ሱዛንራይስና የአፍሪካ ሰለስተ እርኩሳን*

ከፕሮፌሰር  ዓለማየሁ  ገብረማርያም
ትርጉም  ከነጻነት ለሃገሬ

Click here for English version

Click here for PDF

የሰለስተ  እርኩሳን  እመቤት

ሱዛን ራይስ፤የወቅቱ በተባበሩት መንግስታት የዩ ኤስ አሜሪካ አምባሳደር ከአፍሪካ አታላይ፤ጮሌ፤ስግብግብ ራስ ወዳድ ዲክታተሮች ጋር ላለፉት አሰርት ዓመታት ስታሽቃብጥና አሸሸ ገዳሜ ስትል ነበር፡፡ ከዚህ ያለፈ ውግዘታዊ አስተያየት በተቺዎችች ተሰንዝሮባታል::

Susan Rice, the current U.S. Ambassador to the U.N.

በአፍሪካ የራይስ አፍቃሪ መሪዎችም ‹‹ሰለስተ እርኩሳን › ናቸው: — የሩዋንዳው ፓውል ካጋሚ፤ የዩጋንዳው ዩዌሪ ሙሳቪኒ፤ እና በቅርቡ ወደማይቀረው የሄዱት የኢትዮጵያው መለስ ዜናዊ፡፡ (ተጠቃሾቹ በሙሉ ቀድሞ የተቃዋሚ ጦረኞች የነበሩና በቢል ክሊንተንና በቶኒ ብሌይር ቡራኬ ስመ ክርስትናቸው ‹‹የአፍሪካ የአዲሱ ትውልድ ›› መሪዎች የተሰኙ) በክሊንተንና ራይስ ራዕይ እነዚህ የአዲሱ ትውልድ መሪዎች ለአፍሪካ አዲስ አስተሳሰብ በማምጣት፤ነጻነትንና ልማትን ያፋጥናሉ ተብለው የታጩ ነበሩ፡፡ ራይስም ለዚህ ራዕይ ጠባቂ መልአክ፤ተጋዳይ፤ረቺ፤ አሳዳጊ፤ጠበቃ፤እና የነዚህ ሰለስቱ ጓደኞች ታላቋ እመቤትና የሴት አስተዳዳሪ ሆና ኖራለች፡፡ አሰቃቂዎቹን ሰለስቱ ቡድኖች ጋሻ መከታ በመሆን ከፍትህና ከፖለቲካ ተጠያቂነት በመከላከል፤ ከበርካታ ውግዘታዊ  ነቀፌታና ትችቶች ተድበስብሰው እንዲታለፉ በማሰናከል የተባበሩት መንግሥታትና ዩ ኤስ አሜሪካም ማዕቀብ እንዳያደርጉባቸው ከፍተኛውን ሚና ሱዛን ራይስ፤ ተጫውታለች፡፡

ራይስ፤ካጋሚ፤ሩዋንዳእናያልታመነውየዘርማጥፋት

በኤፕሪል 1994 የክሊንተን አስተዳደር በሩዋንዳ ይካሄድ የነበረውን ጭፍጨፋና ግድያ ያላወቁ በማስመሰል ከእውነቱ ሁኔታ አይናቸውን ሲጋርዱ፤ ራይስ በራሷ አገላለጽ “ወጣቷ የብሔራዊ ደህንነት ዋስትና ዲረክተር” የወቅቱን የብሔራዊ ዋስትና ካውንስለሩ (አማካሪ) አንቶኒ ሌክ በሩዋንዳ ስለሚካሄደው ጭፍጨፋ ያሁኗ የሃገር አስተዳደር ክሊንተን ወቅታዊ ምላሽ ለጭፍጨፋውና ለሩዋንዳ ሕዝብ እልቂት አጣዳፊ ምላሽ እንዳይሰጥ የማከላከልን የደርጊቱን ገጽታ በመሸፋፈን እልቂቱ ወደ ከፍተኛ ደረጃ እንዲደርስ የደረገችው ይቺው ሱዛን ራይስ ነበረች፡፡ እውነቱን በማውጣት ሂደቱን በማቆም ፈንታ፤ራይስ ሁኔታውን በመሸላለም፤የሩዋንዳን  እልቂት የዘር ማጥፋት በማለት መናገሩ፤በዚያን ወቅት በሚደረገው የዴሞክራቶች ምርጫ ላይ ሊያስከትል የሚችለውን ውድቀት በማጋጋል እያስቀመጠች ጉዳዩ እንዲታለፍ ጭፍጨፋው ግን እንዲቀጥልና የዘር እልቂቱንም ታሪክ በማይረሳው መንገድ እንዲዘገብ አደረገችው፡፡ አጥፊና አበላሽ በሆነ መልኩ የሩዋንዳን እልቂት የዘር ማጥፋት ብለን ግን ምንም ሳናደርግ ብናልፈው በኖቬምበር በሚካሄደው የኮንግሬስ ምርጫ ወቅት ምን ይውጠናል›› በሚል ማስፈራሪያ: ራይስ ሃላፊ ወዳጆቿን በማማከር በዝምታ እንዲታለፍ አድረገች፡፡

ጭፍጨፋው በተጀመረ ከ100 ቀናት ባነሰ በሩዋንዳው የዘር ማጥፋት እልቂት ሳቢያ ከ800 ሺህ ያላነሱ ሩዋንዳዊያን ንጹኃን ዜጎች ለሞት ተዳረጉ፡፡ በዚህ እልቂት ወቅት ራይስና አለቃዋ ሌክ፤ እና ሌሎችም በጎ ፈቃድ ያጡ ቢሮክራቶች ውጣ ውረድ የሞላበትን ጨዋታቸውን በመቀጠል ስለሩዋንዳው እልቂት፤ጅምላ ጭፍጨፋ የዘር ማጥፋት አንዳችም ሕጋዊና ግልጽ መግለጫ እንዳይሰጥ ተደረገ፡፡ በኋላ ግን ራይስ ስለሁኔታው እንዲህ አይነት መግለጫ መስጠቷ እንደማይታወሳት የአዞ እንባዋን እየረጨች ለማስተባበል ጣረች፡፡ ራይስ በድርጊቷ በመጸጸትና ራሷን ለንስሃ ከማስገዛት ይልቅ አውነቱን በመካድና የራሷን አባባል የዘነጋች በማስመሰል፤ ካለፈው ተምራ ወደፊት እንዳትደግመውና ከተጠያቂነት ከማምለጥ ይልቅ የለመደባትን  ቅጥፈት ራት ምሳዋ በማድረግ ከሶስቱ የአፍሪካ ውጉዞች ጋር እጅና ጓንት በመሆንድ ጋፏን ከመስጠት አልታቀበችም፡፡  እነዚህን ዋጋቢስ አርባና ቢስ የአፍሪካን ሰለስቱ እኩዮች ማሞላቀቅ፤ሞግዚት ሆና ማንቆላበስ፤ማበላሸት፤መጥፎ ተግባራቸውን በማለባበስና በመደበቅና የሌለ ተግባራቸውን፤ በማውሳትና በማሞካሸት ስትዘፍንላቸው፤ ስታዋድዳቸው፤ ስታሞግሳቸው እስካሁን አለች ማለት አንዳችም ግነት የሌለው ሃቅ ነው፡፡

የ1994ቱ በሩዋንዳ ጭፍጨፋና የዘር ማጥፋት የአሜሪካ ፖሊሲ፤የዲፕሎማቲክ አታላይነት  ዲፕሎማሲያዊ ማደናገሪያ እና ቅጥፈት  እስከዝንተ ዓለም የማፈሪያ ምስክር ሆኖ ይኖራል፡፡ በ1994 ኤፕሪል 6 የሩዋንዳን ፕሬዜዳንት ጁቫኔል ሃቢያርማናን እና ሌሎችንም ከታንዛንያ ወደ ኪጋሊ፤ ሩዋንዳ ሲያጓጉዝ የነበረው አውሮፕላን፤ ተመትቶ ወደቀ፡፡ለዚህም ግድያ ተጠያቂ የሆኑት የሩዋንዳ የጦርሃይሎች አባላት ባለፈው ዓመት (1993) የተደረሰበትን ስምምነት ለመቀበል ፈቃደኛ ያልሆኑት የተቃዋሚ ሃይሎች የሩዋንዳ የአርበኞች ግንባር ነበሩ፡፡ ወዲያው የሃቢያርማናን ግድያ ተከትሎ የዚሁ የተቃዋሚዎች አባላት እና አፈንጋጭ የሚሊሺያ አባላት (ኢንተርሃምዌይ) ጭፍጨፋቸውንና አሰቃቂውን የዘር ማጥፋት ግድያቸውን ማካሄድ ቀጠሉ፡፡ በዚህም የግድያ እልቂት በርካታ ቱትሲዎችና ገለልተኛ የሆኑ ሁቱዎች ሰለባ ሆኑ፡፡

አር ኤ ኤፍ ይህን ጭፍጨፋውንና ሲጀምርና አለአንዳች ልዩነት በየመንገዱ ላይና በየመንደሩ ግድያውን ሲያከናውን ራይስና ሌሎችም የዩ ኤስ አሜሪካ ከፍተኛ ባለስልጣናት የዘር ማጥፋት ሂደት መጀመሩን ሊገነዘቡ ይገባነበር፡፡ ከተባበሩት መንግሥታትና ከራሳቸውም የስለላ መዋቅሮች በታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ግድያና ጭፍጨፋ በኪጋሊ ከኤፕሪል 6 ጀምሮ በመካሄድ ላይ እንደሆነ ማስታወሻው በኤፕሪል 6 በተጣፈ ደብዳቤ እንደደረሳቸው ያሳያል፡፡ የሃገር አስተዳደር ምክትል ጸሃፊ የነበረችዉና የአፍሪካ ጉዳይ ሁለተኛው ባለስልጣን ፕሩዳንስ ቡሽኔል ሲተነብይ፡-

“እንደተገመተው ሁለቱም ፕሬዜዳንቶች ሞተው ከሆነ በሁለቱም አለያም በአንዱ ሃገር ስር የሰደደና ማለቂያ የሌለውእልቂት ሊከሰት እንደሚችል ይገመታል፡፡ በተለይም የአውሮፕላኑ ተመትቶ መውደቅ ከተረጋገጠ የኛ ሚና ሊሆን የሚገባው፤በሁለቱም ሃገሮች ሰላም እንዲሰፍን ጥሪ ማድረግ ነው፡፡ ለሁለቱም ገሃራት ይፋ መግለጫ በማውጣት አለያም መሰል ዘዴን በመጠቀም…

በኤፕሪል 11 1994 ለመነጋገርያ የሚሆን ማስታወሻ ለምክትል የመከላከያ ጉዳዮች ጸሃፊ ቀረበ፡፡ የመካከለኛው አፍሪካ የመከላከያ ዲፒዩቲ ምክትል ጸሃፊም ሲያጠቃልል፤ “ሁለቱም ወገኖች ለሰላሙ ጥሪ መልካም ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆኑ ከቀሩ የተጀመረው እልቂት ማቆሚያ ወደሌለው ግድያ እልቂት የደም መፋሰስ ሁኔታ ከመሸጋገርም አልፎ ወደ ብሩንዲም መዛመቱ የማይቀር ነው፡፡ በዚህም ሳቢያ በሚሊዮን የሚቆጠሩት ወደ  አጎራባች ሃገራት ኡጋንዳ፤ታንዛኒያ፤ እና ዛይር መሰደዳቸው አይቀርም፡፡  ፈረንሳዮችም ሁኑ ቤልጂጎች በሁለቱም ወገን ታማኝነት ስለሌላቸው አሜሪካ ታማኝ አሻሻ ጭ ሆኖ መቅረብ ይኖርበታል::››

ራይስና ባልደረባዎቿ ግን ሆን ብለው ያፈጠጠውን የእልቂት አደጋ በማንኳሰስና በማሳነስ፤ ሁሉም የተኩስ አቁም ማድረግ አለባቸው የሚል ባዶ መግለጫ በማውጣት ብቻ ተገደቡ፡፡ የእልቂቱ ሂደት ለሁለት ሳምንታት ከተካሄደና እልቆ መሳፍርት የሌለው ሰብአዊ ፍጡራን ካለቁ በኋላ፤ የራይስ አለቃ አንቶኒ ሌክ ‹‹አስደናጋጩን የሩዋንዳና የብሩንዲን ፕሬዜዳንቶች ድንገተኛ ሞት ተከትሎ የተቀሰቀሰው እልቂት ሁሉም የጦር ሃላፊዎችና መሪዎች እነዚህን የግድያውን ተካፋይ የጦር አባላት በአስቸኳይ ወደ ድርድሩ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ ሳይሆን ቢቀር ግን፤እልቂቱ

የከፋና አሰቃቂ እንደሚሆን መገንዘብ ተገቢ ነው›› በማለት መግለጫ አወጣ፡፡ በኤፕሪል ማብቂያ ድረስ የአሜሪካን መንግስት አንዳችም ጄኖሳይድ አላየንም፤ አልሰማንም፤ አላወራንም የሚል ጨዋታውን ቀጥሎ ነበር፡፡›› በኤፕሪል 28 ቡሽኔል ለሩዋንዳው የመከላከያ ሚኒስቴር ካብኔት ዳይረክተር ኮሎኔል ባጋሶራ ግድያውን እንዲያስቆም ተማጽኖ ላከች››:: በመልእክቱም ቡሽኔል ለባጋሶራ ‹‹በዓለም አመለካከት የሩዋንዳ የጦር ሃይል በወንጀልና ግድያ ተግባር ላይ ተሰማርቶ የሲቪሎችን ግድያ በማደፋፈር ላይ ነው፡፡›› በማለት ‹‹የሩዋንዳ መንግስት ይህን ሁኔታ እንዲቆም ለማድረግና ሁኔታውን ወደ ሰላም ለማምጣት ማንኛውንም ጥረት ሊያደርግ ይገባል›› አለች፡፡

በሜይ 1 ሁኔታው ሶስት ሳምንታት ከሆነውና ብዙ እልቂት ከተፈጸመ በኋላ፤ በሩዋንዳ መደረግ ስለሚገባው ጉዳይ እንደአዲስና ጨርሶ ያለፈውን ሁሉ ሽምጥጥ አድርጎ በመካድ፤አሜሪካ ሁኔታውን ለመከላከል ሊወስድ የሚገባውን ተግባር ልክ ቀደም ሲል ራይስ እንዳረገችው ሁሉ በመሸፋፈንና እውነቱን በማለባበስ አረቀቁ፡፡ እንደ ቡድኑ የ ‹‹ውይይቱ ረቂቅ ጽሁፍ››  ማእከላዊው ጥያቄ ይህን ዘግናኝና ለሕሊና የሚከብድ ጭፍጨፋ ምን ስም ሊሰጠው እንደሚችል ነበር፡፡

1. የጭፍጨፋው ምርመራ፡:  በዚህ የሰብአዊ መብት ጥሰት የዓለም አቀፉን ምርመራ ተሳትፎ በሚጠየቅበት ጊዜ ጥንቃቄ

ሊደረግ አስፈላጊ ነው፡፡ ትናንትም ቢሆን ያሳስብ የነበረው ይሄው ነው፡፡ የጭፍጨፋው ጉዳይ ሲጣራ የአሜሪካ

መንግስት ‹‹ምንም አላደረገም›› ሊያሰኝ ወደሚችል ትችትና አመለካከት ያስኬዳል፡፡

በሜይ 5 ዩ ኤስ አሜሪካ የሚል:ኮሊንስን ሬዲዮ ጣቢያ ያስተላልፍ በነበረው አበጠባጭና ሞት ጠሪ፤ እርስ በእርስ ቱትሲዎችን  እንዲሁም ቤልጂኮችንና አሜሪካንንም ጨምሮ በመኮነን ሲያስተላልፍና ለግድያውም ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማድረጉ ሳቢያ የጣቢያውን ማስተላለፍ ለማፈን  ቢስማሙም ወጪው የናረ ሆነና ተዉት፡፡

በሜይ 21 እልቂቱ ስድስት ሳምንታት ከሆነው በኋላ፤እልቂቱን የጅምላ ጭፍጨፋ እንበለው አንበለው በሚል ክርክር ላይ ነበሩ፡፡ የመከላከያ ስለላ ተቋም ዘገባ በሜይ 9 1994 ከጭፍጨፋው ከወር ባነሰ ጊዜ ውስጥ ውሳኔ ላይ ደረሰ፡: በቱትሲዎች ላይ በሁቱ ሚሊሺያዎችና በግለሰቦች በዘፈቀደ በተወሰደው ጭፍጨፋ ባሻገር የተደራጀ የጦሩ የግድያ ሂደትም የቱትሲዎችን የአመራር አሻራ ጨርሶ ለማጥፋት በሚል ይካሄድ የነበረ ደባም ነበረ፡፡ ቅድሚያ እቅዱ እርቅን የሚደግፉትን ምሁራንና የፖለቲካ መሪዎችንና ደጋፊዎቻቸውን ማጥፋት የሚል ሲሆን፤ መንግስት ሂደቱን መቆጣተርና ሚሊሺያውንም ስርአት ማስያዝ ባለመቻሉ፤ግድያው እንደሰደድ እሳት ተቀጣጠለ፡፡  ሂደቱም የማይቆምና ሊገታም የማይችል ሆነ፡፡

ለውጭ ሃገር አስተዳደሩ ጸሃፊ ክሪስቶፈር በተላከው ‹‹የስምምነቱ አጭር የማስታወሻ ውል›› እንደሚለው ያስከተለው ጥያቄ ‹‹እውነት በሩዋንዳ ጭፍጨፋ ተፈጽሟል›› የሚል ነበር፡፡ ምንም እንኳን የአሜሪካን ባለስልጣናት ሀ ብሎ ግድያው ሲጀመር ጀምሮ ቱትሲዎችና የዘር ማጥፋቱ ትኩረትም የቱትሲን ስመጥር ባለስልጣናትና  መሃል ሰፋሪ ሁቱዎችንና ሌሎችንም ባለስልጣናት ግድያ እውቅናው ቢኖራቸውም፤መላልሰው ያነሱ የነበረው ጥያቄ የሚታወቀውን ጉዳይ ነበር፡፡የቀረበውም ማስታወሻ ‹‹ለውሳኔው ሃሳብ መንስኤ” በማለት የፖሊሲ ጥያቄ የያዘ ነበር፡፡

የዲፓርትመንቱ ሃለፊዎች በይፋ ‹‹የጅምላ ጭፍጨፋ›› መካሄዱን መናገር እንደሚችሉ:  2. የአሜሪካን  ልኡካን

በሚሳተፉበት ዓለም አቀፉ ስብሰባ ላይ በሚተላለፈው ውሳኔ ላይና ከዚሁ ጋር ተያይዘው በሚነሱ ነጥቦች ላይ ሁሉ በረዋንዳ የጅምላ ጭፍጨፋ መኖሩን እንዲያምኑ መመርያ መስጠት: በሩዋንዳ የጅምላ ጭፍጨፋ በመኖሩና ባለመኖሩ ላይ ትክክለኛውና  ሕጋዊ የሆነው ትንታኔ  ከተግባራዊው ማስታወሻ ቀድሞ ሲወጣ ቀጥተኛ ነበር፡፡ በ1948 የጸደቀውን ኮንቬንሽን ተንተርሶ የጅምላ ጭፍጨፋ

መከላከልንና የሚያስከትለውንም መቀጮ ዝርዝር ያካተተ ሆኖ ነው የተጠናቀረው፡፡

በሩዋንዳ የዘር ማጥፋት መኖር የተዘረዘሩት ሁኔታዎች በሩዋንዳ ለመፈጸማቸው የሚነሳ ጥያቄ ቢኖርም ከቁጥር የማይገባ ነው፡፡እጅግ ለቁጥር ያሚያታክቱ ግድያዎችና ለሕሊና ማጣት መነሾ የሆኑ፤ በአካላት ላይ የሚዘገንን ጉዳት ያስከተሉ ድርጊቶችተከናውነዋል፡፡ ዓለም አቀፋዊ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች በማስረጃ የተደገፈና ሊካድ በማይችል ሁኔታእንዳስረዱት፤የግድያውን መጠን በኤፕሪል 6 ዕለት ከ200000 እስከ 500000 እንደሆነ መስክረዋል፡፡(ድርጅቶቹ ከላይ የተገለጸው አሃዝ ግነት ሊኖርበት ይችላል ቢሉም የሚከተለውን ግምገማ የሚያፋልስ አይሆንም:: (ከኤፕሪል 6፣ 1994 ጀምሮ የተፈጸመውን ግድያ ቁጥር የተባበሩት መንግስታት የሩዋንዳ መንግሥት ካቀረበው 1071 000 በተለየ  መጠኑን 800000 መሆኑን ይዘግባል፡፡)

ሕዝቡ በሩዋንዳ ስለነበረው ጭፍጨፋ ባለማወቁ ሳቢያ ተቃውሞ ባያነሳም፤ራይስና ሌሎች በክሊንተን አስተዳደር ስር የነበሩት ካለአንዳች ጥርጣሬ የጅምላ ጭፍጨፋው በመታቀድ ላይ በነበረና ተግባራዊም መሆን ሲጀምር ሃባሪማና ከሞተበት ዕለት አንስቶ በሚገባ ቢያውቁትም የራይስ ቅጥፈት ማለቂያ የሌለው ነውና አሁንም ድረስ ክህደቷ ያው እውነትን መሸምጠጥ ነው፡፡

ራይስካጋሚ፤ሙሴቪኒ፤ኤም 23፤እና ‹‹አይቶእንዳላየ››

በ1966 የጅምላ ጭፍጨፋው ባለቀ ከሁለት ዓመታት በኋላ፤ የሁቱን ወንጀለኞች እና የሚሊሺያ አመጸኞች በሩዋንዳ ለተፈጸመው የጅምላ ጭፍጨፋ ተጠያቂዎች ናቸው በሚል ሰበብና እንዲሁም ኮንጎ(በወቅቱ ዛይር) ካለው ሰፈራቸው መልሰው ወረራ እንዳያደርጉ  በማለት ካጋሚ በስተምስራቅ ክፍል የሚገኙትን የቱትሲ ነገዶች መሳርያ ማስታጠቅ ያዙ፡፡በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎችን ለሞት የዳረገው የኮንጎ ጦርነት በመባል የሚጠራው በዚያን ወቅት ጀምሮ እስካሁን ድረስ ጦሱ ሞትን ከማስከተልና ደም ከማፋሰስ አልቆመም፡፡

የመጀመርያው የኮንጎ ጦርነት የዘለቀው ከ1966  እስከ 1997 ነበር፡፡ የኮንጎው የተቃዋሚ መሪ ሎውረንት-ዴዚሬ ካቢላ ለረጂም ዘመን በስልጣን ላይ የኖሩትን ሞቡቱ ሴ ሴ ሴኮን ከስልጣን አውርዶ ስልጣኑን ጨበጠ፡፡ በስተምስራቅ ኮንጎ መረጋጋትና ያጠፋው የሩዋንዴው ሂኔታ ለሞቡቱ መውደቅ ዋናዋ መረማመጃ ነበር፡፡ ካቢላም በ1997 ስልጣን ለመያዝ ቢበቃም ወዲያው በጃንዋሪ 18 2001 በራሱ የጥበቃ አባል ተገደለ፡፡በማርች 2012 የቀድሞው ካጋሚ የቀኝ እጅ የነበረውና የአር ፒ ኤፍ ዋና ጸሃፊ ቲዎጎኔ  ሩዳስኢነጉዋ  አስደንጋጭ  የሆነውን ወሬ ይፋ በማድረግ የኮንጎውን ፕሬዜዳንት ካቢላን የገደላቸው ፖውል ካጋሚ ነው በማለት ተናገረ፡፡ ሁለተኛው የኮንጎ ጦርነት ካቢላ ስልጣን ከያዙ ከጥቂት ጊዜያት በኋላ ተጀምሮ እስከ 2003 ተካሄደ፡፡ በዚህም ከ 8 ያላነሱ የአፍሪካ ሃገራት እና ከ12 የማያንሱ መሳርያ የታጠቁ ቡድኖች በግጭቱ ተሳትፈውበታል፡፡

በማርች 2009 የዴሞክራቲክ ሪፑብሊክ ኮንጎ መንግስት ከናሽናል ኮንግሬስ ኢን ዘ ዲፌንስ ኦፍ ዘ ፒፕል ፓርቲ ጋር ሲ ኤን ዲ ፒን እንደ ፓርቲ በመቀበል የሰላም ውል ተፈራረሙ፡፡ በኤፕሪል 2012 በርካታ የሲ ኤን ዲ ፒ ፓርቲ አባላት የሆኑ የቱትሲ ጎሳዎች፤ በማርች 2009 የተደረሰበትን ስምምነት ተግባራዊ ሳይደረግ በመቅረቱ ሳቢያ በዴሞክራቲክ ሪፑብሊክ ቾንጎ አመራር ላይ በማመጽ  ኤም 23 የተባለውን እንቅስቃሴ መስርተው ትግል ገቡ፡፡ መሪያቸውም በጦር ወንጀል ስሙ የታወቀው ጄኔራል ቦስኮ እንታጋንዳ  (አጥፊው (ዘ ትረሚሜተር) በመባልም ይጠራል):: እንታጋንዳ በዓለም የጦር ፍርድ ቤት ሕጻናትን በማስታጠቅና ጦር ሜዳ በማዋልና በጦር ወንጀል ግፍ ተፈላጊ ነው፡፡ ለሁለተኛ ጊዜም በአይ ሲ ሲ በጁላይ 13 2012 በሶስት የሰብአዊ መብት ጥሰት ወንጀሎች፤ በአራት የጦር ወንጀል፤በተጨማሪም፤ በግድያ፤በአስገድዶ  መድፈር፤ በሲቪል ማሕበረሰቡ ላይ በፈጸመው ደባ ክስ ተመስርቶበታል፡፡ በጁላይ 2012 በአይ ሲ ሲ የተፈረደበት ቶማስ ሉባንጋ ዳይሎ የ እንታንጋደ አለቃ ነበር፡፡የእንታንጋንዳ  ኤም 23 አመጸኞች የክልል ከተማ የሆነችውንና አንድ ሚሊዮን ነዋሪ ያለባትን ጎማን ሲቆ ጣጠሩ 140000 ነዋሪዎች   ሀብት ንብረታቸውን ጥለው ለስደት ተዳረጉ፡፡

የኤም 23 ጠንካራ ደጋፊዎች ካጋሚና ሙሴቪኒ ነበሩ:: ይህንን ድጋፍና ደጋፊዎቹን በተመለከተ በርካታ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ማስረጃዎችን አሰባስበዋል፡፡ በቅርቡ በተባበሩት መንግስታት በወጣው የዴሞክራቲክ ኮንጎ ባለሙያዎች ዘገባ፤ (ኦክቶበር 2012) “የኤም 23ን የአመጽ ቡድን መፈጠርና የወታደራዊ እንቅስቃሴውንም በማጠናከሩ ረገድ ተቀዳሚ የኡጋንዳ ባለስልጣናት መሆናቸውንና ከዴሞክራቲክ ኮንጎ ጋር ባለው ወሰናቸው መሳርያ በማስተላለፍ፤ የቴክኒካል ድጋፍ በመስጠት፤እቅድ በማውጣት፤የፖለቲካ ማማከር፤የውጭ ግንኙነትም በማስተባበር በኩል፤ ወታደራዊ ድጋፍም በማድረግ ላይ ናቸው፡፡ ሁለቱም መንግስታት የ ኤም 23ን የፖለቲካ ፓርቲ ቅርንጫፎች መስፋፋትና መደርጀት ከይ በአመጸኞች ወገን ቆመውም ይሟገቱላቸዋል፡፡ የኤም 23 ደጋፊዎች 6 ሕግን በመጣስ ተፈላጊዎችና ወደ ሩዋንዳና ኡጋንዳ በተደጋጋሚ የሚመላለሱ ናቸው፡፡”

ባለፈው ኦገስት ሙሴቪኒ በሚስጢር ከኢንታጋንዳ ጋር ተገናኝቶ ነበር፡፡ባለፈው ሳምንትም የኤም 23 አማጽያን ታላቅ የማዕድን ክምችት ያላትን ጎማን እንዲለቁ ከሙሴቪኒና ከካጋሚ ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ባደረገው ጫና የቀረበላቸውን ጥሪ አሻፈረን አሉ፡፡ የኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲው ፕሮፌሰር ሆዋርድ ፍሬንች በኒውዮርክ ታይምስ ላይ ባወጣው ‹‹የካጋሚ ስውር ጦርነት በኮንጎ››  ‹‹የኮንጎውን ግጭት አስመልክቶ፤ ስድስት ሚሊዮን ሰዎች በታላቁ ሃይቅ ክፈለ ሃገር በጦርነቱ፤በችጋር፤እና በበሽታ ለሞት ተዳርገዋል፡፡ ይህም ጦርነቱን በዘመናችን ካጋጠሙት ሁሉ የከፋና አጥፊ ያደርገዋል›› በማለት ይሞግታሉ፡፡ ይህን ግጭት በመምራተ ቀዳሚ የሆነው በአጎራባች ሩዋንዳ የሚገኘው የቱትሲ ነገዶች ጥርቅምና በሩዋንዳ የሚደገፉ በርካታ የኮንጎ ተወላጆች መሆናቸውን የሚያውቁ ጥቂት ናቸው፡፡ እስካሁን ድረስ አሜሪካና ሌሎችም የአውሮፓ ሀገራት ካጋሚን በዲፕሎማቲኩ በመደገፍ ላይ ናቸው፡፡ላለፉት ዓመታትም በኮንጎ ለተፈጠረው ሁከት በሩዋንዳ የሚደገፉት ሃይሎች ለብጥብጥ በሃላፊነት ተጠያቂ ናቸው፡፡ የሩዋንዳ ፓትሪዮቲክ ፍሮንት፤በኮንጎ ውስጥ የማዕድን ማምረት ተግባር ያካሂዳል፤ እንደ ተባበሩት መንግስታት አጥኚ ቡድን ዘገባ መሰረት ሩዋንዳ የምስራቁን ኮንጎ ግዛት በተለያዩ ወኪል ጦረኞች ለመቆጣጠር ጥረት እንደምታደርግ ይናገራሉ፡፡

ሙሴቪኒና ካጋሚ በዴሞክራቲክ ኮንጎ የሚያከናውኑትን ደባ ራይስ ጋሻ መከታ ሆና ትሸፋፍናለች፡፡ ካጋሚ ኤም 23ን  መደገፉንና የገንዘብና የመሳርያ ድጋፍ መስጠቱን የተባበሩት መንግስታት አጥኚ ቡድን ይፋ እንዳያደርግ ያላደረገችው ጥረት የለም፡፡ እንደ ናሽናል ጆርናል አባባል ራይስ በሩዋንዳ ላይ ጠንካራ ትችት ለማቅረብ በማስረጃ የተደገፈ ሃቅ ያነሱትን የሃገር አስተዳደር የአፍሪካ ጉዳይ ምክትል ጸሃፊ ከሆነው ጆኒ ካርሰንና ከሌሎችም የቢሮው አባላት ጋር ሙሴቪኒንና ካጋሚን አትንኩብኝ ጭቅጭቅ አንስታ አንደነበር ዘግቧል፡፡ ጆርናሉ በዘገባው፤ የፈረንሳይ አምባሳደር የተባበሩት መንግስታት በዴሞክራቲክ ኮንጎ ችግር ጣልቃ መግባት እንደሚገባው ሲያማክራት ሃሳቡን አጣጥላ ችላ እንዲባል አድርጋለች፡፡ ራይስ ለፈረንሳዩ አምባሳደር፤ ‹‹የምስራቁ ዴሞክራቲክ ኮንጎ ነው፡፡ ኤም 23 ካልሆነም አንድ ሌላ ቡድን ይሆናል›› እንዳለችው ጆርናሉ የፓሪሱን ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር ጌራርድ ፕሩኒየርን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡

በሃገር አስተዳደር የአፍሪካ ጉዳዮች ምክትሏ ሱዛን ራይስ ከታላቁ ሃይቅ ክልል የመጀመርያ ጉዞዋ ስትመለስ፤ አንድ የቡድኗ አባል፤ የዩጋንዳው ሙሴቪኒና ካጋሚ የክልሉ መሰረታዊ ችግር የጅምላ ጭፍጨፋው ግርሻ ነው በመሆኑ መደረግ ያለበትን እናውቃለን፡፡ እኛ (የአሜሪካን መንግስት) ማድረግ ያለበት አይቶ እንዳላየ መሆን ብቻ ነው›› ብለውናል ብሏል፡፡ ይህ ነው የራይስ በሩዋንዳ ለተፈጸመው እልቂት የአዞ እንባ እዬዬ፡፡ በአጠቃላይ በቀላሉ ራይስ ስለአፍሪካውያን የጅምላ ጨፍጫፊዎች ‹‹መጥፎ አናይም›› ‹‹መጥፎ አንሰማም›› ‹‹መጥፎ አንናገርም›› እንደማለት ነው ማለት ይቻላል፡፡

ሱዛን ራይስና መለስ ዜናዊን ማከባበሯ

በመስከረም 2/2012 ራይስ በመለስ ዜናዊ ቀብር ላይ ከመገኘቷ አስቀድሞ ያዘጋጀችውን 3 “የድንቢጥ ጫጫታ” (ትዊተር) አክብሮተ መለሷን ለአንባቢ መሰሎቿ ልካ ነበር፤ ጫጫታዋም፡-

‹‹ከባድ የሃዘን ስሜት በአዲስ አበባ ይታያል፡፡ ለኢትዮጵያ ሕዝቦች ያደረብንን ሃዘን እንገልጻለን፡፡ መለስ ለኢትዮጵያ  #ሕዝብ ከተቃዋሚ እስከ አፈንጋጭ፤ ከድሆች እስከ መርዳት የማይጠፋ ቅርጽ ትቷል፡፡ በዚህ የ#ኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር የቀብር ስነ ስርአት ላይ የአሜሪካንን መንግስት ወክዬ በመገኘቴ ክብር ይሰማኛል››

ምናልባት ራይስ ‹‹የአሜሪካንን መንግስት ወክያለሁ›› ብላ ታምን ይሆናል፤ የቀብር ዋይታ ጫጫታዋ ግን የሚያሳየው በግል መለስን መባረኳን ነው፡፡ በከንቱ ውዳሴዋ መለስን ታይቶ የማይታወቅ፤ ያልተለመደ ባለራዕይ፤ ለኔና ለብዙዎች ታማኝ ወዳጅ ብላለች፡፡  በመቀጠልም ‹‹ቁጣን ማብረድ የሚችል፤ የማያስመስል፤ ቀጥተኛ፤ራሴን የማይል፤ የማይደክም፤ሙሉ በሙሉ ለቤተሰቡና ለሥራው እሱን ያሳደረ›› በማለት ተንጫጭታ ያለፈውን ተሞክሯቸውን እያስታወሰች ከመለስ ጋር የዝምድና ያህል መተሳሰራቸውንም ይፋ አደረገች፡፡

“በተገናኘን ቁጥር ምንም ያህል በሌላ ነገር ቢዋጥ ንግግሩን ሲጀምር ስለ ልጆቼ በመጠየቅ ነበር፡፡ ስለልጆቼ ሲጠይቀኝም ለይስሙላ ብሎ አልነበረም፡፡ ስለዕለት ተዕለት እድገታቸው ዝርዝር ማወቅ ይፈልጋል፡፡ የኔን ካዳመጠ በኋላ ስለራሱ ልጆች በዝርዝር ይነግረኛል:: መለስ ኩሩ አባትን ታማኝ ባል ነበር፡፡ ስለልጆቹ ተግባር ይነግረኝና ስለእድገታቸው ያወራኛል፡፡ በሃሳብና በጭንቀት የተዋጠ ገጹ ወዲያው በደስታ ይሞላል፡፡ መለስ በራሱና በሌሎችም ልጆች የወደፊት ተስፋና የተለየ ደስታ ይታየው ነበር፡፡”

‹‹የመለስ አይኖች መቁለጭለጫቸውን አያቆሙም፤የዘወትር ዝግጁ ፈገግታው፤የማያቋርጠው ሳቁ፤የቀልድ ችሎታው ዘወትር ያለ ነበር››  መለስ ‹‹ምን ያህል ቆራጥ፤ ስሜቱ የማይነካ፤ አልፎ አልፎም የማይበገር ….. እናም እሱ እንደሚጠራቸው ለሞኞችና ለደደቦች ደንታ የሌለው›› ነበር፡፡

ይህ የራይስ የክብርና ሞገስ ጫጫታዋ ግን ያቺን ኮከብ ተከትለው ወደ ቤተልሔም የተጓዙትን ሰብአ ሰገሎችን የሚያሳፍር ነው፡፡

ከጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ብዙ የሚደነቁ ችሎታዎች ውስጥ ከሁሉም በላይ አቻ የማይገኝለት ጭንቅላቱ ነው፡፡ የእድሜ ልክ ተማሪ በመሆን እራሱንና ሌሎችንም ብዙ አስተማረ፡፡ ግን ብልህ ብቻ አልነበረም፤ የማይደክም ተደራዳሪና ተከራካሪ ነበረ፡፡ የተጠማ ያገኘውን ጠጪም እውቀት ፈላጊ አይነትም ነበረ፡፡ ከሚታመን በላይ ብልጥ ነበር፡፡ትልቁን የጨዋታውን እቅድ መመዘን የሚችል ነበር፡፡ ያጋጠሙት አሳሳቢና ያልተለመዱ አጋጣሚዎች አስተምረውታል፡፡

ለበርካታ ጊዜያት እንደ መንግስትና እንደ ወዳጅ ያልተጋጨንባቸውና ያልተስማማንባቸው ወቀውቶች አልነበሩም አይባልም፡፡ ስንከራከር፤ ስለኤኮኖሚ ስለ ዴሞክራሲ፤ ስለ ስብአዊ መብቶች፤ ስለአካባቢ ደህንነት፤ ወይም የየግላችን የውጭ ግንኙነት ፖሊሲም ስንከራከር በተለይ ሁለት ጉዳዮች ያገርሙኝ ነበር፡፡ መለስ በተከታታይነት በአመለካከቱ ምክንያታዊ፤ በውሳኔዎቹም በሚገባ የሚያስብ ነበር፡፡ የሚመራውም በፍልስፍና ሳይሆን፤ወደፊት ስለሚታየው የውድ ሃገሩ እድገትና ልማት እንጂ፡፡በድርድራችንና በውይይታችን ወቅቶች የምናነሳቸው ጠቃሚ ነጥቦች በሞቱ ይጎድሉብኛል፡፡

ራይስ በስንብት ጫጫታዋ መለስ አሰቃቂ ስለሆነው የሰብአዊ መብት ጥሰት ሬኮርድ ጨርሳ ታውራ ነበር፡፡ የራሷ የአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት ያወጣውን የ2011 የሰብአዊ መብት ጥሰት ሜይ 2012 የወጣውን ዘገባ  ሆን ብላ ችላ ብላዋለች፡፡ ዘገባውም፡-

በኢትዮጵያ አግጥጦና በግልጽ የሚታየው የሰብአዊ መብት ጥሰት መንግስት 100 የፖለቲካ ተቃዋሚዎቹን መሪዎች፤ ንቁ የፖለቲካ ተሳታፊዎችን፤የነጣውን ፕሬስ አባላት፤ ማሰሩ ነው፡፡ መንግስት የፕሬስ ነጻነትን አፍኗል፤ የመያዝና ለእስር መዳረግን፤ ጥቃትን በመፍራት ጋዜጠኞች በራሳቸው ላይ ሳንሱር ማድረግ ግድ እየሆነባቸው ነው፡፡ የችሮታና መንግስታዊ ያልሆኑ ድጋፍ ሰጪዎች ላይ የተደቀነው እገዳና አዲስ ደንብ፤……ሌሎች የሰብአዊ መብት ጥሰቶች በዘፈቀደ በየቦታው መያዝ፤መታገት፤ያለክስ በእስር መጉላላት፤ ማለቂያ የሌው የቀጠሮ ጊዜ፤ያለፍርድ ቤት ተእዛዝ የግለሰቦች መኖርያ ብርበራ፤አላስፈላጊ በሆኑ ሰበቦች ክስ መመስረትና ማስረጃ ሳይኖር አስሮ ማስፈረድ፤………የሚል ነበር፡፡

ራይስ እንደገናም በኦክቶበር 2ር›› 2012 ‹‹ለጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ መታሰቢያ ጸሎት በጥቂት አፍቃሪ መለሶች በተዘጋጀበት ስርአት ላይ ተገኝታ ነበረ›› በአቢሲኒያ ቤተክርስቲያን ተገኝታ ያደረገቸው ሁለተኛው ውዳሴዋ፤

እንደገና አመጣጤ እንደ አሜሪካን መንግስት ወኪልነቴና በግል እጅጉን ላጣሁት ሰው ወዳጅነቴም ነው፡፡ እኔ የማውቀው ለሰብአዊ መብት ተጨናቂና በተጨበጠ ነገር የሚመራ ሰው ነበር፡፡ ምናልባትም መለስ በአካባቢው ካሉት ሁሉ እጅግ ብልህ ነኝ ብሎ ያስብ ይሆናል:: እናም ብዙ ጊዜ እሱ ልክ ነበር፡፡ ትቶት ያለፈው ውርስ ከአፍሪካ ፈጣን የኤኮኖሚ ዕድገት ማስገኘትን ነው፡፡ ለኢትዮጵያ የፈጣን እድገት መሰረት ጥሎላታል፡፡ ስለ ዓየር ጠባይ ለውጥም ለአፍሪካ ታላቅ አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡ ለሕዝቦቹም የምግብ ምርት እድገቱ በእጥፍ እንዲያድግ ሲያደርግ ያ በተደጋጋሚ ሕዝቡን ለሞት ሲዳርግ የነበረው ችጋርም ዳግም እንዳይከሰት ዘዴ ፈጥሯል፡፡………..›› እና ሌሎችም ድርጊቶች ማከናወኑን በመግለጽ እዚያም ተንጫጭታ ስታጠቃልል፤‹‹የመለስ ዜናዊ መንፈስ ለበለጠ ስራ ለአንድነት እና ለተሸለች ኢትዮጵያ እንድንሰራ ይኮርኩረን፤ ለተሻለች አፍሪካ፤ ለተሻለ ዓለም፡፡›› አለች፡፡

ሱዛን ራይስ 2005 ምርጫን ተከትሎ ባዶ እጃቸውን ለመብታቸው ጥያቄና ሕገ መንግስቱ እንዲከበር ለማስገደድ ሰላማዊ ተቃውሞ በማድረግ ላይ የነበሩትን ኢትዮጵያዊያን ሕገ መንግሰቱን በመተማመን ባዶ እጃቸውን የወጡትን ከአፍ እስከገደፋቸው ዘመናዊ መሳርያ በታጠቁና የግዳጃቸውን ተልዕኮ በቀጥታ ከመለስ ዜናዊ ብቻ በሚቀበሉት በፖለስና በደህንነት አባላት በተከፈተ ተኩስ 200 ንጹሃን ዜጎች ለሞት መዳረጋቸውንና ከ800 በላይ ደግሞ የመቁሰል አደጋ እንደደረሰባቸው ለዚህም ትዕዛዙን በሏቸው ብሎ ያስተላለፈው ይሄው በራይስ ጫጫታ ክብርና ሞገስ የተቸረው መለስ ዜናዊ መሆኑን ጨርሶ ችላ ብላ አልፋዋለች፡፡

በ2004ም በጋምቤላ ስለተፈጸመው የሰብአዊ መብት ጥሰትና ጅምላ ጭፍጨፋ ዓይኔን ግምባር ያድርገው ብላ ሽምጥ ክህደት ፈጽማለች፡፡መለስ በ2010 በተሰረቀና በተጭበረበረ የምርጫ ሂደት 99.6 በመቶ አሸንፌያለሁ በማለት፤የፓርላማ ወንበሮችን የብቻው ንብረት ማድረጉንም እያወቀች ግን አታስታውስም፡፡ራይስ ያን የመሰለ ውዳሴዋን ስትዥጎደጉድ በሺ የሚቆጠሩ የፖለቲካ እስረኞች፤በእስር ላይ ያሉ የተቃዋሚ ፓርቲዎች አመራሮች፤ የነጻው ፕሬስ አባላት፤ በእስር ለበርካታ ጊዜያት በመማቀቅ ላይ መሆናቸውን ወዳ የዘነጋችው ይመስላል፡፡ ያንን ሁሉ ሁልቆ መሳፍርት የሌለውን የውዳሴ ጫጫታ ስታስተጋባ ይታያት የነበረው፤ተወዳዳሪ የሌለው ብልጠቱ እንጂ  አላዋቂነቱ ብልጭም አላለላት፤ከፍተኛ ችሎታው እንጂ የልቡ ጥቁረትና ጭካኔ አልታወሳትም፤ በማያወላዳ ብልጣብልጥ ነበር ትበለው እንጂ ከንቱነቱ አልታወሳትም፤ስለ ዴሞክራሲና ሰብአዊ መብት ጥልቅ የሆነ አለመግባባት እንደነበራቸው ብታስታውስም ያንን ግን በመሃከላቸው የነበረው የጠበቀ ወዳጅነት እንድትረሳው አድረጓታል፡፡

በእጅጉ አስገራሚ የሆነው ደግሞ በኖቬምበር 23 2011 ራይስ ኪጋሊን በጎበኘችበት ጊዜ ጸጸት የተሞላበት ንግግርዋን ያዘነች አስመስላ ማቅረብ ታውቅበታለችና፤ በአዲስ አበባ ባደረገችው ውዳሴ ጫጫታው ወቅት ልትለው ተገቢ ይሆን በነረ መልኩ ስትመልስ፡

ዛሬ እዚህ ያለሁት የአሜሪካንን መንግስት ወክዬ ነው፡፡ በሌላ በኩልም በግሌም ከልቤ ነው ለመናገር ይምፈልገው፡፡ እኔ ሩዋንዳን ለመጀመርያ ጊዜ የጎበኘሁት በዲሴምበር 1994 የጅምላ ጭፍጨፋው በተካሄደ ስድስት ወራት በኋላ ነው፡፡ በዚያን ጊዜ በሁዋይት ሀውስ  የብሔራዊ ደህንነት ወጣቷ ዳይረክተር ነበርኩና የወቅቱን የብሔራዊ ደህንነት አማካሪውን አንቶኒ ሊክ አጅቤ ነበር የመጣሁት፡፡ ያን ጊዜ የተባበሩት መንግስታትንና ሰላም ጥበቃን በተመለከተ ሃላፊነቱ የኔ ነበር፡፡ በወቅቱ በተወሰደው ልፍስፍስ ውሳኔ ሳቢያ የተከተለውን አሰቃቂ ውጤት በዓይናችን ለመመልከት ስንበቃ፤ ያንን ውሳኔ የወሰዱትን ሃገራት የኔንም የናንተንም ሃገራት በእጅጉ የሴኪውሪቲ ካውንስሉንም አባላት ለትዝብት እንዳበቃ ተረድቻለሁ፡፡

በዚያ ቤተ ክርስቲያንና በአጎራባቹ  ጭፍጨፋው በተካሄደበት ትምህርት ቤት ጎዳናዎች መራመድ ያሳደረብኝን ታላቅ ድንጋጤ ጨርሶ ልረሳው አልችልም፡፡ ከስድስት ወራት በኋላ አካባቢው ለሰላም እንቅስቃሴ ሊውል ሲገባ እስካሁን ድረስ የበሰበሱ የንጹሃን አስከሬኖች መታያና መከማቻ ሆኗል፡፡ በነዚያ የሙታን በድን ላይ መረማመድና ባጠገባቸው ማለፌ  የሰው ልጅ በሰው ልጅ ላይ እንዲህ አይነት ግፍና ጭካኔ ሊረው እንደሚችል አስታዋሽና የማይጠፋ ጠባሳ ጥሎብኛል፡፡ዛሬ በማከናውነው ተግባሬ ላይ እነዚህ የንጹሃን አስከሬኖች አብረውኝ ይኖራሉ፡፡ጨርሶ እንደማይረሱኝ በማረጋገጥ ወደፊትም ይህን መሰሉ የጅምላ ጭፍጨፋ እንዳይደገም ማስታወሻ ይሆነናል፡፡

አላስፈላጊና አጥፊ የሆነው ይህን መሰሉ ተግባር ለመከላከል ለሁላችንም በተለይም ለሱዛን ራይስ ምን ያህል አስፈላጊና አሳሳቢ ይሆን፡፡ ሕግን በማፍረስ ስቃይ፤ እስራት፤በዘፈቀደ መታገት፤ያለክስ እስር፤ የሚጠየቅ የተጨማሪ እስር ቀጠሮ፤የዜጎች ግላዊ መብት መጣስ፤ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ ብርበራ ማካሄድ፤ በነጻነት ላይ የሚጣል ገደብ፤የመሰብሰብ ነጻነት እገዳ፤ ማህበራት፤እንቅስቃሴዎች፤ መከልከል…….. በአፍሪካ አህጉር?

ሱዛን ራይስና የኢትዮጵያ ጣዕረሞቶች

በሴፕቴምበር2 እና በኦክቶበር 27 2012 ባዶ እጃቸውን በወጡ ንጹሃን ኢትዮጵያዊያኖች ላይ የደረሰው የሞት አደጋ ጭፍጨፋ፤ በአነጣጥሮ ተኳሾች በጎዳና ላይ የተቀጠፉት ኢትዮጵያዊያን ዜጎች፤ ለራይስ ምንም ማለት አይደሉም ትውስታም አላሳደሩባትም፡፡ዛሬም ቢሆን በኢትዮጵያ ወህኒ ቤቶች ስቃይ የሚቀበሉትንና ፍዳቸውን የሚያዩ ንጹሃን አይታወሷትም፤ራይስ በሩዋንዳ የተካሄደውንም ጅምላ ጭፍጨፋ ላለማስታወስ ሕሊናዋን ሆን ብላ ዘግታው ነበር፡፡በ2012 በኢትዮጵያ ለተፈጸመው ግድያና የሰብአዊ መብት ጥሰት ደንታ የላትም፡፡ከአፍሪካ ጭራቅ ፈላጭ ቆራጮች ጋር እጅን ጓንት የሆነና በፍቅር የሰከረ የሃገር አስተዳዳሪ ለአሜሪካ አየስፈልጋትም:: አሜሪካ ያየሁትን አላየሁም የሰማሁትን አልሰማሁም የተናገርኩትን አልተነፈስኩም ባይ ሹም አያስፈልጋትም:: አሜሪካ ልበ ድንጋይ የሆነ የአዞ እንባ አንቢ ሹመኛ አያስፈልጋትም፡፡አሜሪካ የሚያስፈልጋት የሃገር አስተዳደር የሚያዩ አይኖች ያሉት፤የሚያዳምጡ ጆሮዎች፤የሚናገሩ አፎች፤ የሚያመዛዝን ሕሊና፤የሰብአዊ መብት ጥሰትን ከመንግስታት ስህተት የሚለይ እንጂ፡፡

ማንም ቢሆን ወንድን ይሁን ሴትንም በጓደኞቻቸው ማንነታቸውን ማወቅ ይቻላል የተባለው ሃቅ አይደለምን?

*የተቶረገመው ጽሁፍ (translated from):

http://open.salon.com/blog/almariam/2012/12/10/susan_rice_and_africas_unholy_trinity

(ይህን ጦማር ለሌሎችም ያካፍሉ::) ካሁን በፊት የቀረቡ የጸሃፊው ጦማሮችን  ለማግኘት እዚህ ይጫኑ::

http://www.ecadforum.com/Amharic/archives/category/al-mariam-amharic

http://ethioforum.org/?cat=24

 

 

Leave a Reply