ኢትዮጵያ፤ ወደ ዴሞክራሲ የመጓዣው ጎዳና ካርታ ላይ

Click here for PDF

ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ

Professor Alemayehu G. Mariam teaches political science at California State University, San Bernardino.

ፕ/ር አለማየሁ ገ/ማርያም

ባለፈው ሳምንት በሲያትል ከተማ የኢትዮጵያን ራዕይ በተመለከተ ሰፊ ሕዝባዊ ውይይት፤ ክርክር፤ ለማካሄድ በተመሰረተ  የኢትዮጵያ ሕዝባዊ  ፎረም ላይ (EPFS)ላይ ተጋብዤ ተገኝቼ ነበር::  በዚህምስብሰባ ላይ በቅርቡ ሳቀርባቸው በነበሩት የኢትዮጵያን ከፈላጭ ቆራጭ ግዛት ወደ ዴሞክራሲያዊ አስተዳደር ሽግግርን በተመለከተ ማብራሪያ እንድሰጥ ተጠይቄ ነበር፡፡ እኔ በኢትዮጵያ ከፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ ወደ ዴሞክራሲያዊ አስተዳደር ሊካሄድ ስለሚገባው የሽግግር ሁኔታ የማቀርባቸው ሃሳቦች፤ በሃገራችን በመካሄድ ላይ ያለውን ጭካኔ የተመላበት አገዛዝ፤የሰብአዊ መብት ረገጣ፤የፍትሕ እጦት፤ እስራትና ወከባን በተመለከተ ካለኝ ወገናዊነት የተነሳ የተፈጠረብኝ የግል አመለካከቴ ነው፡፡ ይህ ወገናዊነቴና ለሰብአዊ መብት ሙግት መቆም የጀመርኩበት ምክንያት በቀጥታ ትእዛዝ መለስ ዜናዊ በባዶ እጃቸው መብታቸውን ለማስከበር የወጡትን ንጹሃን 193 ኢትዮጵያዊያን ካስጨፈጨፈና 763 የሚሆኑትን ደግሞ ካስቆሰላቸው ከ2005 ጀምሮ ነው፡፡ ከ2005 በፊት ግን በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ የነበረኝ ትኩረቴ፤ትምህርታዊ፤ እንዲሁም ስለኢትዮጵያ ጉዳይ በሚያነሳ አንድ ምሑራዊ መጽሔት ላይ መስራትና በኤዲቶሪያል በኩልም ሕትመቱን ማገዝ ነበር፡፡ የ2005ቱ ጭፍጨፋ በሁዋላ  ፤ጭፍጨፋው አልተፈጸመም ብዬ ዝም የማለት ምርጫ ነበረኝ፤ በደረሰው አስከፊና ዘግናኝ ሁኔታ ለራሴ በራሴ ተብሰልስዬና ውስጤ ቆስሎ ነገሩን ችላ የማለት አማራጭም ነበረኝ፡፡ እነዚህ በግፍ የሞቱትን ንጹሃን ጉዳይ ግፈኞቹና ነፍሰ ገዳዮች ስልጣናቸውን ለግፍ መፈጠሚያ የሚያውሉትን አረመኔዎች ሊሞግትና ጥብቅናሊቆም የሚወስን አካል ይፈጠራል፤ በማለት ዝም ማለት፤ እችል ነበር፤ አለያም ስልጣናቸውን አላግባብ ለግፍ የሚያውሉትን ፈላጭ ቆራጮች በተመለከተ ቆራጥ ሆኜ ለተበደሉት ጥብቅና ለመቆምና ድምጸቸውን ለማሰማት የመወሰን ግዴታ  እንዳለኝ ተገነዘብኩ፤  ምርጫዬም የሰብአዊ መብትን መሟገትና ለዚህም ጥብቅና መቆምን ሆነ፡፡

ዴሞክራሲ (ቢያንስ በጥቅል ትርጉሙ) በሕዝብተቀባይነት ያለው መንግስታዊ ቅርጽ ነው፡፡ የነጻነትን ምንነትne ያላገናዘበ፤(ማለትም በነጻ ማህበራትን ማደራጀትን፤ሃሳብን በነጻ መግለጽን፤ የነጻውንፕሬስ አለማክበር ባዶ ቀፎ ነው የሚሆነው፡፡ ዴሞክራሲ ሲባልም ሰብአዊ መብትንና  ፍትህን ተጠያቂነትን ማክበርና፤የሕግ የበላይነትን መጠበቅ ፤ነጻ የፍትህስርአት፤ግልጽነት፤ተፎካካሪ ተቃዋሚ ፓርቲዎችንና የሲቪል ማሕበረሰቡን ያካተተ ነጻና ፍትሃዊ ምርጫን፤ማካተት አለበት ፡፡የዓለም አቀፍ ሰብአዊ መብቶች ጥበቃ ድንጋጌ  ቁ. 21(3)ዴሞክራሲንና ሰብአዊ መብትን ያዋህዳቸዋል፡፡ ለማንኛውም የመንግስት ስልጣን መሰረቱ የሕዝቦች ፈቃደኝነት በመሆኑ ይህም ሕዝባዊ ፈቃደኝነት በማንኛውም ጊዜ ሊከበር የግድ ነውናበፍትሃዊ ምርጫ ወቅትም ሊተገበር ይገባል ፤ የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ትርጉምና ጠቀሜታ ያለውን የዴሞክራሲ መብቶች ያካተተ ጥላ ነውና የዴሞክራሲን ተግባራዊነት በትክክለኛው መንገድላይ ያስኬደዋል፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ የሞካሄደውን ለሰብአዊ መብት  ትግል ለዴሞክራሲና ለመሰል ትገሎች የሚካሄድ ትግል ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ለዚህም ነው በኢትዮጵያ ከፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ ወደ ዴሞክራሲያዊ አስተዳደር ለሚደረገው ሽግግር የእኔነቴ ስሜት የተነሳሳው፤ ምክንያቱም ሽግግሩ ከተሳካ፤ሰብአዊ መብት ይከበራል፤ ይረጋገጣል ይጠበቃልም ብዬ አምናለሁ፡፡

በዴሞክራሲው ጎዳና ላይ ያለው ድልድይ

ከጭቆና አገዛዝ ወደ ዴሞክራሲያዊ የሽግግር ጎዳና እንደ ነጻነት፤የሰብአዊ መብት መከበር ብርሃን (የዴሞክራሲ) ተምሳሌታዊ ጉዞ  ልንወስደው እንችላለን፡፡በዚህ ጎዳና ላይ ሕዝቦችም ሆኑ የማሕበረ ሰቡአባላት በሁሉም አቅጣጫ የሚንቀሳቀሱት፡፡የፈላጭ ቆራጭ ስርአትም ወደ ዴሞክራሲያዊ አስተዳደር የሚቀየረው ፡ በዚህ ድልድይ ላይ ነው:: የሕዝቦችም ሆነ የሕብረተሰቡ፤ ትልቅምሆኑ አናሳዎች የሚፈጠሩትና የሚጠሩትና የሚጠፉትም፡፡በድልድዩ ላይ የሚከናወነው ሽግግር ስርአትን የጠበቀ፤ምክንያታዊ ሆኖ በዘዴ የሚመራ ከሆነ ዴሞክራሲ በእውን ይገነባል፡፡ ድልድዩየተተረማመስ፤መግባባት የጎደለው፤ አፍራሽነት፤ጉልበትን መሰረት ያደረገ ከሆነ ግን ድልድዩን መሻገር ዘበት ሆኖ ወደ ተጠላው ፈላጭ ቆራጭ ስርአት መልስ ይሆናል፡፡ ስለዚህ ጊዜው ሲቃረብና የፈላጭቆራጭነትና የዴሞክራሲያዊ ስርአትን የሚያስተላልፈው ሰአት ላይ ስንደርስ ምን ሊፈጠር ይችላል የሚለው ጉዳይ ነው የሚያሳስበኝ፡፡

በበርካታ ምክንያቶች የተነሳ ኢትዮጵያ ወደዚያ የዴሞክራሲ አስተዳደር ድልድይ በተፋጠነ መልኩ በመጓዝ ላይ ነች ብዬ አምናለሁ፡፡ምንም እንኳን ፈላጭ ቆራጭ ገዢው 99.6 በመቶ ምርጫውንአሸንፌያለሁ በማለት ዜማ የለሽ የሃሰት ከበሮውን ቢደልቅና የመርገጫ ማህተም የሆነውም ፓርላማ ቢያጸድቅለትም፤ ገዢው ፈላጭ ቆራጭ መንግሥት አንዳችም ሕዝባዊ ይሁንታና አመኔታ የሌለውነው፡፡ ኤኮኖሚው ተፈረካክሷል፤በአዲስ አበባ የሚገኘው አክሴስ ካፒታል ሼር ኩባንያ የተባለው ተመራማሪ ድርጅት እንዳለው፤በ2011 40.6 የዋጋ ግሽበት በማስመዝገብ ኢትዮጵያ በዓለም ሁለተኛውን የዝቅዝቅ ደረጃ ይዛለች ብሎ ዘግቧል፡፡የዓለም ባንክም እንደጠቆመው፤ ኢትዮጵያ በርካታ ባለባት ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት ሳቢያ በበርካታ ችግሮች ተወጥራለች፡፡የድህነት ቅነሳውም በዚሁግሽበት ታግዷል፡፡በጣም የተዋከበና ያልተረጋገጠ የገንዘብ ፖሊሲ፤ እድገትን እንደግመል ሽንት ወደኋላ ከመሳቡም አልፎ የማይክሮኤኮኖሚውን መረጋጋት ያዋዥቀዋል፡፡የኢትዮጵያ ወደ ኢንዱስትሪውእድገት ማዝገም በብዙ ሰበቦች ወደ አዘቀዘቀ የአምራጭነት ደራጃ ያወርደዋል፡፡

እናም ውጡቱ የማይሰተካከል የንግድ ኪሳራ ነው፡፡ በገዢው መንግስት ስረአት አልበኝነትና በራሱ በመሰነጣጠቁ የተነሳ ተቃውሞ የበዛበት ሆኗል፡፡ በርካታ ዜጎችን ከመኖርያ መንደራቸው ማፈናቀል፤ብዙዎች‹‹ የዘር፤ የጎሳ ማጥፋት››የሚሉት  በግልጽ ገዢውን ስርአት በመቃወምና በጎሪጥ ወደመመልከቱ አድረሷቸዋል፡፡በገዢው ፈላጭ ቆራጭ መንግሥትና በደጋፊዎቹ በሌላ ጎኑ ደሞ ብዙሃኑ ሆነውበመሃላቸው በእጅጉ የናረ ጥላቻ እየታየ ነው፡፡ ገዢው መንግስት ያፈጠጠውንና ሕብረተሰቡን ለችጋርና ለመረረ ኑሮ የዳረገውን፤ ማህበረሰብአዊ፤ ኤኮኖሚያዊና ፖቲካዊ፤ ዝብርቅርቅ ችግሮች ለመፍታትአዳዲስ ዘዴዎችን የመጠቀም ፈቃደኝነትም ሆነ መንገዱ ስለጠፋበት ሙሉ በሙሉ ጨልሞበት አጉል የሕዝብ ግንኙነት ፕሮፓጋንዳ መርጦ ግድብ መገንባት፤ኢንቬስትመንትን ማበረታታና ማጎልበት የሚልችግሮችን የመሸፈኛ ጭንብል ለማጥለቅ መመኮሩ በሃገር ውስጥና ከውጭውም የበለጠ ተቃውሞ እያስከተለበት ነው፡፡ በአንዳንድ ሁኔታዎችም የፈላጭ ቆራጩ መንግሥት መበስበስ በተደጋጋሚ ታየቷል፡፡የዚህ መሰረቱ የተናጠ አገዛዝ አወዳደቁ በውስጡ ከሚፈጠር እምቢተኛነት ይሁን፤ሕዝባዊ እምቢታ ወይም በሌላ መንገድ ይሀን አሁን መተንበይ ያስቸግራል፡፡፡

በቅርብ ርቀት ያለው ድልድይ

የሰው ልጅ ታሪክ ከመነሻው አንስቶ ከጭቆናና ከፈላጭ ቆራጭ አረመኔያዊ አገዛዝ ለመላቀቅ የሚደረግ የትግል ታሪክ ነው የሚለውን ፍልስፍናዊ ዓላማ የምንቀበል ከሆነ፤ በተፈጥሮ የሰው ልጅ ፍላጎትምነጻነትን በመቀዳጀት ጭቆናንና ተገዢነትን በማስወገድ ላለመመለስ መቁረጥ ነው፡፡ ጨቋኞችና ፈላጭ ቆራጭ ገዢዎች፤በሙስናና እና በጉልበት ነጻነትን ማፈን እንደሚችሉ በማመን እራሳቸውን ያሞኛሉ፡፡ሆኖም  ማቆም የማይቻለው የነጻነት ሂደት ግን በነዚህ ግፈኞች ላይ የራሱን ታሪካዊ ሕግጋት ያሳርፋል፡፡

የፈላጭ ቆራጭና የጨቋኞች ቀዳሚ ሕግጋትም የእነሱ መውደቅ አለመቅረቱ  ነው፡፡ጋንዲ ስለዚህ ጉዳይ ‹‹በታሪክ ሂደት ሁሉ ፈላጭ ቆራጮችና ነፍሰ ገዳዮች ነበሩ፤ጊዜያዊም ቢሆንየማይደፈሩ መስለው ይታያሉ፤ በመጨረሻው ግን መውደቃቸው የማይቀር ነው፡፡ይህንን ምንጊዜም በህሊናችሁ አስቡት›› ባለፈው ዓመት ብቻ ፈላጭ ቆራጭ አረመኔ ገዢዎች በቱኒዚያ፤በሊቢያ፤በግብጽእና በየመን እንደቅጠል ሲረግፉ መስክረናል፡፡ በነዚህ ሃገሮች በተዘጋጁና ለግፈኛ ገዢዎች መኖር ብቻ በቆሙ ሰላዮች፤ የጦር ወታደሮችና ፖሊሶች የሕዝቡ የነጻነትና ሰብአዊ ክብር ፍላጎት ጨርሶ ሊገታአልተቻለም፡፡ ሁለተኛው የታሪክ ህግ ደግሞ እነዚህ  ከ ስልጣን የወደቁ ፈላጭ ቀራጭ አረመኔዎች ከውድቀታቸው በኋላ ዘወትር ብጥብጥን አለመግባባትን፤ግጭትን ነው ትተውየሚያልፉት፡፡ ይህም ‹‹በአረቦቹ መነሳሳት›› ወቅት የታየ ነው፡፡ሶስተኛው ታሪካዊ ህግ ደግሞ የፈላጭ ቆራጮች መውደቅ የሚያስከትለው ዳፋ ለመገመት አስቸጋሪ መሆን ነው፡፡በእርግጠኝነት ግን የፈላጭ ቆራጮች መውደቅ የዴሞክራሲን መምጣት አያረጋግጥም፡፡ይልቁንስ በፈላጭ ቆራጭ ገዢዎች መውደቅ ሌላ ፈላጭ ቆራጭ ገዢ መነሳትን ነው የሚያስከትለው፤ ምክንያቱም እነዚያ ፈላጭ ቆራጮችን ከዙፋናቸው ያስወገዱት፤ አላማቸው እራሳቸውን በባዶውየዙፋን መንበር ላይ በማስቀመጥ እንዳለፉት ለመግዛት በማቀዳቸው ነው፡፡ ማለትም ‹‹ጉልቻ ቢቀያየር ወጥ አያጣፍጥም›› እንደሚባለው ያለ ነው፡፡ ወይም ጠርሙሱ ተለዋወጠ እንጂ ወይኑየድሮው ነው እንደማለት፡፡ አራተኛው ሕግ ደግሞ  አንዳንድ ጭክ ብለው ሙጢኝ ሥልጣኔ አምባገነኖች እስከመጨረሻው በመቸክ ሥልጣናቸውን ለማቆየት ሲብገታገቱ ነው::

በዴሞክራሲ መሸጋገርያው ድልድይ ላይ ሥልጣንን በማሳደድ ላይ ባሉት ግለሰቦችና ቡድኖች መሃልና እንዲሁም ጭቆናና ግፍ በሰለቻቸው የሕብረተሰብ አባላትና በስልጣን አንለቅም ባዮች ፈላጭ ቆራጭ ገዢዎች መሃል የግጭት መፈጠር ይከሰታል፡፡በዚህ ከፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ ወደ ዴሞክራሲ በሚወስደው የሽግግር ድልድይ ላይ የፖለቲካ ስልጣንን ለመጥለፍ አመቺው ሁኔታ ይፈጠርና፤በዴሞክራሲ ስም የፈላጭ ቆራጭነትን ሥላጣን መልሶ ለመገንባት አጋጣሚውን ይጠቀሙበታል፡፡ይህን በሚገባ የሚገልጽ አባባል በኢትዮጵያችን አለ ‹‹ግርግር ለሌባ ይመቻል›› ሁሉም አይነት የሂደቱ ተካፋዮች ከያሉበት ወደ ዴሞክራሲው መሸጋገርያ ድልድይ ይሰባሰባሉ፡፡ ሁሉም አይነት ተንኮል፤የሥልጣን ሽሚያ፤ችግሮች ሁሉ ይመጣሉ፡፡ በኢትዮጵያ እንደታየው የታሪክ እውነታ የሚከተለውን ያስገነዝበናል፡፡ ሊሆን የሚችለውም ይህን የመሸጋገርያ ድልድዩን ዋነኛ የተባሉት የውጭ ሃይሎች የሽግግሩን ወቅትና ሽግግሩን ራሱን ሊቆጣጠሩትና ሊመሩት ፈቃደኛነታቸውን በማሳየት ራሳቸውን እንደሸምጋይ ያቀርባሉ፡፡ በዚህም ራሳቸው ያስቀመጧቸውን ምልምሎችቸውን ቦታ ለማስያዝ የሽግግር ድራማቸውን በማቅረብ  ሕዝቡም የፈላጭ ቆራጮች አገዛዝ ሰልችቶት አዲስ ዴሞክራሲያዊ ስርአት ናፍቋልና  እነዚህ ሽማገሌ ሆነው የቀረቡት አሸማጋዮች በሽግግሩ አውቶቡስ መሪው መቀመጫ ላይ ይቀመጣሉ፡፡ ተሳፋሪዎቹንም ወደፈለጉት አቅጣጫ ያጓጉዟቸዋል፡፡

የጦሩ ክፍል (ቢያንስ በአመራር ላይ ያሉት) በሽግግሩ ወቅትና በሃሰት ወርቀዘቦ በተጠቀለለ ነጻና ፍትሃዊ ምርጫ ተስፋ፤  ሕግና ስርአትን ማስጠበቅ ሰላምን ማረጋገጥ አስፈላጊ ነው በሚል ሽፋን፤የሕዝቡን አመኔታ ለማግኘትና የእርዳታ ሰጪዎችን ችሮታ ለመቧገት ሲሉ ተጠያቂነትን፤ ሙስናን መከላከልን፤ሰብአዊ መብትን ማስከበርን፤ ሰበብ በማድረግ የፖለቲካ ስልጣን ለመያዝ ይጥራሉ፡፡በዚህም ለሕብረተሰቡ ከሽግግር ይልቅ የወታደራዊ አገዛዝን በሲቪሉ ሕዝብ ላይ ይጭናሉ፡፡ የፖለቲካ ድርጅቶችም ተሰባስበው ለስልጣን ሽኩቻ ይዘጋጃሉ፡፡  አንገታቸውን ደፍተው የነበሩ የውስጥ ሃይሎችም ከጨቋኝ ገዢዎች ስርአት ግፍና መከራ ከተላቀቁ በኋላ  የስልጣን ተጋሪነታቸውን ለማረጋገጥ በድርድሩ ጠረጴዛ ላይ ይሰየማሉ፡፡ አዳዲስ ቡድኖችም በመሰባሰብ ተደራጅተው፤የስልጣን ተጋሪነታቸውን ያሳውቃሉ፡፡ የየክልሉም ሰዎች ለራሳቸው የሚመቻቸውን ለማረጋገጥ በሽግግሩ ወቅት ሚና እንዲኖራቸው ያደርጋሉ፡፡የወደቀው ስርአትም ርዝራዦች እራሳቸውን በማደራጀት አለያም ከአለውና ፍላጎታቸውን ከሚጠብቅላቸው ቡድን ጋር በመቀላቀል ራሳቸውን ከተጠያቂነት ነጻ ለማድረግ ጥረት ያደርጋሉ፡፡

እያንዳንዱ ቡድን ለስልጣንና ለማግባባት ሲጋልብ በዚህ የስልጣን ስርቆት ውስ ይበልጡን ተጎጂ የሚሆነው ሕብረተሰቡ ነው፡፡ ወደ ዘር፤ ቋንቋ፤ ሃይሞኖት እና ጎጥ ጎራ ያስገቡታል፡፡ የቆየ ታሪክ እየተነሳ ለክስ ይቀርባል፤ የመገንጠል ማስፈራራትም ይከሰታል፤ክስና ቁርሾ ይነሳና የህብረተሰቡን አስተሳሰብ ያስጨንቀዋል፡፡በመጨረሻም ሕብረተሰቡ የግራ መጋባት፤እሮሮ ድህነት፤ችጋር፤መከራና የተሰበረ ልብ ሻንጣ ተሸካሚ ሆኖ ይቀራል፡፡

በግርግሩ የሽግግር ድልድይ በእርግጠኝነት አንድ ነገር ያጋጥማል፡፡የስልጣን ክፍተት፡፡በዚህ የስልጣን ክፍተትና ግርግር መሃል ነው ብልጣ ብልጦችና በደንብ የተደራጁ ቡድኖችና ግለሰቦች በሚገባ የተነደፈና የተዘጋጀ እቅዳቸውን በማቅረብና በመጠቀም፤የስልጣኑ ኮርቻ ላይ በመፈናጠጥ ከፈላጭ ቆራጭ ስርአት ወደ ዴሞክራሲ የሚደረገውን ሽግግር የሚያጨናግፉት፡፡

ውድቀትን  ማቀድ  ለመውደቅ መዘጋጀት ነው

በኢትዮጵያ ለሚከሰተው ፤ለማይቀረው፤ለማይቆመው፤ ለማይታለፈው ከፈላጭ ቆራጭ  አገዛዝ ወደ ዴሞክራሲያዊ ስርአት ሽግግር በሚገባ ማቀድ ያስፈልገናል፡፡የፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ በኢትዮጵያ ያልቅለታል፡፡ዋናው ቁም ነገር የዴሞክራሲ ትንሳኤ መቼ ነው ነው፡፡ ጥያቄውም  መቼና ምን መሳይ የሚለው ነው፡፡አሁንም አንድ ሌላ ኢትዮጵያዊ አባባል ሃሳቤን ይግለጽልኝ ‹‹ሠርገኛ መጣ በርበሬ ቀንጥሱ›› እንዳይሆንብን ከአሁኑ ለዴሞክራሲያዊ ስርአት ችግር የለሽ ሽግግር  አስፈላጊውን ዝግጅት በማድረግ ፈላጭ ቆራጩ ስርአት ሲወድቅ ሳይሆን አስቀድመን ልንዘጋጅና መሰረታዊ የሆኑትን ቅድመ ሁኔታዎች በመነጋገር ማዘጋጀት ይኖርብናል፡፡ቢያንስ ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ከአሁኑ ውይይቱ ሊጀመር ይገባል፡፡

1)  በሽግግሩ ወቅት የባለመብቶችን አስተሳሰብና አመለካከት በማዳበር ሊያጋጥምና በሸረኞች ሊጫር የሚችለውን ግርግርና አላስፈላጊ ረብሻ ለመከላከል የሚያስችላቸውን ንቃት ማስገኘት፡፡

2)  የሽግግሩን መምጣት አይቀሬነት በማወቅና ተከታዩን ሁኔታ በመፍራት ቀድመው የዘር፤የሃይማኖት፤የጎሳ፤ግጭት ለመፍጠር የሚደረገውን ደባ በተቻለ ለማስቀረትና ሰላማዊ ሁኔታ ለመፍጠር የሚያስችል ዘዴ መቀየስ፡፡

3)  የሲቪል ማሕበረሰቡን ተቋሞች ሕዝባዊ ግንኙነቶች እንዲካሄዱ የማድረግ ጥረታቸውን አዳብረው በሽግግሩ ወቅት ተግባራዊ ማደረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡

ለዴሞክራሲያዊ ስርአት ሽግግር አስፈላጊውን ከወዲሁ በማቀድ አለመንቀሳቀስ ሂደቱን ከማኮላሸት ጋር ተመሳሳይ ከመሆንም አልፎ የዴሞክራሲ ስርአትን ማምጣት ሳይሆን ሌላ ፈላጭ ቆራጭ መንግስት እንዲተካ ማመቻቸት ይሆናል፡፡ ከቅርብ ሁኔታዎችና አጋጣሚዎች መማር ይገባናል፡፡ሊቢያውያን አሰቀድመው ስለሽግግር ባለማሰባቸው የተነሳ፤ በውጭ ሰዎች አደራዳሪነት አንድነት ፈጥረው በአጋጣሚው በመጠቀም ጋዳፊን ለማውረድና ለማዋረድ በቅተዋል፡፡ዛሬም ቢሆን ሊቢያ በጎሳ ግጭት ወከባ ውስጥ ገብታ፤በከረረ የፖለቲካ፤የአካባቢ ልዩነት ባስከተለው የመረረ ቁርሾ ውስጥ ናት፡፡ ቤን አሊ አስቀድሞ ጥሎ በመፈርጠጡና ወታደራዊ ተቋሙም ከሽግግር ሂደቱ በመገለሉ፤ ቱኒዝያ በነዚህ ሁለት ምክንያቶች የተሻለ ሁኔታ አላት፡፡ ግብጽ ደግሞ በሽግግሩ ድልድይ ውስጥ መውጫ ያጣች ትመስላለች፡፡ወጣት የዴሞክራሲ ፋና ወጊ ወጣቶች ሥልጣንን በብር ሰሃን አስጊጠው ለወታደሩ ካስረከቡ በኋላ ሙባረክን ለዓመታት ሲጠብቅና ሲከላከልለት የነበረው ወታደራዊ ሃይል ስልጣኑን ከተረከበ በኋላ ወጣቱ የትግሉ ባለቤት ወደ ጎን ተገፍቷል፡፡ የዚህ ትግል ፋና ወጊ የነበረውም  የሲቪሉ ማህበረሰብ ተቋማትም በወታደራዊው ሃይል  ገሸሽ ተደርገው  ለጭቆና በድጋሚ ተዳርገዋል፡፡ ብዙ ልውውጦች በተከናወኑ ቁጥር ለውጡ ይቀርና እንደነበር መሆንን ያስከትላል፡፡

የግብጹ ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ ለመጪው ሜይ ታቅዶ ሳለ፤የግብጽ አስተዳደራዊ ካውንስል ችሎት አዲሱን የግብጽ ሕገመንግስት ከጨቋኙ ስርአት መውደቅ በኋላ የሚያረቁትን 100 አባላት ያሉትን ሕጋዊ ኮንግሬስ አገደ፡፡ ይህም እገዳ በተለያዩ የእምነት አባላት መሃል እና ሃገሪቱን በመምራት ላይ ያለውን ወታደራዊ ካወንስል ሁሉንም  ወደ መደናገጥና ውጥረት ጨምሯል፡፡ ሕገመንግስት አልባ በሆነ ወይም በቀድሞው ሕገመንግስት የሚመራ ፕሬዜዳንት መምረጥ ከፈረሱ ጋሪውን እንደማስቀደም ያህል ነው፡፡ እንደእውነቱ ከሆነ ግን አብላጫውን ቁጥር በያዙት በሙስሊም ብራዘርሁድ የነጻነትና የፍትህ ፓርቲ እና የሳላፊስት ኑር (በፓርላማ አብላጫውን መቀመጫ የያዘው) ፓርቲ የሚመራው የዚህ ሕገ መንግስት አርቃቂ ካውንስል የመረረ ችግር አለበት፡፡ ሃይማኖታዊ አባለት የእስልምናና የክርስቲያን ተወካዮችን ጨምሮ በግድግድው ላይ በእጅ የተጻፈውን በማንበብ ከካውንስሉ ለቀቁ፡፡ ሴቶችና የሲቪል ማህበረሰቡ አባላት ውክልናቸው በጣም አናሳ ነው፡፡ይህንን የአንድን ሀገር መተዳደርያ የሆነውን ሕገመንግሥት ለማርቀቅ ከተሰየሙት መሃል ጥቂቶች ናቸው የሕግ ችሎታና እውቀት ያላቸው፡፡ከባለጉዳዮቹ ውክልና ሚዛን ማጣት ባሻገር፤ አንዳንድ ሕገመንግስታዊ ችግር የሚያስከትሉ ጉዳዮች አሉ፡፡ዋነኛው አሳሳቢ ነጥብ፤የእስልምና ሕግ (ሻርያ) በሕገመንግሥቱ ውስጥ የተሰጠው ሚና ነው፡፡የሴቶችን መብት፤የአናሳ ሃይማኖታዊ ተቋማት መብት፤ የግለሰብ መብትንና የሌሎችንም የማህበረሰብ አባላት መብት ጥበቃ ባላሟላ ረቂቅ፤ ሚዛናዊ የመብት ጥበቃ እንዴት ሊኖር ይችላል፡፡ በዚህ ሁሉ ግርግርና ውጥንቅጥ ሁኔታ ውስጥ አንድ ሰው ብቻ በፖለቲካው ሜዳ ላይ ገዝፎ ይታያል፡፡ ከወታደራዊው ተቋም በተሰጠው ይሁንታ መሰረት የቀድሞው የግብጽ ምክትል ፕሬዜዳንትና የደህንነት ሹም፤ለፕሬዜዳንታዊ ምርጫ ተዘጋጅቷል፡፡ይህ ግለሰብ ከምር ምርጫውን ካሸነፈ ለዴሞክራሲ ስርአትና ለነጻነት ብዙ ሕይወት የተከፈለበትና ሕዝብ መከራ ስቃዩን የበላለት የግብጽ የዴሞክራሲ ጨዋታ ፍጻሜ ይሆናል፡፡የግብጽ ግስጋሴ ወደ ዴሞክራሲያዊ ስርአትም መሆኑ ቀርቶ፤ ወደ ግብጽ የፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ ስርአት ምለስት ይሆንል፡፡ ስለዚህም፤ነገሮች በተደጋጋሚ በተለዋወጡ ቁጥር እነበሩበት ቦታ ይመለሳሉ፡፡ ከግብጽ የዴሞክራሲያው ስርአት ሽግግር ኢትዮጵያ በእጅጉ ብዙ ልትማር ትችላለች፡፡

ከፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ ወደ ዴሞክራሲያዊ ሥርአት የሚደረገውን የሽግግር ውይይት ማን ይመራዋል?

የኖረው አስተሳሰብ ከፈላጭ ቆራጭ የግፍ አገዛዝ ወደ ዴሞክራሲያዊ ስርአት ለሚደረግ  ሽግግር ውይይቱ ለምሁራን–ለፖለቲካ ሰዎች፤ ለፓርቲ መሪዎች፤ለቢሮክራቶች፤ለምሁራ እና ለሌሎችም ተቋማት መሪዎች ሊተው ተገቢ ነው ይላል፡፡ የአካሄዱን መንገድ ቅያስና ተግባራዊ እቅዱን በሚገባ ለማዳበር ጥሩ ጠቃሚና ጉልህ ሃሳብ ስላላቸው ለዴሞክሲያዊ ስርአት የሚደረገውን ሽግግር ውጤታማ ያደረጉታል፤ በዚህም ውስጥ ሁሉም የማህበረ ሰቡ አባላት የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች፤የሲቪሉን ማህበረሰብ ተቋማት፤ሴቶችና ወጣቶች ሊካተቱበት የግድ ነው፡፡ እንደእውነቱ ከሆነም የዚህ ሽግግር ሂደት በሲቪሉ ማህበረሰብ ተቋማት፤ሴቶችና ወጣቶች መሪነት ቢካሄድ ውጤታማነቱ የበለጠ ፍሬያማ እንደሚሆን ይታመናል፡፡በሽግግር ወቅት እነዚህ ስብስቦች በርካታውን የማህበረሰቡን አባላት ሊያሰልፉ ስለሚችሉ ለሚገኘውም ውጤት ፍሬያማነት ወሳኝ ሚና አላቸው፡፡ድምጻቸው የታፈነውን፤ምሰኪኖች፤ጭቁን የማሕበረሰቡን ተገፉትን ድምፅ ስለሚያሰሙላቸው ተሳትፎውን የሁሉም የማድረግ ሃይል አላቸው፡፡

የወደፊቱ የራሱ ስለሆነ ወጣቱ እጅጉን አስፈላጊና ጠቃሚም ነው፡፡ጆርጅ አይቴ እንደሚለው በአፍሪካ ሁለት ትውልዶች አሉ፡፡አንዱ የአነር ትውልድ ሲሆን ሌላው ደሞ የጉማሬ ትውልድ ነው፡፡አነሮች እውቀት ዘመናዊነት ፈላጊ ና ለሚከሰቱ ችግሮች መውጫ መንገድ ይፈጥራል፡፡ጉማሬ ደሞ ሌሎችን ይወቅሳል፤ ይኮንናል፤ ይረግማል፤ምጽዋት ጠባቂ ስለሆነም አህጉራችንን ወደመቀመቅ ይወስዳታል፡፡ አዲሱ የአፍሪካ ፍጡርና ስለ ሙስና አርቲ ቡርቲ የማያወራው አነሩ ወጣት ነው፡፡ተጠያቂነትና ዴሞክራሲያዊ ስርአት ምን እንደሆነ ጠንቅቆ የተረዳ ነው፡፡ መንግሽት ምንም እንዲያደርግላቸው አይጠብቁም፡፡የአፍሪካ ምጽአትና ትንሳኤም በነዚህ አነር የአፍሪካ ልጆች ጫንቃ ላይ ነው፡፡‹‹የኢትዮጵያ መዳንና ከክፉ በሽታ መላቀቅም በነዚህ አነሮች መዳፍ ውስጥ ያለ ነው፡፡ ታሪክ እንደሚመሰክረው እስከዛሬ ድረስ ተገልለው፤ ተገፍተው፤ተረስተው፤ተንቀው የነበሩት ሴቶችም በዚህ ሂደት ውስጥ በቂ ሚና ሊኖራቸው አስፈላጊ ነው፡፡ የጾታ እኩልነት ባልተረጋገጠበት ሁኔታ እውነተኛውና ትክክለኛው የዴሞክራሲ ስርአት ጨርሶ ሊፈጠር አይችልም፤ በግልጽ የሚታየው የኢትዮጵያ ሁኔታም የሚያረጋግጠው ይህንኑ ነው፡፡ በግልጽ እንደሚታወቀውና ሊካድም የማይችለው፤ሴቶች በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ  የሶሽዮ ካልቸርና የኤኮኖሚ ጭቆና ሰለባ ከመሆናቸውም አልፎ በግላቸው ለልማት ለመንቀሳቀስ፤ ለትምህርት፤በሥራ ለመሰማራት ከወንዶች እጅጉን ያነሰ እድል ነው ያላቸው፡፡ በሽግግሩ ሂደት ንግግር ላይ የሴቶች መሳተፍ ጠቀሜታው  የራሳቸውን ልዩ አመለካከትና ግንዛቤ ይዘው ስለሚቀርቡ ነው፡፡ ልዩ የመሪነት ችሎታ ስላላቸው ለዴሞክራሲው ሽግግርና ለአስተዳደሩ የሚበጅ  ዘዴ ይዘው ይቀርባሉ፡፡ከዚያም አልፎ ከወንዶች ይበልጥ ታማኝ፤ብልህ፤ተግባቢና ታማኝ ናቸው፡፡ሩሩህ በመሆናቸውና፤ከወንዶች በተሸለ መደራደር ስለሚችሉ፤መቻቻል ስለሚያውቁበትም አስፈላጊነታቸው አያጠያይቅም፡፡በኢትዮጵያ ጥቂቶች ብቻ  ማንነታቸውንና ችሎታቸውን ለማስመስከር እድል ያገኙ በመሆናቸው በትክክል ስለሴቶች ችሎታና ብቃት ማወቅ አንችልም፡፡ ስለዚህም በኢትዮጵያ በሚካሄደው የዴሞክራሲያዊ ስርአት ሽግግር ውስጥ በሚካሄደው የመወያያ መድረክ ላይ ሴቶች በቂ ሚና ሊኖራቸው ተገቢ ነው፡፡

ውይይቱ የዴሞክራሲ ስርአቱን ራዕይ መዳረሻ በማድረግ ወደ ብሔራዊ መግባባት ሊያመራ ስለሚችል፤ይሀ ደግሞ በኔ ግምት ሁልጊዜም ሕዝብን ወደሚያከብርና የሚፈራ መንግስት መመስረት፤የፖለቲካ ስርአቱም ሕዝቡ ጨርሶ የማይፈራውን ስርአት የሚያመጣ—የኢትዮጵያን ሕዝቦችም ወደ መግባባቱ የሚያቀራርብ ይሆናል፡፡ ስለዚህም ውይይቱ በሕዝባዊ አዳራሾች፤ በጎዳናዎች፤መፓርኮችና በሕዝባዊ መናፈሻዎች፤ በመንደሮች፤ በገጠር መኖርያዎች፤ በየመንደሩ፤በጋዜጣዎች ላይ፤ በቢሮዎች፤በስብሰባ አዳራሾች፤በስታዲዩሞች፤በወጣቶችና በሴቶች ማእከላት፤በንግድና በገበሬ ማህበራት፤በት/ቤቶችና በዩዮ፤ቴሌቪዢን፤በድህረ ገጾች፤በፌስቡክ፤በቲዊተር፤በዩቲዩብ፤በስካይፔ፤በኢሜይልና በሁሉም አቅጣጫ ሊጀመርም ሊቀጥልም ይገባል፡፡

Leave a Reply