ኢትዮጵያ፡ ሕብረት በዓምልኮት (ዓምልኮተ ሕብረት) ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም

Click here for PDF

ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ

አንድ ህዝብ፤ አንድ ሃገር

ላለፉት ሁለት አሰርት ዓማታት ኢትዮጵያ የሰብአዊ መበት ጥሰት፤ የወንጀል እና ጸረ ተፈጥሮ፤ ድርጊት መታያ ሃገር ሆና ከርማለች፡፡ አሁን ግን የሃይማኖት አባቶች  እስላም ክርሰቲያኑEthiopian Muslims and Christians በአንደነት በመቆም  ዓምለኮታቸውን ለማስከበር ትግል ጀምረዋል፡፡ የሙስ ሊሙና የክርስትና ሃይማኖት መሪዎቻቸውና ተከታዮቻቸው፤ አንድነት በመሆንና ሕብረት በመፍጠር የሃይማኖት ነጻነታቸውን ለማስከበር እጆቻቸው ላለመላቀቅና ሕብር ሆነው ለመኖር ተያየዘው ህሊናዊ አስተሳሰባቸውብ በነጻነት ለመጠቀም እንዲችሉ ውህደታቸውን አረጋግጠዋል፡፡ይህንንም ለማክሸፍ ጠንካራ ጉልበቱን የተማመነ ሃይል ውህደታቸውን ለማፈራረስና አለመግባባት ለመፍጠር በተንኮል የተሳለ ምላሱን ጎልጉሎ ተጋርጦባቸዋል፡፡በቅርቡም ከማያልቀው የእርግምት አስተሳሰበ የተወለደ ሁለቱን በአንድነት የኖሩና በመሃላቸው እንከን ያለነበረባቸውን ሃይሞኖቶች ለማጋጨት እኩይ ነገር ተጭሮ ነበር፡፡ የገዢው ፓርቲ ቁንጮ ውሸት አይታክቴ ተንኮል ምሳ ራቱ፤ በፈቀደው መንገድ እየጎተተ ለሚመራውና ያሻውን ‹‹አዎን›፤እሺ›› ለሚያሰኘው ፓርላማው እንዲህ ብሎ ውንጀላ አቅርቦ ነበር፡፡

በቅርቡ የጥምቀት በዓል እለት አንድ ሃገር አንድ ሃይማኖት የሚል መፈክር ነበር፡፡  መፈክሩን ያነሱት ደግሞ ጥቂቶች ነበሩ፡፡ እኛ ደሞ አንድ ሃገር አንድ ሃይማኖት የሚል ህገመንግስት የለንም፡፡አንዳንድ በቁጥር አናሳ የሆኑ በኢትዮጵያ የክርስቲያን መንግስት ብቻ እንዲኖር የሚመኙ አሉ፡፡ እነሱም በትምህርት ወደ ህሊናቸው  ሊመለሱ ይችላሉ፡፡ ማንም ቢሆን ሳላፊ የሆኑት ሁሉ አልቃይዳ ናቸው ማለት አይችልም፡፡ ይሄ ስህተት ነው፡፡ ግን እርግጥ ሁሉም አልቃይዳዎች ሳላፊስ ናቸው፡፡በኢትዮጵያ ለመጀመርያ ጊዜ የአልቃይድ ቡድን ተገኝቷል፡፡ የዚህ ቡድን አባላት በሙሉ ሳላፊ ናቸው፡፡ይህ ማለት ግን በኢትዮጵያ ያሉት ሳላፊ በሙሉ አልቃይዳ ናቸው ማለት አይደለም፡፡ አብዛኛዎቹ አይደሉም፡፡ እነዚህ ሳላፊዎች ግን ትክክለኛውን የማስተማር መንገድ የሳቱ ናቸው፡፡ እነዚህ  ሳላፊዎች በኢትዮጵያ አብዛኛው ሕብረተሰብ ሙስሊሞች ናቸው ይላሉ፡፡ ትክክለኛው የሕዝብ ቆጠራ ግን ይህን አያሳይም ይላሉ፡፡ እነሱ እንደሚሉት አባላጫው ቁጥር ሙስሊሞች ስለሆኑ መንግስቱ የሙስሊም መሆን አለበት ነውየሚሉት፡፡ ይህ አመለካከት ደግሞ አሰባስቧል፡፡

በአክራሪነት ላይ፤በጎጠኝነት ላይ፤በሃይማኖቶች ላይ እሳት መጫሩ ማንን ነው የሚጠቅመው?አንድ ሃገር አንድ ሃይሞነት የሚለውንስ የቁራ ጩኸት ማን ነው ከጀርባ ሆኞ የሚያስተጋባው?  ከሴብቴምበር 9/11 በኋላስ የአልቃይዳን ተክል ማን ነው የዘራው? አሁን በኢትዮጵያ ያለው ከፍተኛ ችግር  የእስልምና መንግስት በሚሉና የክርስቲያን መንግስት በሚሉት መሃል ያለ ግብግብ ነው? ኢትዮጵያን የገጠማት እልህ አስጨራሽ ችግርስ በዴሞክራሲና በፈላጭ ቆራጭ ገዢ መሃል ያለው ልዩነት ነው ወይስ የእስልማናና የክርስትና አክራሪነት ነው? አል ቄይዳስ ለኢትዮጵያ ፈታም ችግር ነው? ወይስ የኢትዮጵያ ነቀርሳ የሆነው በኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይ የተጫነው የአንድ ሰው አንድ ፓርቲ ስርአት ነው?  የእስልምና አክራሪነት በአሁኑ ወቅት ለኢትዮጵያ ዋነኛው ችግር ነው? የክርሰቲያን አክራሪነትስ ቢሆን? ኢትዮጵያን ወጥሮ የያዛት ችግርስ አልቃይዳ ነው? ወይስ በሙስና የተዘፈቀውና ብቸኛው የኢትዮጵያ ዋነኛ ችግር ቀፍድዶ ያዛት አንድ ሰው አንድ ፓርቲ የሚለው ፈላጭ ቆራጭ ግፋዊ አገዛዝ ነው?

በሃይማኖቶች መሃል ቅራኔዎችን ለመዝራትና ሙስሊሙንና ክርስቲያኑን ለማበጣበጥ የሚደረገው  ውጤት አልባ መንደፋደፍ  የገዢው ፓርቲ  የግፍ አገዛዝ፤ ለፈላጭ ቆራጭ ስርአታቸው እድሜ ማራዘሚያ የሚጠቀሙበት ኤጭ የተባለ ስትራቴያጂቸው  በመሆኑ ቁንጮው የሃገር ጦስ መለስ ዜናዊ ይህን እንደፖለቲካ ነበልባል ሊያጫርስ ይችላል በሚል እመነት ነው አሰካክቶ ያቀረበው፡፡ የኢትዮጵያ ሕገ መንግስት  ስለ አንድ ሃገርና አንድ ሃይሞኖት አይደለም፡፡ ያንን የችግር እሳት ጫሪ የሆነውን አባባል በመጠቀም፤ ታላቁን የሕዝቡን የጉዳይን ሃሳብ ገለል በማድረግና አቅጣጨውን ለማስቀየር ሲል፤ ጭብጡን ከሕገመንግስቱ ሃማኖታዊ ትንታኔ አውጥቶ ሌላ መንገድ ሊያስዬዘው ይጥራል፡፡የሕገ መንግስቱ አንቀጽ 11 በግልጽና በቀጥታ እንዳስቀመጠው፡- ‹‹የመንግስታዊ ሃይማኖትየለም: መንግስትም በሃይማኖቶች ጣልቃ አይገባም፤ሃይማኖቶችም በመንስት ጣልቃ አይገቡም፡፡ አንቀጽ 27ም ቢሆን አጠናክሮ የሚያስረዳው፤‹‹ሁሉም የነጻነት፤ የአስተሳሰብ እና የሃይማኖት ነጻነት  አለው፤ ይህም መብት በራሱ ፈቃድ ላይ የተመሰረተ እምነት ሊኖረው፤ ብግለሰብም በቡድንም በተናጠልም በመሰባሰብም፤በዓምልኮት ቦታዎች እምነቱን ሊያካሂድ፤ ሊያስተምር እንደሚችል በግልጽ ያስቀምጣል፡፡ማንም የማንንም እምነት ያለፈቃዱ እንዲቀበል ማስገደድ አይችልም፤ይህን ማድረግም የምርጫ ሃይማኖቱን መድፈር ስለሚሆን አይፈቀድም፡፡

‹‹ሃይማኖት የግል ምርጫ ጉዳይ ነው፤ሃገር ደግሞ የጋራ ሃላፊነት ነው››

የታወቁ የሙስሊሙና የክርስቲያኑ መሪዎች፤በሃይማኖታዊና፤የፖለቲካዊ አክራሪነት ላይ ተጋሪ አይሆኑም፡፡በማንኛውም ጊዜ ቢሆን የየትኛውም እምነት መሪ በሃገሪቱ ውስጥ የዚህ ሃይማኖት ተከታይ መንግስት ብሎ ተናግሮ እንደማያውቅ እንጂ ብሏል ለሚባለው መላው የጠፋ የተፈበረከ ውንጀላ ማሰረጃ ማቅበር አይቻልም፡፡ ሃይማኖቶችን ለመከፋፈል የተቀረጸው የሚያሳፍረው ተንኮላዊ ሙከራ በግልጽ የሚታይ ነው፡፡ ማንም ቢሆን የአልቃይዳን የተፈበረከ ኢትዮጵያን መቆጣጠር ቅዠት ማንም አያምንም ወይም ፈንድሜታሊስቶች የኢትዮጵያን መንግስት ለመውረስ ያስባሉ ብሎ አያምንም፡፡ የክርስታናና  የሙስሊሙ እምነት ተከታዮች አንድነትና ሕብረት በሃይማኖት ነጻነት ላይ ያላቸው ውህደት ለሌላው ዓለም ምሳሌ ነው፡፡

በቅርቡ በካናዳ ቶሮንቶ፤የሙስሊሙና የክርስታናው ሃይማኖት እምነት ተከታዮች ለውጪ ኢንቬስተሮች የእርሻ ቦታ ለመሸጥ በሚል ሰበብ የቆየውንና የእምነትና የሃገር አውራ የሆነውን  የዋልድባ የእምነት ገዳም ከተሰነዘረበት ደባ ለማዳን ጥሪ ለማቅረብ በአንድነት ግንባር ፈጥረው ከውጭ ኢንቬስተሮች የማፈራረስና የማውደም እኩይ ተግባር እንዲድን ጠይቀዋል፡፡ ገዢው ፓርቲ በአሁኑ ወቅት በዋልድባ ባጠገብ የሚገኘውን ገዳም አፍርሶ ለሸንኮራ አገዳ ማምረቻ እርሻ ለመስጠት በመዘጋጀት ላይ ነው፡፡የኢትዮጵያ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን  ሊቀ ካህናት መሰለ እንግዳ በክርስቲያኑና በሙስሊሙ አማኞች መሃል ያለውን ታሪካዊ የጠነከረ ሁኔታ እንደሚከተለው ገልጸውታል፡፡

የሙስሊሙ እምነት ተከታዮች ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ሃገሪቱን በመጠበቅ ከፍተኛ ሚና የተጫወቱ ናቸው፡፡ታሪክ መዝግቦ እንዳስቀመጠው የሙስሊም ሕብረተሰብ አባላት አባቶች የኢትዮጵያን ነጻነት ለማስጠበቅ ከጠላት ጋር ተዋግተዋል፡፡የኦርቶዶክስ ሃይማኖትን የሚጎዳ ሁኔታ ሲፈጠርም የሙስሊሙ ህብረተሰብ አባላት ወገኖቻችን ከጎናችን ቆመው አብረውን ችግሩን ተጋፍጠዋል፡፡ዛሬም የቶሮንቶ የሚስሊሙ አማኞች መሪ አብረውን ቆመዋል፡፡እንደምታውቁት በአሁኑ ሰአት የሚስሊሙ ሕብረተሰብ እህቶቻችንና ወንድሞቻችን ፈታኝ የሆነ መከራና ችግር ተጋርጦባቸዋል… ሁላችንም በህብረት አብረን እንቆማለን፡፡

የኢትዮጵያ ተዋህዶ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች በመላ፡፡ ከጨለማው ሃይልና አንዳችም ፍሬ ከማያፈረው ጋር ህብረት አትፍጠሩ፤ጥንታዊቷና ታሪካዊዋ ኢትዮጵያ የጥቁሮች ሁሉ ነጻነት አብሳሪዋ ኢትዮጵያ፤በዚህ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ታላቃ አደጋ ገጥሟታል፡፡የገዢው ፓርቲ የወያኔ ኢንቫየርሜንታል ፕሮግራም (ለም መሬትን ለውጭ ነጋዴዎች ማከፋፈል) ሃይማኖታችንንና እምነቶቻችንን እያጠፉት እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ የወያኔ ውጥንቅጥነትና ግርግር ሽብር በኢትዮጵያ ላይ ታላቅ ሃፍረትን እያስከተለባት ነው፡፡ ቀደም ሲል የወዲ ዜናዊና የአባ ገብረመድህን የቤተክህነቱ አስተዳደር ከገዢው ፓርቲ ጋር ግምባር ፈጥረው በቤተክህነቶች ላይ የመቃጠል አደጋ፤እስራት ስቃይ እና በሃይመኖት አባቶች ላይ የግድያ ተግባር እንዲፈፀም አድርገዋል፡፡ የዝቋላ ገዳምንም ለቃጠሎ ዳርገውታል፡፡ አሁን ደግሞ የስኳር ፋበብሪካ በሚል ሰበብ የዋልድባ ገዳምን ለቤተክህነታችን ዋነኛ ቅዱስ ስፍራ የሆነውንና ታሪካዊውን ገዳም ለማፈራረስ አቆብቁበዋል፡፡ ምሁራን የፈለቁበት ስፍራ ነው፡፡  አባቶቻችንም ከአደጋ ለመከላከል ሲሉ ለዋልድባ ቆመው ደማቸውን አፍሰዋል፡፡ ሞተዋል፡፡ በመሆኑም የዋልድባን ነዋሪዎች የንግድ እርሻ ለመጀመር፤ እንዲሁም የአባቶቻችንን ቅሪት በማስቆፈር ማንከራተት ማፈናቀል፤ እጅጉን አሳፋሪና አዋራጅ ተግባር ነው፡: የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ ምን ተስባለህ፤ ምን እያየህ ነው፤ የሃይማኖት ገዳማት ሲፈርሱና የአባቶቻችን አጽም ካረፈበት ተቆፍሮ ሲጣል፤የኢትዮጵያ አብያተ ክርስቲያናት ሲዋረዱና ሲቃጠሉ የሃይማኖት አባቶች ምን ሚና እየተጫወቱ ነው፡፡

ሃጂ ሞሃመድ ሰይድ የሃገሪቱን አንድነት በተመለከተ የሁላችንንም ግዴታ እንደሚከተለው አስቀምጠውታል‹‹

… እንደምታውቁት ኢትዮጵያ የተለያየ ሃይማኖት፤ያለባት በተለይም ኦርቶዶክስና ሙስሊሙ፤ለረጂም ዘመን፤የኖረባት፤የተማከለባት የተዋደደባት ሃገር እንደሆነች በታሪክ የተመዘገበ ነው፡፡ ኢትዮጵያ በኛ እንኳ እድሜ በ50 ዓመት እንደዛሬ ያለ ችግርና መከራ ኢትዮጵያ ደርሶባት አያውቅም፡፡ሃይማኖት የግል ነው፡፡ሃገር ግን የጋራ ነች፡፡ሃገር ከሌለ ሃይመኖት የለም፡፡ሃገር ላይ ነው ሁሉ ነገር የሚገኘው፡፡በአሁኑ ወቅት ላይ ኢትዮጵያ በሃይማኖቷ ጸንታ የኖረችው ሃገር፤ፈራርሳለች፡፡ ሙስሊሙን ከክርስቲያኑ ጋር ለማጣላት፤ረጂም ጊዜ ዘመቻ ተደረገ፡፡ አልተሳካም፡፡ኦሮሞውን ከአማራው ጋራ ለማጋጨት ተጣረ፡፡ አልተሳካም፡፡ አሁን የሃይማኖት መሪዎቹ ቀደም አድርገው ተናግረውታል፤ በኢትዮጵያ ሙስሊም በአሁኑ ወቅት ላይ፤እኛ እምናውቀው በታሪክ ተመዝግቦ፤እስላም ማለት አንድ አይነት ሙስሊም ነው፡፡ የሰውም አይፈልግ አደራ ሚቀበል፤አደራ የሚያደርስ፤እስላም ካበለ፤ ሰማይ ካልዘነበ፤ሃገር ጠፋ ነው፡፡ አደራ ሚሰጠው ዱሮ፤ለወንድሞቻቸው ለሙስሊሙ አደራህን  ብሎ ማንኛቸውም ወገን ሁሉ፤ለልጄ ይህንን፤አድርስለት ሲባል፤የማይቀንስ የማይጨምር የነበረውን፤ከሊባኖስ ሌላ የተፈጠረ ሃይሞኖት አምጥተው፤ኢትዮጵያን እያበጣበጧት ነው፡፡

ዛሬ እንደምታውቁት አርብ ነው፡፡አርብ ወደ መስጊድ እንጂ ወደ ስብሰባ ወደ ዓለማዊ ጉዳይ መምጣት ባልተገባኝ ነበረ፡፡የሃገር ጉዳይ ነው፡፡ሃገር ከሌለ፤ሃይማኖትን ማስከበር፤ ለጸሎት የማይመችበት ጊዜ ነው፡፡አብያተ ክርስቲያናትና ገዳማት ተከብረው የኖሩት፤በሙስሊሙም በክርስቲያኑም ነው እንጂ፤የኢትዮጵያ ቅርስ ነው፡፡ የሃይማኖት መሰረቱ፡፡ ደብር ማለት፤ እንደምናውቀው፤ቅጠል በልተው፤ጥሬ ቆርጥመው፤ውሃ ጠጥተው የሚኖሩባት ሃገር እንጂ፤ለቻይናና ለህንድ ኢትዮጵያ ተሸጣ፤ ሰዉ ዛሬ ያያችሁት እንደሆነ ዳገት እየቆፈረ ቆፍር ተብሎ በራበው አንጀቱ ላይ አካፋና ዶማ ይዞ ሲጭር ያውላል::  በራበው አንጀቱ ላይ አካፋና ዶማ ይዞ ሲጭር ይውላል፤ሲጥር ያመሻል፤ ይሄ ለኢትዮጵያ ትልቅ ውርደት ነው፡፡ሜዳውን ሸጠውታል፤ለሙን መሬት ይዘውታል፤ገንዘቡ ሃገራችን ላይ የለም::

የኢትዮጵያ ትውልድ አለ ወይ በአሁኑ ወቅት? ዩኒቨርሲቲ የገባው ወጣት፤ሞራሉ ወርዶ፤ተነክቶ፤ጫት እያላመጠ፤ሲጃራ እያጨሰ፤ትውልድ እንዲጠፋ አድርገውታል፡፡ እኔ በእውነት፤እንዲህ ያለ አመራር፤እንዲህ ያለ አስተዳደር፤በዓለም ላይ በወገኑ ላይ ፤ በደል የሚያደርስ፤ታሪክ አላነበብኩም፡፡ ስለሆነም፤በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት የደረሰውን ችግርና መከራ ለመግለጽ፤ለያንዳንዳችን አንድ ቀን ቢሰጠን አይበቃም፡፡ እንግዲህ ከሃይማኖት ከማጥፋት የበለጠ በደል አለ? የለም፡፡ አለእንዴ? (ብለው ላቀረቡት ጥያቄ ተሰብሳቢው ሕዝቡ በአንድ ቃል የለም ሲል መለሰ) ሃይሞነት ከጠፋ ኢትዮጵያ የለችም ማለት ነው፡፡ ስሟ ብቻ ካርታ ላይ ኢትዮጵያ የሚባል እንጂ፤የውጭ ሃገር እንደሆነ መሬቱን ገዝቶታል፤ገንዘባቸውን አሻግረዋል፤በገንዘባቸው ይጠቀማሉ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ግን፤ ዘጠኝ ባንዲራ ተተክሎ፤እነሱ የለሉ ለት፤ለዘጠኝ ተከፍለን ስንታኮስና ስንጋደል እንድንኖር፤ በፕሮግራማቸው ላይ ያዘጋጁልን ስለሆነ፤ የሃይሞነት፤ የዘር፤የጎሳ፤ልዩነት ሳናደርግ፤ኢትዮጵያን እንድንታደጋት፤የታሪክ ሃላፊነት አለብን፡፡

ልጆቻችንና የልጅ ልጆቻችን፤እንዲሁ እንደኛ እንደተሰደዱ ሊኖሩ ሃገር እንደናፈቃቸው ትውልዱ መበተኑ ነው፤ እስቴ እንዲያው ቆም ብለን ሌትም ሆነ ቀን ስናስበው፤ያሁኑን አስተዳደር የመሰለ በኢትዮጵያ ላይ ተፈጥሮ ታሪክ አንብባችሁ ወይም ለዚህ የደረሳችሁ ሰዎች አይታችኋል? (ብለው ላነሱት ጥያቄ ተሰብሰዳቢው አላየንም ብሎ መለሰላቸው) ስለዚህ የመፈክር ብቻ ሳይሆን ሙስሊሙም፤ሌላውም ሃይማኖት ተከታይ፤ አቤቱታችንን  ለማይናወጠው ለዓምላካችን አቤቱታ ማቅረብ፤ ደግሞ፤ መሰረት መጣል አለብን፡፡  እኔ ለደረስኩበት በኢትዮጵያ ላይ፤ አንበጣ፤ ዘይሪ ተምች የሚባል አውሬ ነበር፤ በዚያን ወቅት ላይ የሃይማኖት መሪዎች  ሙስሊሙም ወደ አላህ ዱሮ ዱሮ ዱሮ ይላል ክርስቲያኑም ደግሞ፤ እነዚህኑ ጸሎቶች በቤተክርስቲያንና በየአድባራቱ አድርሷል፡፡ በዚያን ወቅት ላይ ፈረጃ ወይም መልእክት ይተላለፍ ነበር፡፡ ስለዚህ በሃይሞኖታችን ጸንተን፤ ለአንድነታችን ደግሞ ጠንክረን ሃገራችን ኢትዮጵያን፤ እምንጠብቅበት ባለአደራዎች ስለሆንን  እውጫ ያለነው፤ ከኢትዮጵያ ክልል ውጭ ያለነው ደሞ ወንድሞቻችን ልጆቻችን በአሁኑ ወቅት ላይ ትውልድ እንዲጠፋ የተደረገ ስለሆነ፤ ሁላችሁም የተቻላችሁን ያህል እርዳታ ማድረግ አለባችሁ፡፡ የገነዘብ ብቻ አይደለም፤ የሞራል ድጋፍ መስጠት አለብን፡፡ መምከር አለብን፤ኡኡ ማለት አለብን፡፡ ከዚህ በኋላ ብዙ ቢናገሩት፤ሚዛኑ ሊሞላ ስላማይችል ንግግሬን እዚህ አቆማለሁ፤ ኢትዮጵያ በሠላም የምትኖርበት፤ ይህ አስተዳደር የሚለወጥበት፤ በአንድነት ሁነን፤ ወደ ዓምላካችን እንለምን እያልኩ ንግግሬን እዚህ ላይ አቆማለሁ፡፡

ብዝሃ ሃይማኖቶች፤ ሃገር አንድ ብቻ!

በኢትዮጵያዊያን መሃል ‹‹ሃይማኖት የግል ምርጫ መሆኑን፤ ሃገር ግና የጋራችን›› መሆኑን  ሃጂ ሞሃመድ ሰኢድ በአጽንኦት አስረድተውናል፡ ሊቀ  ካህናት መሰለ እንግዳ  ሙሲሊማኑና ክርስቲያኑ በኢትዮጵያ ውስጥ በታሪካቸው ሁሉ በሰላማዊና በመተሳሰብ በመተጋገዝ፤ አብረው እንደኖሩ በ ትክክል  ሁኔታ አስገንዝበውናል፡፡በክርስቲያን ወንድሞቻቸው ላይ ችግር ሲጋረጥ ሙስሊማኑ አብረውን ቆመዋል፡፡ አሁን ደግሞ ሁለቱንም ሃይማኖቶችና አማኞቹን የሚፈትን  ግዙፍ ችግር መጥቷል፡፡ ችግሩ ደግሞ የፈላጭ ቆራጭ አረመኔያዊ አገዛዝና ስላጣንን አለአግባብ የሚጠቀም ስርአት ውልደት ነው፡፡ጉዳዩ ለሃገርና ለእመነት አሳሳቢና አደገኛ ነው፡፡ችግሩም መፍትሄ ሊያገኝ የሚችለው፤በተለያዩ  እምነት ተከታዮች፤ዘሮች፤ቋንቋ ተጠቃሚዎች ኢትዮጵያ ዊያን የጠነከረና የማይፈታ አንድነት ብቻ ነው፡፡ የነዚህ ሁለት ሃይማኖቶች መሪዎች ምሳሌነት፤ ለምእተ ዓመታት ሲካሄድና በተግባርም ሲታይ የኖረውን የሁለቱን ሃይማኖቶች ትስስር በእሳ ላሙና በክርስቲያኑ መሃል የኖረውን  መተሳሰብና አንድነትን ነው የሚያሳየን፡፡የበለጠ አንድነታዊ  መግባባትን የሚጠይቅ ነው፡፡ያለውን እያዳበረ የጎደለውን በመሙላትና በማስተካከል ሊቀጥል ተገቢነቱን  ነው፡፡ይህን ስናደርግ ደግሞ አዲሲቱን ኢትዮጵያችንን ለመቅረጽና የሃይሞኖት ነጻነትም በተግባር የሚረጋገጥበትን ና ማንም ግለሰብ እንደየምርጫው በሚከተለው  ሃይማኖት አስተሳሰቡን በነጻ የሚያራምድበትን መንገድ  መፍጠር  ነው፡፡

የመለያየት ጣጣ ዋጋው

የሃይማኖት አለመግባባት ጣጣ ምን ሊያስከትል እንደሚችል የቅርቡ የናይጄርያ ሁኔታ ሊያስተምረን ይገባል፡፡ በናይጄርያ ውስጥ በተለያየ የህብረተስብ  ክፍል ውስጥ ያሉ ሙስሊማኖችና ክርስቲያኖች አላንዳች ችግር በውህደትና በመግባባት አብረው በመኖር ልማዶቻቸውን እየተካፈሉ፤በስራም አብረው በመሰለፍ በሰላም እንደኖሩ ታሪክ ምስክር ነው፡፡ ከጊዜ ወደጊዜ ግን አንዳንድ መቆራቆሶች እየታዩ ከርመዋል፡፡በአጠቃላይ ግን ሰላማዊ  ሕይወት ይመራሉ፡፡

ባለፉት ጥቂት ዓመታት ግን ሰላማዊው ግንኙነት ፈተና  ገጥሞታል፡፡አንዳንድ አስተሳሰባቸው የተዛባ ስብስቦች በእምነት ቦታዎች በመስሪያ ቦታዎች በመንግስት ቢሮዎች ላይ አደጋ በመጣል ላይ ተሰማርተዋል፡፡ የንጹህ ዜጎች ህወት ማለፍና የንብረት መውደምም አስከትሏል፡፡ የሙስሊሙና የክርስቲያኑ አማኞች ሁኔታው የሃይማኖቶች ልዩነትና አለመግባባት ሳይሆን በመሬት ይዞታ ላያ ያተኮረ ችግር እንደሆነ ይመሰክራሉ፡፡ ለራሳቸው ጠባብ  ግብ ሲሉ ብቻ እሳቤያቸው የጎደለ የፖለቲካ ሰዎች ደጋፊዎች ጉዳዩን የማንነት ጥያቄ በማድረግ ልዩነቱን በማባባስ  ይጠቀሙበታል፡፡ መገናኛ ብዙሃኑም ቢሆኑ የሚያስፈሩ ዘገባዎችን ከነዚሁ እርባና ቢስ ደጋፊዎች ጎን በመሰልፍ ዘገባ በማቅረብ በህብረተሰቡ መሃል ፍራቻን መረበሽን አስከትለዋል፡፡ የሙስሊሙ ጥላ ከለላ የሆነው ጃማ አቱ ናስሪ እስላም የተባለው በናይጄርያ የሚገኝ ድርጅት፤41 ሰዎችን አቁስሎ የ3ቱን ሕይወት ያሳለፈውን የቦንብ ጥቃት በመቃወም በቦስና ቢዩ የተፈጸመውን ድርጊት አውግዟል፡፡ የክርስትና እምነት ተከታይ የሆኑት ፕሬዜዳንት ጉድላክ ጆናታን በዚህ ሰበብ የሚገኘው የሃገር ጥፋት ብቻ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ የአስተዳደራቸው ግንዛቤና መግለጫም እንዳሉት “በክርስቲያኑ ሕብረተሰብና በሙስሊሙ ሕብረተሰብ መሃል የጠነከረ ግጭት የለም፡፡ብድር መመላለሻ ሊሆን አይችልም በመልሶ ማጥ ቃት የሚገኝ ጠቀሜታም ሆነ ለጉዳዩ ማብቂያ ማግኘት አይቻልም፡፡አንዱ ያደረገውን አጸፋ መስጠቱስ የት ሊቆም ነው?፡፡ናይጄርያ እንደ ሃገር መቀጠል አለባት፡፡” ኢትዮጵያም እንደ ሃገር  መቀጠል አለባት፡፡

የአንድነት ፈተና

ለዘመናት ክርስቲያኖችና ሙስሊማኖች በሰላም አብረው ኖረዋል፡፡ያ እንደሚቀጥልም አያጠራጥርም፡፡ በፈላጭ ቆራጭ  አረመኔያዊ  ገዢ ግን ሁለቱም ለአደጋ  ተጋልጠዋል፡፡ የፖለቲካ ሰዎች የከሸፈባቸውን የእምነት መሪዎች ያሳኩታል፡፡ የክርስቲያኑና የሙስሊሙ ሃይማኖቶች መሪዎች አለመግባባትን በማሰወገድና የመግባቢያና የአንድነት ድልድይ በመፍጠር ታላቅ ወሳኝ ሚና ሊጫወቱ ይችላሉ፡፡ በመግባባትን በመከባበር የስራ አንድነትን ሊፈጥሩ ይችላሉ፡፡ የመግባባትን፤የመተሳሰብን፤ዘር በመዝራት የጥላቻና እኩይ አስተሳሰብ ዘር ለመርጨት ሌት ተቀን የሚያንቧችሩትን መርዘኞች ሊያሸንፉ ብቃቱ አላቸው፡፡ ሕግን በማረጋገጥና ነጻነታቸውን ለማግኘት እንደሚናፍቁት ሁሉ፤ ሕዝቡ  መልካም እንዲያስብና የሞራል ብቃትም እንዲኖረው የሃይማኖት መሪዎች ያስፈልጉታል፡፡ የእምነት አባቶች መንገድን ሲያመላክቱት ሕዝቡም  በሕብረት በአንድነት የመግባባትና የመከባበር የመተሳሰብ ድልድይን ይገነባል፡፡

በአሜሪካና በሌሎችም ሃገራት የእምነት ድርጅቶች የተጓደኑ የእምነት ካወንስሎች ይመሰርታሉ፡፡ይህም ካውንስል በተለያዩ አማኞች መሃል መግባባት መተሳሰብና መፋቀር ሊኖር እንዲችል፤ በህብረተሰቡ መሃል ያለውን ችግር ለመቅረፍም አብረው እንዲቆሙ መሳርያ ይሆናል፡፡የተጓደኑ ሃይማኖቶች ካውንስል ከመነጋገርና ከውይይትም ባለፈ የህብረት ስራ በመፍጠር የህዝብ አግልግሎትና በማዋቀር፤ የአካባቢ ችግሮችን በማስወገድ በሃይማኖቶች መሃል ያለውን ልዩነት እያከበረ በቀናው መንገድ ተሳስበውና ልዩነቶቻቸው እንደተጠበቁ  ሆነው አብረው ለሃገርና ሕዝብ የሚቆሙበትን መንገድ የሚመራ ነው፡፡ይህን መሰሉ የሃይማኖት ተጓዳኝ ካወንስል በኢትዮጵያ የመያፈጠርበት አንዳችም ምክንያት የለም፡፡

አንድነትን ፈተናው በአግባቡ ሊታይ ተገቢ ነው፡፡‹‹ሃይማኖት የግል ሃገር የጋር ነው›› የሚለውን  መርህ በትክክሉ ከተገበርነው የአንድነትን ፈተና በድል አድራጊነት እንወጣዋለን፡፡ ዓላማው የማንኛውም ሃይማኖት አክራሪነት በመወገዝና በመቀዋም ብቻ የሚያበቃ ስለማይሆን ሕብረተሰቡን ማስተማርንና ማንቃትንም ይጠይቃል፡፡በግልጽ እንደሚታየው በኢትዮጵያ ውስጥ፤ ከማንኛቸውም የፖለቲካ መሪዎች በላይ የሃይሞኖት መሪዎች ተቀባይነትና ክብር አላቸው፡፡የፖለቲካ ሰዎች ስለ ሃይመኖቶች መቆራቆስ ሲያነሱ የሃይሞኖት አባቶች ደግሞ መቻቻልን ማስተማር አለባቸው፡፡የኢትዮጵያ ችግር ከቴዎሎጂ ልዩነት የመነጨ አይደለም፡፡የኢትዮጵያ ችግር ምንጩ ቲዎሎጂን በተሳሳተ ትርጉም ሊጠቀሙበት በሚሹ አላዋቂዎች የተነሳ ነው፡፡

‹‹ሃይሞኖት የግል ምርጫ ነው፤ ሃገር ግን ጋራ ነው›::
‹‹የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ ምን ታስባላችሁ?!ምን ያታያችኋል?፤የሃይማኖት ማምለኪያ ቦታዎቻችን ሲቃጠሉና እምነቶቻችን ሲጠፉና ለአደጋ ሲጋለጡ እያየን ባለንበት ወቅት የሃይማኖት አባቶች ሚና ምነድን ነው?›

ካሁን በፊት የቀረቡ የጸሃፊው ጦማሮችን  ለማግኘት እዚህ ይጫኑ::

http://www.ecadforum.com/Amharic/archives/category/al-mariam-amharic

http://ethioforum.org/?cat=24

Leave a Reply