ፍጥረታዊ ፍትሕ ወይስ ዘረኛ ፍርደገምድልነት?

Click here for PDF

ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም ከነጻነት

ተበዳዩን  እንደ  ወንጀለኛ!

Professor Alemayehu G. Mariam teaches political science at California State University, San Bernardino.

ፕ/ር አለማየሁ ገ/ማርያም

ባለፈው ሳምንት በኢትዮጵያ የመርገጫ ማህተም የሆነውን ፓርላማ ግፈኛው ፈላጭ ቆራጭ መለስ ዜናዊ ተገደው ከደቡብ ኢትዮጵያ  ‹‹የተፈናቀሉትን›› የአማራዎች (አንዳንዶች‹‹በተንኮል ዘዴ ዘር ማጥፋት›› ብለውታል) በተመለከተ፤ በጉዳዩ ላይ ተቃውሞ ያሰሙትንና ፤ ዜናውን እንዲሰራጭ ያደረጉትን፤ በደፈናው ሃላፊነት የሌላቸው በማለት በማዉገዝና እውነቱን ሸምጥጦ በመካድ ጨርሶ መፈናቀል እንዳልተካሄደ ለማሳመን ሲፈላሰፍ ታይቷል፡፡  መለስ  ስለመፈናቀሉ  ማሳሳቻውን ማስረጃ ሲያቀርብ አንዳችም መፈናቀል ያልተካሄደ በማስመሰል  አንዳንድ  ሕገወጥ ከሰሜን ጎጃም የፈለሱ (‹‹ሰፋሪዎች›› ይላቸዋል) ከደቡብ መኖርያቸው የተነሱበት ምክንያት ቦታው የአካባቢ ደንና ፊጥረታዊ  ሃብት ጥበቃ ነው ሲል ሊሞግት ሞክሯል፡፡ እንዲያውም ለምን ያሉትንና የጋራነት መታወቂያችን ኢትዮጵያዊነት ነው በማለት የቆሙትን ድርጅቶች በተመለከተ፤ መለስ በጠራራ ጸሃይ ሲሰብክ:

….. ባለፉት አሰርት ዓመታት በታሪክ አጋጣሚ፤በርካታ ሰዎች፤… ወደ ሰላሳ ሺህ የሚጠጉ ሰፋሪዎች፤ ከሰሜን ጎጃም (የፈለሱ) በቤንጅ ማጂ ዞን (በደቡብ ኢትዮጵያ)ሰፍረዋል፡፡ በጉራ ፈርዳ 24.000 ሰፋሪዎች አሉ፡፡ ቦታው ጫካማ ስለሆነ ብዙ ሰው አይኖርበትም፡፡በተለያየ ሰበብና አጋጣሚ ሁሉም የድርሻውን ያገኛል የሚጎዳ አይኖርም፡፡እነዚህ ህገወጥ ሰፋሪዎች ባልተቀናጀ መልኩ ነው የሰፈሩት፡፡ እነዚህ ህገ ወጥ ሰፋሪዎች በተናጠልና በተመሰቃቀለ መንገድ፤ የአካባቢውንም የዓየር ሁኔታ በሚበክል መልኩነው የሰፈሩት፡፡ይህ ደሞ አጥፊና ጎጂ ነው፡፡

ሰፈራው የአካባቢውን ዓየር ሁኔታ ባገናዘበ፤ የጫካውን መጥፋት ከግንዛቤ ባስገባ መልኩ ታስቦ የተከናወነ አይደለም፡፡ድንግል የሆነው ጫካ መጠበቅ አለበት፡፡ሰፋሪዎቹበቀላሉ ሊለማ የሚችልና አፍሪ ቦታ ነው የፈለጉት፡፡ደን ሆነ አልሆነ ደንታ የላቸውም፡፡ደኑን እየጨፈጨፉ ለኑሮ የሚያስፈልጋቸውን ከሰል ያከስላሉ፡፡ በዚህ የተነሳም በርካታየአካባቢ ብክለትና ጉዳት ተፈጽሟል፡፡…… ሰፋሪዎች ወደፈለጉበት ቦታ ሄደው በመስፈር የአካባቢውን ደን በማጥፋት መኖር አይችሉም፡፡ሕገ ወጥ በመሆኑ ሊቆምይገባዋል፡፡ ይህን እውነታ ለማጭበርበር የሚጥሩ ሁሉ ሃላፊነት የጎደላቸው ናቸው፡፡ ዕውነትን አጥርቶ ማየት ያስፈልጋል፡፡የሁሉም ኢትዮጵያዊያን መብት በእኩል ደረጃሊጠበቅ ይገባል፡፡ አማሮች ተፈናቀሉ ለስደት ተዳረጉ በማለት የሚጮሁት ማንንም የማይጠቅም ቅስቀሳ ነው በማድረግ ላይ ያሉት፡………..

መለስ በቀላሉ ሲያስቀምጠው፤ እነዚህ ‹‹የሰሜን ጎጃም ሰፋሪዎች›› የአካባቢውን የደን ሁኔታ ያጠፉ ወንጀለኞች ናቸውና ተገደው መነቀልና መሰደድ አለባቸው፤ እንዲያውም በወንጀል ባለመጠየቃቸው እድላቸውን ሊያመሰግኑ ይገባል፡፡

የአፍሪካ  የከባቢ ዓየር  ዋና  ሹም

ስለአካባቢ ዓየር ሲነሳ በአፍሪካ ካሉት ከማንኛቸውም በበለጠ እውቀትና  ችሎታ ያለው ሰው ቢፈለግ ከመለስ ሌላ ጨርሶ የት ሊገኝ?! ምንስ ቢሆን የአፍሪካ ዋና የከባቢ ዓየር መኮንን ተብሎ የለም እንዴ!   በ2009 መለስ በኮፕንሃገን በተካሄደው ስብሰባ ላይ የአፍሪካዊያንን ተደራዳሪዎች በመምራት ተገኝቶ ነበር፡፡  በዚህ ቦታ የአፍሪካ ተደራዳሪዎች መገኘት መንስኤውም፤የምእራቡ ዓለም እያጠፋና እያዛባ ያለውን የተፈጥሮ ዓየር፤ ደግሞም የተከተለውን የአየር ለውጥ፤በዓለም የሙቀት ሁኔታው መባባስን፤እና ሌላውንም በተመለከተ የሞራል ካሳና የገነዘብ መቀጫ ለመጠየቅ ነበር ዘራፍ ብሎ የተነሳው፡፡ በዚህም 40 ቢሊዮን ዶላር ካልተፋ ስብሰባውን  እንደሚያጨናግፈው ረግጦ እንደሚወጣ ደንፍቶ ነበር፡፡

እኛ በአናሳው የምናቀርበው ስምምነት ተቀባይነት ካጣ፤ ቁጥራችንን በመጠቀም ውሳኔው ውድቅ እንዲሆን እናደርጋለን…….እንዲያውም አካሄዳቸውና ውሳኔያቸውአህጉራችንን አስገድዶ የሚዳፈር ከሆነ ስብሰባውን ረግጠን እንወጣለን፡፡……..ከዚህ ቀደም ይደረግ እንደነበረው የአፍሪካ ፍላጎትና አቋም ሊታፈን አይችልም አይገባምም፡፡……. አፍሪካ፤የአፍሪካ ሕብረት አባላትን ሀገራት የሚወክልና ሙሉ ስልጣን ያለው አንድ ብቸኛ ተደራዳሪ ቡድን ትሰይማለች፤…. ለኔ ዋነኛው ቁልፍ ጉዳይ፤አፍሪካ የዓለምን አየር መዛባት አስመልክቶ በተፈጠረው ጉዳት ልትካስ ተገቢ ነው፡፡ በርካታ ኢኒስቲቲዩሽኖች ይህን በቁጥር ለማስቀመጥ ሞክረው የተለያየ ተመን አስቀምጠዋል፡፡ከዚህ በመነሳትም ማእከላዊው ቀመር በዓመት 40 ቢሊዮን ዶላር ይሆናል፡፡

ስብሰባው በተጀመረ በማግስቱ ፤ መለስ ከ‹‹አፍሪካ አስገድዶ ደፋሪዎች›› ጋር በ10 ቢሊዮን ዶላር ውለታ ለመፈጸም ስምምነት ለማድረግ ዝግጁ ሆነ፡፡ አፍሪካውያን ወንድሞቹንም ጥሬ ብር ከአርቲ ቡርቲ ቃላት ይሻላል በማለት አሳመነ፡፡

……እርግጥ ይሄ የኔ ሃሳብ ምናልባትም ከሕግ አኳያ ለደረሰብን በደልና ጥፋት፤ በልማታችን ላይ ለደረሰብን በደል ሙሉ ካሳ ይገባናል በማለት ሃሳብ ያቀረቡትንአፍሪካውያንን ቅር ሊያሰኝ ይችላል፡፡ የኔ ሃሳብ ቀስ በቀስ ወደ ተነሳንበት ቁጥር ያደርሰናል፡፡ ይህን ፈንድ መቆጣጠርና በዚህም የአስተዳደር ስልጣን ማግኘትና በወሳኝነት መቀመጥ ዋነኛ መሳርያችንና አስተማማኝ የፋይናነስ ፍሰት ማግኛችን ነው፡፡

በኦክቶበር 2011 መለስ በአፍሪካ ኤኮኖሚ ኮንፍራንስ ላይ ተገኝቶ ባደረገው ንግግር፡-

……..በአህጉራችን ያለው መሬት፤ከመሬቱ መሳሳትና ከማለቁ የተነሳ ዛፎቹ ሁሉ ወድመዋል፤በአፈሩ መሸርሸር፤ለድርቅና ለጎርፍ፤በዓለም ላይ በመከሰት ላይ ባለው የዓየርመዛባት ሳቢያም ከዚህ ቀደም ታይቶ ወደማይታወቅ የጎርፍና የድርቅ ሁኔታ ተዳርገናል፡፡የአርሻዎቻችን መሰረትም እጅጉን አስፈሪ ሁኔታ ውስጥ ነው ያለው፡፡

ስለዚህም በመለስ አተማመን ወደ አውሮፓውያን አስገድዶ ደፋሪዎቻችን በመመለስ በድጋሚ ተጨማሪ የገንዘብ ካሳ ማግኘት ይኖርብናል፡፡

በኢትዮጵያ የመለስ ዜናዊ ፍጥረታዊ ተሰጥኦዎችi ተንከባካቢነት

በአፍሪካ የዓየር ለውጥና የዓለምን የሙቀት ሁኔታ በተመለከተ መለስ ዜናዊ አዋቂ የሚል የለበጣ ስያሜ አግኝቷል፡፡ ይሁንና ግን በኢትዮጵያ ውስጥ በመካ ሄድ ላይ ስለአለው የአካባቢ ብክለት፤በተለይም በኢትዮጵያ የደኖችን መጨፍጨፍና መጥፋት በተመለከተ ግንዛቤ አለውን? የኢትዮጵያ የእርሻ ምርምር ኢኒስቲቲዩት (በሃገሪቱ ያለው ግንባር ቀደም የእርሻ ኢኒስቲቲዩት) ዘገባ እንደሚያመላክተው በ2020 ኢትዮጵያ ጠቅላላ ደኖቿን ታጣለች ብሏል፡፡

ባለፈው የምዕተ ዓመት ለውጥ ላይ የኢትዮጵያ ደን 40 በመቶ ነበር፡፡ በወታደራዊው አገዛዝ ዘመን በ1987 ላይ ወደ 5.5 በመቶ አዘቀዘቀ፡፡ በ2003 ወደ 0.2 ወረደ፡፡የትዮጵያ የእርሻ ምርምር ኢኒስቲቲዩት ኢትዮጵያ በየዓመቱ 200.000 ሄክታር ደን እንደምታጣ ይናገራል፡፡ በ1990 እና በ2005 መሃል ኢትዮጵያ 14.0 በመቶ የደን ሽፋኗንአጥታለች፡፡(2.114.00 ሄክታር) በተጨማሪም 3.6 ከመቶ የዛፍ ተክሎችን አጥተናል፡፡ ሁኔታው በዚህ ከቀጠለ በመጪው 11 ዓመታት ኢትዮጵያ በ2020 ደን አልባ ሃገር ወደመሆኑ ትሸጋገራለች፡፡

በ 2004 የተደረገ ጥናት እንደሚያስረዳው፤ኢትዮጵያ 60 ሚሊዮን ሄክታር መሬቷ በደን በቀል ዛፎች የተሸፈነ ሲሆን ከዚህም ውስጥ 7 በመቶው የደን እርሻ ነው፡፡63 በመቶ ገደማው ጫካማው ቦታ ደሞ በኦሮሚያ ክልል ያለ ሲሆን የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ክልል ደግሞ በ19 በመቶ ተከታይ ሲሆን፤ጋምቤላ 9 በመቶውን ያካትታል፡፡ በጣም የሚያስገርመውታዲያ መለስ ዜናዊ  የደን እንክብካቤን አስመልክቶ ትኩረት የሰጠው ለቤንች ማጂ/ ጉራ ፈርዳ መሆኑና፤ በ2012 በእጅጉ መጠን ያጣው ችግር፤ ስርአት አልባ የሆነው የውጪ የንግድሁኔታ በአካባቢው መዳበሩ መሆኑን ነው፡፡ ከዚሁ ጋርም የደኖችን መጨፍጨፍ ሰበብ ያደረገው እንቅስቃሴው በዘር ላይ የተመሰረተ ማሳደድና ነዋሪዎችን በትውልድ ሀረጋቸው ብቻ ለማፈናቀል መወሰኑ ነው፡፡ ያም ሆኖ ግን፤መለስ ለአካባቢ ደህንነት ተቆርቋሪ ለመምሰል ‹‹የሰሜን ጎጃሞችን ሰፋሪዎች›› በማስረጃ የተደገፈ መፈናቀል አወዛጋቢውን ርእስ ለመሸፈንና ከወቀሳና ከትችት ለመዳን በማታለያነት ተጠቀመበት?

መለስ ዜናዊ ስለአካባቢ ዓየር መቆርቆርን፤በሃሳብ መባዘንን ስለደኖች እንክብካቤ መቆጨትን፤ በማስመሰያነት ከመጠቀም ውጪ አንድም የእውነት ፍንጭ የሌለው ነው፡፡ ባለፉት አምስት ዓመታት፤መለስ ዜናዊ  በጣም ፍሬያማ የሆኑትን ለም የደን መሬቶች  ለሳውዲዎች ለሼሆቹ፤ለህንዶች፤ለቻይናዊያን፤ለኮርያውያኖችና የዶላርን ስም ለጠሩና ቁጥር ለጠቀሱ ሁሉ በሊዝ ስም ሸጦላቸዋል፡፡  እንደ የተከበረው የኦክላንድ ኢኒስቲቲዩት  [OI]  ግንዛቤ ከ2008 ጀምሮ የመለስ ዜናዊ አገዛዝ

በትንሹ 3.619.509  ሄክታር  መሬት ለውጪ ኢንቬስተሮች (ቁጥሩ ሊበልጥም ይችላል) አስተላልፏል፡፡….የኢትዮጵያ ገዢ መንግስት በመሬቶች ላይ ስለተከናነው ድርድር ሁሉ በውይይት መግባባት ተደርሶበት ነው፡፡ አንድም የተፈናቀለ ነዋሪየለም፡፡ የተሰጠው መሬትም በጥቅም ያልዋለ ጦም አዳሪ የነበረ ነው በማለት ቀልመድመድ ቢያደርግም የኦክላንድ ኢንስቲቲዩት ግን ከነዋሪዎች ጋር ተካሄደ ስለተባለው ውይይትአንዳችም ማረጋገጫ አላገኘም፡፡ ………..በውሃ አጠቃቀም ላይ አንዳችም ገደብ አልተደረገም፤ በአካባቢው ዓየር ላይ ሊያደርስ ስለሚችለው ብክለት(EIA)  ምንም የተወሰደ ጥናት  አልነበረም፤ቁጥጥርም አልተደረገም፡፡ ኢንቬስተሮች ውሃን ያላንዳች ገደብ እንዲጠቀሙበት መፍቀድ እጅጉን የሚያስገርምና አሳዛኝ ደንታ ቢስነት ነው፡፡ የኦክላንድ ኢንስቲቲዩት ከኢንቬስተሮች በተደረገት ገለጻ፤ ምንም አይነት ቁጥጥርና ገደብም ስለሌባቸው የአካባቢውን ወንዝ በመገደብ ሊገለገሉበት እንዳቀዱና በአካባቢ የዓየር ቁጥጥርም አንዳችም ችግር እንዳላጋጠማቸው ገልጸዋል፡፡ ምንም እንኳን ገዢው መንግስትና ባለስልጣኖቹ የአካባቢ ዓየር ጥበቃ ይደረጋል በማለት ቢናገሩም  ከመንግስት በኩል አንድም የማስረጃ ማሳመኛ ሊያቀርቡ፤ ጥናትና ቁጥጥር ለመኖሩና ለመከበሩም ቢሆን አንድም የመንግስት ባለስልጣን ወይ ም የየአካባቢው ሹም በዚህ ጉዳይ ላይ ወደ ቦታው ደርሶ እንደማያውቅ ነዋሪዎች ሲመሰክሩ፤ ኢንቬስተሮችም ይህ ሁኔታ ለመከናወኑ አንዳችም ማስረጃ የላቸውም፤ የጠኝውም ሃገር ደግሞ ይህን አይነት ሁኔታ ተካሂዶበት አይውቅም፡፡………… ከአርሻ ይዞታ ላይ መፈናቀል በሰፊው የሚካሄድ የእለት ተእለት ሂደት ነው፤ አብዛኛዎቹ ተፈናቃዮችም ተገቢውን ማካካሻ አልተከፈላቸውም፤ከመኖሪያና እርሻቸው ሲነቀሉም በሌላ አካባቢ የእርሻ ቦታ እንዲፈልጉ በመደረግ በመሆኑ ከሌሎች የአካባቢው አርሶ አደሮች ጋር በቦታ ሰበብ ውጥረት እንዲፈጠር እየተደረገ ነው፡፡

በመጨረሻውም ሼሆቹ፤ሳውዲዎች፤ህንዶች፤ቻይናዊያን፤ ኮርያዎች (ሼሳህቻኮ)  ለሙን  መሬት በማቃጠል ለውጭ ገበያ የሚሆን ምርት ለማብቀልና ለመክበር የተሰባሰቡትና መሬቱንም በሻጩ መንግስት የተከፋፈሉት ኢንቬስተሮች ሲባሉ፤ ለእለት ጉርስና ቤተሰቡን ለማኖር በማለት ኩራማን በምትሆን መሬት ላይ ኑሮውን ለማሸነፍ የሚጥረው ዜጋ ግን፤ ሕገወጥ ኗሪ (‹‹ሰፋሪ››) ይባላል፡፡ እነዚህ ስብስቦች (ሼሳህቻኮ) ለ‹‹ልማት›› በሚል የማደናገርያ ቃል፤በሚሊዮን ሄክታር የሚቆጠር መሬት ለ99 ዓመታት ተሰጥተዋል፡፡ ኢትዮጵያውያን ደግሞ ከሞነርያ ቀያቸው በጉልበት በመፈናቀል የእርሻና የመኖርያ ቦታቸውን ለነዚህ ሼሳህቻኮች እንዲያስረክቡ ተፈርዶባቸዋል፡፡  ሼሳህቻኮች ከግምት በማይገባ ገንዘብ ያሻቸውን ያህል የመሬት ባለቤት እንዲሆኑ ሲፈቀድላቸው፤ ኢትዮጵያውያን ግን የባለቤትነት ይዞታቸውን አንዳችም የገንዘብም ሆነ የቦታ ትክ ሳይደረግላቸው እንዲባረሩ ተፈርዶባቸዋል፡፡  ሼሳህቻኮ  በብርሃን በግላጭ በአክብሮት የደስታ አቀባበል ሲደረግላቸው፤ ዜጎች ግን ጸሃይ ከመጥለቋ በፊት አካባቢውን ጥለው እንዲሰደዱ ይደረጋሉ፡፡ ሼሳህቻኮ የመሬት ባለቤትነት መብት ሲኖራቸው ኢትዮጵያውያን ደግሞ ለመሬት አልባነት ይዳረጋሉ፡፡  ሼሳህቻኮ የነገስታታነት ከበሬታ ሲሰጣቸው፤ ኢትዮጵያውያን ደግሞ በዱላ መባረርን ይቸራሉ፡፡ እንደ ኦክላንድ ኢኒስቲቲዩት ጥናት  ከሁሉም በላይ የሚያሳፈረው በ ሼሳህቻኮ እርሻዎች ላይ ለመስራትና ኑሮን ለመታገል የፈቀዱትም ኢትዮጵያውያን በመጤዎቹ እንደ እንስሳ በመቆጠር ለግፍ መዳረጋቸው ነው፡፡

ወደ ሼሳህቻኮ ግዛት እንኳን በደህና መጣችሁ!

የ‹‹ሰሜን ጎጃም ሰፋሪዎች›› ሊያከብሩትና ሊከተሉት የሚገባ የአካባቢ ዓየር ሕግ አለን?

የ‹‹ሰሜን ጎጃም ሰፋሪዎች›› ከይዞታቸው መነቀል አስፈላጊ መሆኑን መለስ ሲያስረዳ፤ ‹‹ሰፋሪዎቹ›› ሕገወጥ፤በዘፈቀደ ቦታውን የያዙ፤ እና የአካባቢ ዓየርንም ደህንነት የሚያበላሹ ናቸው በማለት ይወነጅላቸዋል፡፡ ለመሆኑ የመለስ ገዢ መንግስት፤ሕጋዊነትን የሚጠይቅ፤ ስርአት የተቀመጠለት፤የገጠር አሰፋፈር ደንብ አለው? ለምሳሌ በጉዳዩ ላይ የተቀመጠው ወሳኙ ሕግ፤ ‹‹የገጠር መሬት አስተዳደርና አጣቃቀም አዋጅ ቁጥር 456/2005›› በእርሻ ለመሰማራት ለሚፈልጉ ሁሉ፤ መሬትን ያለምንም ገደብ ይፈቅዳል እንጂ አሰፋፈርን በተመለከተ እንዴት መከናወን እንደሚገባው የሚለው አንዳችም ነገር የለም፤ ስለአስተዳደሩም የሚገልጸው ስርአት የለም፡፡ አተገባበሩን በተመለተ ሙሉ መብቱን ሙያው፤ብቃቱ፤ችሎታውም ለሌላቸው ‹‹የአካባቢው ባስልጣናት›› ትቶታል፡፡ በእርግጠኝነት አዋጅ ቁጥር 456 ስለ ደን መሬት ጥበቃ፤አስተዳደር አንዳችም የሚለው ቃል የለውም፡፡በደፈናው የግብር ይውጣ ያህል፤ ደን፣የደን መመናመን፤እና የደን መሬት በማለት ይዘጋዋል፡፡

የተሸሻላና አዋጅ ቁጥር 456ን የተካውም አዋጅ ቁጥር 106/2007 ቢሆን፤ እንዲያው በይሆናል ግምት፤የታወጀ እንጂ  ክልሉ የአካባቢ ዓየር ጥበቃ ኤጀንሲ የለውም፡፡ አዋጅ ቁጥር 456ን ተግባራዊ የማድረጉ ሃላፊነት በእርሻና የገጠር ልማት ቢሮ ስር የተጣለ ሚንቀሳቀሰው ግን የተፈጥሮ ሃብትንና የዱር አራዊትን በመጠበቁ ላይ እንጂ  የደን ጥበቃውን በተመለከተ ጨርሶ የተጣለበትን ሃላፊነት አልተረዳውም ወይም ከጉዳይ አላስገባውም፡፡ የመሬት አጠቃቀም ገደብን በተመለከተ በገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ድንጋጌ ቁጥር 66/2007 ከጫካማ ቦታዎች ወይም ደኖች ጋር ምንም ግንኙነት የለውም፡፡ ግንኙነቱ ከውሃማ ቦታዎችን ከተንሸራታች መሬቶች ጋር ነው፡፡ በደፈናው ብቻ ደኖችን ስለማመናመን ወይም ስመጨፍጨፍና ለእርሻነት ስለማዋል የሚጠቅስ አንዳችም ክልላዊ ሕግ የለም፡፡ እና ታዲያ ‹‹ሰፋሪዎች›› ምን አድርጉ ነው የሚባሉት?

የፌዴራሉ ‹‹የደን ልማት ጥበቃና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 542/2007›› ቢሆንም ዝም ብሎ የእቅድ አቅጣጫ ጠቋሚ እንጂ ሌላ አይደለም፡፡አዋጁ የመንግስትንና የግል ደኖችን ያከብራል ይላል እንጂ፤ደኖች እንዴት ሊለሙ እንደሚችሉ የሚየሳየው አካሄድ አለያም ደግሞ ግለሰቦች በስራው ለመሰማራት ፈቃዱን ከየት እንደሚያገኙ አይገልጽም፡፡ አዋጁ የግል ደኖች አልሚዎችን ግዴታ ሲደረድር ስለመብታቸው ግን ምንም አይልም፡፡ የአዋጁ ብዘው ቦታ የተሞላው ወደፊት ምን ሊደረግ ይገባል በሚል የምኞት እቅድ ላይ ነው፡፡

መለስ የቤንች ማጂ ‹‹ሰፋሪዎች›› ከአስፈላጊው የአካባቢ ዓየር መመርያ አዋጅ ቁጥር 299/2002 ጋር በሚጋጭ ሁኔታ ነው በማለት ሊያሳስት ይሞክራል፡፡ ይህ አዋጅ አስቀድሞ የተባለው ፕሮጄክት ተግባራዊ ከመሆኑ አስቀድሞ ሊጠናና ሊመረመር ይገባዋል፡፡ የዚህ አዋጅ ቁጥር 299 አባባልና አተረጓጎም ‹‹ሰፋሪዎቹ››  የአካባቢን ዓየር ሁኔታ ከሚመለከተው ሕግ ተጠያቂነት ውጪ ናቸው፡፡ከዚያ ይልቅ ለአዋጅ ቁጥር 456 (የገጠር መሬቶች አስተዳደርና ጥቅም) ተገዢ ይሆናሉ፡፡ይህ ሁሉ የሕጋ ቃልና የቴክኒክ አጠራርና አላስፈላጊው ክርክር ሁሉ ይቀርና ጉዳዩ በሙሉ የፖለቲካ ጥያቄና የፖለቲካ ፍላጎት ማስፈጸሚያ ይሆናል፡፡  በጊቤ ግድብ 3 ሂደት ላይ የቀረበው የከባቢ ዓየር አስተያየት በግልጽ የሚያሳየው ሁኔታ የፖለቲካ ጉዳይ ሲሆን የሚያስከትለውን ነው፡፡

የዘር ጥሰት ወይስ የደን እንክብካቤ?

ከደቡብ ኢትዮጵያ ቤንች ማጂ/ጉራ ፈርዳ በአስር ሺህ የሚቆጠሩ አማራዎች በግዴታ መፈናቀላቸው አያጠያይቅም፡፡በአሜሪካ ድምጽ ላይ የተስተናገዱት ቃለ መጠይቆች፤ በግዳጅ መባረራቸውን በግልጽ ያስረዳል፡፡ስለዚህም ቸል የማይባለውንና ሊታለፍ የማይገባውን ጥያቄ ልንጋፈጠው የግድ ነው፡፡ይህ አስገድዶ ከቀዬ ማፈናቀል የዘር ጥላቻ ነው ወይስ የተለመደ የተፈጥሮ ሃብትን መጠበቅ ነው? መለስ ዜናዊ ይህን አስገድዶ ማፈናቀልን በተመለከተ ማሳመኛ አድርጎ የሚያቀርበው  የ‹‹ሰሜን ጎጃም ሰፋሪዎች›› የተፈናቀሉበት ምክንያት ደኑን በማጥፋታቸውና አሰፋፈራቸውም በተለምዶ እንደሚያደርጉት ስርአት ያጣና ከህግ ውጪ በመሆኑ ነው ሲል፡  የደቡቡ ገዢ ሽፈራው ሽጉጤ በበኩሉ ደሞ  መለስ ስላነሳው ‹‹ሰፋሪዎች›› ስላደረሱት የደን መጨፍጨፍ፤ አንድም ቃል አልወጣውም፡፡ የፈጣሪ ያለህ ታዲያ ማን ሊታመን ነው?

ዘር ማጥፋት እንዲህ ነው ሊባል የሚችል ህጋዊ ትርጉም የለውም፡፡በ1993 የተባበሩት መንግስታት ኮሚሽን ቃሉን ሲተነትነው ‹‹ሆን ተብሎ ታቅዶ ከተወሰነ አካባቢ የተወሰነ ዘር ተወላጆች የሆኑትን በጉልበት፤ በማስፈራራት አፈናቅሎ ቦታውን ለሌሎች ዘሮች ለመስጠት የሚፈጸም››  ይለዋል፡፡የተባበሩት መንግስታት ሴኪውሪቲ ካውንስል የባለሙያዎች ኮሚሽን ድንጋጌ 780 የዘር ማሳደድን ሲተነትንም በሰብዊ ፍጡሮች ላይ የሚፈጸም ወንጀል በመሆኑ እንደጦር ወንጀል ይቆጠራል ይላል፡፡የተለያዩ ድንጋጌዎችና ትንታኔዎች ወንጀልነቱን በተደጋጋሚና በተለያየ ጊዜ ያረጋገጡት ነው፡፡የነዚህም ‹‹ሰፋሪዎች›› መፈናቀል ሆን ተብሎ በተመረጡ ብሄሮች ላይ የተፈጸመ ነዋሪውን የማግለል ደባ መሆን አለመሆኑ በተጠናቀሩት ማስረጃዎች ሊረጋገጥ የሚችል፤ጉዳይ ነው፡፡

ማካካሻ አይገባምን?

‹‹ሰፋሪዎቹ›› የተፈናቀሉት  የሃገሪቱን ደን ከጥፋት ለማዳን ነው ተብሎል የሚለውን የመለስ ሰበብ አምነን የምንቀበል ከሆነ፣ የተፈናቀሉትና ርስታቸውን፤ መኖርያ መንደራቸውን፤ ንብረታቸውን ያጡት ከፍ ላለ የሀገር ጥቅም መሆኑን ያረጋግጣል፡፡ አባባሉ የሚታመን ሆኖ ፤በአዋጅ ቁጥር 456 ‹‹ሰፋሪዎቹ›› መሰረት መብታቸው ሊከበርላቸው የግድ ነው፡፡ በአዋጁ ላይ ‹‹የገጠር መሬት ይዞታው ለሕዝባዊ ጠቀሜታ የተወሰደበት ሰው፤ በነበረበት ቦታ ላይ ባለማውና ባፈራው ሃብት መሰረት ተመጣጣኝ ማካካሻ ሊያገኝ አለያም ተመጣጣኝ የሆነ ትክ ሊሰጠው ይገባል›› ይላል፡: እነዚህ ሰፋሪዎች ግን ለተዘረፉት ቦታ፤ እንስሳትና ንብረት እንዲሁም ላደረጉት የልማት ውጤት አንዳችም ማካካሻ አልተደረገላቸውም፡፡ ጸሃይ ስትጠልቅ በድቅድቅ ጨለማ አካባቢያቸውን ለቀው፤ በጀርባቸው የለበሱትን ጨርቅ ብቻ ይዘው: ሕጻናት ልጆቻቸውን አዝለው እንዲጠፉ ብቻ ነበር የተገደዱት፡፡ ሌላው ቢቀር ከሕጉ አባባል  አኳያ ማካካሻ ሊደረግላቸው አይገባም?

እረ የህግ ያለህ!     እረ የህግ ያለህ!

ካሁን በፊት የቀረቡ የጸሃፊው ጦማሮች ለማግኘት እዚህ ይጫኑ: http://www.ecadforum.com/Amharic/archives/category/al-mariam-amharic

Leave a Reply