የአንዱዓለም አራጌና የሌሎችም የፖለቲካ እስረኞች ግፍና መከራ

Click here for PDF

ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረ ማርያም
ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ

በቀድሞው ሶቭየት ሕብረት ስርአት ውስጥ የሰብአዊ መበት ተሟጋቾችንና ተቃዋሚ ፕርቲዎችን እያጎረ በስቃይ ይጠብሳቸው የነበረበት የስርአቱ ገሃነም‹‹ጉላግ›› ወህኒ ቤት

Andualem Arage

ነበር፡፡እነዚህ ‹‹ገሃነሞች›› ጉላጎች ተግባራቸው፤ በሶቭየት ሕብረት ያሉትን ተቃዋሚዎች በአጠቃላይ ለማጥፋትና ዳጋም እንዳያቆጠቁጡ ማደረግ ነበር፡፡የሶቭየት የሽብርና የመከራ ቁጥቋጦዎች ሆነው ያደጉና የሃገሪቱና የህዝቦቿ ቀንደኛ ጠላቶች ነበሩ፡፡በተላበሱት የጭካኔና ኢሰብአዊነት ጎሬነታቸው ‹‹የሥጋ መፍጪያዎች›› በሚል ይታወቁ ነበር፡፡

በወህኒ ባለስልጣኖችና አጋፋሪዎቻቸው በሚካሄደው ሥቃይ፤አካላዊ እንግልትና መከራ፤ በግፍ በጭለማ ቤት በማሰር፤በወረደና እዚህ ግባ በማይባል የጤናጠንቅ የምግብ እደላ፤እንዲሁም በነዚህ ሃላፊዎችና አጋሮቻቸው በሚሰጥና በሚቀናበር የእሰረኞች ረብሻና ህግ ወጥ ድርጊት የሚፈልጉትን ማስፈጸም ነበር የጉላጎች ተንኮል፡፡

አሁን በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኘው ወህኒ ቤት፤በፖለቲካና በሌሎችም እስረኞች አያያዝና በሚያደርስባቸው ሰቆቃ፤የሶቭየት ሕብረቱ ጉላግ ቅሪት ነው፡፡ስለዚህ ጉዳይ ማስረጃዎቹ ከሰው ባላነሰ ምስክርነታቸውን ለማንም ሳይወግኑ፤ለዕውነት በዕውነት በመቆም ይናገሩ፡፡በቅርቡ በማን አለብኝነት፤ በሥርአት አልበኝነትና በሥላጣን አለአግባብ በመባለግ፤በዘርና በመንደር ተውላጅነትበመመካት፤የመንግሥት ባለስላጣናት ለእስር የዳረጓቸውን ሁለት ስዊዲናውያን በተመለከተ፤የኒውዮርክ ታይምስ አምደኛ ኒኮላስ ክሪስቶፍ ወህኒ ቤቱን ሲገልጸው እንዲህ አድርጎ ነው፡፡-

ቆሻሻና በቅማል የተጥለቀለቀ፤ትላልቅ አይጦች(ምናልባትም ሆን ተብሎ በታሳሪዎች ላይ በሽታ እንዲያስተላልፉ የረቡ፤)ቁንጫና ትኋን ከአካባቢው ንጽህናና ለንጽህና አስፈላጊ የሆኑ መገልገያዎች ሆን ተብሎ በመከልከል የተራቡበት………..የበሽታ መራቢያ ጣቢያ፤ታሳሪዎቹ በሳልና በብርድ ምች በመሰቃየት የደም አክታ እየተፉ የሚኖሩበት፤የገሃነም ቦታ…………፡፡ከ250 በላይ ኢትዮጵያዊያን በታጎሩበት በዚህ ቦታ ነበር ስዊዲናውያኑም የተካተቱት፡፡ስዊድናውያኑ ለነዚህ ከራሳቸውም አልፈው፤ ታዛቢና አለሁ ባይ ለሌላቸው የግፍ ታሳሪዎች እየጸለዩና፤ጎናቸው የሚያርፍበትን አልጋ ‹‹የስዊዲሽ ኤምባሲ›› በማለት በቀልድ መሰል አጠራር ሰይመውት የግፍ እስር ባልደረባነታቸውን በመሳተፍ ላይ ናቸው፡፡
እ አ አ በኤፕሪል 2011 ይፋ የሆነው የዩናይትድ ስቴትስ ሰብአዊ መበት ዘገባ በኢትዮጵያ ስላለው የሰብአዊ መብት ረገጣ የሚከተለውን ብሏል፡፡

በቅርቡ የተጠናከረው የሰብአዊ መብት ረገጣ፤ሕገወጥ ግድያን፤የግፍ ድብደባን፤ማሰቃየትን እና የእስረኞችን አለአግባብ መንገላታት፤ኢሰብአዊ በሆነ አያያዝ መጎሳቆልንና የፖለቲካ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በደህንነት ሰራተኞችና በልዩ የፖሊስ ሃይሎች፤ በቀበሌ ሚሊሺያ ታጣቂዎች የሚደርስባቸውን ግፍ ኢሰብአዊ ድርጊት፤አሳዛኝና አሳሳቢ ነው፡፡የወህኒ ቤቱ አያያዝም ቢሆን ለሰው ልጅ ሊሆን ከሚገባው በታች የወረደ ነው፡፡ያለምንም ማስረጃና ትዕዛዝ በየመንገዱና ከየመኖርያ ቤት መያዝ፤ በተለይም ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው በሚጠረጠሩት ላይ፤ በተቃዋሚ ፓርቲ አባላት ላይ፤የሚደርሰው የማን አለብኝነትና ‹‹ካለኛ ፈቃድ አንዳች እንቅስቃሴ የማይታሰብ ነው›› በሚል ጀብደኝነት የሚፈጸመው ግፍ እጅጉን አሳዛኝ ነው፡፡ በተለይም 7ማዕከላዊ በሚባለው ልዩ የፖሊስ ሃይል የመመርመሪያ ጣቢያ ውስጥ ያሉት መርማሪዎች ‹‹ተጠርጣሪ›› ብለው የሚየዟቸውን፤ማስረጃ አውጡ በማለት በግፍ ከመደብደባቸውም በላይ ተጠርጣሪዎች መራማሪዎች የሚፈልጉትን እንዲሉና ቃላችን ነው ብለው እንዲፈርሙም ዱላና ስቃይ ያደርሱባቸዋል፡፡

በ2010 የሁዩማን ራይትስ ዎች የዓለም አቀፍ ሪፖርት ስለ ኢትዮጵያ

ስቃይና መከራ፤ በደልና ግፍ፤ በኢትዮጵያ ፖሊሶችና ወታደሮች በተለይም የደህንነት አባላት፤ የጠረጠሯቸውን የህብረተሰብ አባላት፤የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን፤የተቃዋሚ ሃይሎችን አባላት፤የሌሎችንም ደጋፊ ናቸው ብለው የሚጠረጥሯቸውን በሚስጥራዊ መንገድና ቦታ በወታደራዊ ካምፖችና በልዩ ልዩ ሰውር ቦታ በተዋቀሩ ጎሬዎች አስረኞችን ማጎር የደህነንቱ የተለመደ ተግባር ነው፡፡ የደህንነት አባላት ለሃገርና ለሕዝብ ደህንነት እንዲቆሙ ተብለው የተደራጁ ናቸው ቢባልም፤ እውነቱ ግን የአንድን ሰው በስልጣን የመቆየት ዘመን ለማራዘም፤ ታተቃዋሚ ድርጅቶችን አላላውስ በማለት በየቤታቸውና በየሚሄዱበት በመከተል ተስፋ ለማስቆረጥ መጣርና የግለሰብ አገልጋይ ሆነው ነው ከመንግሥት ካዝና የሚወጣ የሕዝብ ገንዘብ ደምወዝና የውሎ አበል የሚከፈላቸው፡፡

በ2010 ኖቬምበር የተባበሩት መንግሥታት ስለእስረኞች ስቃይ ሁማን ራይትስ ዎች የወጣውን ዘገባ አረጋግጦታል፡፡

በኢትዮጵያ ስላለው ‹‹ጉላግ›› የደዋር ዘገባበኢትዮጵያ ያለው መደበኛና ሚስጥራዊ እስር ቤት የትም ተወዳዳሪ የማይገኝለት ኢስበአዊ፤ ኋላ ቀርና፤የግፍ ሱስ ባለባቸው አውሬዎች የሚተዳደር ነው፡፡ በ2008 ዓም ፈላጭ ቆራጩ የመለስ የግዛት አስተዳደር ጡረታ ላይ ያለውንና በዓለም በደህንነት ጥበቃ ላይ ታዋቂ የሆነውን የብሪቲሽ ኮሎኔል ማይክል ደዋርስን የኢትዮጵያን የወህኒ ሁኔታ እንዲያጠናና ሃሳብ እንዲያቀርብ በሙስጥር ቀጥሮት ነበር፡፡ድዋርስ ባጠናቀረው ዘገባ ላይ እንደገለጸው፤በጊበኘው በአዲስ አበባው አንድ ወህኒ ቤት ያጋጠመውና ያያው፤ እጅግ የሚሰቀጥጥና የሚያስጨንቅና፤ ለማየት የሚቀፍ ነው ብሎ ሲቀጥልምታሳሪዎቹ ወዳሉበት ሥፍራ እንዲወስዱኝ ጠየቅሁ፡፡ያየሁት ቦታ ከለላ መሰል ጣራ ያለው ረጂም ጋጣ ነው፤ ወህኒ ቤቱ፡፡ግቢው በግምብ የታጠረና ለጠባቂዎችም ማማ ያለው ሆኖ መሳርያ ያነገበ ጠባቂ ወታደርም አለው፡በደረስኩበት ቦታ ላይ ከ70 እስከ 80 የሚሆኑ እሰረኞች በሚገማና በሚያሰጠላ ቦታ ውስጥ አሉ፡፡እነዚህ እስረኞች ሁሉም በአንድ ጊዜ ሊተኙ የሚችሉበት በቂ ቦታ የለም፡፡በቂ ብርሃን የለውም፡፡ የሽንትና የዓይነምድር ሽታው አያስቀርብም፡፡በግቢው ውስጥ ለመታጠቢያና ለመጸዳጃ የሚሆን ውሃ የለም፡፡ራቅ ብሎ አንዲት ጎጆ መሰል ቤት ለሴቶች ተመድባለች፤ ማንም የቦታውን ሁኔታ ለማሻሻል ፍላጎትም ሃሰዳብም የለውም፡፡አብዛኛዎቹ ታሳሪዎች በመናኛ ጉዳይ የታሰሩ ናቸው፡፡ ለአራትና ለአምስት ወራት ሲያልፍም በርከት ላለ ጊዜ የታሰረቱ ናቸው፡፡

የኮ/ል ደዋር ማጠቃለያ

የእስረኞቹ የታሳሪዎች ሁኔታ እጅጉን የሚያሳዝንና በጣም የተጨማለቀ ሁኔታ ያለበት ነው፡፡ ለሰው ልጅ ይህ በጣም ግፍ ነው፡፡ይህ ደግሞ የፌዴራል ፖሊስን ለሰብአዊ መበት ተጠያቂነት ያበቃዋል፡፡ እኔ ያየሁት እስር ቤት በጣም አሳፋሪ ነው፡፡ ማንም ሂልተን ሆቴል ይታሰሩ የሚል የለም ሆኖም ግን ማንኛውም የሰብአዊ መብት ተሟጋች ይህን ሁኔታ ቢያይና ቢያውቅ ልፋትና ጥረታችንን ሁሉ ገደል የሚከተው ልንከላከለው የማንችለው ውድቀት ሊያደርሱብን የሚያስችላቸው በቂ መሳርያ ነው፡፡፡፡
ኮ/ል ዴዋርስ

በኢትዮጵያ ወህኒ ቤቶች አሁን ያለውን ሁኔታ መንግስት በትጋትና በጥንቃቄ ሊያስብበትና ለማሻሻልም ፈቃደኝነት ሊኖረው ይገባል፡፡አሁን ያለው ሁኔታ ሰውን ያህልክቡር ፍጥረትን ከእንስሳት ባነሰ ደረጃ ላይ ያስቀመጠ ነው፡፡ እኔ ያየሁትን ወህኒ ቤት የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሚኒስትሮችና የፖሊስ ባለስልጣኖች ሊጎበኙት ይገባል፡፡

ላለፉት በርካታ ዓመታት ስለ (እስረኞች ስቃይ (ቶርቸር) እና በኢትዮጵያ ውስጥ በአገዛዙ የግፍ ሰቆቃ ውስጥ ስለሚገኙ የፖለቲካ እስረኞች ብዙ ጽፌያለሁ፡፡ በርከት ባሉት ጽሁፎቼ ውስጥ በተለይም ገዢው መንግሥት በብቸኛዋ የፖለቲካ መሪ በዳኛ ብርቱካን ሚዴቅሳ ላይና በሌሎችም የፖለቲካ ተቃዋሚ አባላት ላይ ሲፈጸም ስለነበረው ለስላሳ ቶርቸርና ሕሊናዋን አቁስሎ ለማላሸቅ ያደረገው ሙከራ ምን ያህል ሰብአዊነት የጎደለው ጭካኔያዊ ድርጊት እንደነበር ለማሳየት ሞክሬያለሁ ፡፡ ብርቱካን ለረጂም ጊዜያት በብቸኛነት በአንድ የስቃይ ጉረኖ ክፍል ውስጥ በመታሰር ከእንቅልፍ፤ ከቤተሰብ ግንኙነት፤ከመገለሏም ባሻገር ከሰብአዊ ህሊና ውጪ ብቻ በሚፈጸም ክፋትና ሕሊና በጎደላቸው የገዢው መናፍቆች ይደረግባት የነበረው የምርመራ ዘዴ የክፋትና የክፉዎች ተግባር ነበር፡፡መለስ ዜናዊ አንድ ጊዜ ወደ ወህኒ ካወረዳት በኋላ መልሶ ነጻ ማድረግን ማሰብ እንኳን የማይቻል እንደነበር ነው ደጋግሞ በአካኪ ዘራፍ ስሜረት ሲወተውት የነበረው፡፡ይህንንም ሲያረጋግጥ ‹‹ብርቱካንን ብርቱካንን በነጻ ለመልቀቅ ከማንም ጋር ስምምነት ላይ መመድረስ አይቻልም፡፡ በጭራሽ፡፡አራት ነጥብ፡፡ ይሄ ያለቀለት የሚተ ርዕስ ነው፡፡››ብሎ ነበር፡፡ በመቸረሻም ድል ሆነና ተፈታች! ነጻነቷን በዘዴዋ አወጀች!፡፡ባለፈው ሳምንት ነበር ብርቱካን ባለችበት የሬጋን ፋሴል-ፌሎው ዊዝ ዘ ናሽናል ኢንዳውሜንት (Reagan-Fascell Fellow with the National Endowment for Democracy) ሆና የኢትዮጵያን ተቃዋሚ ፓርቲዎችን የሚሞግታቸው ችግርና መፍትሔው በሚል መነሾ ጽሁፏን ያነጣጠረችው፡፡

አንዱዓለም አራጌ በአውሬው ሆድቃ ውስጥመለስ ዜናዊ የብርቱካንን እስር በሌላው ወጣትና ሕዝባዊ መሪ ተክቷል፡፡ባለፈው ሳምንት የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዜዳንት፤ የአሁኑ የወቅቱ የአንድነት ለዴሞክራሲ ፓርቲ መሪ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ በወህኒ ቤቱ ውስጥ ሞት የተፈረደበትና በኋላም እድሜ ልክ በተባለበት አንድ እስረኛ አንዱዓለም አራጌ በክፍሉ ውስጥ ሳለ በከባድ ሁኔታ መደብደቡንይፋ አድርገዋል፡፡ የአንዱዓለም መደብደብ በጣም የሚያስገርም ነው፡፡እንደ ዶ/ር ነጋሶ አገላለጽ፤ አንዱዓለም በአንዲት መስኮት በሌላት ጠባብ ክፍል ውስጥ ከሌሎች ጋር 14 ሆነው ነው ያሉት፡፡ከነዚህም ውስጥ በቀለ ገርባ፤ሌሊሳና ጥላሁን ፋንታሁን የሚገኙበት ነው፡፡ከአንድ ወር በፊት የሞት ፍርድ ፍርደኛውና ያም በዕድሜ ልክ እስራት የተቀየረለት ታሳሪ አንዱዓለም ያለበትን ክፍል 9 ይቀላቀላል፡፡ይህ ነፍሰገዳይ አንዱዓለምን ክፉኛ በመደብደብ በጭንቅላቱ ላይ ጉዳት አደረሰበት፡፡
ይህንንም ተከትሎ አንዱዓለም እራሱን ስቶ ነበር፡፡የአሜሪካን ድምጽ ሬዲዮ “አንዱዓለም በራሱ ላይ የደረሰበት ጉዳት ሚዛኑን እንዳሳተው ቤተሰቦቹና የጎበኙት ወዳጆቹ ተናግረዋል” ሲል ዘግቧልይህ ነፍሰ ገዳይ በእስር ቤቱ በዱለኛነቱ በጣም የታወቀ ሲሆን፤ አብረውት የሚኖሩ ታሳሪወችን በተለያየ ጊዜ ያሰቃየ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ለእስር ቤቱም እንደታሳሪዎች ቀጪ ስለሚያገለግል መልካም እንክብካቤ፤ ጥሩ ይዞታና ምቹ የመኝታ ቦታም ተመድቦለት ያለ ነው፡፡ በእስር ቤቱ ውስጥ እንደሚናፈሰው ወሬም ሰውየው አንዱዓለምን እንዲህ አድርጎ በመጉዳቱ ጠርቀም ያለ ክፍያም ተሰጥተፐታል፡፡

በተፈጠረ የቴረሪዝም ውንጀላ ከመያዙና ለወህኒ ከመዳረጉ በፊት፤ አንዱዓለም በአንድነትለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ ውስጥ እየታወቀና እያደገ የሚገኝ ብልህ መሪ፤ፓርቲውንምአፈጉባኤና የውጭ ግንኙነት ሃላፊ በመሆን ያገለግል ነበር፡፡አንዱዓለም ከአዲሴ ትውልድ የተገኘ ወጣት፤ የፖለቲካ መሪዎች፤ጋዜጠኞችም ሕብረተሰቡ አክብሮት የቸረው የፖለቲካ ተስፋነው፡፡ባለፈው ሜይ ላይ በተደረገውና መለስ 99.6 በመቶ ምርጫውን አሸንፌያለሁ በማለትለሰውም ለድርጅቱም ለሌላውም ዓለም ለራሱም በዋሸበት ምርጫ፤ ዓነዱዓለም ዝንፍ የማይል፤የዴሞክራሲንና የሕግን የበላይነት የፖለቲካ አቋሙን በይፋ አሳይቷል፡፡

በሴፕቴምበር 2011 ‹‹በጸረ-ሽብር ሕጉ›› አንዱዓለምና ሌሎች 23 ግለሰቦች፤የሽብርተኛ ድርጅቶችና የድረገጾቻቸው አባላት፤ሽብርተኛችና በማገዝና በመደገፍ፤ክስ ተመስርቶባቸዋል፡፡ በወሩ መግቢያ ላይ ግለኛ የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብት ቡድን ባለሙያዎች የኢትዮጵያን የጸረ ሽበርተኛነት ህግን በተመለከት ከዓልም ተመሳሳይ ህግጋት ጋር የሚቃረን፤ ፈሩን የለቀቀን በጸረሽብር ስም ግፍ እየተሰራበት ስለሆነ በግልጽ መቀረጽና በኢትዮጵያ የወንጀል ሕግ ውስጥ በሚገባ ተስተካክሎ ሊቀመጥ ይገባል፡፡›› ብለዋል፡፡ ማርች 5 2012 አንዱዓለም የተለመደውን የመለስን የቅጥፈት የአዞ ፍርድቤት ቀጠሮ በመጠበቅ ላይ ነው፡፡

ስቃይ ፍርደገምድልነትና ክህደትየታወቀ ክህደት እውነትን ለመካድ ብቃት ማግኘት፤ወይንም የወንጀል አለያም ሌላ ተንኮላዊ ድርጊትን ወደ ሌላ መለጠፍ ማለት ነው፡፡ መለስ ዜናዊም በአንዱ ዓለም ላይ በእስር ቤት ውስ የተካሄደውን የእስር ቤቱን ሃላፊዎች ድርጊት አለያም መመርያ መስጠት፤አለያም ስላጣን ሳይኖራቸው ግን ጉዳዩን የፈጸሙትንም ሆነ ማንኛውን ድርጊት እያወቀው አለውቀውም አልሰማሁም ለማለት አመቺ ሁኔታ አለው፡፡ ነፍሰገዳዩ በአንዱዓለም ላይ ይህን ሕገወጥና ግፍ ማድረሱን ፈቅደውለትም፤ እያወቁ አለማወቅን መርጠዋል፡፡በአንዱዓለም ላይ የተፈጸመውን ድርጊት እንዳይጠየቁበት እጃቸውን፤ ጣቶቻቸውን፤ መዳፋቸውን ሁለንተናቸውን ንጹህ በማድረግ ከተጠያቂነት ርቀው ባሻጋሪ እያስፈጠሙ አናውቅም ለማለት ደፍረዋል፡፡ምንም ይሁን ምን፤ ሕገ ወጥ ሰዎቻቸውን አዘውም ይሁን አለያም በቀበሮ ባህታዊነት ተሸፍነው ወንጀል ፈጽመውም ቢሆን፤ በእስር ቤቱ ውስጥ ላሉት ታሳሪዎች ደህንነት ተጠያቂው እስርቤቱን የሚያስተዳድሩት መሆናቸው አሌ የማይባል ነው፡፡ አላወቅንም ብለው ምለው ተገዝተው ቢክዱም መጠየቃቸው አይቀሬ ነው፡፡በአንዱዓለም ላይ የተፈጸመውና በሌሎችም ቀደም ሲልም 10ሆነ ወደፊትም የሚፈጸመው ግፍና በደል የኢትዮጵያን ህግ የሚቃረንና ኢትዮጵያ የተቀበለችውንም ዓለም የሰብአዊ መብት ሕግ የሚያፋልስና የሚቃረን ነው፡፡

ስለሕገመንግሥትና ስለዓለም አቀፍ ሕግጋት…የኢትዮጵያ ሕገመንግሥት ገና ውሳኔ ላልተላለፈባቸውን ፍርድን በመጠበቅ ላይ ስላሉ ታሳሪዎች ስለደህንነታቸውን ሊደረግላቸው ስለሚገባው የደህንነት ጥበቃ ደንብ አለው፡፡ አንቀጽ 16 ማንም ታሳሪ በሰውነቱ ላይ ከሚደርስ ጉዳትናጥቃት ጥበቃ ይደረግለታል ስለሚል አንዱዓለምም ፍርድ ጠባቂ ስለሆነ አስፈላጊው ጥበቃ ሊደረግለት ተገቢ ነው፡፡የኢትዮጵያ ወንጀለኛ መቅጫ አንቀጽ 110 ቁጥር 414/2004 እንደሚያዘው ‹‹በጥብቅ እስር የተፈረደባቸውና ወይም በልዩ መልክ እስራት የተፈረደባቸው በቀላል እስር ከተፈረደባቸውና ገና ፍርድ ከሚጠብቁት ተለይተው ሊታሰሩ እንደሚገባ ያዛል፡፡በዓለንዱዓለም ጉዳት ያደረሰው ወንጀለኛ ነፍሰ ገዳይ የሞት ፍርድና በኋላም ዕድሜ ልክ የተባለለት በጭራሽ ፍርድ በመጠበቅ ላይ ወዳሉት ሰፈር መድረስ አልነበረበትም፡፡ አንቀጽ 18 ማንኛውም ሰው ከኢሰብአዊ ጥቃት፤ከግፍ አያያዝና እንግልት፤ወይም ስብእናን ከሚያዋርድ አያያዝና ቅጣት ሊጠበቅ ይገባዋል፤ በማለት ያዛል፡፡ አንቀጥ 20ም በሕጉ መሰረት በፍርድ ሂቱ ወቅት ማንኛውም ታሳሪ በማስረጃና ነጻና ፍትሃዊ ዳኝነት አግኝቶ እስኪፈረድበት ድረስ ነጻ ነው ሲል ያትታል፡፡ አንዱዓለምም ገና በፍርድ ስላልተወሰነበት፤‹‹እንደሕጉ አባባል›› በተመሰረተበት ክስ እስኪፈረድበት ድረስ ነጻ ነው፡፡ አንቀጽ 21 ደግሞ በቁጥጥር ስላሉ ተጠርጣሪዎች ፍርድ እስኪተላለፍባቸውም ሆነ ከተፈረደባቸውም በኋላ ሰብአዊ መብታቸው ሳይጓደል ሊጠበቁ ይገባል ይላል፡፡

በተለያዩ ወቅቶች የወጡትና የጸደቁት ዓለም አቀፍ ሕግጋት ኢትዮጵያም ተቀብላ ያጸደቀቻቸው፤ ሁሉም በየአንቀጾቻቸው የሰውን ልጅ ክቡርነት በማጣቀስና ሊደረግለት ስለሚገባው ጥበቃና ስለመብቱም መጠበቅ፣ ማንኛውም ታሳሪ፤ በተለይም የፖለቲካ ታሳሪዎች፤ማንኛውም ሰብአዊ ፍጡር በነጻነት ባለበት ጊዜም ሆነ፤ አለያም ተጠርጥሮ ነጻነቱን ካጣበት፤ አለያም በተጠረጠረበት ክስ ተፈረርዶበትም በእስር ላይ ቢሆንም፤ ሰብአዊ መብቱ እንደስብእናው ክቡርነት ሊከበርና መብቱም ሊጠበቅለት ተገቢ መሆኑን ያውጃሉ፤ ኢትዮጵያም ይህን አምናና ተስማምታ ተቀብላ አጽድቃለችና በተግባር የተርጉም ግዴታ ይጠበቅባታል፡፡

ይህን ዓለም አቀፍ ህግ ከተቀበሉ በኋላ ትግበራው ላይ ማወላዳትና ማፍረስ ግን ራሱን የቻለ ሽብርተኝነት ይሏል ይሄ ነው፡፡እስረኞችን ለመጠበቅ የተዋቀረው የተባበሩት መንግሥታት ሕገ ደንብ( በ1988) ‹‹በቁጥጥር ስር የዋሉ ሰዎች ክብራቸው እንደተጠበቀና ደረጃቸው ሳይገዋደል ሊታሰሩ ይገባል፡፡ከሌሎች ታሳሪዎች በተቻለ ሁሉ ሊለዩ ተገቢ ነው፤ ስለቶርቸር ሲያብራራም፤‹‹…..ማንኛውም ለችግር የሚዳርግ ተግባር፤ለስቃይ የሚያደርስ ሁኔታ፤ ስብእናን የሚያዋርድ ድግጊት፤ አካላዊና ስነልቦናዊ ጫናም የሚያሳድር ድርጊት፤በባለስልጣናት ሚዋጋው ሃይል ጨርሶ የማይቀበለው ነው በማለት ያስቀምጠዋል…….. ኢትዮጵያ አምናና ፈቅዳ የተቀበለችውም የሰብአዊ መብት ጥበቃ እንደሚለው፤……….. ይህን አምነውና ፈቅደው የተቀበሉትና ያጸደቁት ሃገራት ሁሉ የጭካኔ ድርጊቶችን የመከላከል፤ኢሰብአዊ ሁኔታዎችን የማገድ የፈራሚነት ግዴታ እንዳለባቸው እያዘዘ በማሰሪያውም ላይ ይህ መብት ሌላው ቀርቶ የስቃይ ድርጊትን (ቶርቸር) በተመለተ በሰብአዊ 11መብት ማጉደልና መግፈፍ የተወነጀሉትንና የጦር ተከሳሦችንም የሚያካትት መብት እንደሆነ ይናገራል፡፡ ስለፖለቲካ እሰረኞች ጥበቃ ሕግ የምጽፈው እንዲያው ህጉን ለማሳወቅ ያህል እንጂ ሕግ አልባነት መፍለቂያቸው፤ ኢሰብአዊነት ማደጊያቸው፤ ፍትሕን ማጓደልና ግፍን በሕዝብ ላይ ማድረስ መኖሪያቸው ለሆነ ሰው ደጋግሞ ስለሕግ የበላይነት ስለደንቦች መጠበቅ ማውራት በድንጋይ ላይ ውሃ ማፍሰስ እንደሆነ ይገባኛል፡፡

በኦገስት 2009 ዓም ‹‹ጋሻ ለኢትዮጵያ›› የተባለ የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅት ባዘጋጀው ስብሰባ ላይ ተገኝቼ ‹‹የኢትዮጵያን የፖለቲካ አስረኞችን የማስታወስ አስፈላጊነት ተናግሬ ነበር፡-ዶር. ማርቲን ሉተር ኪንግ በመጨረሻም ልናስታውሰው የሚገባን የጠላቶቻችንን ቃላት ሳይሆን፤ የወዳጆቻችንን ዝምታ መሆን ይገባዋ ……….. ብለው ነበር፡፡

ለፖለቶካ ታሳሪዎች ከምንም በላይ ልባቸውን የሚሞላው ብርቱ ነገር ቢኖር በውጪው ዓለም እንዳልተረሱና ችላ እንዳልተባሉ፤ እንደሚታወሱና ምንግዜም እንደሚታሰቡ ማወቃቸው ነው፡፡እነሱን ለማሰብ በእንዲህ አይነቱ አዳራሽ ተሰባስበን በምንገኝበት ወቅት በፈጣሪ ሃይልና ፈቃድ በነጻነት ለመኖርና ንጹህ ዓየር ተንፍሰን በሰላም ለመኖር የምንችለው ሰላምን አጥተው፤ ነጻነታቸውን ተገፈው፤ በጨቋኝ ፈላጭ ቆራጭ ገዢዎች የጭለማ አለም ውስጥ ያሉትን ልንዘነጋቸውና ለአንዲት ሴኮንድ እንኳን ችላ ልንላቸው አይገባንም፡፡

በኢትዮጵያ የሚገኙ አንዱዓለም አራጌና ቁጥር ሥፍር የሌላቸው የፖለቲካ እስረኞች፤ አሁንም በፈላጭ ቆራጭ የግፍ አገዛዝ ጭለማ ውስጥ ይገኛሉ፡፡በየእለቱ በመደብደብና ለስቃይ በመዳረግ እንዲንበረከኩ እየተደረጉ ነው፡፡ስቃያቸውን፤ መከራቸውን፤ ዋይታቸውን መስማት አልተቻለንም፡፡ በመከራ የተቆራመደና ስቃይ የበዛበትን አካላቸውን የሚያላቸው ጥቂቶች ናቸው፡፡ድምጻቸው ታፈኗልና እኛ ነን ድምጻቸው ሆነን ልንጮህላቸው፤ዋይታቸውን ልናሰማላቸው፤መከራቸውንና የሚፈጸምባቸውና ግፍና በደል ልናሰማላቸው የሚገባን፡፡

እነሱ በገማና በበሰበሰ ግምብና አስተዳደር ታጥረው ያሉና፤ ለዕውነትና ለፍትሕ ቆመው ኢሰብዊ ድርጊት በሚፈጸምበት፤ ጭካኔ በሰፈረበት ለመከራ ተዳርገዋልና እኛ ለዓለም አቤት ልንላቸው፤ ድምጻቸው ሆነን፤ በኢትዮጵያ ላሉ የፖለቲካ እስረኞች ብሶታቸውን ልናሰማላቸው የግድ ነው፡፡ይህን ማድረግም ዝም ብሎ ለይስሙላ ሳይሆን፤ግዴታችን በመሆኑ፤ክብር እና ትክክልም ስለሆነ ሊሆን ይገባል፡፡ኢትዮጵያችንን ኢትዮጵያ የሚያደርግልን፤ የነዚህ ግፈኞች፤ዘረኞች፤ፍትሕ አልባ ሴረኞች፤ ጸረ ዴሞክራሲ ወንበዴዎች፤አውሬዎች፤በሙስናና በስርቆት የተዘፈቁ አምባገነን ገዢዎች የግፍ አመራር ሳይሆን፤በግፍ ለታፈኑት ኢትዮጵያውያን እኛ የምናሰማው፤በሰብአዊ ክብር በተሞላ፤በቆራጥነት ለሰው ልጆች ደህንነት በመቆም፤ ለወገኖቻችንና ግፍ ለበዛበት ሕዝብና ሃገራችን የምናሰማው እውነት ነው፡፡

ስለዚህም ነው እጅ ለእጅ ተያይዘን፤በጠነከረና በአንድነት በተሳሰረ እንቅስቃሴ በኢትዮጵያ ውስጥ በግፍ የታሰሩትን የፖለቲካ እስረኞች ከሚታወቁና ሚስጥራዊ ከሆኑት ጉላጎች(ግፍ የበዛባቸው ወህኒዎች) መታገል ያለብን፡፡‹‹የተቸቆኑት ነጻ ይሁኑና ሕዝብ ላይ 12በግፍ የተጠመጠመው የግፈኛ ገዢዎች ሰንሰለት በነጸነት ሃይል ይበጠስ›› አንዱዓለም አራጌና ሌሎችም የፖቲካ እስረኞች ከታፈኑበት የግፍ ጉረኖ ይውጡ!

Leave a Reply