ለኢትዮጵያዊያን፤ የጨለመው ስደት በኖርዌይ

Click here for PDF

ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ

በሃገራቸው ባለው ጨካኝና አረመኔያዊ አገዛዝ ሳቢያ፤ገዛዙ በፈጠረው የኑሮ ውድነት፤ የነጻነት እጦት፤በችጋሩ፤ በሙስና፤ አረመኔው መንግሥት ሆን ብሎ፤ አውቆ፤ ፍጥረቱ ለጥፋት ተልእኮው በኢትዮጵያዊያን ላይ ስደትናእንግልትን ማደርጀት ነው፤ በሚፈጽመው የዲያቢሎስ ተግባር ሃገራቸውን ጥለው የተሰደዱት ኢትዮጵያዊያን በሰሜን አፍሪካ፤በመካከለኛው ምስራቅ በሌሎችም የአፍሪካ ሃገራት ለባሰ መከራና ስቃይ እየተዳረጉ ነው፡፡ ኢትዮጵያውስጥ መኖር ሳይሆን ለመኖር ማሰብ እንኳ ችግር ሆኖባቸው ስደትን ቢመርጡም ስደቱም ዳግም እያሰደዳቻው ነው፡፡

ባለፈው ጃንዋሪ በሺህ የሚቆጠሩትን ኢትዮጵያዊያን የቤት ሰራተኞች፤ ወደሰሜን አፍሪካና ወደመካከለኛው ምስራቅ ፍልሰትን፤ ስደትን በተመለከተ ‹‹ኢትዮጵያ፤ ለመካከላኛው ምስራቅ የሽግግር ሰርጥ›› የሚል አንድ ጽሁፍአውጥቼ ነበር፡፡ ተጨባጭ የሆኑ ማረጋገጫ ማስረጃዎች፤በነዚህ ኢትዮጵያዊያን ላይ የሚደርሰውን ግፍ፤ በደልና ኢሰብአዊ ድርጊትና ‹‹በውል የታሰረ ባርነት›› የሚደርስባቸውን መደፈርና የኤኮኖሚ ጫናና ግፍ በገሃድ ያሳያል፡፡ባለፈው ኦገስት መጨረሻ ላይ የጋዳፊ ልጅ ሚስት የኢትዮጵያዊት የቤት ሰራተኛዋ ላይ የፈላ ውሃ በመላ ሰውነቷ ላይ በመገልበጥ እንዳቃጠለቻትና ፊቷ ማንነቷን ማሳየት እስከሚያስቸግር ድረስ አድርሳት እንደነበረ ምስሏንተመልክተናል፤አለያም ሰምተናል (ለቪዲዮ እዚህ ይጫኑ) ፡፡ ሌላዋ ወጣት የቤት ሰራተኛ፤ግፉ ስላንገሸገሻትና ምሬት ስለበዛባት፤የመለስ ዜናዊን አገልጋይ በአንድ ስብሰባ ላይ ፊት ለፊት ተጋፈጠችው(ለቪዲዮ እዚህ ይጫኑ)፡፡ ጥያቄ እያነሳች መልስ እጣ ብላ አፋጠጠችው፡፡‹‹ለምንድን ነው ይሄ መንግሥታችን ስለእኛ ደንታ ቢስ የሆነው?ለምን ስለእኛ ትንሽ እንኳን አያስብም፤ምን ሆናችሁ? መን ገጠማችሁ? ለምን አይለንም? ዓይኖቿ በእንባ ተሞልተው እያነባች ‹‹የታለ ባንዲራችን? አሁንስ በቃ አንገፈገፈኝ ከዚህ በላይ ዝምታ አልችልም››!!!!! (ለቪዲዮ እዚህ ይጫኑ)

ከሁለት ሳምንታት በፊትም ሌላዋ ስደተኛ ኢትዮጵያዊት የቤት ሰራተኛ፤ያድኑኛል፤በችግሬ ይደርሱልኛል፤በዜግነቴ ከጎኔ ቆመው ይሞግቱልኛል፤ አያስነኩኝም ብላ በሞኝነት የዜግነት መብቷ በምታምንባቸውበሌባነን በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ደጃፍ፤ በጎዳና ላይ እንደቆሻሻ እቃ ስትጎተትና ስቃይ ሲደርስባት፤ እየተረገጠችና እየተጠፈጠፈች ፍዳዋን ስትበላ፤ አመኔታዋን የጣለችባቸው የቆንሲላው ባለስላጣን፤የገዢው መንግስትአገልጋዮች፤በየመስኮታቸው ሆነው ከማየት ውጪ ሳይደርሱላት ቀሩ(ለቪዲዮእዚህይጫኑ)በግድና በጉልበት መንገደኛው እንደ ትርኢት ጉዱን እያየ፤ የቆንሲላውም የገዢው ሹሞች ድርሽሳይሉላት፤በጠራራ ጸሃይ ታፍና በመኪና ተወሰደች፡፡ ከቀናት በኋላም፤ የሊባኖስ ባለስልጣናት፤ ኢትዮጵያዊቷ ዓለም በነበረችበት የስነልቡና ታካሚዎች ሆስፒታል ውስጥ እራሷን መግደሏን ይፋ አደረጉ፡፡ባለፉት ጥቂት ቀናት ኢትዮጵያዊያን የመን ከሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ ኮሚሽን እርዳታ ለማግኘት በሄዱበት ጊዜ በየመን ፖሊሶች በአደባባይ እንደተደበደቡ ተዘግቦ ነበር፡፡ ከነዚህም ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች መሃል 25ቱ ለእስር ሲዳረጉ፤ ሌሎች ደግሞ በየመን ሰብአዊ ምት ጠባቂ ቢሮ ለአቤቱታና ለደህንነታቸው ጥበቃ ለመጠየቅ ቢሄዱ ዳግም በየመን ፖሊስ የዱላ ናዳ ወርዶባቸዋል፡፡ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በኬንያ፤ በሱዳን፤በደቡብ አፍሪካም በሕግ አስከባሪፖሊሶችና በጎዳና የሃገሬው ጉልበተኞች ግፍና መከራ ደርሶባቸዋል፡፡በዓለም ላይ መብታቸውን የተገፈፉና መድረሻ ያጡ፤በሃገራቸውም እንደዜጋ፤ በስደትም እንደ ሰብአዊ ፍጡር ሕልውናቸው ተገፎ ለመከራና ለስቃይ የተዳረጉሕዝቦች ኢትዮጵያዊያኖች ናቸው፡፡

በቅርቡ አዲሱ አሳዛኝና የበደል በደል የሆነው፤የኢትዮጵያዊያን ስደተኞች የግፍ ዜና ደሞ የተሰማው ከኖርዌይ ነው፡፡ሰሞኑን የኒርዌይ መንግስት፤የግዴታ ምልሰት፤(forced deportation) በሚል አዲስ አስገድዶ ወደ መጡበትለመመለስ ባወጣው ደንብ፤ ከመቶ እስከ ሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን የፖለቲካ ስደተኞችን፤ወደ ኢትዮጵያ ሊመልስ ነው፡፡ እንደሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ዘገባ፤እነዚህ ኢትዮጵየዊያን ስደተኞች ላለፉት በርካታዓመታት በኖርዌይ በስራ ተሰማርተው እንደነበር ያስረዳሉ፡፡እነዚህ ስደተኞች በመጀመርያ ወደ ኖርዌይ ሲገቡ በሃገሩ መንግሥት የስራ ፈቃድ ደብተር በህጋዊ መንገድ ተስጥቷቸው እንደነበርና፤ በኖርዊጂያን ሕብረተሰብ መሃልሠርተው እንዲኖሩ መብት አግኝተው እንደነበር ይገልጻሉ፡፡ስደተኞቹ ኢትዮጵያዊያንም፤የሃገሪቱን ቋንቋ አጥንተው፤ከባሕሉ ጋር ተግባብተውና ተስማምተው በመኖር ላይ ናቸው፡፡ ከነዚህ ለመከራ የተዳረጉ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችመሃልም፤በኖርዌይ የተወለዱና ለበርካታ ዓመታት የስደተኛነት ፍቃድ ጠያቂዎች ማእከል ውስጥ የሚኖሩ 450 ሕጻናት ይገኙበታል፡፡ከሕጻናቱ መሃል በርካታዎቹ ከኖርዌጂያን ቋንቋ ውጪ አያውቁም፤ ሕጻናቱ በሙሉትምህርታቸውን በመከታታል ላይ ያሉ ናቸው፡፡

እነዚህ ስደተኞች በሃገራቸው ያለውን ግፈኛና ጨቋኝ የመለስን ገዢ መንግሥት መከራ ለማምለጥ በጥፍራቸው ቆመው፤እድላቸውን ብቻ ተስፋ በማድረግ እግራቸው እስኪላላጥና፤ችጋር በስቃይ ቆልቷቸው የስደት ዓላማቸውየተሳካላቸው ናቸው፡፡ አብዛኛዎቹም የመለስን ግፈኛና ዘረኛ፤ ፈላጭ ቆራጭ፤ አምባገነን መንግሥት ተቃዋሚዎች ናቸው ፡፡ በአለፈው ኦክቶበር 2011 በኦስሎ የተካሄደውን የኤነርጂ ስብሰባ ምክንያት በማድረግ የመለስንበስብሰባው ላይ መገኘት በመቃወም፤በሃገራቸውና በወገናቸው ላይ የሚደርሰውን ግፍ ፈጻሚውና አስፈጻሚው መለስ የተባለ ነቀርሳ መሆኑን በማጋለጥ፤ በኦስሎ ከተማ አደባባይ የተቃውሞ ሰልፍ ያደረጉ ናቸው (ለቪዲዮእዚህይጫኑ) በኖርዌይ ያለውን ነጸነት፤ የሰብአዊ መብት መከበር፤ ሃሳብን በነጻ የመግለጽ ነጻነት መሰረተ በማድረግ፤ላለፉት በርካታ ዓመታት በዓለም ዙርያ ያሉ ኢትዮጵያውያን የሚያነሱትን ርእሰ ጉዳይ በመቀላቀል ይሳተፉየነበሩ ቀንደኛ ተቃዋሚዎችና ለሃገርና ለሕዝብ የቆሙ ስደተኞች ናቸው፡፡

‹‹የመግባቢያው ስምምነት ሰነድ››

የዚህ አስገድዶ ወደ መጡበት የግፍና የመከራ፤ ከዚያም አልፎ ለሞት አገዛዝ ወዳለበት መመለስ መሰረቱ፤የመግባቢው ስምምነት ሰነድ (MOU) (መ ስ ሰ) መፈራረም ነው፡፡ይህ ስምምነት የዓለም አቀፍ ሰብአዊ መብትን ድንጋጌበተመለከተ፤ወደ መጡበት መመለስን የሚያመላክተውን አንቀጽ ሰበብ በማድረግ በግፈኛውና ዘረኛው መለስ ዜናዊና፤በኖርዌይ መንግሥት መሃል የተፈረመ ነው፡፡ የስምምነቱ አላማም የኢትዮጵያ መንግሥት፤ ወደ መጡበትየሚመለሱትን መብት እንዲያከብር ይላል፡፡የምልሰቱንም ሂደት በተመለከተ የኖርዌይ መንግስት አስፈላጊውን ቁጥጥር ማድረግ፤ ድጋፍ መስጠትን፤ለኢትዮጵያ ግፍኛና ፈላጭ ቆራጭ መንግስት እንደሚያደርግ ስምምነት ተደርጓል፡፡በፍቃደኝነት ወደ ሀገራቸው ለመመለስ የተስማሙት በሙሉ ሃገራቸው እንደደረሱ የተወሰነ የገንዘብ መቋቋሚያ ድጋፍ እንደሚደረግላቸው ቃል ተገብቶላቸዋል፡፡

በጣም አሳፋሪውና አሳዛኙ ጉዳይ ደግሞ፤በመስማሚያውሰነድ ተለጣፊ ሰነድ (annex) ቁጥር 3 ላይ የሰፈረው ነው፡፡ ‹‹ የኖርዌይ መንግሥት ስለኢያንዳንዱ ተመላሸ ስደተኛ የግል ታሪክ፤ፓስፖርት፤ማንነት (ዘር) የመንጃ ፈቃድ፤ በአዲስ አበባ በሚገኘው የሮያል ኖርዌይ ኤምባሲ ቢሮበኩል ለመለስ ግፈኛ መንግስት የስለላ ድርጅት ቢሮ እንደሚሰጥና ሁሉንም ሂደትና አፈጻጸም በተመለከተም የኖርዌይ ፖሊስና ደህንነት ቢሮ እንደሚከታተል ይገልጻል፡፡ይህም ማለት የእያንዳንዱ ተመላሽ ስደተኛ ማንነትና ተግባርከታወቀ በኋላ ለወህኒ መዳረግንና ግርፊያን፤መከራን ያስከትላል፡፡በዚህም የኖርዌይ መንግሥት ለዘረኛውና አምባገነኑ መለስ የደህንነትና የቁጥጥር ስራ እየሰራለት ነው ማለት ነው፡፡

ስምምነቱ እንደተፈረመ ወዲያው፤የኖርዌይ ዓለምአቀፍ ልማት ሚኒስትር ኤሪክ ሶልሄይም የመለስ ገዢና ግፈኛ ኢሰብአዊ፤ጸረ ዴሞክራሲ፤ ፍትህ አልባ መንግስት 350 ሚሊዮን ክሮነር ዓመታዊ እርዳታ እንደሚመጸወት አስታወቀ፡፡(ይህ ሁኔታ እነደአዲስ ሊያስገርመን አይገባም፡፡ በዘመነ ደርግ ቤተእስራኤሎችን የማጓጓዙ ሂደት ላይ የመንግሽትን ይሁንታ ለማግኘት 35 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ክፍያ ተፈጽሟል፡፡ይህም ስደተኞችን በዘመናዊ የኖርዌጂያዊ ዘዴ የስደተኞችሽያጭ መሆኑ ነው፡ ኖርዌይን ያህል ሰላማዊ ነኝ ብሎ፤ የሰብአዊ መብት ሊከበር እንደሚገባ የሚዘምር መንግሥት፤በሕዝቡ ሳይሆን በግዴለሽ ባለስልጣናት እንዲህአይነት ተግባር መፈጸሙ የሚያሳዝን ነው፡፡ ጉዳዩን በተመለከተ በርካታ የዓለም አቀፍ ሰብአዊ መብት ተሟጋቾች፤የኖርዌይ የተለያዩ የፖለቲካ መሪዎች፤የሃገሪቱ ተቃዋሚ ፓርቲዎችና ግለሰቦችም ስለ ምልሰቱ የጠነከረ ተቃውሞ አሰምተዋል፡፡

የመግባቢያ ሰነድ ወይስ ስደተኞችን ሽያጭ

በቅድሚያ ሊብራራ የሚገባው ጉዳይ አለ፡፡ በማንኛውም የዓለም አቀፍ የሕግ ዘርፍ፤ይህ የመግባቢያ ሰነድ በጭራሽ የስደተኞች በግዳጅ የመመለስ ስምምነት ሰነድ ሊባል አይችልም፡፡በዓለም አቀፍ ሕግጋት መሰረት፤ የመግባቢያሰነድ በዋናነት ሊጠቀስ የሚችል የሕግ ሰነድ ነው፡፡ይህም ብዙ የስምምነት ሰነዶች አካል(treaty) ሊሆን ስለሚገባ በተባበሩት መንግሥታት ጽ/ቤት ተመዝግቦ እውቅና ሊያገኝ የሚያስፈልገው ነው፡፡ የመግባቢያ ስምምነት ሰነድበሚገባ በሥራ ላይ ከዋለ እንደመደበኛ የስምምነት ሰነድ ሊያገለግል ይችላል፡፡ይህ ሰነድ ዋስትና ነው አይደለም ለሚለውም ዓለም አቀፉ ደንብ በሚጠይቀው መሰረት በሁለቱ ተስማሚዎች መሃል የሚኖር ውለታ ነው፡፡

የኖርዌይ መንግስትና ግፈኛው የመለስ ገዢ ስርአት ውለታ የተግባቡበት ያላዋቂ ሳሚ አይነት ሙንጫሪ እንጂ ሰነድ ነው ለመባል ያላሟላው ግድፈት ስላለበት ሕጋዊ ሰነድ ሊባል አይችልም፡፡የሞራል ልሽቀትን ለመሸፈኛ፤ይህንንምተጠቅሞ ለሰው በላውና ግፈኛው መለስ ዜናዊ ወህኒ ቤቶችና ከፍ ብሎም ጣታቸው የመሳርያቸውን ቃታ ለመሳብ፤ሰብአዊ ፍጠርን ስብእናውን አሳጥቶ ለመግደል፤ጣታቸውን ለሚያሳክካቸው፤ የመግደል ሱሰኞች፤ የመለስአገልጋዮች ለማስረከብ የተነደፈ ነው፡፡

‹‹የመለስ ወህኒ ቤቶች ግፍና በንጹሃን ዜጎች ላይ የሚያደርሰው በደል በሰፊው የተነገረለትና የታወቀ ነው›› ሰነዱ በቀድሞው አጠራር ‹‹የጨዋ ሰዎች ስምምነት››

(gentlemen’s agreement) አለያም‹‹የሰነድ ልውውጥ›› (exchange of notes) ይባል የነበረው አይነት ነው፡፡(በግምትና በምናልባት ላይ የተመሰረተ ሃሳብ ነው፡፡) ሊሆን ይችላል በሚል ግንዛቤ የተቀረጸ ስለሆነ ጨርሶ ግዴታ አያስገባም፡፡በመለስና በኖርዌይመንግስት መሃል የስደተኞችን ደህንነትና ቀጣይ ሰላማዊ ኑሮን በተመለከተ አንዳችም ዋስትና ያላዘለው ይህ ሰነድ፤የኖርዌይ መንግስት በሃገሩ በሕጋዊ መንገድ ገብተው ዓለም አቀፍ የስደተኞች ሕግ በሚጠይቀው መሰረት ዛሬ ነገእየተባሉ፤ መልስ በመጠባበቅ ላይ ያሉትን ኢትዮጵያዊያን፤ለመለስ የግፍና የኢሰብአዊ አገዛዝ አሳልፎ በመስጠት ባለፈው በመሃላቸው ለተፈጠረው አለመግባባት ማለዘቢያ ማድረግ ነው፡፡ ሰነዱ አንድ ጊዜ በአውሮፕላን ተጭነውለግፍና ለመከራ ድርጎ ከተራገፉ በኋላ አንዳች መብት ማስከበርያ አለያ የመለስን መንግሥት ለተጠያቂነት የሚያበቃ ቃል የለውም፡፡ የኖርዌይ መንግሥት ከሃገሩ አውጥቶ ለጅብ መንጋ ካስረከበ በኋላ ተበሉ አልተበሉ፤ተነከሱ አልተነከሱ ጠፉ ኖሩ ጉዳዩ አይደለም፡፡ ምናልባት፤ የኖርዌይ መንግሥት ይህን ሰነድ የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ሊለው ይችላል፤ቀሪው ዓለም ግን ‹‹ስደተኞችን ለንዋይ›› አለያም ሰብአዊ ፍጡሮችን ለተፈጠረአለመግባባትና ቁርሾ ማለዘቢያ ከማለት ውጪ ምንም ብሎ ሊጠራው አይችልም፡፡

ጠቦቶችን ለቀበሮ መንጋ ማቅረብ

ኔቪል ቻምበርሊን፤ በሁለተኛው ዓለም ጦርነት ዋዜማ፤ በጀግንነትና በድል አድራጊነት ‹‹ይህ ውል ሁለቱ ሃገሮች ወደ ጦርነት እንዳይገቡና ከጦርነት እንዲርቁ የተፈረመ ነው………ስሙ የሰፈረበት ሰነድ ይሄው፤የኔም ስምአለበት……››ብሎ ተናገረ፡፡ወዲያው ግን የሙኒክ ውለታ ወይም ስምምነት፤ ከተጻፈበት ወረቀት ያነሰ ዋጋ ያለው እንደነበረ ለመገንዘብ ተቻለ፡፡ ሂትለርም በቻምበርሊን የስላቅ ሳቅ ሳቀበት፡፡

የራሱን ሕገ መንግሥት የረገጠና የጨፈለቀ ራሱ ያወጣቸውን ሕግጋት የጣሰ እና የደመሰሰ ፤ የዓለም አቀፍ ሰብአዊ መብቶች ድንጋጌ ያሾፈናያላገጠ፤ በአሰርትሺ የሚቆጠሩ ዜጎችን ለእስርና ለመከራ የዳረገ፤ በምርጫ 99.6 በመቶ አሸነፍኩ ብሎ ከሰውም አልፎ ለራሱ የዋሸ፤ የአጠቃላይ ተቃዋሚ ድርጅቶችንና ዴሞክራሲያዊ ተቋማትን እንቅስቃሴ የገታ፤ጋር መዋዋል ዘበት ነው፡፡ በጣም መጥፎ የሆነ አላዋቂነት ላይ የተመሰረተ ክህደት ነው፡፡አለያም የኖርዌይ መንግሥት ስለ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ደንታቢስ መሆኑንና ለወደፊትም ኖርዌይን ለስደት የሚመኙትን ተስፋ በማስቆረጫነት ለመጠቀም የተዘረጋ መረብ ነው፡፡

ይህንን የመግባቢያ ሰነድየኖርዌጂያን መንግሥት የስደት ተቀባይነት ላጡ ኢትዮጵያዊያን እንደ ‹ሰብአዊ›› እና ‹‹የክብር›› የምልሰት ‹‹ሰብአዊ ቅልቅል››በመጥራቱ መሳቂያና መሳለቂያ ነው የሆነው፡፡የኖርዌይ መንግሥት ረዘም ያለየቅሌት መንገድ ተጉዞ፤ዓለም ይህን የስምምነት ሰነድ ‹‹የሰብአዊነት መልሶ መቀላቀያ›› ቢለውም በመጨረሻው ግን ግፈኛውና ፈላጭ ቆራጩ ዘረኛው መለስ ዜናዊ፤በኖርዌይ መንግስትና ባለስልጣናት ሞኝነትና፤ ባሳዩት የሞኝአመኔታ እንደአምሳያው ሂትለር ፍቅፍቅ ብሎ ይስቅባቸዋል፡፡ ወደ ሃገራቸው በመገደድ የተመለሱትም ኢትዮጵያዊያን በመለስ የማጎርያ ወህኒዎች ተመልካች አጥተው ለተለያዩ መከራና ስቃይ ተዳርገው እምባዎቻቸው አልቀው፤ደም ያጎርፋሉ፡፡ በዚህ የመግባቢያ ስምምነት ሰነድም የኖርዌይ መንግሥት የእነዚህን ተመልካች ያጡ መከረኛ ኢትዮጵያዊያን በብርና እንቁ ያጌጠ ሰሃን ላይ አድርጎ ለመለስ ዜናዊ የቀበሮ መንጋ በዳረጎት መልክ አቅርቧል፡፡ዕውነታው በምንም መልኩ አጠያያቂ አይደለም፡፡

በኢትዮጵያ ወቅታዊውና ትክክለኛው ሁኔታ፤ በዓለም ላይ ባሉ በአብዛኛዎቹ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች እና በዓለም ግንባር ቀደም መገናኛዎች የታወቀና የተሰራጨ ነው፡፡ሃቁ ያማይታበልና በአጭሩ በሁማን ራይትስ ዎች የ2012 ስለኢትዮጵያ ሁኔታ የቀረበ ነው፡፡ የሂዩማን ራይትስ ዎች ዘገባ እንዲህ ብሏል

የኢትዮጵያ መንግሥትና ባለስልጣናት መሰረታዊ የሆነውን ራስን በነጻ የመግለጽ መብትን፤ የዜጎችን የሰላማዊ ሰልፍ መብት እየገደቡት ነው፡፡በ2011 በርካታ ኢትዮጵያዊያን በግፍ ታፍሰው ለእስር ተዳርገዋል፤እስከአሁንድረስም ለግፍ ተዳርገው፤በስቃይና በመከራ በእስር ላይ ናቸው፡፡ክስ ሳይመሰርትባቸው፤በመታሰርና በተለዋጭ ተጨማሪ ቀጠሮ በመጉላላት፤ከጠበቆቻቸ ውና ከቤተሰቦቻቸው ጋር ግንኙነት ተከልክለው፤በተለይሽብርተኛነትን ለመከላከል በወጣው አዋጅ መሰረት፤መብትን እንደፈለጉ መንፈግ በመቻሉ፤በዚያ እየተጠቀሙ ታሳሪዎችን ለግፍ ያበቃሉ፡፡ይህንንም እስከ አራት ወራት ድረስ ለመጠቀም አዋጁ ይፈቅዳል፡፡ በ2009የጸደቀው አዋጅም፤ መንግሥታዊ ያልሆኑ ሃገር በቀል እርዳታ ለጋሽ ድርጅቶችን፤ከ10 በመቶ በላይ የውጭ እርዳታ ማግኘት የሚያግድ በመሆኑ፤ምንም አይነት ጠቃሚ እንቅስቃሴ እንዳያደርጉ አግዷቸዋል፡፡ ሃገር በቀሉምሆነ ዓለምአቀፋዊ ድርጅቶች ጨርሶ ወህኒ ቤቶችን መጎብኘት አይችሉም፡፡በእስራት ላይ የሉትን የፖለቲካ አስረኞችም ይሁን ሌሎች ታሳሪዎች ያሉበትን ሁኔታ ማወቅ አዳጋች ነው፡፡
በኖርዌይ በሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ላይ በማንዣበብ ላይ ያለው ተጨባጭ ፍርሃት

ኖርዌይ ስለ ስደተኞች ያላትን ሕግ ለኖርዌይ ሕገደንብና የፍትሕ ስርአት የሚተው ይሆናል፡፡ያም ሆኖ ግን የኖርዌይ የስደተኞች ሕግጋት በ1951 እ አ አ የተደነገገውንና በ ማርች 23 1953 የጸደቀውን፤ በ1967 የተሸሻለውንየስደተኞች መብት መጠበቂያ ዓለም አቀፍ ደንብን ግን ያከበረ ሊሆን ይገባል፡፡

የኮንቬንሽኑ ቁጥር 1 ስደተኛን በተመለከተ ‹‹በተጨባጭ ማስረጃ በዘሩ፤ በሃይማኖቱ፤በብሔሩ የአንድ ፖለቲካ ድርጅት፤የአንድ ስብስብ አባል በመሆኑ፤ከትውልድ ሃገሩ በመሰደድ በሃገሩ ላይ ሰብአዊ መብቱ የተጠጋውን ስደተኛነው››ይለዋል፡፡›› ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችም ይህን ደንብ አጣቅሰው ነው ክርክራቸውን የሚያቀርቡት፡፡

በኮንቬንሽኑ ቁጥር 33 (1) መሰረት ‹‹በጎሳው፤በሃይማኖቱ፤በብሔሩ፤በፖለቲካ አቋሙ፤ ማንኛቸውም ሃገር ስደተኛውን ለማባረር አለያም ሸሽቶ ወደ ወጣበት ሃገርና ስብእናው ወደሚደፈርበት የአረመኔ ገዢዎች ወደሚገዙበት ሃገሩመልሶ ሊልከው፤እንዲሄድ ሊያስገድደው ጨርሶ አይገባም፡፡›› አስገድዶ ወደመጡበት መመለስን ዓለም አቀፉ ሕጋዊ ተቋምም በጽኑ የሚያወግዘውና የሚቃወመው ተግባር ነው፡፡ ይህ ሲጣስ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞችኮሚሽን ጣልቃ ገብነት ያስፈልጋል፡፡ በዚህ በኖርዌይ የኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ጉዳይ ግን የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ኮሚሽን ጣልቃ ገብነት የታሰበበት አይመስልም፡፡

በኖርዌይ ያሉት ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በዘራቸው፤በሃይሞነታቸው፤በብሔራቸው፤ባላቸው የፖለቲካ አቋም፤ የተነሳ በሕይወታቸው ላይ ሊደርስባቸው የሚችለውን ከፍተኛ ስጋት በተመለከተ ከኮነቬንሽኑ ድንጋጌ በመነሳት ሕጋዊየመብት ጥያቄን ያስነሳል፡፡ ተቀባይ ሀገራት፤አለያም ስደተኞቹ ያሉበት የስደት ሃገር፤ሊያጣራ የሚገባቸው ጉዳዮች በግልጽ በኮነቬንሽኑ ላይ ሰፍረዋል፡፡የሃገራቱ የስደተኞች ሕግ መመርያ የስደተኛውን የትውልድ ሃገር ወቅታዊ ሁኔታማጣራት እንዳለበት ያመለክታል፡፡ማስረጃዎችን የማቅረቡ ግዴታ በስደተኛው ላይ የሚጣል ሲሆን፤የማስረጃው ክብደትና ጥንካሬ በስደት ወቅት ግን ያለምንም ጥርጣሬ የስደተኛውን ፍርሃት እርግጠኛነት ላይሆን እንደሚችልሳይሆን ሊሆን እንደሚችል መቀበልን ይጠይቃል፡፡

የግፈኛውን የመለስ ዜናዊን ተለዋዋጭና እስስታዊ ፤የዲክታተርነት ባሕሪው በየወቅቱ እየባሰ ማደግ መሰረት ባደረገ መልኩ፤ኢትዮጵየዊያን ስደተኞች ላይ ሊደርስባቸው የሚችለውን ስቃይ መከራና ፍዳ፤ ከኢትዮጵያውያን ውጪላሉ በማረጋገጥ ማስረጃ ማቅረብና ማሳመን አስቸጋሪ ነው፡፡ መለስ ካለራሱ ስልጣንና ጥቅም ውጪ የማየት ችሎታው ስለጠፋበት፤ ለውጭ ሰዎችና ለሃገር ውስጥ ሕዝቦች ካባውን መቀያየሩን ያውቅበታል፡፡ ሃሰቱን እውነትለማስመሰልም ከራሱ ጤፍ ከሚቆላ ምላሱ ባለፈ፤ ሌሎችን በመቅጠር ተሟጋቾች እያቆመ፤የውጪውን ዓለም ሲያታልል፤ ሲያስመስል፤የከረመና አሁንም ያለ ነው፡፡ እነዚህ ስደተኞች ሃሳባቸውን ባሉበት ሃገር ላሉ ባለስልጣናትበቋንቋቸው ማስረዳት ባለመቻላቸው፤ ሕጉን ካለማወቅ፤የእያንዳንዱን የድርጊት ቀናት በውል ካለማስታወስ፤ቅደም ተከተልን ካለመገንዘብ የተነሳ በዘገባ አቀራረብ ላይ መመሳቀል ሳቢያ፤ያላሟላና የማያሳምን ለማለት ቀላል ነው፡፡ኮንቬንሽኑ በስደተኞች ጉዳይ ሂደት ላይ ሊከሰቱ የሚችሉትን አንዳንድ ድክመቶች በማገናዘብ፤ስደተኛውን በመደገፍ ለውሳኔው ቀናነት መቆምን መሰረት ማድረግ እንደሚገባ ያስቀምጣል፡፡

በኖርዌይ መንግሥት በግዴታ ወደ ሃገራቸው እንዲመለሱ በሚደረጉ ስደተኞች ላይ ምን ሊደርስባቸው ይችላል?

የመግባቢያ ስምምነት (MoU) ይኑርም አይኑርም፤የኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ወደሃገራቸው እንደተመለሱ በግፈኛው ገዢ መንግስት ጫና እንደሚፈጠርባቸው፤ ለእስርና እንግልት እንደሚዳረጉ አያጠያይቅም፡፡ ካላንዳች ጥርጣሬበዚህ የግዳጅ ምልሰታቸው መብት አልባ ይሆናሉ፡፡ ምንም እንኳን ሕገመንግሥቱ መብት አላቸው ቢልም( የኢትየዮጵያ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 13 (የዓለም አቀፍ ሰብአዊ መብቶችን፤ያካትታል፡፡) በፍጹም ሕገመንግስታዊ መብታቸው አይከበርላቸውም፡፡ሃሳብን የመግለጽና የነጻው ፕሬስ በታገደበት ሃገር፤የሚደርስባቸውን በደል አቤት የሚሉበት ጨኸታቸውን የሚያሰሙበት መንገድ አይኖራቸውም፡፡ ፍትህ በተዋረደበትና በዘቀጠበትምድር፤ፍትሕን ያገኙበትና፤ የሚደርስባቸውንም በደል የሚሞግቱበት መንገድ ጨርሶ የማይታሰብ ነው፡፡ የሲቪል ማሕበራት ተቋማት በታፈኑበት፤ማንም ሊቆምላቸው አይችልም፡፡የሕግ የበላይነት በማይተወቅበት፤ፈላጭቆራጭነት በነገሠበት፤ የዘር መድልዎ በተንሰራፋበት፤ አድልዎና ማንአለብኝነት በተዘረጋበት የመለስ ግዛት፤ያለጥያቄ አንድ ባንድ እየታገቱ ለሥቃይና ለመከራ ይጋለጣሉ፡፡ እነዚህ በግዳጅ ለምልሰት የተዳረጉ ኢትዮጵያዊያን፤መብታቸውን የሚያስከብሩበት ምንም ዘዴ የላቸውም፡፡በኢትዮጵያ፤ሕግ እራሱን ከሕግ በላይ አድርጎ በኮፈሰው አንድ ሰው እጅ ነው ያለው፡፡በግፈኛው ፈላጭ ቆራጭ መለስ እጅ!

መለስ ዜናዊ አካሄዱን ሁሉ፤በተንኮልና በንፉግ ስሌት እያሰላ፤ወደ ተንኮል ማስገቢያ ዘዴዎች ብቻ፤ህልምና ቅዠቱ የሆኑ፤ቆሞም ተቀምጦም ለጥፋት ተግባር የቆመ፤ጉድለተ ብዙ የሆነ ግለ ሰብ ነው፡፡የነዚህ ስደተኞች ዜና ከተወሰኑ ሳምንታት በኋላ ከሕዝብ ግንዛቤ እንደሚርቅ ያውቃል፡፡ስለ ደህንነታቸውም ሆነ ስለ ሁኔታቸው የሚከታተል አይኖርም ብሎም ያስባል፡፡የነዚህን ስደተኞች ጉዳይ የሚከታተልና መብታቸውንየሚያስከብርላቸው አንድም ተቋም እንደሌለና፤የነበሩትንም ሰንክሎ እንደአገዳቸው ያውቃል፡፡ መለስ ዜናዊ ጊዜውንና ወቅቱን በእኩይ ሚዛን መርምሮ ያገናዝባል፡፡ማንም ትኩረት በማይሰጥበት ጊዜ፤እነዚህን ተገደው የተመለሱስደተኞች፤አንድ ባንድ እያሳፈነ ለመከራ ይዳርጋቸዋል ያጠፋቸዋል፡፡ያ ነው የመለስ የስምምነት ሰነድ ውጤቱ፡፡በቅድሚያ በእርግጠኛነት መተንበይ እንደሚቻለውም ከአንድ ዓመት በኋላ በጣት የሚቆጠሩ ተመላሽ ስደተኞች ብቻበሕይወት ይተርፋሉ፡፡

የ ኖርዌዩ የመግባቢያ ስነት (MoU) እንደ ኢትዮጵያው ሕገመንግሥት ሁሉ፤ከባዶ ተስፋና፤ ከማይጨበጡና ትርጉም አልባ ከሆኑ ቃላት ውጪ፤ሌላ የሚያስገኘው ጥቅምም ሆነ ቁምነገር የለውም፡፡ በመለስ ዜናዊ ፈላጭ ቆራጭአስተሳሰብና ዙፋን ፊት፤በጣም አናሳ የሆነ ትርጉም ብቻ ነው የሚኖራቸው፡፡ የስደተኞቹ ሕገመንግስታዊ ጥበቃ በቅዠት ላይ እንደተመሰረተው ሁሉ በመግባቢያ ሰነዱም (MoU) ላይ የሰፈረውም አርቲ ቡርቲ እንደዚያው ነው፡፡ይህ ሰነድ(MoU) ወደፊት ታሪክ እንደሚመሰክረው ከብጣሽ መጫርያ ወረቀት የተለየ እንደማይሆን የታወቀ ነው፡፡

ስለኢትዮጵያውያን ስደተኞች ዶ/ር ፍሪድትዮፍ ናንሰን ምን ያደርጋሉ?

ኖርዌይ በብዙ ታላልቅ ጉዳዮች ትታወቃለች፡፡–በዓለም አቀፍ የኖቤል ሽልማት፤በዓለም አቀፍ የሰላም እና የኦስሎ አኮርድ፡፡በ2007 እ አ አ ኖርዌይ በዓለም በከፍተኛ ደረጃ የሰላማዊነት ክብር ተጎናጽፋ ነበር፡፡በዓለም ዙርያም ላሉ ስደተኞች በምታደርገው ሰብአዊ ድጋፍም ጭምር ትታወቃለች፡፡ ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት ማግስት አንስቶ ዓለም አቀፍ እውቅና ያለው የኖርዌይ የስደተኞች ካውንስል ለተፈናቀሉ፤በሃገራቸው የነበረው አስከፊ ስርአት በዴሞክራሲበመተካቱ፤ሰብአዊ መብቶች በመከበራቸው፤ፍትሕ በአግባቡ መተርጎም በመጀመሩ ወደ ትውልድ ሃገራቸው በፈቃደኝነት ለተመለሱት ድጋፍና እገዛ ችሯል፡፡

የስደተኞችን ጉዳይና ስደተኞችን መርዳት በተመለከተ፤ ለስደተኞች ዘላቂ መፍትሔን በመሻትና ተግባራዊ ማድረግን አስመለክቶ የኖርዌዩን ተመራማሪ፤ሳይንቲስት፤ዲፕሎማት፤ሰብአዊ አገልግሎት ሰጪ፤ ዶር ፍሪድትዮፍ ናንሰንንየሚስተካከል የለም፡፡ዶ/ር ናንሰን፤በ1922 እ አ አ ሃገር አልባ በሆኑ ሰዎች ስም (የ‹‹ናንሰን ፓስፖርት›› በመባል በዓለም አቀፍ ታዋቂ የሆነው ለሃገር አልባ ሰዎች የሚሰጥ መታወቂያ) የዓለም የሠላም ሽልማት ተሸላሚ ለመሆንበቅቷል፡፡የዶር ናንሰን ተግባርና እንቅስቃሴ፤በሚሊዮን የሚቆጠሩ የሩስያውያን፤ የግሪኮችን የቱርኮችን፤ የአርመናውያንን፤ ሕይወት አድኗል፡፡ በቅርቡም የኖርዌዩ ተወላጅ ኳስ ተጫዋቹ ቢዮርን ሄይደንስቶርም በስደተኞች ሕይወትለውጥ ለማምጣትና ግንዛቤ ለማስጨበጥ ሲል ዓለምን በቢስኪሌት ዞሯል፡፡ ታዋቂው ኖርዌጂያዊው ደራሲ ያን ኪየርስታድ የኢትዮጵያዊያንን ስደተኞች ጉዳይ አስመልክቶ በሚገባ ገልጾታል፡፡‹‹ከቢሮክራሲያዊ አካሄድ አኳይ የተፈጸው ተግባር ልክ ነው፡፡(ለምልሰት መዳረግ) ያም ሆነ ይህ ግን ለዚህ የግብር ይውጣ ውሳኔና ትግበራ አንድ ቃል ብቻ ነው መገለጫው፡ ያሳፍራል፡፡››

ዶር ናንሰን ስለ መግባቢያ ስምምነቱ (MoU) እንዲያውም ስለ ስደተኞችን በሽያጭ (RfC) ቢያዩ አለያም ቢሰሙ ምን ሊያደረግ እንደሚችሉ ሳስብ ይገርመኛል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ጀንስ ስቶልተንበርግን አንድ ጥያቄ መጠየቅ ብችል የምላቸው፡ ዶር ናንሰን የእርስዎን የመግባቢያ ስምምነት (MoU) ምን ያደርጉ ነበር? ዶር ናንሰን በጣም እርግጠኛ ነኝ ለኖርዌጂያን ወገኖቻቸው ‹‹የሞራል ቁጣ ሲገደድ›› በሚል ሌላ የመግባቢያ ስምምነት (MoU) ያቀርቡላቸዋል፡፡

Leave a Reply