ይድረስ ለተከበረው ኢትዮጵየዊ ጀግና እስክንድር ነጋ!

Click here for PDF

ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም

ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ

አይበገሬው እስክንድር ነጋ!

በሜይ 1 2012 ኢትዮጵያዊው  ግንባር ቀደም ጋዜጠኛና የፖለቲካ እስረኛ፤ የመጻፍ ነጻነት ተሟጋች አርበኛ፤ እስክንድር ነጋ፤ ከ1922 ጀምሮ በእንቅስቃሴ ላይ የሚገኘውና ለነጻ

Eskinder Nega and his Son Nafkot

እስክንድር ነጋ እና ልጁ ናፍቆት

ፕሬስጥብቅና በመቆምለ ዓለም የጽሁፍ ነጻነት ተነፋጊዎች በመሟገት ላይ ያለው ታዋቂው የአሜሪካ ፔን ፤ ድርጅት ጭቆናንና አፈናን አሻፈረን በማለት በግፈኛ ገዢዎች ወደ ወህኒ ለሚታፈኑ የሚሰጠው ታላቁ ሽልማት ለ እስክንድር  ይሰጠዋል፡፡ ይህ ሽልማት፤ከበሬታ የሚሰጠው፤በአልበገርነትና  ለዲክታተሮች  ግዛት እምቢ፤አሻፈረን በማለት ከታፈነ የማስመሰያ ነጻነትለእውነትና ለነጻነት በክብር በመቆም በአፋኞቹ ገዢዎች የሚጣለውን ማንኛቸውንም ግፍና መከራ ለመቀበል፤ እራሳቸውን መስዋእት ለማድረግ በቆራጥነት፤ ግፍና መከራውን ለመቀበልየቆሙትን  ሃሳብን በነጻ የመግለጥ ተሟጋቾች የሚደፋ የክብር ሽላማት ነው፡፡

እስክንድር በግፍ አገዛዝ ሃገሪቱን ረግጠው በመግዛት ላይ ባሉት በነመለስ አስገዳጅ ባለስልጣኖች ለእስር በመዳረጉ ሽልማቱን በኒውዮርክ በግንባር በመገኘት ሊቀበለው አይችልም፡፡ሽልመቱ እስክንድር ነጋ ዓለም አቀፍ የዴሞክራሲና የነጻነት ጀግና መሁኑን ማረጋገጫ ነው፡፡ከዚህም አልፎ እስክንድር ነጋ ሰብአዊ መብትን ዴሚክራሲን፤ነጻነትን ለሚያከብሩአፍሪካውያን  ሁሉ  ጀግናቸው ነው፡፡እስክንድር  የጭቆና፤የግፈኛ ገዢዎች ጫና አልቀበልም! በማለት የቆመ የነጻነት አርማ ነው፡፡

‹‹ሽብርተኛ›› በመባል ሀጋሪቱን በመግዛት ላይ ባሉ ሽብርተኞች እስክንድር ለእስር ተዳርጓል፡፡ ያም ሆኖ በዓለም ላሉ በርካታ የፕሬስ ነጻነት ጀግኖች፤ ጀግናchew  ነው፡፡ በቅርቡ በዓለም ዙርያ በጭቆናና በአፈና አገዛዝ ለእስራት ተዳርገው የነበሩና ሌሎችም እስክንድርነጋ በግፍ ከታፈነበት ወህኒ እንዲለቀቅ  ሙግት ከከፈቱትና ለነጻነቱ ድምጻቸውን ካሰሙት መሃል

የዴይሊ አብዘርቨር (የላይቤርያ ቀደምት ነጻ ጋዜጣ) መስራች ኬነዝ ቤስት፤የሜክሲኮ ግንባር ቀደም ታዋቂና የተከበረች ጋዜጠኛና ደራሲ ሊዲያ ካቾ፤በጄኔራል ፒኖቺ የግፍአገዛዝ ዘመን የቺሊ መሪ ጋዜጣ አናሊሰስ ኤዲትርና በቺሊ ዩኒቨርሲቲ የጆርናሊዚም ፕሮፌሰር፤ በሌባነን የሜይ ቺዳክ ፋውንዴሽን መስራችና ፕሬዜዳንት፤ በቅርቡ ከተቃጣባትየፈንጂ አደጋ ከሞት ለጥቂት የተረፈችው ሜይ ቺዳክ፤በእንግሊዝ የተከበረው ጋዜጠኛና የሰንዴይ ታይምስ ጋዜጣ ኤዲትር ሰር ሃሮልድ ኢቫንስ፤የኢራን ግንባር ቀደም ጋዜጠኛአክባር ጋንጂ፤ የእስራኤል ታዋቂ ነጻ ጋዜጠኛና በጆርዳን የሚገኘው አማንኔት በዓለም የመጀመርያው ዓለም አቀፍ ሬዲዮጣቢያ መስራች ዳውድ ኩታብ፤ ጉዌን ሌስተር፤ዘናሚቢያን ተባለው የናምቢያ ነጻ ጋዜጣ ኤዲተር፤ሬይሞንድ ሉው የነጻው ፕሬስ አበው ተሟጋችና የደቡብ አፍሪካ ጽሁፍ ነጻነትና የጋዜጠኞች እንቅስቃሴ ነጻነት ተከራካሪየደቡብ አፍሪካ የፕሬስ ካውንስል ሊቀመንበር፤ ቬራን ማቲክ በሳይቤርያ የሬዲዮ ቢ92 ተባባሪ መስራችና በ1990 አድልዎና ወገናዊነት ያልነበረው ቀጥተኛ ዘገባ ስታቀርብየነረችው ዘጋቢ፤አዳም ሚቺንክ  የፖላንድ ተወዳጅና ከፍተኛ የሽያጭ ቁጥር ያለው የፖላንድ ጋዜጣ ዋና ኤዲተር፤ፍሬድ ሜምቤ፤የ ዛማቢያ ፖስት ጋዜጣ ኤዲተር፤ኒዛር ናዩፍየሲሪያው ትሩዝ(ሃቅ) ጋዜጣ ኤዲተር፤ፓፕ ሳይን የሳዊት አል ዴሞክራሲ ኤዲተርና ለምእራብና ለመካከለኛው አፍሪካ የሬውተር ዘጋቢ፤የዘመናት የኢራን ኤዲተርና ጸሃፊበሻህም ሆነ በቅርቡም ለእስር ተዳርጎ የነበረው ናዲም ሰነር፤በሕንድ አወዛጋቢ ጋዜጠኛ በመባለክ የሚታወቀውና  በእንግሊዝኛ ቋንቋ የሚጽፈው የደይሊ ኢንዳያኑ አሩንሹሬ፤በፔሩ ኢንቬስትጌቲቭ ጋዜጠኛና ኤዲተር የእለታዊው ሲግሎ ቪየንቲኖ፤ እነዚህ የነጻው ፕሬስ ተሟጋች ነጻ ጋዜጠኞች ለፈላጭ ቆራጩና ግፈኛው ገዢ ለመለስዜናው፤የኢትዮጵያ ግፈኛና ይሉኝታ ቢስ ገዢ መንግስት እስክንድር ነጋን ያለወንጀሉና ሃጢአቱ እውነትን ይዞ ለእውነት ቆሞ ለሕዝብ ፍትህን ዴሞክራሲን ሰብዊ መብትንበመጠየቁ ብቻ ለእስር በማደረጉ ያላቸውን ውግዘት በማሳወቅ፤ በእስክንድርና በሌሎችም ሃዜጠኞች ላይ የሚደርሰውን ጭፍንና ጊዜው እያለፈበት ያለውን የማን አለብኘነትአገዛዝ ድርጊት የሚቃወሙ መሆናቸውንና መንኛውም ዴሞክራሲያዊ መንግሽት በዜጎቹ ላይ እንዲህ አይነት ደባ እንደማይፈጽም አሳስበው ድርጊቱን አውግዘዋል፡፡

በሴብቴምበር 2011 ዊሊያም ኢስተርሊ በኒው ዮርክ ዩኒቨርሲቲ የኤኮኖሚክስ ፕሮፌሰር፤ማርክ ሃምሪክ የዋሽንግተን ናሽናል ፕሬስ ክለብ ፕሬዜዳንት፤ የ ኒው ዮርክ ኦፕን ሶሳየቲፋውንዴሽን ፕሬዜዳንት አሬህ ኒየር፤ኬነዝ ሮዝ የሁማን ራይትስ ዎች ጋዜጠኞችን መብት ለማስጠበቅ ኮሚቴ ኤክሲኪዩቲቭ ዳይረክተር፤እስክንድር ከወህኒ እንዲወጣ የአሜሪካ መንግሥትጣልቃ እንዲገባና ሽብረተኝነትንምይህም ጨርሲ ተቀባይነት እንደሌለው እንዲያስታውቅ ጠይቀው፤ በእርዳታ መልክ ለዚህ ፈላጭ ቆራጭ ግፈኛ መንግስት የሚደረገውም የ600,000,000 ዶላር ችሮታም ለዚህ መለሰል ተግባር መዋል እንደሌለበት እንዲታወቅላቸው አሳስበዋል፡፡

እስክንድር ነጋን ያጀገነው ምንድን ነው?

በተረትና በባህላዊ ወጎች በርካታ የተለያዩ ጀግኖች አሉ፡፡አንዳንዶች በሚያጋጥማቸው አደጋ ወቅት በሚያሳዩት የሞራል ጥናካሬ  ይጀግናሉ፤አንዳንዶች ደሞ ለክብራቸውን ለዓላማቸውበመቆማቸው ይጀግናሉ፡፡ እንዲሁም አንዳንዶች ጠላቶቻቸውን በፍልሚያው ሜዳ በመግደላቸው ድል በማሸነፋቸው ጀግና ይባላሉ፤ለፍቅር የተሰዉ ጀግኖችም አሉ፤ዘመናዊና ባህላዊ ጀግኖችም ይታያሉ፤ያልታወቀላቸውም  ጀግኖች አሉ፤ደግሞም የድል አጥቢያ ጀግኖችም አሉ፡፡  በዚህም ሆነ  በዚያ ሁሉም የሚጋሩት አንድ ባህሪ አላቸው፡፡መስዋእትነት፤ታማኝነት፤ጥንካሬ፤ቆራጥነት፤ እርግጠኛነት፤ ያለማወላወል እና ሌሎችም ሁኔታዎች፡፡

ከዚህ ሁሉ በተለየ አካሆን ግን እስክንድር ጀግና ነው! እስክንድር እውነትንና ሃሳቦችን ብቻ በመያዝ የሚዋጋ ጀግና ነው፡፡መነሻው ሃሳብ መድረሻው ሃቅ ነው፡፡ መቀላመድን በእውነት ሰይፍ ያነበረክካል፡፡መሰረተ ቢስና መደለያ ማታለያ የሆኑ ሀሳቦችን በሚቻል፤በሚታመን፤ትክክለኛና ሕዝባዊ በሆነ ሃሳብ ይረታዋል፡፡ብእር ብቻ የጨበጠው እስክንድር ነጋ የሚዋጋው በብእሩ ነው፡፡ ጥርጣሬን የሚዋጋው በመታመን፤ጭካኔን በርህራሄና በችሮታ፤ መሃይምነትን በዕውቀት: ጠባብ አስተሳሰብን በትእግስት: ቁጣን በምክንያታዊነት፤ጭቆናን በጥንካሬ ብልግናን በረጋ አንደበት ያሸንፋል፡፡ያንን የጨካኝና የሰው በላ አውሬ መሰል ፊቱን ፊት ለፊት እያየ  ለስምንተኛ ጊዜ ልትይዙኝ ልታስሩኝ ትችላላችሁ፤በተዘጋና ብቸኛ በሆነ ጉረኗችሁ ውስጥ ልታስገቡኝ ትችላላችሁ፤ ልትደበድቡኝ ግፍና መከራ ልታደርሱብኝ ልታሰቃዩኝ ትችላላችሁ፤መድረሻ  ልታዋክቡኝ  ለሃሰት ፍርድም ልታቀርቡኝ ልትወነጅሉኝ ትችላላችሁ፤ በዚያ በስቃይ በታጠረና የግፍ አምባ በሆነው ወህኒያችሁ ያለምግብ ያለህክምና ያለምንም የቤተሰብ ግንኙነት፤ልታፍኑኝ ትችላላችሁ፡፡ ስሜን ለማጥፋት ክብሬን ለማዋረድእኔነቴን ለማጉደፍ፤ ከኔም አልፋችሁ ባለቤቴን ልታስሩ ቤተሰቤን ልታሰቃዩ ትችላላችሁ፡፡ልጄንና ሚስቴን በማዋካብ ኑሮ የገሃነም ያህል እንዱሆንባቸው ማድረግ አያቅታችሁም አውቃለሁ፡፡ያሻችሁን አድርጉ፤የፈላጋችሁትን ፈጽሙ፤ እስኪበቃችሁ በኔና በቤተሰቤ ላይ የግፍና የመከራ ጫና አውርዱብን እንጂ ሕይወቴ እሳከለችና  መተንፈስ  እስከቻልኩ ድረስይህን የናንተን የጭቆና የግፍ አገዛዝ ተቀብዬ አልኖርም፡፡ ጭካኔያችሁን፤አውሬነታችሁን፤ግፋችሁንማ ጨርሶ ለመቀበል ቀርቶ ላበውም አልሞክርምና እሱን መዋጋት ብቻ ነው ፍላጎቴ: በማለት የሞገተና በጽናት ቆሞ አልበገርም የዕጣ ፈንታዬ ወሳኝ የመንፈሴ አዘዥ እኔ እስክድር ናጋ ነኝ: ያለ ኢትዮጵየዊ ጀግና ነው::

እስክንድር ነጋ፤ የወቅቶች ሁሉ ጀግና

እስክንድር ወኔው የሞላ ነው፡፡ ከሰባት ወራት በፊት ‹‹በፖሊስ ኮሚሽነሩ‹‹ ታዛዦች ተይዞ ወደ ኮሚሽነሩ ቢሮ በመውሰድ በኮሚሽነሩ ግፋዊ አፍ ዝም እንዲል ካልሆነ ደሞ ለእስርእንደሚዳረግ ና በኢንተርኔት ላይ የሰፈራቸው ጽሁፎቹና በተለያየ ወቅት ለተለያዩ መገናኛዎች የሰጣቸው ቃለ መጠይቆች  እሳት ጫሪ ናቸው፡፡ ጄኔራል ጻድቃን ጡሩን ይጫናል ብለህ ጽፈሃል፡፡ በአንድ ነገር ግን እርግጠኛ ሁን ኢህአዴግ ሕገ መንግስቱን ለመጠበቅ ብቃት አለው፡፡አንድ ነገር ቢፈጠር የመጀመርያው ተጠያቂ አንተ ነህና እንመጣብሃለን አለው፡፡እስክንድርም እና መጻፌንና ቃለ መጠይቅ መስጠቴን እንዳቆም ነው  የምትነግረኝ? ላለው ሲመልስለት አይደለም አለውና በመቀጠል ግን ኮሚሽነሩ፤ ክልሉን ማለፍህን ነገረንሃልናጥንቃቄ ልታደርግ ይገባል አንተን ለመወንጀል በጃችን በቂ ማስረጃ አለን በማለት የከረረ ማስጠንቀቂያም ማስፈራሪያም ሰነዘረ፡፡ እስክንድር ገን መጻፉን ቀጠለና የፖሊሱ ኮሚሽነር ጋር የነበረውን ቆይታ ሁሉ ያላንዳች ፍራቻ ለሕዝብ አቀረበው፡፡በዚህም አላበቃም እስከመጨረሻው እለት ድረስ ሕጸን ልጁን ከት/ቤት ለመውስድ በመጠበቅ ላይ እንዳለ ያዙት፡፡ ያ ሕጻንም የአባቱን በፖሊስ መያዝ ሲያይ ‹‹አባዬ›› ብሎ ሲጮህ ስቃይን መፈጸምና በውጤቱ መደሰት መሳቅ መንፈቅፈቅ የቀን ተቀን ተግባራቸው የሆነው ለግፈኞች እርካታና ለግዛት ማረዘሚያነት የተሰማሩት ፖሊሶችም በሕጻኑ የድንጋጤ ጩኸት ሳቁ! አሁን እስክንድር ፍርድ በሌለበትና ሳይፈረድበት ወንጀለኛ ተብሎ ውሳኔ ተላልፎበት በባዶ ችሎት ባላጠፋው ጥፋት ባልሰራው ድርጊት፤ በማያምንበት ደባ አሁንም ፍርድ እየጠበቀ ነው፡፡

እስክንድር የሃቅ ሰው ነው፡፡ በሴብቴምበር 2010 መለስ ወደ ኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ በድፍረት ብቅ ባለበትና ሹልክ ብሎ በገባባት ጊዜ  አስክንድርና የጋዤጠኝነት ሙያ አቻውየሆነችው  ጋዜጠኛ ባለቤቱ ሠርክ ዓለም ፋሲል ለኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዜዳንት ሲ. ቦሊንጀር የመለስን ገደብ የለሽየ ጭካኔና የግፍ አገዛዝ የሚያስረዳ ደብዳቤ ጽፈው ነበር፡፡

እኛ በክህደት ተፈርጀንና ተወንጅለን የታገድን ጋዜጠኞች ነን፡፡መለስ ዜናዊ በተደጋጋሚ በሚያካሂደው የምርጫ ረገጣና ማጭበርበር፤ሳይፈረድብን፤ ትህን ተነፍገን፤ ባዶችሎት ቀርበን ከ16 ወራት በኋላ የተለቀቅን ነን፡፡በዚሁ ወህኒ ቤት  ሠርክ ዓለም ፋሲል ካለወቅቷ ለመውለድ ተዳርጋለች እንክብካቤም ተነፍጓታል፡፡

ሕጻኑ ሲወለድ የሰርክዓለም የወህኒ ቤት ሁኔታ በፈጠረው እንግልትና ስቃይ ኪሎዋ እጅጉን ያነሰበት በመሆኑ ይህች ሕጻን በአፍሪካ ካሉት ወህኒ ቤቶች ሁሉ ዝቅተኛ በሆነው ቃሊቲ በዚህ ሁኔታ ለተወለደ ህጸን ህይወቱን ለማቆየት ያለው መፍትሄ የማቆያ ሙቀት(ኢነኩቤተር) መሆኑን ቢያሳውቁም በወህኒ ቤቱ ባለስልጣኖች ተቀባይነትሳያገኝ ቀረ፡፡ የእግዚአብሔር ፈቃድ ሆኖ በተአምር ሕጻኑ ጤናማ ሆነ አደገ፡፡….ምንም እንኳን ሃሳቡን የመግለጽ መብቱን ብናከብርም በአገዛዙ የግፍ ቀንበር ስር በመማቀቅላይ ያሉትን ነጻና አንዳችም ወንጀል ያልፈጸሙ ጋዜጠኞችና የፖለቲካ ተቃዋሚዎችን ግፍና በደል ከግምት በማስገባት ይህን መሰሉን ገዢ መንግስት በበላይነት የሚመራውመለስ በዚህ የተከበረ የኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ ቅጥር ግቢ እንኳን መገኘት ስለሚያረክሰው ይህ ሊታሰብበት ተገቢ ነው፡፡

እስክንድር አዛኝና ርህራሄ የተላበሰ ሰው ነው፡፡በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመርያዋ የፖለቲካ ፓርቲ መሪ የሆነችው  ብርቱካን ሚዴቅሳ ከታፈነችበት ወህኒ ቤት ስትለቀቅ እስክንድር አነጋግሯት ነበር፡፡ ‹‹ጀግናችን ስለሆንሽ እንኮራብሻለን›› አለኳት! በፊቷ ላይ የቆሰለ ስሜት ታየኝ  በውስጧ አንድ የተፋነ ነገር እንዳለና ፈንድቶ ለመውጣት ሲታገላት እንደነበር ያስታውቃል:: ግላው የወዳጅነት ውይይ ት ለማድረግ ሁኔታው አመቺ አልነበረም፡፡ በርካታ ሰዎች ነበሩ፡፡ስለዚህም ተናግሬ ስጨርስ ከዓይን ግንኙነት እንደሸሸች አይነት አንገ ቷን ቀለስ አድርጋ መሬት ላይ አይኖቿን መሬቱ ላይ ተክላ እራሷን በአሉታ ነቀነቀች፡፡ከዚያም እጅግ በለሰለሰ ድምጽ ‹‹አመሰግናለሁ›› አለች፡፡ የተናገርኩት መልሶ ኮረኮረኝ አባባሌ ለማባበልና ብርታት ለመስጠት መስሎ ተሰምቷት ቢሆንም እኔ ግን ከምሬ ነበር ያልኩት፡፡ ለብርቱካን አሁን የሚያስፈልጋት ግን ይሄ አልነበረም በሕይወቷ ካጋጠማት ሁሉ መራራውን ወቅት ያሳለፈች አንዲት ሴት አጠገብ ነበር ያለሁት፤ በውጧ ምሬት ያቋተባት ሴት፡፡ባይሳካላቸውም እድሜያቸውን የገፉና የማይጠግቡት የስልጣን ረሃብ በየእለቱ ግፍ የሚያሰራቸውና ሁሉንም እስካሁን ባይሳካላቸውም ተስፋ ለማስቆረጥ የሚታክቱ ጨካኝና አረመኔ ገዢዎች  ለመከራ መዳረግን ሙያቸውን መሳርያቸው ያደረጉ ሰዎች ያደረሱባት ጫና ያብሰለስላታል፡፡አሁን ደግሞ እስክንድር በመለስ የመከራና የግፍ ወህኒ ቤት የብርቱካንን ቦታ ይዟል፡፡

እስክንድር ባህሉንና ከበሬታን የሚያውቅ ሰው ነው፡፡ ‹‹ አቡነ›› ፓውሎስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ‹‹ጳጳስ›› ገና በህይወት እያሉ ግዙፍ የሆነውን ሃውልታቸውን የጵጵስና 18ኛ ዓመታቸውን ሲያከብሩ ባስተከሉበት ወቅት፤ እስክንድር አንድ ጥያቄ አነሳ፡፡

ሃውልት ማቆም በኦርቶዶክስ ሃይማኖት ጨርሶ የተወገዘ ነው ምክንያቱም ያንን ማድረግ ማለት፤ ሰብአዊ ፍጡርን ከቅዱስ መንፈስ አግዝፎ ማሳየት ስለሚሆን መደረግ የለበትም፡፡በኢትዮጵያ ረጂም ታሪክ ያለው የኦርቶዶክስ ቅዱስ መጽሃፍ  ከሰብአዊ ፍጡሮች ይልቅ መንፈሳዊ መለኮቶችን አግዝፎ ማሳየት እንደለብን አበክሮ ያስተምራል፡፡ ስለዚህም ክርስትናን ወደ ኢትዮጵያ ላመጡት አቡነ ሠላማ እንኳን ሃውልት አልቆመላቸውም፡፡ ለቤተክህነት ዜማዎችን ላፈለቀው ቅዱስ ያሬድ፤በላስታ እነዚያን  የድንጋይ ፍልፍል ቤተክርስቲያናትን ላበረከተው ላሊበላ፤ለኢትዮጵያዊው ታላቅ ቅዱስ ለአቡነ ተክለሃይሞነትም ቢሆን ሃውልት አልቆመላቸውምና ለምን አሁን የኢትዮጵያን የኦርቶዶክስ እምት በሚያጎድፈና በሚያንኳስስ መልኩ ሃውልት ይቆማል፤ ለምንስ የኦርቶዶክስ ባህል ይደፈራል?

እስክንድር  በኢትዮጵያ ለግፍና መከራ ለስቃይ ለተዳረጉት ሁሉ   ምስክር ነው::

ጭቆናው ይቅርታን የማያውቅ በየዕለቱ እየበዛ የሚሄድ ነው፡፡የምግብ ዋጋና የገንዘቡ አቅም ተዳክሞ የሚሰጠው የግዢ ዋጋ ከሃምሳ በታች ወርዷል፡፡ሥራ አጥነትም ከመቀነስ ይልቅ ፍጥነቱ በመጨመሩ ላይ ነው፡፡ አነስተኛ ስራዎች የሃገሪቱ የጀርባ አጥንት ቢሆንም ውጤት ከማምጣት ይልቅ ለመከራና ለመሸማቀቅ ደርሰዋል፡፡በገዢው ፓርቲ መንደር ጭንቀትና ፍርሃት፤ መርበድበድና ውጥረት ነግሷል፡፡

እስክንድር  የተስፋ ድምጽ ነው

……. አመጽን ለማነሳሳት የሚያበቃ ተስፋ እንጂ ጭቆናን የሚሰንቅ አይደለም፡፡ ግብጾችና ሊቢያናውያን ለዘመናት ካጋጠማቸው መከራ የባሰ አጋጥሟቸው አይደለም በ2011 ለአመጽ የተነሳሱት፡፡ ጥቂቶች የበለጠ የነጻነት ሕይወትን ተመኙና ከጫንቃቸው ላይ ግፈኛውን  አገዛዝ ከመሰረቱ ነቅለው ለመጣል ግንባር ቀደም ሚና ተጫወቱ፡፡ለዚህ ደሞ የቱኒዚያው ሁኔታ  በአካባቢው  ሁሉንም ነገር ለወጠው፡፡ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል ተረጋገጠ…..በሰብ ሰሃራ ሀገሮች ተስፋ ፈነጠቀና የተረፉትም የአካባቢው ግፈኛ ፈላጭ ቆራጭ ገዢዎች ሊወገዱ እንደሚችሉ  የተስፋ ፍንጭ ታየ፡፡የአረቦች መነሳሳት ተስፋ በየበሩ ማነኳኳት ያዘ፡፡በሩን ከፍቶ ለመግባትም ለረጂም ጊዜ አይጠበቅም፡፡ ማንኛው የሰብሰሃራን ፈላጭ ቆራጭ እንደሚገነደስ ማንም አያውቅም፡፡ ሆኖም ግን አይቀሬ ጉዳይ ነው፡፡አንድ ጊዜ መዛመት ጀምሯልና ማንም ሊያግደው አይችልም፡፡ሙባረክ የአረብ ሃገራት ታላቁ ፈላጭ ቆራጭና ለዘመናትም ቀጥቅጦ የገዛው ግንድ መገንደስ ለሌሎች የአረብ ሃገራት  የወርቅ ስጦታ እንደሆነው ሁሉ፤ኢትዮጵያም በሰብሰሃራ ትልቁ ግፈኛ ፈላጭ ቆራጭ  መገንደስም ለአፍሪካ ሃገራት ሁሉ መነሳሳትና በቃ ማለት  የወርቅ ስጦታ ይሆናቸዋል፡፡ ያለ ግብጽ የአረብ ሃገራት ማመጽ አይኖርም ነበር፡፡ ከኢትዮጵያም ውጪ የአፍሪካ የጭቆና በቃኝ መነሳሳት አይታሰብም፡፡

መልዕክተ እስክንድር

የአፍሪካን አህጉር ትልቁን ፈላጭ ቆራጭ ጨካኝ መንግስት በመምራት ላይ ያለው  መለስ ዜናዊ ጋዳፊ ከውድቀት ቀድሞ ያደርግ እንደነበረው ብለው ብዙዎች እንደሚገምቱት ሳይሆን አስቀድሞ በጥንቃቄ ሊስብበት ተገቢ ነው፡፡ግድያ ሊቢያናውያንን እንዳስቆጣና እንዳስነሳ ፤ከነሱ በፊትም ቱኒሲያኖችንና ግብጾችን እንዳስቆጣ፤ሊያስከትል የሚችለው መራር ሁኔታ ነው፡፡ ባልተጠበቀ ሁኔታ በድንገት ወጣቱ ለሞት ያለውን ፍርሃት እርግፍ አድርጎ ጣለ፡፡ ሞትን ረሳ፡፡ጋዳፊ በእጽ የደነዘዙ ብቻ ናቸው ሞትን የሚደፍሩት ያለውን በተግርባር በማስተባበል ከፊታቸው የሚታያቸው ተስፋ አመጹን እንዲያቀጣጥሉና ለድል እንዲበቁ አደረጋቸው፡፡

 ፈላጭ ቆራጭ ግፈኛ ገዢዎችን የሚያሸንፋቸው ተስፋ ብቻ ነው፡ በኢትዮጵያ ተስፋ እንዲያብብ ተስፋ እንሰንቅ::

ምነው ችሎታውና መራቀቁ፤ ብቃቱና የቅኔው ችሎታ በኖረኝና ለእስክንድር ነጋ በውስጤ ታምቆ ያለውን አክብሮት መግለጽ በቻልኩ፤: እስክንድር ነጋ ለዚህ በ2012ቱ ፔን/ ባርባራ ጎልድ ሰሚዝ የጽሁፍ ነጣነት ሽልማት በመብቃቱ ከፍተኛ ደስታዬን ባክብሮት ላስታውቀው እፈልጋለሁ:: ለዚሁም በ1875 ዊሊያም አርነስት ሄኔሊ በጻፈው‹‹ አይበገሬ›› (Invictus) በሚለው ግጥም  አክብሮቴን ልግለጽለት፡፡ ይህ ግጥም ነበር የኔልሰን ማንዴላን ተስፋ በአፓርታይድ ወህኒ ቤት ሲያለመልም የነበረው፡፡ አሱ ማለት እኮ ፍጹም የሆነ ተስፋና ጥንካሬ ያለው፤የእያንዳንዱን ሰብአዊ ፍጡር ውስጣዊ የነጻት ስሜት የሚወክል ተስፋ የሰነቀ ነው፡፡

‹‹ጥንካሬ ከጡንቸኝነት የሚገኝ አይደለም፤ ከጠንካራ መንፈስና ልቦና እንጂ›› ጋንዲ

ለእስክንድር ነጋ ነጻነቱ ይመለስለት!
ካሁን በፊት የቀረቡ የጸሃፊው ጦማሮች ለማግኘት እዚህ ይጫኑ: http://www.ecadforum.com/Amharic/archives/category/al-mariam-amharic

Leave a Reply