመዝግባለች“ ሲል ሌላ ምንም ነገር ሳይሆን ዓይን ያወጣ አሀዛዊ ቅጥፈት ነው፡፡ ይህ ዓይነት በሸፍጥ ላይ የተመሰረተ አሳፋሪ፣ ማጭበርበር የታጨቀበት እና ቅንነት የጎደለውን መግለጫ ለመስጠት ያስቻለውን የፍብረካ፣ በሀሰት የተመረተ እና የተዘጋጀውን መረጃ ለአቅመ ቢሱ ባንክ የሰጠው ሌላ ማንም ሳይሆን የወያኔ የኢትዮጵያ ማዕከላዊ የስታቲስቲክስ ባለስልጣን (ኢስባ) እየተባለ የሚጠራው እምነተቢስ መስሪያ ቤት ነው፡፡

ሌላ ተጨማሪ ማስረጃ ላቅርብ፣

የዓለም ባንክ ኢትዮጵያ ባለፉት አስርት ዓመታት ጊዜ ውስጥ በየዓመቱ በአማካይ 10.7 በመቶ ዓመታዊ የምጣኔ ሀብት እድገት አስመዝግባለች ሲል ይህ አባባል በቂ የሆነ ማስረጃ የሚሰጥ እና ግልጽ በሆነ መልኩ አሀዛዊ ቅጥፈት መስራቱን ያመላክታል፡፡ (የእራሴን አስተያየት ዕቅድ እየተባለ በሚጠራው እ.ኤ.አ ሰኔ 2011 “የመለስ ዜናዊ የውሸት ኢኮኖሚከስ” በሚል ርዕስ እና እንዲሁም እ.ኤ.አ ግንቦት 2011 “የመለስ ዜናዊ የሸፍጥ ኢኮኖሚክስ” በሚል ርዕስ ትችት አዘጋጅቸ ማቅረቤ የሚታወስ ነው፡፡

በመጀመሪያ ደረጃ የምጣኔ ሀብት ዕድገት አሀዙ በዓለም ባንክ እና በሌሎች ለጋሽ እና አበዳሪ ድርጅቶች አሳፋሪ በሆነ መልኩ ገለልተኛ ባልሆኑ መረጃዎች በባንኩ (ወይም በሌላ ነጻ አካላት) ያልተሰበሰቡ ወይም ደግሞ ትንተና ያልተካሄደባቸው ናቸው፡፡ የዓለም ባንክ ስለ “የዕድገት እና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ” አፈጻጸም (ከጥቂት ትንበያዎች በስተቀር) ሁሉም አሀዞችን የመሰብሰብ ስራ መሰረት ያደረገው በውሸት በተሰበሰቡ፣ በተከተፉ፣ በተበጣጠሱ፣ በቀላሉ በተጠበሱ፣ ቅመም የገባባቸው ጨው ሌላ ማጣፈጫ የተጨመረባቸው ወያኔ በበላይነት በሚቆጣጠራቸው የወያኔ የቁጥሮች መፈብረኪያ ኩሽና ውስጥ ነው፡፡

የዕድገት እና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ እየተባለ የሚጠራው ዕቅድም ብቸኛ የወያኔ ቢሮክራሲያዊ ምንጭነት በኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ ባለስልጣን አማካይነት የዕቅዱን አፈጻጸም የቁጥር ጨዋታ በሚመስላቸው መልኩ እየመተሩ ያቀርቡታል፡፡ እንደ ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ዘገባ ከሆነ፣ “የድህነት ቅነሳ ስትራቴጅ ወረቀት የዕድገት እና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ 2010/11 – 2014/15 – ቮልዩም II (ገጽ 3)“ እንዲህ ይላል፣

በዕድገት እና በትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ትግበራ፣ ዓመታዊ የዘርፍ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች የአፈጻም ዘገባ እና የኢትዮጵያ የስታቲስክስ ባለስልጣን ጥናቶች ለምሳሌ ያህልም የቤተሰብ ገቢ እና ፍጆታ ወጭ ጥናት፣ በየአምስት ዓመቱ የሚካሄደው የህዝብ ውልደት እና የጤና ጥናት የመሳሰሉት በስራ ላይ ይውላሉ፡፡ የስታቲስቲከስ ባለስልጣን በሚያዘጋጀው እና በወርሃዊ ዋጋ እና የዋጋ ንረት መጣኔ ዘገባ የገንዘብ እና የኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የማክሮ ኢኮኖሚ ልማት እና የድህነት ቅነሳ ቡድን የሚያዘጋጀው ነው፡፡ የኢትዮጵያ ስታቲስቲከስ ባለስልጣን ብሄራዊ የስታቲስቲክስ ልማት ስትራቴጅ በብሄራዊ የስታቲስቲከ ምክር ቤት አማካይነት ጸድቋል፡፡

ከሁሉም በላይ የሚያስደንቀው ነገር ደግሞ የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ባለስልጣን እየተባለ በሚጠራው መስሪያ ቤት ተቀቅለው የሚወጡትን አሀዛዊ መረጃዎች ትክክለኛነት፣ ተቀባይነት እና አስተማማኝነት እንኳ ለስሙም ቢሆን የዓለም ባንክ በእራሱ ጥረት ለማረጋገጥ ምንም ዓይነት ጥረት ሳያደርግ እንዳለ አግበስብሶ በመዋጥ እንዳለ የመትፋቱ ሁኔታ ነው፡፡ (በእርግጥ አሀዛዊ መረጃዎቹ ለትክክለኛነታቸው ቢረጋገጡ ኖሮ የማስባ አሀዛዊ መረጃዎች ምንም ዓይነት አስተማማኝነት የሌላቸው መሆናቸው ይፋ ይሆን እና ይጋለጥ ነበር፡፡) አንዳንድ ጊዜ የዓለም ባንክ የተጠቀመበትን የአሰራር ስልት እና ዘዴ/methodology ሳይገልጽ ድፍን ባለ መልክ የእራሱን ትንበያ በመስጠት ዘገባ እያዘጋጀ ይፋ የሚያደርግበት ሁኔታ አለ፡፡

እንደ ፖሊሲ እና ተሞክሮ በመውሰድ የዓለም ባንክ የ’ማስባ’ን አሀዛዊ መረጃዎች ጥሬአቸውን እንዳለ እንደትክክለኛ በመውሰድ ኃላፊነት በጎደለው መልኩ እውነተኛ፣ አስተማማኝ እና ትክክለኛ እንደሆኑ አድርጎ ለቀሪው የዓለም ህዝብ በማሰራጨት እውነትን ሳይሆን ውሸትን በማጠናከር ላይ የመሆኑን ጉዳይ ስራዬ ብሎ ተያይዞት ይገኛል፡፡ ሆኖም ግን አጥጋቢ መልሶችን ማግኘት ያለባቸው ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው፡ 1ኛ) እንዴት የህወሀት ቢሮክራቶች እና ታማኝ ሎሌዎቻቸው ትክክለኛ እና አስተማማኝነት ያለው የምጣኔ ሀብት መረጃ ያቀርባሉ ተብሎ ይታመናል? 2ኛ) ምሁራዊ፣ ማህበራዊ እና የስብዕና ክህሎት እና ዕውቀት የሌለው የወያኔ የወሮበላ ቡድን ስብስብ በጣም ጥልቀት ያለው፣ አስተማማኝ እና ቀጣይነት ያለው የነጠረ እና የተጣራ መረጃ የመሰብሰብ እና ለፖሊሲ ማውጣት በግብዓትነት ሊያገለግሉ የሚችሉ ሙያዊ ትንታኔ የሚጠይቁ ስራዎችን ለማከናወን የሚያስችል ሙያዊ ክህሎት/technical know how እና ተቋማዊ ብቃት አለውን? 3ኛ) የምጣኔ ሀብት እና የስነ ህዝብ መረጃዎችን ለመሰብሰብ በሚደረጉ ጥረቶች እና ዝግጅቶች ላይ የወያኔ የወሮበላ ቡድን ስብስብ ፖለቲካዊ ጣልቃገብነት ምን ያህል ነው?

የዓለም ባንክ እ.ኤ.አ ጥር 2015 “የኢትዮጵያ የድህነት ዳሰሳ (p.xxv)“ በሚል ርዕስ ባቀረበው ዘገባ መሰረት በጣም የሚያስደንቅ፣ ወይም ሊታመን በማይችል መልኩ ታላቅ እና ጠቃሚነት ያላቸው መረጃዎች እንደሰበሰበ እና በእነዚህም መረጃዎች በመጠቀም በኢትዮጵያ በድህነት ላይ በከፈተው ዘመቻ ድል የተቀዳጀ መሆኑን ያለምንም ሀፍረት ድንፋታ አሰምቷል፡፡ የቀረው ነገር ቢኖር እንደ ወዳጁ እንደ ወያኔ ድህነትን በኢትዮጵያ ተረት አደርጋለሁ የሚል ቃል ያለመጨመሩ ብቻ ነው፡፡ ባንኩ አቋሙን ጠንከር ባደረገ መልኩ በኢትዮጵያ ላይ ያደረገው ጥናት እና የጥናት ግኝቱም ጠንካራ፣ አስተማማኝ እና ትክክለኛ በሆኑ መረጃዎች ላይ መሰረት ተደርጎ የተዘጋጀ መሆኑን አጽንኦ በመስጠት እንዲህ የሚል ዘገባ አቅርቧል፡

ኢትዮጵያ ለዚህ ጥናት አስፈላጊ የሆኑ የመረጃ እና ጥናቶች ሀብት አላት፡፡ የጥናት ትንታኔው ጭብጥ [በዳሰሳ ጥናቱ ውስጥ] እ.ኤ.አ በ1995/6፣ 1999/2000፣ 2004/5 እና 2010/11 (ከዚህ በኋላ 1996፣ 2000፣ 2005፣ እና 2011 እየተባለ የሚጠራውን) የቤተሰብ ገቢ እና ወጭ ጥናትን በዋናነት ተጠቅሟል፡፡ እንግዲህ ከእነዚህ ተከታታይ ከሆኑ ጥናቶች በመነሳት ነው የሕዝቡ የተጠቃለለ ወጭ እና የድህነት የገንዘብ ትንበያዎች እየተጨለፉ የተወሰዱት፡፡

እንግዲህ መጠየቅ ያለበት ዋናው ጥያቄ እነዚህን እጅግ በጣም የተጋነኑ “የመረጃ እና ጥናት ሀብቶች” እና የቤተሰብ ገቢ እና ወጭ ጥናት መረጃዎች የሚሰበስበው እና የሚያጠናው ኃላፊነት ያለው ሰው ወይም አካል ማን ነው? የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ባለስልጣን! (“የዳሰሳ ጥናቱን“፣ በሠንጠረዥ 1 ስር በተጠቀሱት የግርጌ ማስታዎሻዎች 1.2 – 1.13፣ 2.2፣ 2.3፣ 2.4፣ 3.1 – 3.3፣ 3.8፣ 4.1 – 4.3…5.1ን ይመልከቱ….)፡፡ እንግዲህ ነገሩ ሁሉ ቆሻሻ ማስገባት፣ ቆሻሻ ማስወጣት (garbage in, garbage out) ነው፡፡ ጥራቱ አስተማማኝ ያልሆነ የደለበ የመረጃ ሀብት ታስገባላችሁ እናም ቆሻሻ የጥናት ውጤትን ታወጣላችሁ፡፡ ጥራት የጎደለው የደለበ የመረጃ ሀብት ታወጣላችሁ እናም እርባና የለሽ ቆሻሻ የሆነ የጥናት ውጤት ታመርታላችሁ፡፡ ለዚህም ነው እ.ኤ.አ ጥር 2015 በዓለም ባንክ የተዘጋጀውን የድህነት ቅነሳ ዘገባ ማንበብ ጊዜን ማባከን እና የውሸት ተረት ተረት ጨዋታ የማውራት ያህል ነው በማለት ከላይ ለመጠቆም የፈለግሁት፡፡

የዓለም ባንክ ከዚህም በተጨማሪ ኢትዮጵያ ባለፉት አስርት ዓመታት በተከታታይ በየኣመቱ በአማካይ 10.7 በመቶ የምጣኔ ሀብት ዕድገት አስመዝግባለች ብቻ አይደለም ያለው፣ ሆኖም ግን ከዚህም በበለጠ መልኩ ከሰሀራ በታች ያሉ ሀገሮች ከሚያስመዘግቡት ዓመታዊ አማካይ የምጣኔ ሀብት ዕድገት 5.2 በመቶ ጋር ሲነጻጸር ኢትዮጵያ ከሁለት እጅ በላይ እጥፍ አስመግባለች በማለት የውሸት አድማሱን በከፍተኛ ደረጃ አሳድጓል፡፡ እንደዚህ ያለ ክቡር እና ጀግና የሆኑ ወገኖቻችንን ክብር እና የማወቅ መብት የሚንቅ እና የሚያዋርድ፣ ስብዕናን የሚፈታተን ታላቅ ቅጥፈት መሰረተቢሰ፣ እርባና የለሽእና ክብረቢስ እንዲሁም ስለምጣኔ ሀብታቸው ትክክለኛውን መረጃ የሚናገሩትን ሌሎችን የአፍሪካ ሀገሮች የመናቅ ድፍረት ነው፡፡ እውነታው ሲታይ ግን እውነታውን እና ተጨባጩን ለመናገር የሚፈልጉ ባለሙያዎች እጅግ በጣም በተጋነነ እና ተራ ቅጥፈት በታጨቀበት መልኩ የምጣኔ ሀብት ዕድገት ተመዝግቧል የሚሉትን እንደ ዓለም ባንክ ያሉ ደደብ እና ኃላፊነት የማይሰማቸውን ተራ ስብዕና የለሽ ባለሙያዎች ከረዥም ጊዜ ጀምሮ በሚገባ ያውቋቸዋል፡፡ እ.ኤ.አ ህዳር 1/2007 የኢኮኖሚስት መጽሄት እንዲህ ከሚል መደምደሚያ ላይ ደርሶ ነበር፡

“እውነታው ተበጥሮ እና ተንጠርጥሮ ሲታይ ምንም ያህል የእርዳታ ገንዘብ ቢዥጎደጎድም እንዲሁም ግዙፍ የሆነ የቻይና ብድር ቢጎርፍም የኢትዮጵያ የምጣኔ ሀብት ፈጣን በሚባል መልኩ አላደገም ወይም ደግሞ ለዜጎቹ የሚሆን በቂ የሆነ የስራ ዕድል አልፈጠረም፡፡ በአበባ ፕሮጀክት ትግበራ ምክንያት ተፈጠሩ የሚባሉ የስራ ዕድሎችም ቢሆኑ በየዓመቱ በ2 ሚሊዮን እየጨመረ ከሚመጣው የህዝብ ዕድገት እና በአፍሪካ ፈጣን የህዝብ ዕድገት መጣኔ ከሚያስመዘግቡ ሀገሮች መካከል አንዷ ከመሆኗ አንጻር ሲገመገም እዚህ ግባ የማይባል ጉዳይ ነው… መንግስት እ.ኤ.አ ከ2003-04 ጀምሮ የምጣኔ ሀብቱ በየዓመቱ በአማካይ በ10 በመቶ እያደገ እና እየተመነደገ በመምጣት አንጸባራቂ የሆነ የምጣኔ ሀብት ስኬትን ተጎናጽፊያለሁ ይላል፡፡ ሆኖም ግን እውነተኛው አሀዝ ምናልባትም ከሰብ ሰሀራ በታች ካሉ ሀገሮች የምጣኔ ሀብት ዕድገት አማካይ ዓመታዊ የምጣኔ ሀብት እድገት በጣም ትንሽ ከፍ ሊል በሚችል ሁኔታ ከ5 – 6 በመቶ ሊሆን ይችላል፡፡ እንዲያም ሆኖ ያ በመጠኑም ቢሆን የተሻሻለው የምጣኔ ሀብት የዕድገት መጣኔ ለምሳሌም ያህል ጥቂት በሆነ መልኩ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በሚካሄደው የህንጻ ግንባታ እንቅስቃሴ ምክንያት በምትታይ ዕድገት የምጣኔ ሀብቱን ኩነት በማጋጋል መንግስት በዚህ ዓመት የመፍትሄ እርምጃ ከመውስዱ ቀደም ብሎ የዋጋ ግሽበቱን ወደ 19 በመቶ ከፍ እንዲል አድርጎታል፡፡ ለዚህ የምጣኔ ሀብት መሽመድመድ ዋና ዋና ምክንያቶች ናቸው የሚባሉትን ለይቶ ለማውጣት የሚያስቸግር ጉዳይ አይደለም፡፡ መንግስት እጁን ሙሉ በሙሉ አስገብቶ የሚዋኝበት መንግስት- መር የምጣኔ ሀብት ከመሆኑም በላይ የምጣኔ ሀብቱ እጅግ ከፍተኛ በሆነ መልኩ በውጭ እርዳታ እና ብድር ላይ የተንጠለጠለለ ነው፣ እንደዚሁም ደግሞ ከአፍሪካ በተለየ መልኩ ምንም ዓይነት የግሉ ዘርፍ ተዋንያን ያልሆነበት የምጣኔ ሀብት እንቅስቃሴ ነው የሚታየው፡፡”

እውነታው ገለጥለጥ ተደርጎ ሲታይ በኢትዮጵያ የዓለም ባንክ ስራ አስፈጻሚዎች የህዝብ መሰረታዊ አገልግሎቶች ፕሮጀክት 3 ፕሮግራም ሲተገበር በነበረበት ጊዜ የስራ ኃላፊነታቸውን እና ተግባሮቻቸውን እርግፍ አድርገው በመተው በሙስና ለበከቱ እና ለተዘፈቁ የወረዳ ሙሰኞች አስረክበው እንደቆዩት ሁሉ አሁንም ቢሆን በተመሳሳይ መልኩ ለሀገር ጥቅም ሊውል ለሚችል ፖሊሲ ለመቅረጽ እና ለልማት ለማዋል የሚያስችሉ መረጃዎችን የመሰብሰብ እና ሙያዊ የሆነ ትንታኔ የመስጠት ኃላፊነቱን እና ተጨባጭ የሆኑ ተግባራቱን እርግፍ አድርጎ በመተው እንደ ወረዳዎች ሁሉ በሙስና ለተጨማለቀው የወያኔ ወሮበላ ስብሰብ ቡድን ተቋም ለሆነው ለማዕካለዊ ስታቲስቲከስ ባለስልጣን (ማስባ) አስረክቧል፡፡ ግልጽ በሆነ መንገድ ለማስቀመጥ በኢትዮጵያ ያለውን የምጣኔ ሀብት ዕድገት አሀዛዊ መረጃ የመሰብሰቡ እና የማረጋገጡ ስራ በወያኔ የወሮበላ ስብስብ ቡድን የፖለቲካ መዳፍ ስር ተወሽቆ ለሚገኘው የማዕካላዊ ስታቲስቲክስ ባለስልጣን እየተባለ ለሚጠራው ተላላኪ እና ስብዕና የለሽ ታማዕኒነት የጎደለው ድርጅት ኃላፊነቱ ሙሉ ለሙሉ እስከተተወ ድረስ ሁሉም ነገር ዋጋ ቢስና እና እርባና የለሽ ነው፡፡ በወያኔ የወሮበላ ስብስብ ቡድን እና የእርሱ ጥሩንባ ነፊ በሆኑት በዓለም ባንክ፣ ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት፣ በልማት እርዳታ ቡድን እና በሌሎች ድርጅቶች እና ቡድኖች የሚደረግ የምጣኔ ሀብት ዕድገትን የማረጋገጥ ስራ ሁሉ ዋጋ የለሽ እና ትርጉመ ቢስ ነው!!!

በሁለተኛ ደረጃ ከማስባ አሰራር እና ተግባራት አንጻር ስልታዊ በሆነ መልኩ የምጣኔ ሀብት እና ሌሎች መረጃዎችን በማዛባት የቅጥፈት መረጃዎችን ለሚሰሩ ሆድ አምላኩ እና ህሊናቢስ ሙያተኛ ተብዬዎች በወያኔ ወሮበላ ስብስብ ቡድን አለቆች ማበረታቻና እና ሽልማት እንደሚሰጣቸው ከዚያው ከበከተው ድርጅት ውስጥ ሰራተኛ የሆኑ የመጀመሪያ ደረጃ ዕውቀት ካለው ወይም ካላቸው ወገኖቻችን በቂ የሆነ ማስረጃ አለ፡፡ የማስባ ሰራተኞች የምጣኔ ሀብት ዕድገቱን አሀዛዊ መረጃዎች አጋንኖ ለማቅረብ እና ተስማሚ የሆነ የምጣኔ ሀብት አሀዝ ለመፍጠር እንዲችሉ በማሰብ አሀዞችን በመፈተግ፣ በመፍተል እና በመፐወዝ የተቀቀለ የቅጥፈት የመረጃ ውጤቶችን እንዲያወጡ ይታዘዛሉ፡፡ በባለስልጣኑ መስሪያ ቤት ያሉ ዕውቀት ያላቸው መረጃ ሰጭ/ዎች በማስባ ውስጥ የሚካሄዱትን የተለያዩ ጉዳዮች በመግለጽ ላይ ይገኛሉ፡፡ የመንግስት አሀዛዊ መረጃዎች ሆን ተብለው የተጋነኑ እና ሌሎች ጉዳዮች ለምሳሌ ያህልም የዋጋ ግሽበቱ መኖሩ እየታወቀ በምጣኔ ሀብቱ ዕድገት ላይ የተጋነነ አሀዝ እንዲሰጡ ይጨመቃሉ፡፡ ማስባ የተባለው መስሪያ ቤት መረጃዎችን ለመሰብሰብ፣ ለመተንተን እና ትክክለኛ የሆነ የምጣኔ ሀብት አሀዛዊ መረጃዎችን ለማሰራጨት የሚያስችል ተቋማዊ ብቃት ወይም ደግሞ የቴክኒካል እውቀት እና ብቁ የሆነ የሰው ኃይል የሌለው እምነት የለሽ የውሸት ጎተራ እና ቀጣፊ ድርጅት ነው፡፡ ማስባ መረጃዎችን ለመሰብሰብ፣ ለመለካት እና ለህዝብ ለማቅረብ ጉልህ የሆኑ ጉድለቶች ያሉበት ለመሆኑ ይነገራል፡፡ ለምሳሌም ያህል የምጣኔ ሀብቱን ሁኔታ ለመለካት የሚወሰዱት የናሙና ጥናቶች ምልኡ ያልሆኑ እና ብቃት የሌላቸው ብቻ አይደሉም፣ ሆኖም ግን ከቴክኒካዊ ክህሎት አንጻር ሲገመገሙ አስቂኝ ሆነው ይገኛሉ፡፡

ማስባ አሀዛዊ የሆኑ መረጃዎችን ለመሰብሰብ እና ትንታኔ በመስጠት ዘገባዎችን በማቅረብ ረገድ ዓለም አቀፍ መስፈርቶችን አይከተልም፡፡ መረጃዎችን በመለካት፣ ትንታኔዎችን በማቅረብ እና ለህዝብ ይፋ በማድረጉ በኩል ከፍተኛ የሆነ የፖለቲካ ጣልቃገብነት ይታያል፡፡ በጣም ደካማ እና የብቃት እጥረት የመረጃ አሰባሰብ በመኖሩ ምክንያት ስለግል የምጣኔ ሀብት ዘርፉ የተሟላ መረጃ እጥረት በስፋት ይታያል፡፡ ከዚህም የተነሳ በትክክል በተጨባጭ መዋዕለ ንዋይ እየፈሰሰባቸው ወደ ተግባር የተሸጋገሩትን እና ገና ከወረቀት ስራ ላያ ያሉትን ለይቶ ለማስቀመጥ አይቻልም፡፡

ግብርን ላለመክፈል፣ ደንቦችን ወይም ደግሞ ሌሎችን ማዕቀቦችን ለማስወገድ እና ሆን ብለው ገቢዎችን፣ የምርት ውጤቶችን እና ወጭዎችን በውሸት በማናር ገቢ የሌላቸው ለማስመሰል የሚፈልጉት የግል ዘርፉ እና እንዲሁም አንዳንድ በመንግስት ቁጥጥር ስር ያሉት ድርጅቶች ገቢያቸውን አሳንሰው ያቀርባሉ፡፡

እንደዚሁም ሁሉ ትክክለኛውን የመረጃ ዘገባ በትክክል ለማቅረብ የማይፈልጉ የአካባቢ ባለስልጣኖች እና ቢሮክራቶች ይህንኑ ዕኩይ ምግባር ይፈጽማሉ ምክንያቱም የእነርሱ የስራ አፈጻጸም ግምገማ የሚወሰነው በተጨባጩ እውነታ ላይ ተመስርተው ከፍ ያሉ አሀዞችን በማቅረብ ሳይሆን በቅጥፈት ላይ ተመስርተው በውሸት ያበጡ አሀዞችን ማቅረብ ስለሚገደዱ ነው፡፡ ሁልጊዜ በፖለቲካው ከባቢ አየር ውስጥ ተመራጭነት ያላቸውን እውነታዎች እጅግ በጣም አጋንነው የሚያቀርቡ ሲሆን በፖለቲካው ላይ ስህተት ያለባቸውን እና በወያኔ የወሮበላ ስብሰብ ቡድን ዘንድ አሉታዊ ተጽእኖ ያሳድራሉ ብለው የሚገምቷቸውን እውነታዎች ደግሞ በጣም ዝቅ አድርገው ያቀርባሉ፡፡ የማስባ የሁልጊዜ አባዜ “አህዞቹ ጥሩ መስለው እንዲታዩ ማድረግ ነው፡፡” የዓለም ባንክ እ.ኤ.አ ግንቦት 28/2014 የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ባለስልጣንን (ማስባን) አቅም በአደረጃጀት፣ በሰው ኃይል እና በቅርጽ ከፍ ወዳለ እና ወደ ላቀ ደረጃ በማሸጋገር “አስተማማኝ፣ ተደራሽነት ያለው እና በወቅቱ መረጃዎችን ማግኘት የሚያስችል ብቃትን” በማጎናጸፍ አቅሙን መገንባት በሚል ዓላማ ላይ መሰረት ያደረገ የፕሮጀክት ሰነድ በማጽደቅ 10 ሚሊዮን ዶላር ለመስጠት ቃል ገባ፡፡

እ.ኤ.አ መስከረም 4/2014 ስለበርካታ አሀዛዊ መረጃ አሰባሰብ ዘዴዎች እና አጠቃለይ የአሰራር ሂደቶች ማለትም “ጽሁፍን መሰረት ስላደረጉ ግንኙነቶች“፣ “ስለሁለገብ የመረጃ ቴክኖሎጂ ስርዓት”፣ “ቁልፍ ስለሆኑ የሰው ኃይል የገበያ መረጃ አሰባሰብ እና ትንተናዎች”፣ “ስለስርዓተ ምግብ፣ ውኃ፣ ንጽህና እና የጤና አጠባበቅ ትምህርት መረጃዎችን ለመሰብሰብ እና ትንታኔ በማድረግ ጉዳይ ላይ ተዘዋዋሪ ስልክ እና ሌሎች ትንታኔ የሚያደርጉ ቴክኖሎጂዎች ስለሚያደርጉት አስተዋጽኦ“፣ “15 የአይቢኤም/IBM ባለሙያዎችን ባካተተ ቡድን የመፍትሄ ሀሳቦችን በማዘጋጀት ለኢትዮጵያ መሪዎች“ ገለጻ እና ማብራሪያዎችን ሰጥቷል፡፡

የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ በሚሰጠው በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር ብድር የዘመኑን ቴክኖሎጂ በመጠቀም መረጃዎችን ለመሰብሰብ፣ ለመተንተን እና ለህዝብ ለማሰራጨት ወደ አይቢኤም ኪስ የሚገባው ገንዘብ የሚጠናቀቅበት ወቅት መቸ እንደሆነ በግልጽ የሚታወቅበት መንገድ የለም፡፡

በሶስተኛ ደረጃ ለኢትዮጵያ ሁልጊዜ እርዳታ የሚሰጡት የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት፣ የዓለም ባንክ እና የልማት እርዳታ ቡድን እየተባለ የሚጠራው (በእኔ የእይታ አድማስ የዓለም አቀፍ የድህነት አቃጣሪ ቡድን) 27 የሁለትዮሽ እና በርካታ የብዙህን የልማት ወኪል ሀገሮች በማስባ የሚሰበሰቡትን የምጣኔ ሀብት መረጃዎች ሁሉ ሁልጊዜ ዋጋ ቢስ እና እርባናየለሽ መሆናቸውን አሳምረው ያውቃሉ፣፡፡ ሆኖም ግን ታማኝነት በጎደለው መልኩ ሲጠቀሙበት መቆየታቸውን ቀጥለውበታል፡፡ ለምሳሌም ያህል “የሀምሌ 2008 ሀገራዊ ዘገባ (ኢትዮጵያ) ቁጥር 08/264” የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት እንዲህ የሚል መግለጫ ሰጥቶ ነበር፡ “እ.ኤ.አ ከ2003/04 ጀምሮ የምጣኔ ሀብት ዕድገቱ በአማካይ የዓመቱ በ11 በመቶ እያደገ በመምጣት ፈጣን እና ቀጣይነት ያለው የልማት ፕሮግራም (ፈቀልፕ)/Program for Accelerated and Sustainable Development (PASDEP) ያስቀመጠውን ዝቅተኛው የምጣኔ ሀብት ዕድገት መጣኔ 7 ከመቶ በእጅጉ በልጦታል፡፡ ይህም ማለት ከምዕተ ዓመቱ የልማት ፕሮግራም/Millennium Development Goal ጋር ከተተነበየው ዕቅድ ጋር የሚጣጣም በመሆኑ የፕሮግራሙ ተግባራዊነት ሙሉ በሙሉ ተፈጻሚነት እንደሚኖረው የሚያጠራጥር አይሆንም፡፡“ በዚያ ሰነድ ላይ ከገጽ 20 – 24 በቀረበው ዘገባ መሰረት 11 በመቶ አማካይ ዓመታዊ የምጣኔ ሀብት ዕድገት ተብሎ የተቀመጠው ነጻ እና ገለልተኛ ከሆነ የመረጃ አሰባሰብ እና ትንታኔ ምንጭ የተገኘ መሆኑን አያመላክትም፡፡ ሆኖም ግን ያው በቅጥፈት ልምዱ የተካነው የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ባለስልጣን እየተባለ የሚጠራው እምነተቢስ ድርጅት የፈበረከው ነው፡፡ በእውነት ኢትዮጵያ ባለፉት አስርት ዓመታት 10.7 በመቶ አማካይ ዓመታዊ የምጣኔ ሀብት ዕድገት አስመዝግባለችን?

በአሁኑ ጊዜ የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ባለስልጣን የመረጃ አወቃቀር፣ የመረጃ አሰባሰብ ስርዓት እና ትንተና መሰረታዊ የሆነ ድክመት እና ከፍተኛ የሆነ የመረጃ ክፍተት አለበት ከተባለ የዓለም ባንክ እ.ኤ.አ ጥር 2015 “የኢትዮጵያ የድህነት ዳሰሳ” በሚል ርዕስ ባዘጋጀው ዘገባው ለ1995/6፣ 1999/2000፣ 2004/5፣ የማስባን መረጃ መሰረት በማድረግ የሰራው ስለሆነ በምን ዓይነት ሁኔታ ነው ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2015 ድህነትን ታጠፋለች ለማለት የደፈረው? በእርግጥ የዓለም ባንክ እንደሚለው ድህነት በኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2000 ከነበረበት ከ44 በመቶ እ.ኤ.አ በ2011 ወደ 30 በመቶ ወርዷልን?

በአራተኛ ደረጃ የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት እ.ኤ.አ ጥቅምት 2013 ባወጣው ዘገባ መሰረት ለማንኛውም ዓላማ ተግባር በወያኔ የወሮበላ ስብስብ ቡድን የተቀቀለ መረጃ ላይ ምንም ዓይነት እምነት እንደሌለው ግልጽ በማድረግ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የማስባን አሀዛዊ መረጃ በግብዓትነት መጠቀሙን እንዳቆመ እና የእራሱን ትንበያ ብቻ በስራ ላይ እንደሚያውል ይፋ አድርጓል፡፡ “በኢትዮጵያ የሀገር ውስጥ ምርት/GDP አሀዛዊ መረጃ ጉልህ የሆኑ ድክመቶች አሉበት… በገንዘቡ ዘርፍ ጤንነት ላይ ጉልህ የሆነ የመረጃ ከፍተት ይታይበታል፣ ለዚህም ዋናው ምክንያት የባንኮቹ የዕዳ እና ሀብት ማመዛዘኛ/Balance sheet ላይ ምርመራ ለማድረግ ዝርዝር የሆኑ የባንኮቹ መረጃዎች አይገኙም፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የፊስካል እና የገቢ እና ወጭ ዕቃዎች እና አገልግሎቶች ሚዛን/Balance of payments አሀዛዊ መረጃዎች መሻሻልን ይጠይቃሉ፡፡ ለምሳሌም ያህል ዝርዝር የሆነ የመንግስት ዘርፍ መረጃዎች ማለትም የመንግስትን የልማት ድርጅቶች ጨምሮ ብዙ ጉድለቶች ያሉባቸው ስለሆኑ ተገቢ የሆነ የመንግስትን የገንዘብ ድርጅቶች ሁኔታ መመርመር አስፈላጊ ጉዳይ ነው፡፡

በመረጃ አሰባሰቡ ወቅት ጉልህ የሆኑ ክፍተቶች እና ጠቃሚ ድክመቶች የሚስተዋሉ ቢሆንም እንኳ የዓለም ባንክ (እና ሌሎች አበዳሪ እና ለጋሽ ድርጅቶች) እ.ኤ.አ ጥር 2015 አሳፋሪ በሆነ መልኩ ኢትዮጵያ ባለፉት አስርት ዓመታት በአማካይ በየዓመቱ 10.7 በመቶ የምጣኔ ሀብት ዕድገት አስመዝግባለች የሚለውን የቅጥፈት ዜማቸውን ቀጥለውበት ይገኛሉ፡፡ ነገሩ ካፈርኩ አይመልሰኝ መሆኑ ነው! ያ መግለጫ እየተሰጠ ያለው መግለጫው ውሸት እና የለየለት ቅጥፈት መሆኑ እየታወቀ ወይም ደግሞ ለጉዳዩ ምንም ዓይነት ትኩረት ካለመስጠት እና ከእውነት እና ከሀቅ ጋር በመጣላት ከግድለሽነት የተነሳ ወይም መግለጫውን ማስተባበል ምን ያደርግልኛል ከሚል እምነተቢስነት የመነጨ ነው፡፡

“የዕድገት እና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ” እየተባለ ስለሚጠራው ዕቅድ እውነታ በእርግጠኝነት ገና ከጥንስሱ ጀምሮ በኢትዮጵያ የዓለም ባንክ ዳይሬክተር ከሆኑት ከኬን ኦሃሺ ሌላ እ.ኤ.አ ሰኔ 8/2011 ማንም እኔ ነኝ ያለ የተናገረ አልነበረም፡፡ ኦሃሺ ይቅርታ በሌለው መልኩ እንዲህ በማለት ነበር እቅጩን የተናገሩ፡

“ኢትዮጵያ ያለባትን የበጀት ጉድለት ለማሟላት በውጭ መዋዕለ ንዋይ ላይ ጥገኛ የመሆኗ እና የአምስት ዓመቱ የኢንቨስትመንት ዕቅድ ቀጣይነት የሌለው የመሆኑ ጉዳይ… በተዓምር የነዳጅ ክምችት ጉድጓድ ካላገኘች እና በዋናነት ያልተጠበቀ ነፋስ አመጣሽ የሆነ ገንዘብ ከሰማይ እንደ መና ካልወረደ በስተቀር በምንም ዓይነት መልኩ ቀጣይነት ያለው መሆኑ አይታየኝም… እንደዚህ ያለውን በኃይል እና በመፈክር የተሞላ እና የውስጥ ችግሩን በጥልቅ ያልተመለከተ ዕቅድ እንዴት ሊያስቀጥሉት እንደሚችሉ የሚታየኝ ነገር የለም፡፡ እንደ ሀገር በቂ የሆነ ጥሪት መቆጠብ እስካልቻልክ ድረስ ምንጊዜም ቢሆን ጥገኛ የምትሆነው በውጭ መዋዕለ ንዋይ ወይም ደግሞ ጤናማ እና ቀጣይነት በሌለው መልኩ በሌላ የመዋዕለ ንዋይ መሰብሰቢያ መንገድ ነው…በእንደዚህ ያለ ወጥመድ ውስጥ ነው ተጠፍንገው/ተይዘው ያሉት…ዕዳ ካለ አደጋ ይኖራል…ይህ የመንግስት-መር ኢንቨስትመንት ዕድገት አንድ ቦታ ላይ ቢቆም ወይም ለጥቂት ጊዜ መንቀሳቀስ ባይችል እና ቢንገራገጭ እነዚህ ሁሉ የብድር ዕዳዎች ይመሰቃቀላሉ…የግል ዘርፉን ባላሳተፈ እና ጠንካራ ሆኖ ባልተስፋፋበት መልኩ የሚመጣ ፈጣን የምጣኔ ሀብት ዕድገት ዘለቄታ እንደማይኖረው እና ይህ ከሆነ እነዚህ በጊዜ ሂደት የሚደረጉ የብድር ዕዳዎች ሁሉ ከቁጥጥር ውጭ ሊሆኑ የሚችሉ መሆናቸው እጅጉን ያሳስባኛል፡፡”

ስለሆነም ኬን ኢሃሺ አንደዚህ ብለው አቅጬን ተናግረዋል!

ወደ የሚቀጥለው ጉዳይ ልዙር:

ኢትዮጵያ እና አምራች ኢንዱስትሪዎች፡ “የኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሀብት ለዕድገት እና ትራንስፎርሜሽን የሚያደርገው አስተዋጽኦ ሊኖር ይችላልን?”

የዓለም ባንክ ስለኢትዮጵያ አምራች ኢንዱስትሪዎች እና ስለ”ዕድገት እና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ” ስለሚለው ጉዳይ ልዙር፡፡

ከላይ በቀረበው ትረካ መሰረት የዓለም ባንክ እንዲህ የሚል መግለጫ ሰጥቶ ነበር፣ “እ.ኤ.አ ጥቅምት 2014 የዓለም ባንክ ቡድን እና የማዕድን ሚኒስቴር በጋራ በመሆን በ2014 በቅርብ ጊዜ ውስጥ እየተወሰዱ ካሉ ዋና ዋና ከሆኑ እርምጃዎች መካከል አንዱ የሆነውን የኢትዮጵያን የአምራች ኢንዱስትሪዎች መድረክን አዘጋጅተዋል፡፡“ የመድረኩ ዋና ዓላማ በአምራች ኢንዱስትሪዎች ዘንድ መልካም ዕድሎችን እና ተግዳሮቶችን በሚመለከት የህዝቡን ግንዛቤ ከፍ ለማድረግ እና እንደዚሁም ደግሞ ቀጣይ ስለሚሆኑበት ሁኔታ ባሏቸው አስተዳደራዊ ተሞክሮዎቻቸው ላይ ልምድን ለመለዋወጥ ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ መድረኩ በማዕድን ሚኒስቴር እና በሌሎች የልማት አጋሮች በጋራ ያዘጋጁትን “የኢትዮጵያን የማዕድን ዘርፍ ስልታዊ የዳሰሳ ጥናት“ ግኝቶች ላይ ለመወያየት ነው፡፡

ከላይ በቀረበው ትረካ መሰረት የዓለም ባንክ እንዲህ የሚል መግለጫ ሰጥቷል፣ “በጥቅምት የቀረበው ትረካ እንዲህ ይላል፣ “የዓለም ባንክ ቡድን ተወዳዳሪ፣ በቀላሉ ሊተነበይ የሚችል እና ኃላፊነትን የተላበሰ ስልት በመንደፍ ተግባራዊ ለማድረግ፣ ስለዘይት፣ የተፈጥሮ ጋዝ እና ስለማዕድን ኢንዱስትሪ የህግ እና ተቋማዊ ማዕቀፍ ለመፍጠር አቅም የመግንባት ስራዎችን ለማሳለጥ እንዲመች በዘገባው ላይ የተሰጡትን የመፍትሄ ሀሳቦች ወደ ተግባር ለመተርጎም በሚደረገው ጥረት ለኢትዮጵያ መንግስት የቴክኒክ እገዛ ያደርጋል ፡፡ ይህ ሁኔታ የኢትዮጵያ መንግስት የዘይት እና የማዕድን ሀብቶች ለሀገሪቱ ጥቅም በሚሰጥ መልኩ በስራ ላይ እንዲውሉ፣ በጣም ውድ የሆኑ ወጭዎችን ወይም ደግሞ በመጨረሻ ደረጃ ላይ አስቸጋሪ የሆነ የፖለቲካ ችግሮችን በመቀነስ የተሻለ ስምምነት ማድረግ እንዲችል ያደርጉታል፡፡

በኢትዮጵያ ስላለው የማዕድን ክርክር አዲስ አይደለሁም፡፡ አብዛኞቹ አንባቢዎቸ ከአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት/ Extractive Industries Transparency Initiative (EITI) እና ጠብየለሽ በጓሮ ከሆኑት ከድርጅቱ ሊቀመንበር ከክላሬ ሾሆርት ጋር እ.ኤ.አ በ2013 ኢትዮጵያ የድርጅቱ አባል በሆነችበት ጊዜ በጣም የተለጠጠውን የግብግብ ክርክር ሊያስታውሱት ይችላሉ፡፡ ማስረጃዎችን መሰረት ያደረጉ ተቃውሞዎችን በወያኔ ላይ በማቅረብ የEITI አባል እንዳትሆን ሽንጤን ገትሬ በመከራከር በርካታ ትችቶችን ሳቀርብ ነበር፡፡

የእኔ ተቃውሞ በመርህ ላይ የተመሰረተ ነበር፡፡ የወያኔ የወሮበላ ስብስብ ቡድን የEITI አባል በመሆን ለመቀላቀል የሚፈልግበት ዋናው ምክንያት በማዕድን ዘርፉ ግልጽነትን እና ተጠያቂነትን ለማምጣት አልነበረም፣ ሆኖም ግን የእርሱን የEITI የአባልነት መብት እንደ ሽፋን በመጠቀም የውጭ መዋዕለ ንዋይ አፍሳሾችን ወደ ዘርፉ ስቦ በማስገባት ለሀገር ልማት የሚያስቡ በመምሰል በሙስና አዘቅት ውስጥ ለመዘፈቅ እንዲችሉ ለማታለል፣ ለማጭበርበር እና እምነትየለሽ በመሆን ለማምታታት እንዲቻል ነበር፡፡ (ፍላጎት ያለው አንባቢ እ.ኤ.አ የካቲት 2014 እንዲህ በሚል ርዕስ ተዘጋጅቶ የቀረበውን ሊያነብ ይችላል፣ “በEITI ጋሻ ጃግሬነት በኢትዮጵያ የማዕድን ሙስናን ህጋዊ ማድረግ/Dignifying Mining Corruption in Ethiopia Through EITI“፣ እንደዚሁም ደግሞ እ.ኤ.አ መጋቢት 9/2014 “በኢትዮጵያ የማዕድን ሙስና፡ ለክላሬ ሾርት የተሰጠ መልስ/Mining Corruption in Ethiopia: A Reply to Clare Short“ በሚል ርዕስ የቀረበውን ትችት እና እ.ኤ.አ መጋቢት 23/2014 “EITI ወይም የክላሬ የሙስና ቡድን/EITI or Clare’s Corruption Club? በሚል የቀረበውን ትችት ማንበብ ይቻላል፡፡”)

እዚህ ጋ ለማሳየት የምፈልገው የኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ ሀብት የዓለም ባንክ የጥናት ግኝት “በኢትዮጵያ ሙስናን መመርመር“ በሚል ርዕስ ካቀረበው ባለ 417 ገጽ ዘገባ አንጻር ለዕድገት እድገት እና ትራንስፎረሜሽን ዕቅድ ያበረከተውን አስተዋጽኦ ነው፡፡ በዚያ ዘገባ ላይ የዓለም ባንክ የኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ ዋና የሙስና መናኸሪሪያ ሆኖ ተገኝቷል፡፡

እ.ኤ.አ ህዳር 2013 “የማዕድን ሙስና በኢትዮጵያ” በሚል ርዕስ ተዘጋጅቶ በነበረው ዘገባዬ የባንኩን ግኝቶች አሳጥሬ ለማቅረብ ሞክሪያለሁ፡፡ ከዚህ አንጻር በኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ ውስጥ ሰባት ዓይነት የሙስና አደጋዎች እንዳሉ ከእነዚህም ውስጥ “ሶስቱ ዋና ዋና የአደጋ አካባቢዎች ፈቃድ በማደስ፣ ፈቃድ ከመስጠት ሁኔታዎች ጋር ከሚደረጉ ስምምነቶች እና ከማዕድን ገቢዎች አንጻር የሚደረጉ ሙስናዎች ናቸው፡፡“ ሌሎች እጅግ በጣም ወሳኝ የሆኑ የሙስና ዓይነቶች የማጭበርበር ድርጊቶች፣ ለአካባቢ ኗሪዎች ከሚሰጡ ካሳዎች እና ግዴታዎች ጋር በተያያዘ መልኩ ኮንትራክተሮች እና አቅራቢዎች ከማዕድን ኩባንያዎች ጋር ከሚያደርጓቸው የኮንትራት ስምምነቶች ጋር የተያያዙ፣ በማዕድን ኩባንያዎች የምርት ጥራት ደረጃን በማሳነስ ትክክለኛ ያልሆኑ የውሸት ምርቶችን ማቅረብ እና የማዕድን ውጤቶችን እና መሳሪያዎችን መዝረፍ የሚሉት ይካተታሉ፡፡

እ.ኤ.ኤ በ2012 በቀረበው “ፈቃድን ከማደስ” ጋር በተያዘ መልኩ ከሚፈጸመው የማዕድን ሙስና ዘገባ አኳያ ባለስልጣኖች በማስገደድ ወይም ደግሞ ስልጣንን አላግባብ በመጠቀም ፈቃድ ላደሱበት ምላሽ የሚሆን፣ እንደዚሁም በአጭር ጊዜ ውስጥ ፈቃዳቸውን ለማደስ ወይም ደግሞ ብዙ የአስቸጋሪነት ሁኔታ ላለባቸው ፈቃዶች ከማዕድን ኩባንያዎች ጉቦ ይቀበላሉ፡፡ ከዚህ ጋር ተመሳሳይነት ያለው ሌላው አደጋ ደግሞ “ባለስልጣኖች ፈቃድ ከሚሰጥባቸው የስራ ዘርፎች ሚስጥራዊ በሆነ መልኩ በድብቅ ከማዕድን ኩባንያዎች የይዞታ መጠን ይይዛሉ፣ የፈቃድ ማመልከቻ ቀርቦበት ከተሰጠ መሬት ላይ የይዞታ ባለቤትነትን ያገኛሉ፣ ከማዕድን ኩባንያዎች ወይም ደግሞ ከሚገኘው ትርፍ የአክሲዮን ድርሻ እንዲኖራቸው ያደርጋሉ፣ እናም ለአመልካቾቹ እና ለተባባሪዎቻቸው ቅድሚያ ፈቃድ ለመስጠት በተመዘገቡበት የጊዜ ሁኔታ በአግባቡ ለማደል ሳይሆን የምዝገባ ሁኔታን ይፐውዛሉ፣ ያጣርሳሉ፡፡ በፈቃድ አሰጣጥ ስምምነት ላይ የማዕድን ኩባንያዎች ሆን ብለው የማዕድን ሁኔታዎችን በመጠቀም የማጭበርበር ስራዎችን ይሰራሉ (ለምሳሌ ያህልም የአካባቢ፣ የጤና፣ እና የደህንነት ቁጥጥሮችን እንዲሁም የማዕድን ቦታውን ሁኔታ) በማየት ያለምንም ተጠያቂነት ለእነርሱ ጉቦ ማጋበሻ በሚስማማ መልኩ በማዘጋጀት ሙስና ይፈጽማሉ፡፡

ገቢን በሚመለከት ደግሞ “የማዕድን ኩባንያዎች ሆን ብለው ምርቶችን እና የሚገኘውን ትርፍ በመቀነስ ዝቅ እንዲል በማድረግ እና ወጭዎችን ደግሞ እንዲንሩ በማድረግ የሚከፈሉትን ክፍያዎች እና የሚጣሉ ግብሮች እንዲቀነሱ ያደርጋሉ፡፡“ ገዥው አካል የማዕድን ኩባንያዎችን ገቢዎች ነጻ በሆነ መልኩ አይቶ የሚያረጋግጥ አካል የለውም፡፡

እንደ ዓለም ባንክ ዘገባ ከሆነ “ክፍያዎችን እና የግብር ግዴታዎችን ለመሰብሰብ በኢትዮጵያ በፌዴራል፣ በክልል፣ እና በከተማ ደረጃ የተቋቋመ ባለስልጣን ስለሌለ ለመንግስት የሚገባው ክፍያ ሁኔታ ሙሉ ለሙሉ በሚባል መልኩ በማዕድን ኩባንያው በእራሱ የግል የምርት ውጤት እና ትርፍ መረጃ መስጠት ላይ ተመስርቶ ነው፡፡ በዚህም መሰረት የማዕድን ኩባንያው ያለውን ሀብት እና የስራ ማስኬጃ ወጭውን በማጋነን ከፍ አድርጎ የሚያቀርብ ሲሆን ምርቶቹን እና ትርፉን ደግሞ በተጻራሪ መልኩ ዝቅ ያለ ግምት በማድረግ ያቀርባል፡፡“ ፈቃድ የማግኘት ስራ እና የማዕድን ገቢን የማጭበርበሩ ሁኔታ በተደረሰበት ጊዜ የማዕድን ኩባንያው በተጫማሪ ምርመራውን ላካሄዱ መርማሪዎች ማጭበርበሩ እንዳይታወቅ ጉቦ ይሰጣሉ፡፡” “ሙስናን በኢትዮጵያ መመርመር“ በሚለው ሰነድ ላይ በቀረበው ዘገባ መሰረት በማዕድን ዘርፉ የሙስና ዝርዝር ልምዶች ጉቦ ከመስጠት፣ የሀሰት ምዝገባን ማካሄድ፣ ከማዕድን ኩባንያዎች በማስፈራራት እና በማዋረድ ገንዘብ መቀበል፣ እና ለአካባቢው ኗሪዎች ተብሎ ከሚያዘው ካሳ ላይ መስረቅ፣ የውስጥ ስራውን በሚያውቁ ሰዎች መረጃዎች እና ለእራሳቸው በማይሰሩ ኩባንያዎች አማካይነት በርካታ የሙስና ተግባራት ይፈጸማሉ፡፡ በዓለም ባንክ ሰነድ ላይ ተመዝግቦ የተቀመጠው እና በምሳሌነቱ አስደንጋጭ የሆነው በወያኔ የወሮበላ ስብስብ ቡድን የተፈጸመው ሙስና እና ዝርፊያ በጣም አስደንጋጭ እና ጭንቅላትን የሚበጠብጡ የሆኑ የሚከተሉት ይካተታሉ፡

አንድ የማዕድን ኩባንያ የማዕድን ፈቃድ ለማግኘት እንዲችል ከፍተኛ የሆነ ክፍያ እንዲሰጥ ይጠበቅበታል፡፡ ከፍተኛ ባለስልጣኖች እና የማዕድን ኩባንያው ይህንን የማይገባ የጉቦ ክፍያ በሚስጥር ይይዙታል፣ እናም ባለስልጣኖቹ ውጭ ሀገር በሚገኙ የባንክ ሂሳቦቻቸው ላይ ገቢ በማስደረግ ይቀበላሉ፡፡

አንድ ባለስልጣን የማዕድን ስራ ፈቃዱ በአስቸኳይ እንዲወጣለት የሚፈልግ ከሆነ ከፍተኛ የሆነ የበጎ አድራጎት የልገሳ ገንዘብ እንዲሰጥ ይጠበቅበታል፡፡ የልገሳው ገንዘብ በመሰረታዊ ሁኔታው ታማኝነት ያለበት ቢመስልም እውነታው ግን አብዛኛው የልገሳ ገንዘብ ለፖለቲካ ፓርቲ ወይም ደግሞ ለባለስልጣኖቹ ለእራሳቸው ወይም ለቤተሰቦቻቸው የሚሰጥ ነው፡፡

የማዕድን ኩባንያው የማዕድን ፈቃድ ለማግኘት የመልካም ስራ ዋስትና፣ የጤና እና የደህንነት ዕቅድ እንዲያቀርብ ሊጠየቅ ይችላል፣ ሆኖም ግን ባለስልጣኑ ለማዕድን ኩባንያው ጉቦ ካልከፈለ በስተቀር በእርሱ ወይም በእርሷ ሌላ ተጨማሪ እና አስፈላጊ ያልሆነ አስቸጋሪ የጤና እና የደህንነት ሁኔታዎችን ይጨምርበታል ፡፡

የማዕድን ኩባንያው የማዕድን ፈቃድ ለማግኘት መርዛማ የሆኑ ኬሚካሎች የአካባቢውን ስነምህዳር የውሀ ሀብት እንዳይበክሉ የሚያስችል የቁጥጥር ዘዴ በበቂ ሁኔታ በማያየዝ የአካባቢ አስተዳደር ዕቅድ እንዲያቀርብ ይጠበቃል፡፡ ትክክለኛ የሆኑ ቁጥጥሮች እጅግ በጣም ውድ ናቸው፡፡ በዚህም መሰረት ይህንን የገንዘብ ጫና ከግምት ውስጥ በማስገባት የማዕድን ኩባንያው ኃላፊነት ያለው የመንግስት ባለስልጣን በቁጥጥር ስርዓቱ ላይ መሸፈን ያልቻሉትን ጉድለቶች በመዝለል ፈቃዱን እንዲያጸድቅለት ከፍተኛ የሆነ ገንዘብ በጉቦነት ይከፍላል፡፡

ባለስልጣኖች ከማዕድን ኩባንያው ትርፍ የአክሲዮን ድርሻ እንዲኖራቸው ሊጠይቄ ይችላሉ፡፡ የማዕድን ኩባንያ ፈቃዱ ጥቅም ሊያስገኝ በሚችል መልኩ የሚሰጥ መሆኑ ከተረጋገጠ የማዕድን ኩባንያው ከማዕድን ኩባንያ ፕሮጀክቱ ዓመታዊ ትርፍ ላይ ለባለስልጣኖች ዘመዶች ትርፍ ሊሰጥ ይችላል፡፡

ባለስልጣኖች በእራሳቸው በሚስጥር ለተያዙ ኩባንያዎች ፈቃድ ሊሰጡ ይችላሉ፡፡ ባላስልጣኖች ሚስጥራዊ በሆነ መልኩ የማዕድን ፈቃድ ማመልከቻን በመመርኮዝ መሬት ሊይዙ ይችላሉ፡፡

አንድ ባለስልጣን በአንድ በተወሰነ የማዕድን ቦታ ላይ የማዕድን ፈቃድ ሊሰጥ ይችላል የሚል ግንዛቤ የሚኖረው ከሆነ የማዕድን ፈቃዱ ከመሰጠቱ በፊት አስቀድሞ የማዕድን ቦታውን ሊያከራየው ይችላል፡፡ የማዕድን ፈቃዱ አንዴ ከተሰጠ በኋላ የመሬቱ ቁሳዊ ዋጋ ይጨምራል፡፡ ባለስልጣኑ ከውስጥ መረጃ ካገኘ በኋላ በሚያገኘው ትርፍ ያለውን የመሬት መብት ለኩባንያው በመሸጥ ወይም ፈቃዱን በማከራየት ትርፍን ያጋብሳል፡፡

ኩባንያዎች የተሰጧቸውን ፈቃዶች ህገወጥ በሆነ መልኩ ሊሸጡ ይችላሉ፡፡

ባለስልጣኖች በፈቃድ ምዝገባ ወቅት ጉቦ ለማግኘት በሚል ርኩስ መንፈስ ምዝገባን የመፐወዝ እና የማጣረስ ተግባራትን ሊያከናውኑ ይችላሉ፡፡

የማዕድን ፈቃድ የሚሰጥ አንድ የመምሪያ ኃላፊ ባለስልጣን የማዕድን ኩባንያ የማዕድን ስራ ፈቃድ ለመውሰድ ሊያመለክት እንደተዘጋጀ ሊያውቅ ይችላል፡፡ ይህ ባለስልጣን የማዕድን ፈቃድ ለመውሰድ ፍላጎት ካለው ሰው ጋር ግንኙነት ያለው ወይም ያላት የቢዝነስ ሰው በመፈለግ በዚያው የማዕድን መሬት ላይ ለማዕድን ስራው ፈቃድ ማውጣት እንዲችሉ እንዲያመለክቱ ያደርጋል፡፡ በዚህም መሰረት ባለስልጣኑ ቢስነስ ለሚያካሂደው እና እንዲያመለክት ላደረገው ሰው የማዕድን ፈቃዱን ይሰጠዋል፡፡ ከዚያ በኋላ የማዕድን ኩባንያው የማዕድን ፈቃዱን ከቢዝነሱ ሰው ጋ እንዲገዛው ያደርጋል፣ እናም የቢዝነሱ ሰው የተገኘውን ትርፍ ከባለስልጣኑ ጋር ይካፈሉታል፡፡

ማዕድን ፈላጊ ማዕድናት ያሉበትን ልዩ አካባቢዎች ፈልጎ ሲያገኝ ምልክት ያስቀምጥ እና የግኝት ሰርቲፊኬቱን ለመቀበል በቀጥታ የማዕድን ፈቃድ የሚሰጠውን የመንግስት ባለስልጣን ሊያገኘው ይችላል፡፡ በሙስና የተዘፈቀው ባለስልጣን ግኝቱን በዚያ ሰው ስም ላይመዘግብለት ይችላል፣ ሆኖም ግን የቢዝነስ ሰው የሆነ ጓደኛ በመፈለግ በጓደኛው ስም እንዲመዘገብ ያደርጋል፡፡ በሙስና የበከተው እና የተጨማለቀው ባለስልጣን ሀሰትን በተላበሰ መልኩ ይህንን የማዕድን ቦታ ቀደም ሲል ሌላ ሰው አግኝቶታል በማለት ከጨዋታ ውጭ ያደርገዋል፡፡

ባለስልጣኖች ሚስጥራዊ በሆነ መልኩ የማዕድን ኩባንያዎች ለዘመዶቻቸው እየቆረሱ ኮንትራት እንዲሰጡ በድብቅ ስምምነት ያደርጋሉ፡፡ ፈቃዱን የሚሰጠው ባለስልጣን ፈቃዱን ለመስጠት ወይም ደግሞ የማህበራዊ ልማት ዕቅድ ግዴታዎችን እንደ ዝቅተኛ መስፈርት በመውሰድ የማዕድን ኩባንያው በእራሱ ወጭ የመሰረተ ልማት ስራዎችን እንዲሰራ የሚጠበቅበት ይሆናል፡፡ ለምሳሌ ያህል የማዕድን ኩባንያው መንገድ፣ ትምህርት ቤት ወይም ደግሞ ሆስፒታል እንዲገነባ ወይም የተሟላ እድሳት እንዲያደርግ ይገደዳል፡፡ ከዚያም የመንግስት ባለስልጣን የማዕድን ኩባንያው አንድ ወይም ከአንድ በላይ የሆኑ የመሰረተ ልማት ፕሮጅክቶች በሚስጥር የባለስልጣኑ የቤተሰብ አባላት ኮንትራክተር ሆነው እንዲሰሩት በሚስጥር ይዋዋላሉ፡፡

ባለስልጣኖች ወይም ደግሞ የማህበረሰብ መሪዎች ወደ አካባቢው ኗሪ የሆኑ ማህበረሰቦች በካሳነት መሄድ የነበረበትን ገንዘብ ሊሰርቁ ይችላሉ፡፡ የማዕድን ኩባንያዎች ለማህበረሰቦች የሚከፈለው ካሳ ከትክክለኛ ግምቱ በታች እንዲሆን ለማድረግ ለባለስልጣኖቸ ጉቦ ይከፍላሉ፡፡

የአካባቢ ኗሪዎች ፈቃድ እንዲወጣበት የተጠየቀን አካባቢ በውሸት እንደያዙት ወይም በዚያ መሬት ላይ የባለቤትነት መብት እንዳላቸው አድርገው ሊያቀርቡ ይችላሉ፡፡

ኮንትራክተሮች እና ምርት እና አገልግሎት አቅራቢዎች በጨረታ ሂደት ስነስርዓት ላይ፣ የባለቤትነት ጥያቄን በማንሳት እና ጉድለት ያለባቸውን ስራዎች በመደበቅ ወይም ትክክለኛ ናቸው ብሎ በማጽደቅ ሙስናን ሊሰሩ ይችላሉ፡፡

የማዕድን ኩባንያዎች ስለማዕድናት ምንነት እና ጥራት የሀሰት መግለጫ በመስጠት ወይም ደግሞ የሀሰት መግለጫዎች እንዲጸድቁላቸው እና ሰርቲፊኬት ማግኘት እንዲችሉ የማጭበርበር ስራዎችን ይፈጽማሉ፡፡ በአሁኑ ጊዜ እንደዚህ ባለ ሙስና ላይ የሚደረገው ምርመራ በሂደት ላይ ይገኛል፡፡

በአሁኑ ጊዜ የዓለም ባንክ እንዲህ ይላል፣ “ለኢትዮጵያ መንግስት ለዘይት፣ ለተፈጥሮ ጋዝ እና ለማዕድን ኢንዱስትሪው ተወዳዳሪነት ያለው፣ በትንበያ ሊደረስበት እና ኃላፊነትን ሊሸከም የሚችል ስልት፣ ህግ እና ተቋማዊ ማዕቀፍ የቴክኒካዊ እገዛ በመስጠት አቅሙን መገንባት አስፈላጊ ጉዳይ ነው፡፡“ እርግጠኛ ነውን? የዓለም ባንክ ሁላችንም ትላንት የተወለድን መሆናችን ትክክል መሆኑን ሊያውቀው ይችላል የሚል እምነት አለኝ፣ ሆኖም ግን ትላንት ማታ አይደለም የተወለድነው፡፡

የወያኔ የወሮበላ ስብስብ ቡድን ከማዕድን ኢንዱስትሪው ገቢ ጋር በተያያዘ መልኩ ለበርካታ ዓመታት ሰይጣናዊ የሆነ የድብብቆሽ ጨዋታ ሲጫወት ቆይቷል፡፡ እ.ኤ.አ ነሐሴ 2013 የመንግስት ታማኝ ምንጮችን በመጥቀስ እንደወጣው ዘገባ ከሆነ በዚያው ዓመት ውስጥ በ11 ወራት ውስጥ ብቻ በባህላዊ የማዕድን ቁፋሮ አምራቾች አማካይነት ወደ ውጭ ተልኮ ግምቱ 419 ሚሊዮን ዶላር የሆነ ገቢ ተገኝቷል፡፡ ወደ ውጭ ከተላኩት ምርቶች ውስጥ የወርቅ ማዕድን 409.1 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ በማስገኘት ከፍተኛውን ድርሻ የያዘ ሲሆን ለጌጣጌጥ የሚያገለግል ድንጋይ እና ታንታለም ደግሞ የተከታዩን ደረጃ በመያዝ እንደየቅደምተከተላቸው 9.3 እና 1.6 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬን አስገኝተዋል፡፡ ይህ ሁሉ ገቢ የተገኘው 7,878.3 ኪ.ግ የሚመዝን የወርቅ፣ 20,126.3 ኪ.ግ የሚመዝን የጌጣጌጥ ድንጋይ እና 32.9 ቶን የሚመዝን የታንታለም የማዕድን ክምችት ወደ ውጭ በመላክ ነው…

ሚድሮክ የተባለው ኩባንያ በከፍተኛ ደረጃ ወርቅ በማምረት ተግባር ላይ የተሰማራ ብቸኛ ኩባንያ ነው፡፡ ሌሎች ዘገባዎች ደግሞ እንዲህ ይላሉ፣ “ወደ ውጭ የሚላኩት የማዕድን ስራ ውጤቶች በጠቅላላው ወደ ውጭ ከሚላከው ሀገራዊ ምርት ውስጥ 23 በመቶ ድርሻን በመያዝ በሀገሪቱ ውስጥ የውጭ ምንዛሬን በማስገኘቱ በኩል የሁለተኛነት ደረጃን ይይዛሉ፡፡”

እውነታው ሲገለጽ ግን የማዕድን ምርቶችን ገቢ ሳጥን የመክፈቻ ቁልፍ ከሚይዙት ከወያኔ የወሮበላ ስብስብ ቡድን አለቆች በስተቀር በጠቅላላው በማዕድኑ ዘርፍ ምን ያህል ገቢ እንደተገኘ በእርግጠኝነት የሚያውቀው የለም፡፡ የወያኔ የወሮበላ ስብስብ ቡድን የማዕድን ዘርፉ ገቢ በእርግጠኝነት ምን ያህል እንደሆነ ገለልተኛ እና ነጻ በሆነ መልኩ ለማረጋገጥ የሚችልበት መንገድ የለውም፡፡ በዚህም መሰረት ኩባንያዎቹ በሚያቀርቧቸው መረጃዎች ላይ ብቻ መሰረት አድርገው የቀረበውን ገቢ ይይዛሉ፡፡ እንዴት ያለ ምቹ ነገር ነው እባካችሁ!

ዋናዎቹ የማዕድን ዘርፉ ገቢ ተጠቃሚዎች ሀብታሞቹ የገዥው መደብ አባላት እና ለገዥዎቹ በግንባር ቆመው የሚያቀብሉ እና የተላላኪነት ድርሻቸውን የሚወስዱ የቢዝነስ ሰዎች እንዲሁም ሌሎች የወያኔ የወሮበላ ስብስብ ቡድን ድርጂቶች ናቸው፡፡ የማዕድን ፈቃድ ለመሸጥ እና የማዕድን ገቢዎችን ህገወጥ በሆነ መልኩ የመቀራመቱን አሳፋሪ ድርጊት እና የሚፈጸመውን የሙስና ጥልቀት እና ስፋት ከወያኔ የወሮበላ ስብስብ ቡድን አለቆች ውጭ ማንም ሊያውቀው አይችልም፡፡ ሆኖም ግን ታማኝ የሆኑ የዓይን እማኞች እንዳረጋገጡት በመቶዎቹ ኪሎዎች የሚቆጠር ወርቅ ከማዕድን ማምረቻው በቅርብ ርቀት ላይ ከሚገኝ የአውሮፕላን ማረፊያ ድረስ እየተወሰደ በአውሮፕላን መዳረሻውን አውሮፓ ባደረገ መልኩ ምንም ዓይነት ምርመራ ሳይደረግበት እየተጫነ እንደሚላክ ታውቋል፡፡

የዓለም ባንክ በዚህ አሳፋሪ በሆነ ትረካው እንዲህ በማለት ግልጽ አድርጓል፣ “ጥሩ በሆነ ሁኔታ ከተያዘ እና ድጋፍ ከተደረገለት የኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ በኢትዮጵያ የምጣኔ ሀብት ልማት እና ዕድገት ላይ ወሳኝ የሆነ አስተዋጽኦ ሊያደርግ እና ለድህነት ቅነሳው ፕሮግራም ጉልህ ድርሻ ሊያበረክት ይችላል፡፡“ በእርግጠኝነት ግን የማዕድን ዘርፉ ቢዘርፉ ቢዘርፉ ለማይሞሉት የወያኔ አለቆች እና አጫፋሪዎቻቸው ኪሶች እና በውጭ ባንክ ሂሳቦቻቸው የሚያጭቁት ገንዘብ በገቢ ቅርምት ተውኔቱ ላይ ትልቅ ልዩነትን ያመጣል፡፡ ለቀሪው የኢትዮጵያ ህዝብ ሁሉም ወርቅ፣ የጌጣጌጥ ድንጋይ ታንታለም፣ ብረት እና ፖታሽ ለቁጥር የሚገባ አይሆንም!

ትክክለኛው የምጣኔ ሀብት ዕድገት በኢትዮጵያ፣

አሁን በህይወት የሌለው መለስ ዜናዊ በአንድ ወቅት ዋሺንግተን ዲሲ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጽ/ቤት በመገኘት የወደፊት ዓላማው ምን እንደሆነ ተጠይቆ ለነበረው ጥያቄ ምላሽ በሰጠበት የመጀመሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ [ከሩብ ምዕተ ዓመት ገደማ በፊት] የወርቅ ክምችቱ ለምጣኔ ሀብት ልማት ዕድገት ይውላል ብሎ ነበር፡፡ ኢትዮጵያውያን/ት በቀን ውስጥ ሶስት ጊዜ የሚመገቡ ከሆነ የእርሱ መንግስት ስኬት በዚያ ይለካል ብሎ ነበር፡፡ እ.ኤ.አ በ2011 እብሪትን በተላበሰ መልኩ እንዲህ ብሎ ነበር፣ “እ.ኤ.አ በ2015 ትርፍ ምርት ለማምረት የሚያስችለንን እና የውጭ የምግብ እርዳታ ሳያስፈልገን እና ሳንጠይቅ እራሳችንን ለመመገብ የሚያበቃንን አንድ ዕቅድ አዘጋጅተናል [የዕድገት እና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ መሆኑ ነው!]፡፡“

በአሁኑ ጊዜ ጉልበተኛውን የዓለም ባንክን፣ የዓለም አቀፉን የገንዘብ ድርጅትን እና የልማት ዕርዳታ ቡድንን እንዲህ የሚሉ ሶስት ጥያቄዎችን ለመጠየቅ እፈልጋለሁ፡ 1ኛ) እ.ኤ.አ በ2015 አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን/ት ሁሉ በቀን ሶስት ጊዜ መመገብ ችለዋልን? 2ኛ) አብዛኞቹ ኢዮጵያውያን/ት በአሁኑ ጊዜ ከአምስት ዓመታት ከነበሩበት ሁኔታ በተሻለ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም በማግኘት ደረጃ ላይ ይገኛሉን? 3ኛ) ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2015 መለስ በነደፈው የዕድገት እና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ መሰረት “ምንም ዓይነት የውጭ የምግብ እርዳታ ሳይደረግላት” እራሷን መመገብ ችላለችን?

እ.ኤ.አ በ2015 ለአብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን/ት በቀን ሶስት ጊዜ መመገብ መቻል ላም አለኝ በሰማይ ወተቷን የማላይ ነገር ነው፡፡ እውነታው ብጥር እና ግልጥልጥ ብሎ ሲታይ ግን ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ በዓለም ላይ ከሚገኙ 125 ከሆኑ በመጥፎ የአመጋገብ ሁኔታ ላይ ካሉ ሀገሮች መካከል በ123ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡ እንደ ኦክስፋም የተባለው ዓለም አቀፍ ድርጅት የምግብ ቋት /Food database መረጃ ከሆነ “የተትረፈረፈ፣ ጠቃሚ ንጥረ ነገር ያለው፣ ጤናማ እና ከህዝቡ የመግዛት አቅም ጋር የተገናዘበ ምግብ ከማግኘት አንጻር ኔዘርላንድ ከዓለም በአንደኝነት ደረጃ ላይ የምትገኝ ሲሆን ቻድ ከኢትዮጵያ እና ከአንጎላ በመቀጠል በመጨረሻ እና በ125ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች” ብሏል፡፡

የዓለም ባንክ ተገዥነቱ ለእራሱ ሀሳብ ብቻ እንጅ ለእራሱ እውነታ አይደለም፣

አንድ ግልጽ መሆን ያለበትን ነገር መናገር እፈልጋለሁ! የዓለም ባንክ በዕድገት እና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ ወይም ደግሞ በማንኛውም መንገድ ስለኢትዮጵያ ህዝብ ጉዳይ ወይም ፖለቲካ የመሰለውን የእራሱን ሀሳብ መግለጽ በመቻሉ ጉዳይ ላይ ምንም ዓይነት ችግር የለብኝም፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የዓለም ባንክ ማንኛውንም እውነት ነው ብሎ የሚያምንበትን መግለጽ ወይም አትሞ ማውጣት እና በእራሱ የመረጃ ምንጭነት ተጠቅሞ እውነታነትን በተላበሰ መልኩ ሀሳቡን ይፋ ማድረግ እና ማጠቃለያ በመስጠቱ ሁኔታ ላይ ችግር የለብኝም፡፡ እንደዚሁም ደግሞ የዓለም ባንክ የወያኔ የወሮበላ ስብስብ ቡድን ባቀረበለት መረጃ ላይ ተመስርቶ “ኢትዮጵያ ባለፉት አስርት ዓመታት በየዓመቱ በዓማካይ የ10.7 በመቶ የምጣኔ ሀብት ዕድገት አስመዝግባለች” የሚል እምነትን ቢያራምድም እንኳ በፍጹም ችግር የለብኝም፡፡ ሆኖም ግን አጠቃላይ ለመጠየቅ የምፈልገው ነገር ትክክለኛ የሆነ ምሁራዊ ሀቀኝነት እና የባንኩን መርሆዎች በተለይም ስለመዋዕለ ንዋይ ብድር የሚያትተውን ክፍል (OP/BP 10.00) ዝንፍ ሳይሉ ሙሉ በሙሉ ማክበር እና ተግባራዊ ማድረግ መቻል አለበት በሚለው ላይ ነው፡፡

የዓለም ባንክ እያወቀ እና ሆን ብሎ በእርግጠኝነት እና ምንም ዓይነት ጥርጣሬን በማያጭር መልኩ ያፈጠጡ እውነታዎችን አዛብቶ በሀሰት እና አሳፋሪ የሆነ የማጭበርበር ስራ ለዓለም ህዝብ ይፋ በሚያደርግበት ጊዜ በዚህን ጊዜ ነው ችግር እጅግ በጣም የገዘፈ ችግር የሚኖርብኝ፡፡ የዓለም ባንክ በሀገሪቱ ባሉት የባንኩ ስራ አስኪያጆች ስንፍና፣ ብቃት የለሽነት፣ ወይም ደግሞ ግድየለሾች በመሆናቸው ምክንያት የሚያትማቸውን ዘገባዎች እውነት እና ውሸትነት ኃላፊነት እና ጥንቃቄን በተሞላ መልኩ አይቶ እና አረጋግጦ ማውጣት ባለመቻሉ ላይ ነው ግዙፍ የሆነ ችግር እና ቅሬታ ያለብኝ፡፡ የዓለም ባንክ በኢትዮጵያ ላይ የሚወጡ ዘገባዎች ነጭ ውሸቶች እና ቅጥፈቶች መሆናቸውን እያወቀ ወይም ደግሞ ለእውነታው በእንዝህላልነት እና በምንቸገረኝነት በደፈናው የቅጥፈት መግለጫ ሲሰጥ እና ውሸትን ለህዝብ ሲጋብዝ እጅግ በጣም ከባድ የሆነ ችግር ይሆንብኛል፡፡ እንደ ደደብ ወይም ደግሞ እንደ ማይም ደንቆሮ ዓይነት ሁኔታ ለመስተናገድ አልወድም፡፡ ከሁሉም በላይ የእነርሱን ቆሻሻ ማስገባት ቆሻሻ ማስወጣት (ቆማቆማ) ዘገባዎች ጽኑ አንባቢ ነኝ፡፡

ውሸት የሆነን ሰነድ፣ የሚያሳስት እና አጭበርባሪ የሆኑ መግለጫዎችን ወይም መረጃዎችን መስጠት ወይም ደግሞ ማተም በዩናይትድ ስቴትስ መንግስት ህግ ስር ለሚተዳደሩ ኤጀንሲዎች እና ተቋማት ታላቅ ወንጀል ነው፡፡ ይህ ታላቅ የማጭበርበር እና የቅጥፈት ወንጀል ኢትየጵያ ላይ ሲፈጸም አይሰራም ማለት ነውን?!

18 ዩ.ኤስ ኮድ # 1001 የሚከተለውን መብት ያጎናጽፋል፣ “ማንም ይሁን ማን…በየትኛውም ጉዳይ ቢሆን የዩናይትድ ስቴትስ መንግስት የሕግ አውጭው፣ የህግ ተርጓሚው ወይም ደግሞ ቅርንጫፉ አውቆ እና ሆን ብሎ – (1) የዋሸ፣ የደበቀ ወይም ደግሞ በማንኛውም መልኩ በማጭበርበር ለመሸፈን የሞከረ፣ የተንኮል ስልትን ቀይሶ የሰራ ወይም እውነታውን የሚያዛባ መሳሪያ ወይም ሰነድ፣ (2) በሰነድ ላይ የተቀመጠ እና ማንኛውንም ዓይነት ውሸት የያዘ፣ ልቦለዳዊ ድርጊትን የያዘ ወይም ደግሞ የማጭበርበር መግለጫ የሰጠ ወይም ውክልና የሰጠ ወይም ደግሞ (3) ማንኛውንም ውሸት የሆነ ነገር የሰራ ወይም ውሸት የሆነን ሰነድ የተጠቀመ ወይም ደግሞ ውሸት መሆኑን እያወቀ ያንኑ ሰነድ በመጠቀም ውሸት የሆነ መረጃ ያወጣ፣ ልብወለድ ዕይነት ሰነድን እንደ አውነተኛ ሰነድ ቆጥሮ በስራ ላይ ያዋለ ወይም የተጭበረበረ መግለጫ የሰጠ በህግ ይጠየቃል፣ ጥፋተኛ መሆኑ ከተረጋገጠም ወደ እስር ቤት ይላካል…” ይላል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ መንግስት ከዓለም ባንክ ቡድን ውስጥ “ትልቁ ባለድርሻ አካል” እንደሆነ በወሬ ደረጃ ሰምቻለሁ፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ ዓለም አቀፍ ልማት ኤጀንሲ/United States Agency for International Development (USAID)ም የዩናይትድ ስቴትስ መንግስት ኤጀንሲ እንደሆነ አውቃለሁ እንዲሁም ለመሆኑ እምነት አለኝ፡፡

የህዝቡን ቁስል መንካት፣

የእንግሊዝ ታዋቂ ገጣሚ የሆኑት ጆን ሚልተን የመናገርና የመፃፍ ጠንካራ ተከራካሪ በፓራዳይስ ሎስት (ገነት ጠፍታለች) መፅሐፋቸው ላይ የሚከተለውን ግጥማዊ መንፈስ አቅረበው ነበር፣

…በእርሱ [በሰይጣኑ] በእቅዱ እረካለሁ፣
በባዶ ተግበሩ እጅጉን አዝናለሁ፡፡
ቀስ አርጎ ቢቀርብም ውሸት እጠላለሁ፣
ቢስም ቢያባብለኝ አልቀጥፍም ብያለሁ፡፡
ሰማያዊ ቁጣ ቢያስገመግም ከቶ፣
አምላክ ይመልሳል ርህራሄ ሰጥቶ፣
አምሳሉን አይፈጅም ከምድር አጥፍቶ
በምድር ጦር መሳሪያ ቢግተለተል የትም፣
ሰማይ ቢደረመስ በሮኬት ቢፈርስም፣
ለመብቴ ልሞት፣
ለክብሬ ልሟገት፣
ለመንፈሴ ጽናት፣
ለዓላማ ስምረት፣
በህይወት እያለሁ በአስገራሚው ዓለም፡፡
ሰማይ ዝቅ ምድር ከፍ ማለት ቢከጅልም፡፡
ለነጻነቴ ስል ከቶ አልመለስም፣

የዓለም ባንክ ይህንን ጉዳይ ላያውቀው ይችላል፡፡ ይህንን ይወቀው! አሁኑኑ! ኢትዮጵያ አሁንም ቢሆን ለእኔ እና በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ወገኖቸ ሁሉም ነገር ሊገኝባት የምትችል ገነት አገር ነች፡፡ በረዥም ጊዜ ተኩስ እና ጫጫታ አልጠፋችም፡፡ ሁሉም የፖለቲካ እና አሀዛዊ ውሸቶች እና ቅጥፈቶች በእውነት ቀስት ሲወጉ እና በህዝቡ ቁጣ ሲወገዱ የኢትዮጵያን ገነትነት እንደገና እንደምንመልሰው እናውቃለን፡፡

የዓለም ባንክን በኢትዮጵያ ላይ “ትረካዊ ልብወለድ” ጽፎ አንብቤአለሁ፡፡ በቅርብ ጊዜ ደግሞ እውነተኛውን ጽሁፍ ለማንበብ እፈልጋለሁ፡፡ ግን የዓለም ባንክ እውነታውን መናገር ይችላልን!?

ይቀጥላል…

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!
ጥር 28 ቀን 2007 ዓ.ም

Leave a Reply